አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ሰ/መ/ቁጥር 215444 ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ/ም

በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሳይመዘገብ በተወካይ አማካይነት የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ውሉ ስለመደረጉ በተወካዩ ታምኖ ሆኖም ወካዩ ውል መኖሩን ከካደ ህጋዊ ውጤት አይኖረውም።
ውሉ ፈርሶ ተዋዋዮች ወደነበሩበት መመለስ ይኖርባቸዋል። https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ ምጣኔ

በድርጅቶች የሚከፈለው የኪራይ ገቢ ግብር መጣኔ 30% (ሰላሳ በመቶ) ነው፡፡

የተከራይ አከራዮች

የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው ገንዘብ ነው፡፡
ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት ተከራዩ ግብሩን ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡

የግለሰቦች የኪራይ ገቢ ግብር ማስከፈያ መጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
.............. ቅፅ 17 መ/ቁ 96858.......
አንድ የተከራየ ሰው የኪራይ ዘመኑ ሲያልቅ አከራዩ የኪራይ  ተመኑን መጨመሩን ማስጠንቀቂያ ከሰጠው እና ተከራዩም ዝም ብሎ ቤቱን መጠቀም ከቀጠለ አድሱን የኪራይ ተመን ተከራይ እንደተቀበለ የሚቆጠር ነው።

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ከታክስ ነፃ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ ንረት አንድምታና የመፍትሄ አማራጮች
****************
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት በምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች ላይ እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረት ለማርገብ የተለያዩ የመፍትሔ አማራጮችን እየወሰደ ነው። በተለይም ከውጭ የሚገቡ እንደ ፓስታ፤ ማካሮኒ፤ ዱቄትና የሕፃናት ምግቦች፣ የምግብ ዘይትና የመሳሰሉት ምርቶች ላይ የነበረውን ታክስ በማንሳት ከታክስ ነፃ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ በፍራንኮ ቫሉታ በኩል መፍቀዱ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ የእነዚህ ምግቦች ዋጋ አሁን ላይ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ ለኅብረተሰቡ ፈታኝ ሆነው እየተስተዋሉ ነው። ይህ ለምን ሆነ፤ እያጋጠመ ያለውን የዋጋ ንረት ለመግታት የመፍትሔ እርምጃዎች ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=98490
Wednesday is World Press Freedom Day.

A free press is essential for exposing threats such as human rights abuses, corruption, misinformation & much more.

If everything is all right in the news, then something is wrong with journalism. via UNESCO
የመጥፋት ውሳኔ በኢትዮጵያ ህግ

የሰው ልጅ በአንድም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ከሚኖርበት ስፍራ በራሱ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የሚሄድበት እና በዛም አጋጣሚ በሚፈልጉት ሰዎች ይኑር ይሙት የማያውቁበት አጋጣሚ አለ፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተሰቡ እና በስሩ የሚገኙ ንብረቶች ለማን እንዴት እንደሚደረግ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ በዚህ አጭር ርእስ ስለመጥፋት ውሳኔ ትርጓሜ፣ የመጥፋት ውሳኔ በማን እና እንዴት እንደሚሰጥት፣ የመጥፋት ውሳኔ የሚያስከትለው ውጤት እንዲሁም የመጥፋት ውሣኔን ውጤት ቀሪ የሚያደርጉ ምክንያቶች እንዳስሳለን፡፡

አንድ ሰው ጠፋ የሚባለው መቼ ነው

በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 154(1) መሰረት አንድ ሰው ጠፋ የሚባለው ከጠፋ እና ከሁለት አመት ወዲህ ወሬው ያልተሰማ እንደሆነ ነው፡፡ ይህ በሆነ ጊዜ የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥ በማናቸውም ባለጉዳይ ሊጠየቅ ይችላል፡፡

የመጥፋት ውሳኔ በማን እና እንዴት ይሰጣል

የመጥፋት ውሳኔ የሚሰጠው የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥበት የተጠየቀበት ሰው ዋና መኖሪያ አድርጎ በሚኖርበት ቦታ የሚገኝ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ማንኛውም ባለጉዳይ የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ሲያቀርብ ማስታወቂያ ይወጣል፡፡ ማስታወቂያውም ፍርድ ቤቱ በሚወስነው ሁኔታ እና የጠፋው ሰው በመጨረሻ ዋና መኖሪያነት ይኖርበት በነበረበት ቦታ እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ማስታወቂያው ይጠቅማል ብሎ በሚያምንበት ቦታ ነው፡፡
ፍርድ ቤቱ የጠፋው ሰው መሞት በሚመስል መልኩ መጥፋቱ ከተሰማው የመጥፋት ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ውሳኔውን በሚሰጡበት ወቅት ግን የነገሩን አካባቢያዊ ሁኔታ፣ ጠባይ እና መጥፋቱ የተገመተው ሰው ለንብረቱ አስተዳዳሪነት ወኪል ማስቀመጡ እንዲሁም ግለሰቡ ወሬው እንዳይሰማ የከለከሉ ምክንቶችን መመርመር ይጠበቅበታል፡፡ የሚሰጠው የመጥፋት ውሳኔ እስከ 1 አመት ማቆየት ወይም ወይም ስለ መጥፋቱ የሚሰጠው ፍርድ ውጤቱ የሚኖረው ውሳኔው ከተሰጠ ከ1 አመት በኋላ እንዲሆን መወሰን ይችላል፡፡ በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በሚሰጠው ውሳኔ የጠፋው ሰው የመጨረሻ ወሬዎች የተሰሙበትን ቀን መወሰን ይችላሉ፡፡

የመጥፋት ውሳኔ የሚያስከትለው ውጤት

የመጥፋት ውሳኔ በውርስ እና በጋብቻ ላይ ውጤትን የሚያስከትል ነው፡፡ የመጥፋት ውሳኔን ዳኞች ሲወስኑ ጠፋ የተባለው ሰው የሞተ የሚመስልን ማስረጃ ካረጋገጡ በኋላ በመሆኑ የጠፋው ሰው ልክ እንደሞተ ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ ጋብቻ ለሚፈርስባቸው ምክንያቶች አንዱ በሞት ምክንያት ስለሆነ እና የመጥፋት ውሳኔም የጠፋው ሰው እንደሞተ የሚቆጠር በመሆኑ ጋብቻ ይፈርሳል፡፡ ስለውርስ የሚደነግገው አንቀፅ ስር ውርስ የሚከፈተው አውራሽ ከሞተ በኋላ በመሆኑ የመጥፋት ውሳኔም እንዲሁ የጠፋውን ሰው እንደሞተ ስለሚያስቆጥረው ውርሱ ይከፈታል፡፡

 ጋብቻን በተመለከተ፡- የጠፋ ሰው ጋብቻ የሚፈርሰው መጥፋት ማስታወቂያ ፍርድ የመጨረሻ በሆነበት ቀን ነው ሲል የፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 183 ይደነግጋል፡፡ የመጨረሻዎቹ ወሬዎች ከተሰሙበት በኋላ የተፈፀሙት የወንዱ ወይም የሴቲቱ ጋብቻ ጠፋ የተባለው ሰው ካልሆነ በስተቀር ማንም ሊቃወም እንደማይችል አንቀፅ 183(2) ያስረዳል፡፡ ነገር ግን የመጥፋት ማስታወቂያ ክስ በተጀመረበት ቀን ጠፋ የተባለው ሰው በህይወት መኖሩን ዓቃቤ ህግ ካረጋገጠ በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ አንቀፅ 183(3) መሰረት መቃወሚያ ሊያቀርብ ይችላል፡፡

 ውርስን በተመለከተ፡- ጠፋ የተባለው ሰው የመጨረሻዎቹ ወሬዎች ከደረሱ በኋላ በህይወት ቢኖር ኖሮ እርሱ ሊወርስ በሚችለው የአወራረስ ስርአት መሰረት ለእርሱ ሊደርስ የሚቸለውን ድርሻ ግምት ውስጥ ሳይገባ የውርስ ስርአቱ ይፈፀማል፡፡ ከፍትሀብሔር ህግ አንቀፅ 184(1) ሀሳብ የምንረዳው ነገር ጠፋ የተባለው ሰው ምንም እንኳን በቦታው ባይኖርም የውርስ ድርሻው ይቀመጥለታል ማለት ነው፡፡ ለዚህም አብሮ ወራሽ የሆኑት ጠፋ ለተባለው ሰው ድርሻ መብቶች መድህን እንዲያሲዙ ፍርድ ቤት ሊያዛቸው ይችላል፡፡ የጠፋ ሰው ላይ እዳ፣ ውርስ የመሳሰሉት መብቶች ያላቸው እንደሆነ መጥፋትን በሚወስነው ፍርድ መጨረሻ ከሆነበት ቀን አንስቶ እንደሞተ ተቆጥሮ የመብቶቹ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በአንቀፅ 185(1) ስር ተደንግጓል፡፡ ጠፋ የተባለው ሰው መብት ተካፋይ ብቻ ሳይሆን የሚያወርሰው ነገርም ሊኖረው ሲችል ጠፋ የተባለው ሰው ኑዛዜ ያለው እንደሆነ ውርሱ የሚከፈተው የመጨረሻ ወሬው በተሰማበት ቀን ባለጉዳዮቹ (ወራሾቹ) በሚያነሱት ጥያቄ መሰረት ኑዛዜ ይፈሳል (ያነገራል)፡፡ ጠፋ የተባለውን ሰው የውርስ ንብረቶችን አጠቃቀም በተመለከተ እንደ መልካም ቤተዘመድ አባት ሆኖ ጠፋ የተባለው ሰው ሊመለስ ቢችል እንኳን በሚል ተመላሽ ስለሚሆን የንብረቶቹን ዋስ እንዲጠራ ወይም ማረጋገጫ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቶች ሊያስገድድ ይችላል፡፡ የጠፋውን ሰው ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው በሶስት ወር ውስጥ የተቀበላቸውን ንብረቶች በስራ ላይ ማዋል እንዳለበት እንደተጠበቀ ሆኖ ንብረቱ የጠፋውን ሰው ልጅ ለማቋቋም ከሆነ በስጦታ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡

የመጥፋት ውሳኔ የተሰጠበት ሰውን ንብረት በማንኛውም ሁኔታ በስጦታ ማስተላለፍ እንደማይቻል ተደንግጓል፡፡

የመጥፋት ውሣኔን ውጤት ቀሪ የሚያደርጉ ምክንያቶች
ጠፍቷል የተባለው ሰው መመለስ(የመጣ) እንደሆነ፣
ጠፍቷል የሚባለው የፍርድ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ በህይወት ለመኖሩ አስረጂ የተገኘ እንደሆነ፣
የመጨረሻ ወሬዎቹ የተሰሙበት ተብሎ ከተወሰነው ግዜ በሌላ ጊዜ መሞቱ አስረጂ የተገኘ እንደሆነ መሆኑን በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 170 ስር ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡
ጠፋ የተባለው ሰው ስለመመለስ
በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 171 መሠረት ጠፋ የተባለው ሰው በተመለሰ (በመጣ) ጊዜ ንብረቶቹን በሚገኙበት አኳኋን መልሶ የመረከብ እንደዚሁም የተሸጡትን ንብረቶች ዋጋ የማግኘት መብት እንዳለው በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ይህን የህግ ሀሳብ በሚያስረግጥ ሁኔታ ጠፋ የተባለው ሰው ንብረት መሸጡ ከተረጋገጠ ከተጠቀሰው ድንጋጌ አኳያ ሊረከብ የሚገባው የተሸጠውን ንብረት ሣይሆን የሽያጩን ዋጋ ነው በማለት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 30298 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ ነገር ግን በተንኮል እና በክፉ ልቦና ካልሆነ በስተቀር ጠፋ የተባለውን ሰው ንብረት ገቢዎች በይዞታቸው ስር አድርገው ሲጠቀሙ የነበሩትን ገቢ እንዲመልሱ አይጠየቁም፡፡

በአጠቃላይ በአንድ ሰው በመጥፋቱ ምክንያት በቤተሰብ እና በንብረቶች ላይ ውጤት ያለው በመሆኑ በዳኞች የመጣፋተ ውሳኔ ሲተላላፍ ከፍትሀብሔር ህጉ መንፈስ አንፃር ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡ እንዲሁም ጠፋ የተባለው ሰው ሊመለስ የሚችልበት አግባብ ስለሚኖር ለንብረቶቹ ዋስትና ማስያዝ ላይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

ስለዚህ አንድ ሰው ከዋና መኖሪያ ከጠፋ ማንም ሰው የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥ ለማመልከት ይችላል፡፡ የመጥፋት ውሳኔን ለመስጠት ዳኞች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ከህጉ የምንረዳው ነው፡፡ ለዚህም የሰውየውን መጥፋት ለመረዳት ዳኞች ከዓቃቤ ህግ ጋር በመተባበር በማናቸውም ቦታ ይልቁንም የጠፋው ሰው የመጨረሻ ይኖርበት ከነበረው ቦታ እና በመጨረሻ መኖሩ የታየበት ቦታ ጠፋ የሚባለው ሰው ስለመኖሩ ምርመራ እንዲደረግ በማዘዝ እንደሆነ የፍትሐብሄር ህግ አንቀፅ 156 ስር ተደንግጓ እናገኘዋለን፡፡ ይኸውም ዓቃቤ ህግ ስለመጥፋቱ የቀረበውን ማመልከቻ እና ማስረጃዎች ፍርድ ቤቱ ወደ ትክክለኛ ውሳኔ ለመድረስ የሚያስችለውን ማስረጃ ዓቃቤ ህጉን ተቃርኖ የበለጠ እንዲረጋገጥ በማድረግ ነው፡፡
ስለዚህ ዳኞች የጠፋው ሰው አጠፋፍ ‹መሞት የሚመስል› መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ ይጣልባቸዋል፡፡ መጥፋቱን ከተረዱት በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 157 መሰረት የመጥፋት ውሳኔ የመጨረሻ ወሬዎቹን የተሰማበትን ቀን በመጥቀስ ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡ በሌላ በኩል ዳኞቹ ያገኙት ማስረጃ ወደሞት የሚያመዝን መስሎ ከታያቸው ‹የሞት ማስታወቂያ› ፍርድ ይሠጣሉ ሲል የፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 157(1) ደንግጓል፡፡ ዳኞች እንደነገሩ ሁኔታ የመጥፋት ውሳኔውን ወይም የመጥፋት ውሳኔ ማስታወቂያን ለአንድ አመት መቅጠር የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን የመጥፋት ውሳኔው ከተጠየቀ ከአንድ አመት በኋላ ወይም ሰውየው ከጠፋ አምስት አመት በኋላ የመጥፋት ውሳኔ መሰጠት አለበት፡፡

በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
#Allied Chemical Industry PLC#

▪️1 - Diver
▪️2 - Local Purchase Executive
▪️3 - Factory Store Keeper
▪️4 - Receptionist/ Front Desk Executive
▪️5 - Marketing Officer
▪️6 - Legal Officer
▪️7 - Liaison & Public Relations Executive
▪️8 - Senior Accountants
▪️Find More Details here
          💧💧💧💧💧
    https://bit.ly/40ZUCiX

▪️Deadline: May 10/2023
ኢትዮጵያ በዓለም የፕሬስ ነጻነት ዝርዝር በ16 ደረጃዎች አሽቆለቆለች

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (RSF) በዓመቱ በሚያወጣው የዓለም የፕሬስ ነጻነት ዝርዝር፤ ኢትዮጵያ ዘንድሮ 130ኛ ደረጃ አገኘች። የ180 ሀገራት የፕሬስ ነጻነት በሚመዘንበት በዚህ ዝርዝር፤ ኢትዮጵያ አምና ከነበራት በ16 ደረጃዎች አሽቆልቁላለች።

መቀመጫውን በፓሪስ ፈረንሳይ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቱ፤ ይህን የሀገራት ደረጃ ላለፉት 20 ዓመታት ሲያወጣ ቆይቷል። በየሀገራቱ ያሉት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አውዶች፣ የህግ ማዕቀፍ እና የደህንነት ሁኔታ፤ ድርጅቱ ደረጃዎቹን ለማውጣት በጠቋሚነት የሚገለገልባቸው መመዘኛዎች ናቸው።

ዛሬ ረቡዕ ሚያዝያ 25 ይፋ በተደረገው የዘንድሮው ዝርዝር ከተገመገሙ 180 ሀገራት መካከል፤ በሰላሳ አንዱ ያለው የፕሬስ ነጻነት ሁኔታ “በጣም መጥፎ” መሆኑን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል። በዚህ ምድብ ውስጥ ከተካተቱ ሀገራት ውስጥ የኢትዮጵያ ጎረቤት ኤርትራ ትገኝበታለች። በሀገራቸው ያለው ሁኔታ ለፕሬስ ነጻነት “መጥፎ” የሚባል መሆኑ ከተነገረላቸው 42 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ተካትታለች። በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነጻነት ሁኔታ፤ በፈረንጆቹ 2022 ዓመት እንደነበረው ሁሉ “አስቸጋሪ” ሆኖ መቀጠሉን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቱ ገልጿል።
ETHIO-MEREJA
የአፍሪካ ህዝብ ብዛት 1.4 ቢሊየን ደርሷል፡፡

1. ናይጄሪያ 218 ሚሊየን
2. ኢትዮጲያ 118 ሚሊየን👈👈👈
3. ግብጽ 107 ሚሊየን

ምንጫ፡ የተባበሩት መንግስታት
ከቀረጥና ታክስ ነጻ የሚገቡ እቃዎች

የገንዘብ ሚኒስቴር የግል መገልገያ እቃዎች ከቀረጥና ታክስ ለጻ ሆነው ወደ ሀገር የሚገቡበት እና የሚወጡበትን ሁኔታ የሚወስን መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

መመሪያውም ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ ሀገር የሚገቡ ወይም ከሀገር የሚወጡ እቃዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 923/2014 በመባል ይታወቃል፡፡

በዚሁ መመሪያ መሰረት ለግል መገልገያ ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ሆነው የሚገቡ እቃዎች ናቸው፡፡
"ያላግባብ ጉዳይን ማጓተት" የሙስና ወንጀል መሆኑን ያውቃሉ?
==================
“የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007” አንቀጽ 18 ላይ እንደተመለከተው:-
ማንኛውም የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሠራተኛ በኃላፊነቱ ወይም በሥራው ምክንያት በቀረበለት ጉዳይ ላይ ጥቅም ካለው ማንኛውም ሰው በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ጥቅም ለማግኘት በጉዳዩ ላይ ጥቅም ያለውን ማንኛንውም ወገን ወይም ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት ሲል ከህግ፣ ከስራ ደንብ፣ ከመመርያ ወይም ከተለመደው አሰራር ውጪ ያለበቂ ምክንያት ያልወሰነ፣ ያዘገየ ወይም ባለጉዳይን ያጉላላ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ በመቀጮ ወይም በቀላል እስራት ወይም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ አስራት እና ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡
Via Legal consulting limited
Prices of basic food items have skyrocketed this year in many countries affected by conflict and violence.

How has it affected those who are already struggling to put food on their table?

Here's some analysis done by ICRC Analysis & Evidence Unit 📈