ማስታወቂያ
ለፌዴራል የማናቸውም ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 1249/13 አንቀፅ 16/2/ እና 21/3/ በተደነገገው መሰረት የጥብቅና ፈቃድ መግቢያ ፈተና መውሰድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ መመዝገብ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን።
1. የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው ወይም ትውልደ ኢትዮያዊ/ዊት/ የሆነ/ች/፣
2. በሕግ ዕውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በሕግ በዲግሪ የተመረቀ/ች፣
3. የትምህርት ማስረጃ ዲግሪ ከኢትዮጲያ ውጪ የተሰተጠ ከሆነ የዲግሪውን አቻ ግምት ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል፣
4. በኢትዮጵያ ውስጥ ከመንግስት መስሪያ ቤት ወይም ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ባሉ ተቋማት በህግ ለአምስት ዓመት ያገለገለ እና ያለፈተና ፍቃድ ለመውሰድ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ /ስራውን ከለቀቀ አንድ ዓመት /ያለፈው አንቀፅ 16/2፣
5. በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት መስሪያ ቤት ወይም በመንግስታዊ የልማት ድርጅቶች ውጪ ባሉ የግል ድርጅቶች /ተቋማት/ በህግ ሙያ ለሰባት ዓመት ያገለገለና ስራውን ከለቀቀ አንድ ዓመት ያለፈው እና የሚቀርበው የሥራ ልምድ ግብር የተከፈለበት መሆኑ ማረጋገጫ የሚያቀርብ፣
6. የጥብቅና ፍቃዱን በአደራ መልሶ ከህግ ሙያ ውጪ በሆነ ስራ ላይ ከሁለት አመት በላይ ተሰማርቶ የቆየ፣
7. የህግ ሙያ ስራውን በሚሰራበት ጊዜ ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በከባድ ዲሲፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ እና የመልካም ሥነ ምግባር ያለው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
8. ትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ የሚያቀርብ፣
9. ማንኛውም በሌላ ቋንቋ የተሰጠ የስራ ልምድና የስነ ምግባር ማስረጃ በአማርኛ ተተርጉሞ መቅረብ አለበት።
10. የመመዝገቢያ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/የሚከፍል፣
ማሳሰቢያ፡-
የመመዝገቢያ ቀን፡- ከሰኔ 09 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት ብቻ ነው።
የመመዝገቢያ ቦታ፡- በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትህ ሚኒስቴር በጥብቅና ፈቃድ እና ነፃ የህግ ድጋፍ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ ቢሮ፡፡
ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የሚሰጥ ይሆናል።
ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡- ምዝገባው በሚካሄድበት ወቅት የሚገለፅ ይሆናል፡፡
የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር
FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ አዋጅን አጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1294/2015 በአብላጫ ደምፅ አጸደቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስበሰባ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ በሚመለከት ሰፊ ውይይት አድርጓል።
የሰው ሀብት ልማት የሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አዋጁን ለማፅደቅ የቀረቡ የውሳኔ ሀሳቦችን አቅርበዋል።
ረቂቅ አዋጁ ለሀገር ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራና በምርምር የላቀ እውቀት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት የሚሰሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ላይ የሚገኘው parol evidence rule በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ በሚታመንበት ጊዜ ተፈጻሚነት የለውም። የውሉ ይዘት ለምሳሌ የገንዘቡ መጠን፡ በውሉ ላይ ያለው ቀን ወዘተ በሌላ ውጫዊ ማስረጃ ሊስተባበል ይችላል።
በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ ታምኖ የውሉ ይዘት ፊርማን ጨምሮ በአከራከረ ጊዜ በምን አይነት ማስረጃ ሊረጋገጥ ይገባል? የሚለው ጥያቄ በተመለከተ የሰበር ችሎት የሚከተለውን የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
የቤት ሽያጭ ውል በሕግ ሥልጣን በተሰጠው ውል አዋዋይ ፊት መደረግ አለበት በሚል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገበት አንዱ አላማ ውሉ በጽሁፍ በሰፈረው አግባብ በእርግጥ የተደረገ ስለመሆኑ እና ይዘቱም እምነት የሚጣልበት መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡በመሆኑም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ስር በጽሑፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ የተጻፈው ቀን በፈራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው የሚለው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678/ሐ፣1719/2 እና 1723/1 ስር በተደነገገው መሰረት በሕግ የታዘዘውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ ለተደረገ ውል እንጂ ለማንኛውም ውል አይደለም፡፡

የጥቅም ግጭት (conflict of interest)
በሰዎች ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ መስተጋብራቸው ውስጥ የጥቅም ግጭቶች ይፈጠራሉ፡፡ ሰዎች መንግስታዊ በሆኑ ተቋማት፤ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በግል ዘርፉ ተሰማርተው ይሰራሉ፡፡ ተቋማት የራሳቸዉ ህግ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ይኖራቸዋል፡፡
በተቋማት ማቋቋሚያ ህጎች ውስጥ የሰራተኞችን እና የአሰሪዎቸቸውን ስልጣን እና ተግባር ይወስናሉ፡፡ ነገር ግን ተቋማት ዝርዝር በሆኑ መመሪያዎችና ደንቦቻቸው ውስጥ የሰራተኞችን እና ኃላፊዎችን መብትና ግዴታዎችን፤ የተፈቀዱ እና የተከለከሉ ተግባራትን ያስቀምጣሉ፡፡ መሠረታዊ ዓላማው ተጠያቂነትና ኃላፊነትን ለማስፈን ነው፡፡ የጥቅም ግጭት ኃላፊነትን ሊያስከትል የሚችል አንዱ መሰረታዊ ፍሬ ጉዳይ ነው፡፡ በተቋምና በሠራተኛዉ እንዲሁም በተቋምና በሃላፊዉ መካከል የጥቅም ግጭት ቢፈጠሩ በህግ አግባብና የጥቅም ግጭት እንዳይፈጠር ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች ለመዳሰስ ይሞከራል፡፡
የጥቅም ግጭት ጽንሰ ሀሳብ
ጥቅም ለሚለዉ ቃል ወጥ የሆነ ትርጉም ማስቀመጥ የሚያስቸግር ነው፡፡ በተለያዩ ህጎች ውስጥ ጥቅም የተለያየ ትርጉም ተቀምጦለታል፡፡ የጥቅም ግጭት ማለት አንድ የመንግስት ሰራተኛ ወይም ኃላፊ በስራ ተግባር እና ኃላፊነቱ ዉስጥ ከህዝብ ወይም ከመንግስት ፤ ከሀገር ጥቅም ይልቅ የግሉን፤ የቤተሰቡን፤ የራሱን ቡድን ጥቅም ማስቀደም ማለት ነዉ፡፡ በሌላ አነጋገር የመንግስት ሰራተኛዉ ወይም ኃላፊዉ በስራ ኃላፊነት እና ዉሳኔ ሂደት ውስጥ ገንዘብ ወይም ሌላ ጥቅም ሲያገኝ በዚህ ምክንያት የስራ ኃላፊነቱን ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ ሲመራ የጥቅም ግጭት ተከሰተ ይባላል፡፡ የጥቅም ግጭት ከወንጀል ተግባር ጋር ተያይዞ የሚታይበት የህግ አግባብ አለ፡፡ በአንዳንድ ህጎች የጥቅም ግጭትን ከገንዘብ ጥቅም፣ መብት ከማግኘት እንዲሁም መሻሻልን እንደ ጥቅም የተወሰደበት አግባብ አለ፡፡
ለምሳሌ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13 ጥቅም ማለት በገንዘብ ወይም በማናቸውም ዋጋ ባለው መያዣ ወይም በሌላ ንብረት ወይም በንብረት ላይ ያለን ጥቅም (መብት)፤ ማንኛውንም ሹመት፣ ቅጥር ወይም ውል፤ብድርን፣ ግዴታን ወይም ማናቸውንም ዕዳ በሙሉም ሆነ በከፊል መክፈልን፣ ማስቀረትን፣ ማወራረድን፣ ወይም ከእነዚህ ነገሮች ነፃ ማድረግን፤ ከተመሰረተ ወይም ካልተመሰረተ የአስተዳደር፣ የፍትሐብሔር ወይም የወንጀል ክስ ወይም ካስከተለው ወይም ከሚያስከትለው ማናቸውም ቅጣት ወይም የችሎታ ማጣት በማዳን ወይም ይህን በመሰለ ዘዴ የሚደረግን አገልግሎት ወይም ውለታ፤ ማናቸውንም መብት ወይም ግዴታ መፈጸምን ወይም ከመፈጸም መታቀብን፤ በገንዘብ የማይተመን ማናቸውንም ሌላ ጥቅም ወይም አገልግሎት በተመለከተ የሚገኝ እንደ ጥቅም ተደርጎ ተወስዷል፡፡ በዚህ መልኩ የተገኘ ጥቅም ከጥቅም ግጭትነቱ ባለፈ የወንጀል ኃላፊነትን ጭምር የሚያስከትል መሆኑ ተደንግጓል፡፡
ይሁን እንጂ የጥቅም ግጭት እንደየተቋማቱ ህጎች የሚለያይ ሲሆን በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ በአንድ ተቋም ስር የሚተዳደሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች የተሰጣቸውን ስልጣንና ተግባር በመጣስ የሚያስተዳድሯቸውን ተቋም ጥቅም የሚጎዳ ተግባር ወይም ሊያጋጭ የሚችል ተግባር ፈጽመዉ ሲገኙ የጥቅም ግጭት የሚፈጠር መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድሩ ተቋማት የሰራተኞችን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር ፈጸመዉ ሲገኙ የጥቅም ግጭት የሚፈጠርበት ሁኔታዎች አሉ፡፡
የጥቅም ግጭትን በአይነት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም በብዛት የሚከሰቱ የጥቅም ግጭቶች አራት ሲሆኑ እነዚህም የሚከተሉት ናቸዉ፡ የገንዘብ ጥቅም ፍለጋ ግጭት፤ የውጭ ስራ ጥቅም ግጭት፤ የቀረቤታ ስራ የጥቅም ግጭት እና የስጦታ የጥቅም ግጭት ናቸው፡፡
የገንዘብ ጥቅም ፍለጋ ግጭት፡- አንድ የመንግስት ሰራተኛ ወይም ኃላፊ በተሰጠዉ ኃላፊነት አጋጣሚዎችን በመጠቀም ለግል የገንዘብ ማግኛ አድርጎ ሲገለገልበት ነዉ፡፡ በአንድ በኩል ከተሰጠዉ የስራ ኃላፊነት ውጭ የሚሰራ የውጭ ስራ ጥቅም ግጭት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለምሳሌ አንድ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የመንግስት ሰራተኛ በመንግስት የስራ ሰዓት ከተሰጠዉ የስራ ኃላፊነት ውጪ በግሉ ሲሰራ ሲገኝ የጥቅም ግጭት ተፈጠረ የሚያስብል ነው፡፡
በሌላ በኩል የጥቅም ግጭት በመቀራረብና በመግባባት ይፈጠራል፡፡ አንድ የመንግስት ሰራተኛ በመንግስት መ/ቤት ውስጥ ሲሰራ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በመቀራረብ፣ በዝምድና፣ በትውዉቅ በመመስረት አገልግሎት ሲሰጥ ቢገኝ በቀጥታ የጥቅም ግጭት ይከሰታል፡፡
ስጦታ ወይም ግብዣ መቀበል ወይም መስጠት አንዱ የጥቅም ግጭት መንስኤ ነው ፡፡ የመንግስትን የአሰራር ሂደት ሊያደናቅፍ የሚችል ስጦታ መስጠት እና መቀበልን የጥቅም ግጭት ዉስጥ ያስገባል፡፡ ይህ ሁኔታ ባለጉዳዩ በሂደት ለሚፈልገዉ ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ላልሆነ አገልግሎት ተጽዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል የጥቅም ግጭት ይፈጥራል፡፡ በእነዚህ ሁኔታዎች የሚፈጸሙ የሰራተኞች ወይም የኃላፊዎች የጥቅም ተግባራት የድርጅቱን ወይም መስረያ ቤቱን ጥቅም ሊጎዱ የሚችሉ ሁኔታዎች ናቸው፡፡
በጉልህ ከሚታዩ የጥቅም ግጭቶች አንዱ በውክልና ሰጭና ተቀባይ መካከል በሚደረጉ የስራ ግንኙነት አንዱ ነዉ፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፤ የግል ድርጅቶች እና ግለሰቦች ለስራ ወይም ለማናቸውም ጉዳይ ዉክልና ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ በወካይ ተወካይ ሂደት ውስጥ የጥቅም ግጭቶች ሲፈጠሩ ይስተዋላል፡፡ ተወካይ በተሠጠው የውክልና ሥልጣን መሠረት የወካይን መብት የማስጠበቅና የራሱን የጥቅም በማስጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን ዉክልናውን መሰረት አድርጎ ከውሉ ውጭ የግል ጥቅሙን የሚያራምድ ከሆነ ከወካዩ ጥቅም አንጻር ግጭት ይፈጠራል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ወካዩ ውክልናውን ማንሳት ሙሉ ስልጣን እንዳለው በፍትሐብሔር ህግ ሥር ተደንግጎ ይገኛል ፡፡
በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2187(1) መሰረት ተወካይ ከ3ኛ ወገን ጋር በፈፀመው ውል ምክንያት የወካዩና የተወካዩ ጥቅሞች የሚጋጩ የሆኑ እንደሆነና ይህን ውል የፈረመው 3ኛ ወገን ይህን ሁኔታ ያወቀና ሊያውቀውም የሚገባ የሆነ እንደሆነ በወካዩ ጥያቄ መሠረት ይህ በተወካይና በ3ኛ ወገን መካከል የተፈፀመው ውል ሊፈርስ ይችላል፡፡ ወካዩም ከላይ የተገለፀውን አይነት የጥቅም ግጭት መፈጠሩን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ውሉን ለማፍረስ አሳቡን ማስታወቅ እንዳለበት የፍ/ብ/ህ/ቁ 2187(2) ይደነግጋል፡፡
የጥቅም ግጭት መኖሩ ተረጋግጦ 3ኛው ወገንም ይህን የጥቅም ግጭት ያወቀው መሆኑ ሲረጋገጥና ወካዩ የፍትሐብሔር/ህግ/ቁ 2187(1) 2187(2) መሠረት የውል መፍረስ ሃሳቡን ቢያሳውቅ እና በቁጥር 2187(3) መሠረት 3ኛው ወገን የውሉን መቀጠል መፈለጉን ቢያሳውቅ የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም ማስጠበቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2187(1) መሰረት ፍርድ ቤት ሁኔታዎችን ተመልክቶ ውሉን ሊያፈርሰው ይችላል፡፡ ስለሆነም ወካዩ ያጣቸውን ጥቅሞች በህጉ መሠረት የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ በሌሎች ህጎች የተጠቀሱ በርካታ የጥቅም ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሁኔታዎች እንዳሉ ልብ ሊባል ይገባል፡፡

የጥቅም ግጭትን ከግል ማህበራት አንጻር መመልከት ሌላ ጠቃሚ ጉዳይ ነዉ፡፡
ማህበራት በንግድ እና እንዱስትሪ ሚኒሰቴር በኩል አስፈላጊዉን መሰፈርት ሲያሟሉ ይቋቋማሉ (አዋጅ ቁጥር 985/2009)፡፡ ማህበራት የሚተዳደሩበት የራሳቸዉ መተዳደሪያ ህግ /memorandum of association/ አላቸዉ፡፡ የማህበራት ዝርዝር የስራ አፈጻጸሞች በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 ተመላክቷል፡፡ ስለሆነም በአንቀጽ 217 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ሌሎች የማህበሩ ሸሪኮች ካልፈቀዱ በስተቀር ማንኛውም ኃላፊነቱ ያልተወሰነ ሸሪክ ማህበሩ የሚሠራቸውን ተመሳሳይ ሥራዎች ለራሱ ወይም ለሦስተኛ ወገን ለማከናወን እንዱሁም በአንድነትና በተናጠል ኃላፊ በሚያደርግ ተመሳሳይ ዓላማ ባለው ሌላ ማህበር ውስጥ አባል መሆን አይችልም ሲል ይደነግጋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አባል በሆነበት ድርጅት ጋር የጥቅም መጋጨት እንዳይፈጠር ለመከላከል ዓላማ ነው፡፡
በአጠቃላይ ማንኛውም ሰራተኛ ከተጣለበት ሃላፊነት ውጭ ለግሉ፤ ለቤተሰቡ፤ ለወዳጁ እንዲሁም ለማናቸውም ዓላማ ሲባል ከተቋሙ ጥቅም የሚጋጭ ተግባር መፈጸም የተከለከለ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ይህ የጥቅም ግጭት ተቋሙን ከመጉዳት አልፎ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ወይም ብልጽግና አስገኝቶ ከሆነ አግባብ ባለዉ ህግ የሚያስጠይቅ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በየትኛዉም ደረጃ ያለ ሰራተኛ ለተቀጠረበት ተቋም ተገቢዉን አገልግሎት በመስጠት ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፡፡ በተቋሙ ዉስጥ እያገለገለ/ች ከስራው/ዋ ጋር በተገናኘ ለሚፈጠር ጥቅም ራሱን በማግለል ታዓማኒነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡
በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

Forwarded from አለሕግAleHig ️ (ጉዳይ አስፈፃሚ🔷issue executor (Guday Asfetsami))
የሞባይል ስልኩ ግድብ ውስጥ የገባበት ባለስልጣን 2 ሚሊየን ሊትር ግድብ ውሃ እንዲለቀቀ አደረገ
ባለስልጣኑ ስልጣንን አለአግባብ በመጠቀም በሚል ከስራ ታግዷል። ለባለስልጣኑ ስልክ ሲባል ከግድብ የፈሰሰው ውሃ ከ6 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መስኖ የማልማት አቅም ነበረው።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/official-drains-dam-retrieve-phone

አል ዐይን ኒውስ
የሞባይል ስልኩ ግድብ ውስጥ የገባበት ባለስልጣን 2 ሚሊየን ሊትር ግድብ ውሃ እንዲለቀቀ አደረገ
ለባለስልጣኑ ስልክ ሲባል ከግድብ የፈሰሰው ውሃ ከ6 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መስኖ የማልማት አቅም ነበረው
ዳኝነትን የሚመለከቱ አባባሎች፣ ተረትና ምሳሌዎች፣
1) ዳኛ ቢያጋድል በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ፣
2) ዳኛ ለዳኛ ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል፣
3)ዳኛ ምን ያደላ ከተረታው ሊበላ፣
4)ዳኛ ሲመረምር ከራስ ይዞ እስከ እግር፣
5)ዳኛ ሲቆጣ ማር ይዞ ከደጁ፣
6)ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር፣
7)ዳኛ ስበር በእጅ ክበር፣
8)ዳኛ ቢንቁ የተያዘ እህል ይወቁ፣
9)ዳኛ አውጥቼ ዘንግ አቅንቼ፣
10)ዳኛ አይነቀፍ እሳት አይታቀፍ፣
11) ዳኛ ካዳላ ጭነት ቀላል፣
12) ዳኛ የወል ምሰሶ የማሃል፣
13) ዳኛ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት፣
14) ዳኛ የፈረደው ስለት የቀደደው፣
15) ዳኛ ያደላበት እሳት የበላበት፣
16)ዳኛ ያፈሰሱለት ፈረስ የከሰከሱለት፣
17) ዳኛ ይመረምራል ጣዝማ ይሰረስራል፣
18) ዳኛ ፍርድ አይከላ እህል ጎታ ይሞላ፣
19) ዳኛና በሬ ሀብታም ናቸው፣
20) ዳኛን ቢንቁ የተያዘ እህልን ይወቁ፣
21)ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ ይገናል ነገሩ፣
ሌሎች ካሉ ጨምሩ
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
1) ዳኛ ቢያጋድል በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ፣
2) ዳኛ ለዳኛ ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል፣
3)ዳኛ ምን ያደላ ከተረታው ሊበላ፣
4)ዳኛ ሲመረምር ከራስ ይዞ እስከ እግር፣
5)ዳኛ ሲቆጣ ማር ይዞ ከደጁ፣
6)ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር፣
7)ዳኛ ስበር በእጅ ክበር፣
8)ዳኛ ቢንቁ የተያዘ እህል ይወቁ፣
9)ዳኛ አውጥቼ ዘንግ አቅንቼ፣
10)ዳኛ አይነቀፍ እሳት አይታቀፍ፣
11) ዳኛ ካዳላ ጭነት ቀላል፣
12) ዳኛ የወል ምሰሶ የማሃል፣
13) ዳኛ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት፣
14) ዳኛ የፈረደው ስለት የቀደደው፣
15) ዳኛ ያደላበት እሳት የበላበት፣
16)ዳኛ ያፈሰሱለት ፈረስ የከሰከሱለት፣
17) ዳኛ ይመረምራል ጣዝማ ይሰረስራል፣
18) ዳኛ ፍርድ አይከላ እህል ጎታ ይሞላ፣
19) ዳኛና በሬ ሀብታም ናቸው፣
20) ዳኛን ቢንቁ የተያዘ እህልን ይወቁ፣
21)ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ ይገናል ነገሩ፣
ሌሎች ካሉ ጨምሩ
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የዋስትና መብት
የዋስትና መብት ማለት በወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ የሚያዝ ሰዉ ከእስር የሚፈታበት ስነ-ስርዓት ነዉ። ማንም ሰዉ ከህጉ ዉጪ መታሰር የለበትም የሚለዉን የህገ መንግስቱ ድንጋጌ የሚረዳ መብት ነዉ። ዋስትናም ፍርድ ቤት ከመቅረብ በፊት ወይም በኋላ ለሰጥ ይችላል። በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ አንቀጽ 28 መሰረት ጽኑ እስራት የማያስቀጣ ወንጀል፣ወንጀል ስለመፈጸሙ ጥርጣሬ ካለ እና ተጠርጣሪዉ ወንጀሉን እንደፈጸመ አጥራጣሪ ከሆነ ፍርድ ቤት መቅረብ ሳያስፈልግ ፖሊስ በዋስትና መልቀቅ እንደሚችል ይደነግጋለ። በዚሁ ህግ አንቀጽ 63 ስር ደግሞ ፍርድ ቤት ሞት ቅጣት ወይም 15 አመት እና ከዛ በላይ ጽኑ እስራት የማያስቅጣ ወንጀል ከሆነ እና ተጎጂዉ ካልሞተ ዋስትና አስፈርሞ መልቀቅ እንደሚችል ያስቀምልጣ።
ዋስትና የሚከለከልባቸዉ ሁኔታዎች
በወ/መ/ስ/ስ/ህግ መሰረት ተጠርጣሪዉ
-ግዴታዉን እንደማይወጣ ከታወቀ
- ቢለቀቅ ሌላ ወንጀል ይፈጽማል ተብሎ ሲገመት
-ማስረጃ ያጣፋል ወይም ያሸሻል ተብሎ ከታመነ
- በዚህ ህግ አንቀጽ 63 እና 28 ላይ የተገለጸዉ በተቃራኒ ተሙዋለቶ ከተገኘ
ከልዩ ህጎች ለምሳሌ የጸረ-ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007 መሰረት
-ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጣ ወንጀል ከሆነ
-ከ4 አመት በላይ እና ክ10 አመት በታች የሚያስቀጡ ወንጀሎች በተደራራቢነት ተፈጽመዉ ድምራቸዉ ክ10 አመት በላይ ካስቀጣ ዋስትና አይፈቀድም።
ከዚህም በተጨማሪ በሌሎች ልዩ ህጎች በተቀመጡ ምክንያቶች ዋስትና ሊከለከል ይችላል።
ስለ ዋስትና ህግ የሚደነግጉ ህጎች
1. ህገ-መንግስት (አንቀጽ 19)
2. የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ (አንቀጽ 28፣ ከ 63-79)
3. የጸረ-ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007
4. የሰበር ዉሳኔዎች ለምሳሌ ያህል ቅጽ 19 መ/ቁጥር 112725
እና የመሳሰሉት ናቸዉ።
የዋስትና መብት በምን ሊቁዋረጥ ይችላል?
1. ክስ ሲቁዋረጥ
2. በመደበኛ ክርክር ዋስትና ሲያዝ የጊዜ ቀጠሮ
3. ከወንጀል ነጻ መባል
4. ጥፋተኝንት ዉሳኔ ተሰጥቶ ተከሳሹ ቅጣቱን እየፈጸመ ፍ/ቤቱ ዋስትና ይመለስ ሲል
5. የዋስትና ይዉረድልኝ ተብሎ ዋሱ ተከሳሹን በችሎት ሲያቀርብ
6. ዋሱ ሲሞት
7. የዋስትና ግዴታ ሳይፈጸም ሲቀር
8. በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 74 መሰረት አዲስ ማስረጃ /ጉዳይ/ሲገኝ እና የመሳሰሉት ናቸዉ።
የዋስትና መያዣ መጠን በምን ይወሰናል?
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 69 መሰረት
1. የወንጀሉ ክብደት
2. ተጠርጣሪዉ መለቀቁ ለህዝብ አስጊ ከሆነ
3. ተጠርጣሪዉ በተፈለገ ጊዜ የማይቀርብ መሆኑ
4. የተከሳሹ እና የዋሶቹ ሀብት ከግምት ይገባሉ።
የዋሶች ግዴታ
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 70፦ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ተከሳሹ ፍ/ቤት እንዲቀርብ ማድረግ።
ለዋስትና መያዣነት ምን ሊጠየቅ ይችላል?
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 69 ስር የተጠቀሰዉ ከግምት ገብቶ
1.ጥሬ ብር
2. የማይንቀሳቀሱ ወይም ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች
3. የስራ ዋስ።
የአካሌ ነጻ ይዉጣልኝ ክስ የት ይቀርባል?
ፖሊስ ማንኛዉንም ተጠርጣሪ 48 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ በአቅራቢያዉ ወዳለ ፍ/ቤት ማቅረብ እንዳለበት ህጉ ያስቀምጣል። ይህንም ሳያረግ ከቀረ ተጠርጣሪዉ ሆነ ሌላ ሰዉ ወክሎት አካሌ ነጻ ይዉጣልኝ ማቅረብ እንደሚችሉ የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ አንቀጽ 177 ጀምሮ ያለዉ ይደነግጋል። ይህን መሰሉንም ክስ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መቅረብ እንዳለበት የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በአንቀጽ 11(3) ላይ ያስቀምጣል።
የቦሌ/ክ/ከ/የህ/ስ/ህ/ማ/ዳይሬክቶሬት
ዐ/ህግ ዉብአለም መስፍን

አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል !
ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች።
ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው።
በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ።
ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ተቀባይንት ያገኘ ሲሆን፣ ማሻሻያ እንዲደረግበት ለፓርላማው ተመልሶ ቀርቦ ነበር።
ቀደም ሲል ቀርቦ በነበረው ረቂቅ ሕግ ላይ ማንኛውም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም ከዚሁ ጋር በተያያዘው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ የሚያደርግ ነበር።
ሆኖም ግም ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ይህ ሰዎች እንዲታሰሩ እና በአካላዊ ገጽታቸው ብቻ እንዲከሰሱ ያደርጋል ሲሉ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ረቂቅ ሕጉ እንዲሻሻል ወደ ፓርላማ መልሰውት ነበር።
በዚህ መሠረት ተሻሽሎ አሁን ላይ የቀረበው ረቂቅ ሕግ፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀልነት ወንድ ከወንድ ጋር በሚያደርገው ወሲባዊ ድርጊቶች ላይ የተወሰነ ሆኗል።
ይህንን ሕግ ተላልፈው የተገኙም እስከ እድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል።
ለከባድ ወንጀሎች ማለትም ወሲባዊ ጥቃቱ #በሕጻናት_ላይ ፣ በአካል ጉዳተኛ እንዲሁም ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ በሚፈፀምበት ጊዜ አሊያም የጥቃት ሰለባዎቹ ለዕድሜ ልክ ህመም የሚዳረጉ ከሆነ በድርጊቱ ፈፃሚ ላይ #የሞት ቅጣትን ይደነግጋል።
ማኅበረሰቡ #በሕጻናት ወይም በሌሎች ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰቡ አባላት ላይ ማንኛውንም ዓይነት የተመሳሳይ ጾታ ጥቃት በሚያዩ አልያም በሚሰሙበት ጊዜ ለባለሥልጣናት ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ዘግቧል።
በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ቀድሞም ሕገ ወጥ ተደርጎ ነው የቆየው ፤ ይህ ሕግ ከሕገ ወጥነቱ አልፎ ነገሩን ወንጀልና በተራዘመ እስር የሚያስቀጣ ያደርገዋል።
#ምዕራባውያን ሀገራትና #ተቋማት በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ በዩጋንዳ ፓርላማ የተላለፈውን ውሳኔ ሲቃወሙና ፕሬዜዳንቱ #እንዳይፈርሙ ሲያሳስቡ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
@tikvahethiopia