አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Andinet Umoja: Connecting African Businesses 🇪🇹🤝🏿🌍
What an incredible experience at Andinet Umoja, a powerful networking platform uniting Africa’s entrepreneurs, business leaders, and innovators! As the name suggests:
"Andinet" (Amharic) & "Umoja" (Swahili) = Unity
A true reflection of the collaboration driving Africa’s growth.
📅 Date: February 16, 2025
📍 Venue: Monarch Parkview Hotel, Addis Ababa
The breathtaking view of Addis from the venue made the experience even more special! More importantly, I achieved my purpose for attending—it was worth every moment.
🔹 Why this event matters:
Connecting with Africa’s top innovators
Building cross-border partnerships
Strengthening African collaboration
I love Africa, and I sincerely appreciate Mr. Thomas for his dedication in making this event a reality.
Now, we are more connected than ever. This is just the beginning of a powerful journey—expanding networks, fostering regional unity, and creating lasting impact for African businesses. Alehig will always be by your side!
#AndinetUmoja #AfricanUnity #AU2025 #AfricanUnion #Africans #BusinessNetworking #Alehig
#የቤት_ኪራይ ውል ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ ተከራይ ቤቱን ለቆ እንዲያስረክበው ለቆ የማያስረክብ ከሆነ ግን የኪራይ ተመኑ በማስጠንቀቂያው ላይ በተመለከተው ተመን እንደሚሆን በመግለጽ አከራይ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶት ተከራዩ ቤቱን ለቆ ካላስረከበ ተከራይ በኪራይ በቤቱ መገልገሉን እንዲቀጥል አከራዩ አለመፍቀዱን በማያሻማ ሁኔታ የሚያሳይ ቢሆንም ተከራይ ሊከፍል የሚገባውን የኪራይ ተመን በተመለከተ ውሉ ላለመራዘሙ ዋናው ምክንያት የኪራይ ተመን አለመግባባት ከሆነና ተከራይ የኪራይ ተመን መጨመርን በግልጽ ከተቃወመ ሊከፍል የሚገባው በማስጠንቀቂያው ላይ በተገለጸው የኪራይ ተመን ሳይሆን በቀድሞው ተመን ነው።
በዚህ መዝገብ ተከራይ ቤቱን ለ4 ዓመታት ተከራይቶ የውሉ ዘመን ሲያልቅ ቤቱን ለቆ እንዲያስረክብ የማያስረክብ ከሆነ የኪራይ ተመኑ ብር 80,000 እንደሚሆን በመግለጽ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ሊከፍል የሚገባው በ 20,000 ነው በሚል በሰበር ችሎቱ ውሳኔ ተሰጥቷል።
ሰ/መ/ቁ. 220884 ቀን ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ/ም
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/13
አዋጁ የፍርድ ቤት ውሣኔዎችንና ትዕዛዞችን ስለ መፈጸም እና ይህንኑ ትእዛዝ አለመፈጸም የሚያስከትለውን የወንጀል ቅጣት ያስቀመጠ ሲሆን ይህም በአዋጁ አንቀጸ 51 ላይ የፍርድ ቤት ውሣኔዎችንና ትዕዛዞችን በተመለከተ፤በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ እና ትዕዛዝ በህግ እስካልተለወጠ ድረስ የፀና ሆኖ ተፈፃሚ መሆን እንደለበት፤የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸዉን ዉሳኔዎች ወይም ትዕዛዞች በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ዉስጥ ተፈጸጻሚ እንደሚሆኑ፤በማንኛዉም ክልል ዉስጥ የሚገኝ የመንግስት አካል፣ ተቋም ወይም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም ማንኛዉም ሰው ውሳኔዎቹን ወይም ትዕዛዞቹን የመፈጸም እና የማስፈጸም ግዴታ እንዳለበት እና ማንኛዉም ሰዉ የፍርድ ቤት ውሣኔዎችንና ትዕዛዞችን የማይወጣ ከሆነ የወንጀል ተጠያቂነት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ አዋጁ በአንቀጽ 52 ስር የወንጀል ተጠያቂነት ያስቀመጠ ሲሆን ይህም፤-
 የፍርድ ቤት ወይም የዳኞችን በነጻነት መስራት የሚጋፋ ወይም በዳኞች ላይ ተጽእኖ የሚያደርግ ወይም ለማድረግ የሞከረ ማንኛውም ሰዉ በሌላ ህግ ከፍ ያለ ቅጣት ከሌለ በቀር ከሦስት ወር እሥራት ባላነሰ ከሁለት ዓመት ባልበለጠ ጽኑ እስራት እንደሚቀጠ እንዲሁም፤
 የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ወይም ዉሳኔ የማይፈጽም ወይም ለመፈፀም መሰናክል የሚፈጥር ወይም ሲጠየቅ ለመፈፀም ተባባሪ የማይሆን ማንኛዉም ሰዉ በሌላ ህግ ከፍ ያለ ቅጣት ከሌለ በቀር ከሁለት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ ገንዘብ እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡

ፍርድ ቤት ሰዎች ሕግን መከታ አድርገው መብታቸውን የሚያስከብሩበት እንደመሆኑ የፍርድ ቤቱን ክብር መጠበቅ የፍትሕ ሥርዓቱን ሕልውና ለመጠበቅ ፤እንዲሁም ኅብረተሰቡ በዳኝነት አካሉ ላይ ያለውን መተማመን ለመጠበቅ ፍርድ ቤትን ማክበር ወሳኝ ነው፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና የተዘጋጀ
ፍትህ ሚኒስቴር
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር የማስከፈያ ምጣኔዎች

በፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር የማስከፈያ ምጣኔዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚከተሉትን ይላል፡-

• ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡
• ቀጣሪ ማለት ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ለተቀጣሪው ደመወዝ የሚከፍል ሰው ነው፡፡
• ተቀጣሪ ማለት ደግሞ ራሱን ችሎ የሚሰራን የስራ ተቋራጭ ሳይጨምር በሌላ ሰው /በቀጣሪው/ መሪነትና ቁጥጥር ስር ሆኖ አገልግሎት ለመስጠት በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግለሰብ ሲሆን የድርጅት ዳይሬክተር፣ ወይም በድርጅቱ አመራር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ሌላ ሰው እንዲሁም ተሿሚንና የህዝብ ተመራጭን ጨምሮ የመንግስት ስራ ኃላፊን ያጠቃልላል፡፡