አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
መጥሪያ አደራረስ ሥነ -ሥርዓት እና ውጤቱ
በፍትሐብሕር ጉዳይ ተከሣሽ ለሆነ ወገን ከፍ/ቤት የሚላከውን መጥሪያ ለተከሳሹ ሊደርስ የሚችልበትን የተሻለ አማራጭ መንገድ በመለየት ሊላክ ይገባል፡፡ የመኖሪያ አድራሻው በግልፅ ለሚታወቅ ተከሳሽ ፍ/ቤቱ የሚልከውን መጥሪያ በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ብቻ እንዲለጠፍ በማድረግ ተከሳሹ አልቀረበም በሚል በሌለበት ጉዳዩ እዲታይ የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢነት የለውም፡፡  በዚህ መንገድ በአግባቡ መጥሪያ እንዲደርሰው ያልተደረገ ተከሳሽ በሌለበት ታይቶ የተሰጠበት ውሣኔ እንዲነሣለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተገቢነት ያለው ነው፡፡ ተከሳሽን በአግባቡ መጥራት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ከተቀመጡት የመስማት መብት ከሚረጋገጥባቸው መርሆዎች አንደ ነው፡፡ ይህን መርህ ባለመጠበቅ የሚሰጠው ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ በሕጉ አግባብ እንደተሰጠ አይቆጠርም፡፡ በመሆኑም ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ወደጉዳዩ ሥረ-ነገር ገብቶ ተከሣሹን ባለዕዳ የሚያደርግ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ተከሳሹን በአግባቡ ስለመጠራቱ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 105(1), 78. በሌላ በኩል ደግሞ ለተከሳሽ የተላከው መጥሪያ በጋዜጣ ጥሪ ሊደረግ የሚገባው ሌሎች አግባብነት ያላቸው የመጥሪያ አላላክ መንገዶች ቅደም ተከተላቸውን በጠበቀ መልኩ ከተከናወኑ በኋላ ነው፡፡ መጥሪያ በአግባቡ ደርሷል ለማለት የሚላክለት ሰው ስም በተሟላ ሁኔታ ተገልጾ መላክ ያለበት በአድራሻው መላክ አለበት፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 94-110, 78, 70/ሀ/
ለአንድ የመንግስት ተቋም የተላከ መጥሪያ መጥሪያው በአግባቡ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ካልደረሰ በስተቀር መጥሪያው ለተቋሙ መዝገብ ቤት ገቢ በመሆኑ ብቻ መጥሪያው እንደደረሠ ተቆጥሮ ክርክሩ ተቋሙ በሌለበት ሊታይ አይገበም፡፡ የመጥሪያ አሰጣጥ ዘዴና ቅደም ተከተል እንዲሁም መጥሪያው ለማን እንደሚሰጥ የሚመለከተው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ክፍል ዓይነተኛ ዓላማ ከሆኑት መካከል አንዱ ተከራካሪ ወገኖችን እኩል የመከራከር መብት እንዲኖራቸው በማድረግ ጉዳዩን ፍትሓዊ በሆነ አኳኋን ለመወሰን ማስቻል መሆኑን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ መጥሪያ የሚደርስበትን ተገቢ መንገድና ለማን መድረስ እንዳለበት ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ መጥሪያ በተገቢው መንገድ ደርሶት ተከራካሪ ወገን ካልቀረበ ወይም መጥሪያን አልቀበልም ካለ ፍርድ ቤቱ ሊከተለው የሚገባው ስርዓትም በሕጉ በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ከእነዚህም ድንጋጌዎች መካከል አንደ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 70(ሀ)፣ 103፣ 104፣ 105፣ 106 እና 107 ስር የተመለከተው ሲሆን በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት ተከሳሽ በሌለበት ክርክሩ ታይቶ ውሳኔ ሊሰጥ የሚችለው መጥሪያው በአግባቡ የደረሰው መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑ ወይም ሊገኝ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑ ወይም ሊገኝ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ ድንጋጌዎቹ መጥሪያው በትክክል ያልደረሰው መሆኑ ከተረጋገጠ ጉዳዩ ተከሳሽ በሌለበት እንዲታይ የማይታዘዝ ስለመሆኑ ያስገነዝባል፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 70(ሀ) ድንጋጌ ስር ላይ ‛መጥሪያው በትክክል መድረሱ“ የሚለው ሐረግ መኖሩም የሚያሳየው ስለመጥሪያ አሰጣጥና አደራረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 94 እስከ 110 ድረስ የተመለከቱት ሁኔታዎች በአግባቡ መሟላታቸውን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ አንድ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔ ከተሰጠውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78 መሰረት መፍትሔ መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት መፍትሔ ሊጠየቅ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው በሚያቀርበው አቤቱታ ላይ የጥሪው ትዕዛዝ ‛በሚገባ ያልደረሰው“ መሆኑን በመጥቀስ ይህንኑ ማረጋገጥ ሲችል ነው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው አንድ ሰው የመከራከር መብቱን እንደተወው የሚቆጠረው መጥሪያው በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓትና ቅደም ተከተል መሰረት ደርሶት ክርክር ያለው መሆኑን እያወቀ ሳይቀርብ ሲቀር ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት ተከትሎ አማራጭ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት ከፈጸመ መጥሪያው ለተከሳሹ እንደደረሰ እንደሚቆጠርና በቂና ሕጋዊ ምክንያት ካለው ብቻ ወደ ክርክሩ እንድገባ የሚፈቀድ መሆኑን ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያስገነዝባል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ውሳኔ መሰጠት ያለበትም በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት መጥሪያው መድረሱ በሚገባ የተረጋገጠና የተከሳሽ የመከራከር መብት የተጠበቀ መሆኑ ሲታወቅ ሊሆን ይገባል፡፡ የፍ/ሥ/ህ/ቁ 70/ሀ/፣78/2/፣96፣102
ከላይ በተመለከተው መሠረት ለተከሳሽ የተላከው መጥሪያ በአግባቡ መድረስ አለመድረሱ ሳይረጋገጥ ክርክሩ በሌለበት ይቀጥል በሚል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ክርክሩ የቀጠለ እንደሆነ ክርክሩን ወደ ኋለ የሚመልስና ለአላስፈላጊ እንግልት የሚዳርግ ነው፡፡ ስለዚህ በሌለበት ክርክሩ ይቀጥል ለማለት መጥሪያው ለሚመለከታቸው ተከሳሾች መድረስ አለመድረሱን በአግባቡ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ መጥሪያ በአግባቡ ያልደረሰው ሰው ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠው ውሳኔ እንድነሳለት የሚጠይቀው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78 መሠረት ሲሆን አንድ አንድ ጊዜ በስህተት ወይም ባለማወቅ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የውሳኔ መቃወሚያ የሚቀርብበት ጊዜም አለ፤ ይህ ደግሞ ተገቢነት ያለው አይደለም፡፡ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የውሳኔ መቃወሚያ የሚቀርበው ከጅምሩ በክርክሩ መግባት የነበረበት ግን በክርክሩ ውስጥ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ያልተጠቀሰ፤ በተሰጠው ውሳኔም መብቱ/ጥቅሙ የተነከ ሰው ነው፡፡ በክርክር ወቅት መጥሪያ አልደረሰኝም ብሎ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የውሳኔ መቃወሚያ የሥነ-ሥርዓት ህጉን የተከተለ አይደለም፡፡ የሰበር ውሳኔዎች ቅጽ 9 የመ/ቁ. 50022, ቅጽ9 የመ7ቁ.50376    
 ቡታጅራ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ጥናት ማርቀቅ ማሥረጽ ዋና ሥራ ሂደት                                                                                                 
http://facebook.com/lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
#አንድ ሰው #ሁለት #ሚስቶችን #ያገባ እንደሆነ እና #ጋብቻው በሞት ወይም በሌላ ህጋዊ ምክንያት #የፈረሰ እንደሆነ እና ከሁለቱ ሚስቶች አንደኛዋ ንብረቶቹን በማፍራት ሂደት የተለየ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑን ያረጋገጠች እንደሆነ ከተፈራው ንብረት ግማሽ ድርሻ የሚገባት ሲሆን፣ የሌላኛዋ ተጋቢ ከባል ጋር ግማሹን ትካፈላለች።

በእርግጥ ሟች ሁለት ሚስቶች ኖረውት የሞተ እንደሆነ ሁለቱ ሚስቶች የንብረቱን ድርሻ ግማሹን ለሁለት ሊካፈሉ እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅሊይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁጥር 24625 ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በሰ/መ/ቁጥር 45548 ላይ (ቅጽ 13 ላይ እንደታተመው) አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ያሉት እንደሆነ ንብረቶቹን በማፍራት ረገድ ከሚስቶቹ አንደኛዋ ሚስት ከሌላኛዋ የተሻለ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ባደረገችው አስተዋጽኦ ልክ ልትካፈል ትችላለች የሚል ሃሳብ መነሻ በማድረግ ባል ንብረቱን በሚያፈራበት ጊዜ ከእርሱ ጋር በትዳር የነበረች ሚስት ንብረቱን በማፍራት ረገድ በቀጥታ አስተዋጽኦ እንዳደረገች ግምት ተወስዶ ከንብረቱ ግማሹን ድርሻ የማግኘት መብት እንዳላት እና በአንፃሩ በቀጥታ አስተዋጽኦ ያላደረገች ሚስት ከባል ድርሻ ግማሹን የማግኘት መብት ብቻ ያላት ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ በሰ/መ/ቁጥር 50489 (ቅጽ 11 እንደታተመው) ጨምሮ በሌልች በርካታ መዛግብት ላይም ይህንኑ የሚያጠናክር ውሳኔ ሰጥቷል። የሰ/መ/ቁጥር - 219887 ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
via:- @Habesha Legal Advocates
በፌስቡክ FB
https://www.facebook.com/lawsocieties/

በቴሌግራም
https://t.me/lawsocieties

YouTube
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
በመርህ ደረጃ ከሥራ ዉል መቋረጥ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄዎች የይርጋ ጊዜ ዉሉ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ 6 ወር ሲሆን የስራ ዉሉ መቋረጡ በግልጽ ባለመገለጹ ወይም ባለመታወቁ ወይም አሻሚ በመሆኑ ሳይታወቅ በቆየበት ሁኔታ ክስ ለማቅረብ መወሰን በማይቻልበት ሁኔታ ግን የስራ ዉሉ መቋረጡን አዉቆ ክስ መመስረት ይችል ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር 6 ወር ይሆናል፡፡
ሰ/መ/ቁጥር 231470 ሕዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም
👉Constitution
👉 Proclamation
👉Regulations
👉 Directives
👉 Decree and administrative order (circular)

☑️Supreme court decisions
የኢትዮጵያ የህግ ምንጮች እና ተዋረድ
https://t.me/lawsocieties
ህጎች የተለያዩ መመዘኛዎችን መሰረት በማድረግ ሊከፋፈሉ ይችላሉ፡፡

በዚህ መሰረት “የሲቪል ሎው (civil law)” እና “የኮመን ሎው (common law)”፣ “ፐብሊክ ሎው (public law)” እና “የግል ህግ (private law)”፣ “የወንጀል ህግ” እና “የፍትሀብሄር ህግ”፣ “የስነ ስርዓት ህግ (procedural law)” እና “መሰረታዊ ህግ (substantive law) እና የመሳሰሉትን መስፈርቶች በመጠቀም ህጎችን ማከፋፈል ይቻላል፡፡ የሀገራት ህጎች በሁለት ዋና ዋና የህግ ስርዓቶች ማለትም የኮመን ሎው እና የሲቪል ሎው በሚል ይታወቃሉ፡፡ የሲቨል ሎው የህግ ስርዓት ተከታይ አገራት ፍትሀብሄርን የሚመለከት ዐብይ ህግ በአንድ ጥራዝ (codified) ታውጀው እና የወንጀል የሚመለከት ዐብይ ህግ በአንድ ጥራዝ (code) ታውጀው ይገኛሉ፡፡ እነዚህም በአገራችን አጠራር የፍትሀብሄር ህግ እና የወንጀል ህግ ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ስለሆነም ይህን ስርዓት የሚከተሉ ሀገሮች ዋና የህግ ምንጭ በህግ አውጪ አካል ታውጀው የሚጠረዙ ህጎች ናቸው ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል የኮመን ሎው ስርዓትን የሚከተሉ ሀገሮች ዋና የህግ ምንጫቸው በህግ አውጪ አካል የሚወጡ ህጎች ሳይሆኑ በፍርድ ቤቶች በተመሳሳይ ጉዳይ ቀደም ብለው የተሰጡ አስገዳጅ ውሳኔዎች (precedent) ናቸው፡፡ እንዲሁም ያልተፃፉ ህጎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

በሀገራችንም የተለያዩ የህግ ምንጮች ያሉ ሲሆን የህጎች ተዋረድ ወይም የህግ የበላይነት ደረጃ (hierarchy of laws) በህግ ስርዓት ውስጥ ጉልህ ቦታ ካላቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ በዚህ የንቃተ ህገ ፅሁፍ የኢትዮጵያ የህግ ምንጮችን እና የህጎቹን ተዋረድ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

1. የኢትዮጵያ ህግ ምንጮች (sources of Ethiopian laws)
በአገራችን ህጎች በፌደራል እና በክልል ደረጃ ወጥተው ስራ ላይ ይውላሉ፡፡ እነዚህም ህጎች በፌደራል እና በክልሎች የተለያዩ ምንጮች አሏቸው፡፡

1.1. የፌደራል የህግ ምንጮች 
i. ህገ መንግስት (constitution)
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 9 ህገ መንግስት የሀገሪቱ የበላይ ሕግ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ ማንኛውም ህግ ለምሳሌ አዋጅ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ይህ ማለት ህገ መንግስት የማንኛውም ህጎች መነሻ እና ምንጭ እንዲሁም ህጋዊነታቸውን (validation) የሚያገኙበት መሰረት ነው፡፡
ii. አለም አቀፍ ስምምነቶች (international treaties)
ሀገራት አለም አቀፍ ስምምነት ሲፈርሙ ስምምነቱን እንደ አንድ አለም አቀፍ ህግ እንተቀበሉ ማስረጃ ነው፡፡ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 9 (4) እንደሚደነግገው ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ህግ አካል ናቸው፡፡ እነዚህ ስምምነቶች ስራ ላይ ለመዋል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቅ እና በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትመው መውጣት አለባቸው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገሪቱ ህግ አካል ሆነው ተግባራዊ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡
iii. ኮዶች (codes)
በሀገራችን በ1960ዎቹ አምስት ኮዶች ተዘጋጅተው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ እነዚህም የፍትሀ ብሄር ህግ፣ የንግድ ህግ፣ የባህር ህግ በ1960፣ የወንጀል ስነ ስርዓት ህግ በ1961 እና የፍትሀ ብሄር ስነ ስርዓት ህግ በ1965 ናቸው፡፡ እነዚህም ህጎች በነጋሪት ጋዜጣ በአዋጅ መልክ ታውጀው ስራ ላይ ውለዋል፡፡ ከዚህም በኃላ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ፣ የወንጀል ህግ እና አዲሱ የንግድ ህግ በኮድ መልክ ስራ ላይ የዋሉ የአገራችን የህግ ምንጮች ናቸው፡፡
iv. አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ (proclamations, regulations & directives) 
አዋጆች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ደንቦች በሚኒስትሮች ምክር ቤት እና መመሪያዎች ደግሞ በፌደራል ሚኒስትሮች መስሪያ ቤቶች ወይም በሚስትሮች ምክር ቤት መመሪያ እንዲያወጡ በደንብ ውክልና በተሰጣቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ይወጣሉ፡፡ በተጨማሪም የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማወጅ ስልጣን በህገ መንግስቱ ተሰጥቶታል፡፡ እነዚህም የህግ ክፍሎች ወይም አይነቶች የአገራችን የህግ ምንጭ በመሆን የሚያገለግሉ ሲሆኑ በስራ ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ በተመለከተ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ይህም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በሚነስትሮች ምክር ቤት ከታወጁበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ የሚውሉ ወይም በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡
v. አስገዳጅ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች (precedent)
ይህ የህግ ምንጭ አይነት ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ አስገዳጅ ወይም ህግ የሚሆንበት ስርዓት ነው፡፡ በአገራችን  ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸው ውሳኔዎች በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ እንደ ህግ እንደሚያገለግሉ እና አስገዳጅ እንደሆነ የሚገልፀው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10/2 ስር እንደተደነገገው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ ባለ የፌደራል እና የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል ይላል፡፡ ይህ ማለት እነዚህ ውሳኔዎች የህግ ምንጭ ሆነው ስራ ላይ ይውላሉ ማለት ነው፡፡
vi. ልማዳዊ ህጎች (customary laws)
ልማዳዊ ህጎች በኢትዮጵያ ህጎች ውስጥ በተለያየ ጊዜ እንደምንጭ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ለምሳሌ የፍትሀ ብሄር ህጉን ያረቀቁት ፕሮፌሰር ሬኒ ዳቪድ በረቂቁ ውስጥ የኦርቶዶክስን ልማዳዊ ህግ ‘ፍትሀ ነገስትን‘ እንደምንጭ እንደተጠቀሙበት ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በህገ መንግስቱ አንቀፅ 34/5 ስር እንደተደነገገው የግል እና የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ፈቃድ በሀይማኖቶች ወይም በባሕሎች ሕጎች መሰረት መዳኘት እንደሚችሉ ያስቀምጣል፡፡ በመሆኑም ባህላዊ ወይም ልማዳዊ ህጎች እንደ አንድ የህግ ምንጭ ያገለግላሉ ማለት ነው፡፡

1.2. የክልል ህግ ምንጮች
i. የክልል ህገ መንግስት(state constitutions)
በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 52/2 ስር እንደተደነገገው ክልሎች የራሳቸው ህጎች ማውጣት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ክልሎች የራሳቸው ህገ መንግስት ከፌደራል ህገ መንግስት ጋር በሚጣጣም መልኩ አውጥተዋል እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡ የክልል ህገ መንግስት በክልሎቹ ውስጥ የበላይ ህግ ነው፡፡
ii. የክልል አዋጆች (state proclamations)
የፌደራል ህገ መንግስት ክልሎች ለአስተዳደር በሚያመች መልኩ የክልሎቹን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት አዋጅ ማወጅ እንደሚችሉ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ መሰረት ለምሳሌ ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እና የደ/ብ/ብ/ህ ክልል የራሳቸው የቤተሰብ ህግ አውጀዋል፡፡
iii. የክልል ደንቦች እና መመሪያዎች (state regulations & directives)
የፌደራል ህገ መንግስት የክልል አስፈፃሚ ምክር ቤቶች በክልል ወሰን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ እንደሚችሉ እንዲሁም ደንብ እና መመሪያዎችን ማውጣት እንደሚችሉ ስልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡
2. የህጎች ተዋረድ (hierarchy of laws)
የህጎች ተዋረድ (hierarchy of laws) የህጎች የበላይነት ደረጃን ወይም የትኛው ህግ ከየትኛው ህግ የበላይ ህግ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ በአገራችን በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9/1 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ ድርጊት እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ይደነግጋል፡፡ ይህ ማለት በሀገሪቱ ውስጥ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ህገ መንግስቱ ነው ማለት ነው፡፡

የፌደራል ህገ መንግስት በፌደራልም ይሁን በክልል ደረጃ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው፡፡ በመቀጠል የአገሪቱ የበላይ የህግ አውጪ አካል ማለትም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያወጣቸው ህጎች ማለትም አዋጆች ይከተላሉ፡፡ የአለም አቀፍ ስምምነቶችን የህግ ተዋረድ በተመለከተ ወጥ የሆነ መግባባት ባይኖርም በህገ መንግስቱ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገረቱ ህግ አካል ይሆናሉ ስለሚል ከአዋጅ ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ የሚል ሀሳብ አለ፡፡ በህግ ተዋረድ በመቀጠል የሚመጡት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወጡት ደንቦች እና በሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚወጡት መመሪያዎች በቅደም ተከተል ናቸው፡፡

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ተዋረድ (hierarchy) ላይ ባሉ ህጎች መካከል መቃረን ሲኖር ተፈፃሚ የሚሆነው በጊዜ ዘግይቶ የወጣው ህግ (latest prevails) ነው፡፡ ይህ ማለት ዘግይቶ የወጣው ቀድሞ ከወጣው ይልቅ ተፈፃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ልዩ ህግ (special law) ከጠቅላላ ህግ ይልቅ ቅድሚያ ተቀባይነት (special law prevails over general law) ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties

በፌስቡክ FB
https://www.facebook.com/lawsocieties/

በቴሌግራም
https://t.me/lawsocieties

YouTube
https://www.youtube.com/@Lawsocieties

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረ ሰራተኛ
ሰ/መ/ቁጥር 212420 ጥር 27 ቀን 2014 ዓ/ም
አሰሪው ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ ለስራው ተስማሚ አለመሆኑን ሳይመዝን ካሰናበተ ስንብቱ ህገ- ወጥ ነው።
ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ካሳ የሚከፈለው ሲሆን የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች ግን አገልግልትን ታሳቢ ተደርገው የሚሰሉ በመሆኑ አይከፈሉትም።
የካሳው መጠን የሙከራ ጊዜ ማለትም 60 ቀናት በስራ ላይ ቢቆይ ኖሮ ሊያገኝ ይችል የነበረው ማለትም የሁለት ወር ደመወዝ ነው።

Habesha Legal Advocates LLP

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties