አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አማራጭ የህግ እውቀት  https://www.youtube.com/@Lawsocieties
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
የከፋው ጊዜ የሚመጣው የሞራል ህግ የጠፋ ጊዜው ነው!
Anonymous Poll
88%
እውነት
7%
ሀሰት
6%
የተለየ መልስ
አለሕግAleHig ️
Photo
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አለሕግAleHig ️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የግል ድርጅት ሠራተኞችን አስተዳደራዊ በደል የማየት ሥልጣን ተሰጠው
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የማሻሻያ አዋጅ የግል ድርጅት ሠራተኞችን አስተዳደራዊ በደል የማየት ሥልጣን የሚሰጥ መሆኑ ተገለጸ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን የማሻሻያ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቱ አለነ፤ የተቋሙን የማሻሻያ አዋጅ ዝርዝር ሁኔታና አስፈላጊነቱን በሚመለከት ለምክር ቤቱ አባላት በዝርዝር አቅርበዋል።

የተደረገው ማሻሻያ የአስተዳደር በደሎችን ለመከላከል እና ተፈጽሞ ሲገኝ ምርመራ በማካሄድ በደሎች በአፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል።

በተሻሻለው አዋጅ መሠረት የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሹመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ቀርቶ በዕንባ ጠባቂ ጉባዔ የሚመደብ መሆኑንም አስረድተዋል።

የተቋሙ መርማሪ በምርመራ ሥራ ላይ እያለ ዋና ዕንባ ጠባቂ ሳይፈቅድ ወይም ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር አይያዝም፤ አይከሰስም፤ እንዲሁም ያለመታሰር መብት እንዳለው በአዋጁ መደንገጉንም ገልፀዋል።

በተደረገው ማሻሻያ መሠረትም በመርማሪዎች ላይ ይደርስ የነበረውን ያልተገባ ጫና በማስቀረት ነፃነታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በግል ድርጅቶች የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችን የማየት ሥልጣን እንዳልነበረው አስታውሰው፤ በተሻሻለው አዋጅ ግን የማየት ሥልጣን የተሰጠው መሆኑን ገልፀዋል።

በተሻሻለው አዋጅ መሠረት የአስተዳደር በደል አቤቱታዎችን የመቀበል፣ የመመርመር እና ምክረ-ሃሳብ የማቅረብ ሥልጣን የተሰጠው መሆኑንም አስረድተዋል።

በተሰጠው ማብራሪያ ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የአዋጁን ማሻሻያ ተገቢነት በማመን በሙሉ ድምፅ አፅድቀውታል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ አዋጅ ቁጥር 1142/2011 በአዋጅ ቁጥር 1307/2016 ተሻሽሎ በምክር ቤቱ ፀድቆ ሥራ ላይ ውሏል።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሠራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

የጋዜጠኝነት ሥራ በባህሪው በየትኛውም ሰዓት ሥራ ላይ መሆንን የሚጠይቅ በመሆኑ እነሱን የሚመለከት ድንጋጌ ባካተተ መልኩ መሻሻሉ አስፈላጊ መሆኑ ተብራርቷል።

ኢቢሲ ብቃት ያላቸውን ሠራተኞች ይዞ ለማቆየት እና አዳዲስ ልዩ ችሎታና ክህሎት ያላቸውን ሠራተኞች ለመቅጠር እንዲችል ደንቡን ማውጣት አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል።

በዚህም መሠረት የኢቢሲ የሠራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን ደንብ ቁጥር 1/2016 ሆኖ በምክር ቤቱ በሁለት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።

ህዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም
****,
(ኢ ፕ ድ)
አማራጭ የህግ እውቀት  https://www.youtube.com/@Lawsocieties
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
አዲስ አበባ ሥራ አጦች📈

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ አጦች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ።

በመዲናዋ የሥራ አጦች ቁጥር በመቶኛ እየጨመረ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱትሪ ልማት ቢሮ የሥራ ዕድልና የሥነ ምግብ ዋስት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ ሰምቷል።

ለሥራ አጦች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ረገድ ያሉ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ እንዲያስረዱ ከቲክቫህ ኢትዮጵያና ሌሎች ሚዲያዎች ጥያቄ የቀረበላቸው ኃላፊው ተከታዮችን ነጥቦች አንስተዋል።

- ሥራ አጡ በጣም ሰፊ ነው።

- አዲስ አበባ የአገሪቱ ዋና ከተማ እደመሆኗ መጠንና አጎራባች አካባቢ ካለው የጸጥታ ችግርም አንፃር በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወደ ከተማ ውስጥ በሰፊው የሚገቡ አሉ። እዚህም የከተማውን ማህበረሰብ ከሥራ ዕድልም አንፃር የሚሻሙ ናቸው።

- የከተማው ወጣት አለ። የከተማው ሥራ አጥ የሥራ ዕድል በጥራትም በስፋት እዲፈጠርለት ይፈልጋል፤ በዚህ መካከል እኛ መፍጠር የምንችለው የሥራ እድል እና ከተማ ውስጥ ያለው የሥራ አጦች ቁጥር አይጣጣምም።

- የራሱ የከተማው ነዋሪ አለ፣ በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማ ውስጥ የሚገባም አለ። እነዚህን ሁለቱን አጣጥሞ የሚጠበቀውን ያክል የሥራ ዕድል መፍጠር በጣም ፈታኝ ነው።

- የሥራ አጥ ቁጥሩ አምና ስንጀምር ስብጥሩ በጣም ዝቅተኛ ነበር። ወደ 17 በመቶ አካባቢ የነበረው አሁን አድጎ ወደ 22 ነጥብ 8 በመቶ ደርሷል የሥራ አጥ ቁጥር ምጣኔው።

- እኛ በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ወደ አንድ ድርጅት እናወርዳለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው ነገር ግን እየጨመረ ነው የሚያሳየው። የዚህ መጨመር ምክንያቱ የተለያየ ቢሆንም አንደኛው ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ያለመቻልን ያሳያል።

- እኛ እየፈጠርን ያለነውና የሥራ ስምሪት ውስጥ የሚገባው ሥራ አጥ ቁጥሩ ሰፊ ነው ይሄ አልተመጣጠነም።

- የሰው ሀይላችን እስኪልድ ማን ፓወር አይደለም በጣም የሰለጠነ ብቁ ሞያተኛ የሆነ የሰው ሀይል እጃችን ላይ የለም።

-  የሰው ሀይላችን ሥራ አጡ በተለይ የትምህርት ደረጃው ዝቅተኛ ነው፤ ይህን ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ያለው የሰው ኃይል አሰልጥኖ የክህሎትና የሙያ ባለቤት አድርጎ ወደ ኢንስትሪዎቹ ማስተሳሰርን ይጠይቃል።

በሌላ በኩል ፤ ሥራ ያገኙ ሰዎች ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎች የሚከፈላቸው #ደመወዝ_በጣም_አነስተኛ በመሆኑ የቤትና ኪራይና አስቤዛ እንኳ ማሟላት እንደማይችል በተደጋጋሚ ቢገልጹም መፍትሄ እያገኙ እንዳልሆነ፣ ሥራ አጥ የሆኑትም የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ይደመጣል።

ይህንን በተመለከተ አቶ ፍስሃ ምን አሉ ?

" ኢንዱስትሪዎቹ የሚከፍሉት ደመወዝ ዝቅተኛ ነው የእነርሱ ምክንያት ደግሞ እምታቀርቧቸው ሰዎች ሙያቸው ከዚህ በላይ አያስከፍልም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ "  ብለዋል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ማብራሪያ ያገኘው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኅዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር  ልህቀት አካዳሚ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ለተገኙት አቶ ፍስሃ ጥበቡ ጥያቄ አቅርቦ ነው)

ጥንቅሩ በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
@tikvahethiopia
አማራጭ የህግ እውቀት 
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
የውሰት ነገር በሕግ ዓይን
“ዕቃ ከተዋሱ፣ መመለስ አይርሱ!”

“ስትዋስ ያሳየኸውን ትህትና ስትመልስም አትርሳ።”

እነዚህን ጥቅሶች የደጎቹ አዋሾች ምሬቶች ይወለዷቸው ይመስላሉ።

አዋሾች ደጎች ናቸው። የጠየቅናቸውን ነገር አልከለከሉምና ለውለታቸው መርቀናቸው መዋዋስን ወደ ሚመለከቱት በፍብሔር ሕጋችን ላይ ከቁጥር 2767 እስከ 2777 የተደነገጉት አንቀፆች ስለ ውሰት ሕጋዊ ግንኙኑት የሚሉንን እንመልከት።

1. የትውስት ውል

የምናውቃትን መዋዋስ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2767 በሌላው ስሟ ‘የመገልገያ ብድር’ ይላታል። መገለጫዋ አዋሽ ለተዋሹ አንድን የሚንቀሳቀስ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረቱን በነፃ እንዲገለገልበት የውል ግዴታ የሚገባባት ውል መሆኗ ነው። አውሳለሁ ብሎ ክፍያ መጠየቅ አይቻልም። ኪራይ ትከፍላለህ የሚል ቃል ካለ ነገሩ ውሰት ሳይሆን ኪራይ ነው።

2. የተዋስነው ነገር የማን ነው?

አደራ የኛ እንዳይመስለንና እንዳንዘናጋ! በእኛ እጅ (ይዞታ) ላይ ይቆይ እንጂ ባለቤቱ አዋሻችን ነው። ስለዚህ ጊዜው ሲደርስ ይመለሳል።

3. መቼ ይመለስ?

ከተዋስን መመለሳችን አይቀርም። መቼ ለሚለው በውሰት ውላችን ላይ የተስማማንበት ጊዜ ሲያልቅ ነው የምንመልሰው።

4. አዋሹ እንዲሁ በዝምታ ካዋሰንስ?

ይህም ቢሆን አንመልሰውም ማለት አይደለም። ልማዳዊ አሠራር ካለ ለምሳሌ ዕቃውን የፈለግንበት ጉዳይ ሲጠናቀቅ መመለስ አለብን። መቼ እንደምንመልስ የሚጠቁም ልማዳዊ አሠራር ከሌለ ደግሞ አዋሹ እስኪጠይቀን መጠቀም እንችላለን። እንደጠየቀን ግን ወዲያውኑ መመለስ አለብን።

5. አጠቃቀም

የተዋስነውን ዕቃ በሚገባ መጠበቅ አለብን። ወጪ የሚያስወጣ ከሆነም ወጪውን የምንችለው ተዋሾች ነን።
👇👇👇👇👇
👆👆👆👆👆👆👆 የቀጠለ ........

6. እንደ ባለቤት አንሁን

በውል ከተስማማንበት ጉዳይ ውጭ በተዋስነው ንብረት መገልገል አይፈቀድልንም። ለምን እንደምንጠቀምበት በውሰት ውሉ ላይ ባንስማማም እንኳን የዕቃው ተፈጥሮ ከሚፈቅደው ውጭ መጠቀም አንችልም።

ሌላ አንድ ነገር እናስታውሳችሁ፤ ምንም ያህል ደግ ብትሆኑ የተዋሳችሁትን ዕቃ አዋሻችሁ ካልፈቀደ በስተቀር ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት አይቻልም።

በተዋስነው ዕቃ ከመጠን በላይ በመገልገላችን ወይም ለሌላ ሰው ያለአግባብ በመስጠታችን ዕቃው ከተበላሸ የመተካት ወይም ብልሽቱን የማስጠገን ግዴታ አለብን።

ሆኖም እኛ የተዋሽነት ግዴታችንን ብንወጣም ዕቃው ከመበላሸቱ እንደማይድን በቂ ማስረጃ ካቀረብን ለብልሽቱ ተጠያቂነት ሊቀርልን ይችላል። በጣም ከአቅም በላይ ችግር ገጥሞን ከራሳችን ዕቃ እና ከተዋስነው አንዱን መምረጥ ግድ ሆኖብን የራሳችንን ዕቃ አትርፈን የተዋስነው ዕቃ ከጠፋ ለራሳችን አድልተነልና ኃላፊነቱ አይቀርልንም። የትውስት ውሉ የዕቃውን ዋጋ ከጠቀሰ ዕቃው በማናቸውም መልኩ ቢጠፋም ተጠያቂ ነን። የዕቃው ዝርዝር በውሉ ላይ ካልተጠቀሰ ግን ስትረከበው በመልካም ሁኔታ እንደነበረ ይቆጠራልና በተረከብነው መልኩ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ማስረከብ አለብን።

7. የተዋሽ እና የአዋሽ መብት

እንበልና ለ6 ወር የተዋስነውን ዕቃ በ2ኛው ወር ጉዳያችንን ስለጨረስን በቃን። የግድ 4 ወር ሙሉ መጠበቅ የለብንም፤ ለባለቤቱ መመለስ እንችላለን። ሆኖም ዕቃውን ያለጊዜው መመለሳችን ባለውለታችን የሆነው አዋሻችን ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ባንፈልገውም የተዋስንበት የጊዜ ቆይታ እስኪያልቅ መጠበቅ ሊኖርብን ነው።

አዋሻችን ደግሞ የተዋስንበት ጊዜም ባያልቅ ከፈቀደልን ሁኔታ ውጭ በዕቃው ከተጠቀምን፣ ዕቃውን ካበላሸን፣ ለሌላ አሳልፈን ከሰጠን ወይም አዋሻችን ለራሱ በአስቸኳይ እና በድንገት ዕቃውን ከፈለገው እንድንመልስለት ሊያስገድደን ይችላል።

8. ሞት ከመጣስ?

አያድርገውና የተዋስነውን ነገር ሳንመልስ ከሞትን አዋሻችን ለረጅም ጊዜ ፈቅዶልን የነበረ ቢሆንም ጊዜው ሳይደርስ ወራሾችን ዕቃውን እንዲመልሱለት መጠየቅ ይችላል። አዋሹ ያዋሰው ዕቃ ሳይመለስ ከሞተ ደግሞ ውርሱ ሲጣራ ያዋሰው ዕቃ መኖሩ ከታወቀ ወደ ውርሱ ሀብት ተካቶ ለወራሾች ይከፋፈላል።

አዋሽም ሆነ ተዋሽ ጋብቻ ካላቸው ከ500 ብር በላይ የሆነ ነገር ለማዋስም ሆነ ለመዋስ የባልየው ወይም የሚስትየው ስምምነት እንደሚያስፈልግ በተሻሻለው የፌዴራሉ የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 68 (መ) ላይ ተደንግጓል።

በመጨረሻም በዚህ መልዕክት ጽሑፋችንን እንቋጨው፤

ስንዋዋስ ምስክር ባለበት፣ የፈቀድነውን የአገልግሎቱን ዓይነት ጠቅሰን፣ መቼ እንደሚመለስ ተስማምተን ቢሆን ይመረጣል። የምንዋዋሰው ትንሽ ዋጋው ጠንከር ያለ ንብረት ከሆነ ደግሞ የዕቃው ዋጋ እና ልዩ መለያው ቢጠቀስ፣ የውሰት ውሉም በጽሑፍ ቢሆን ጥሩ ነው።

ለማንኛውም የጠንካራ ማኅበራዊ ሕይወታችን መገለጫ ነውና መዋዋሳችን እንቀጥላለን። ቸር እንሰንብት!
EBC
አማራጭ የህግ እውቀት 
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ማስታወቂያ
በረዳት ዳኝነት ተመዝግባችሁ መስፈርቱን በማሟላት ተመርጣችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች የተገለፀው አመልካቾች ለህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 3፡30 ለፈተና እንድትቀርቡ የተጠራችሁ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን
ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ማስታወቂያ👇👇👇👇👇👇👇👇
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በዕጩ ዓቃቤ ሕግነት አወዳድሮ ለመቅጠር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማውጣቱን ተከትሎ  መስፈርቱን ያሟሉ አመልካቾችን መመዝገቡ ይታወቃል።
በመሆኑም እሁድ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በቦሌ ክፍለከተማ ቅጥር ጊቢ ውስጥ  ፈተና የሚሰጥ  መሆኑን ተመዝጋቢዎች ይህንን ተገንዝባችሁ በተባለው ቀን እና ቦታ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያችሁን በመያዝ እንድትገኙ  እንገልፃለን።
አማራጭ የህግ እውቀት 
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
አለ_ህግ Ale_Hig
አለህግ Alehig
@Lawsocieties

@Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Legal Solutions for Everyone, Provided by Legal Experts.
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ህግ ባለሙያዎች መገኛ