አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በኢፌዴሪ_የወንጀል_ሕግ_አንቀጽ_543_ንዑስ_ቁጥሮች_መካከል_ያለው_የልዩነት_ወሰን.pdf
596.8 KB
በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543 ንዑስ ቁጥሮች መካከል ያለው የልዩነት ወሰን እና በሥራ ላይ የሚታዩ ተግባራዊ ችግሮች
ጸሐፊ፡- ታፈሰች ወልዴ
Share Premium .pdf
301 KB
የገቢ ግብር ደንብ (ማሻሻያ ) ደንብ ቁጥር  520/2014
ይቅርታ በኢትዮጵያ ህግ

በወንጀል ህግ ውስጥ ይቅርታ ማለት የቅጣት ፍርድ በሙሉ ወይም በከፊል ቀሪ እንዲሆን ወይም የቅጣት ፍርዱ አፈፃፀምና አይነት ቀለል ተደርጎ እንዲፈፀም ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይቅርታ መብት ሳይሆን እድል ሲሆን በሀገራችን ይቅርታ የሚገዛው በይቅርታ አሰጣጥና አፈፃፀም ስነስርአት አዋጅ ቁጥር 840/2006 ነው፡፡
የይቅርታ አላማ የህዝብ፣ የመንግስትና የታራሚዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል መንግስት የወንጀል ጥፋተኞች በጥፋታቸው የተፀፀቱና የታረሙ መሆኑን በማረጋገጥ ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቅለው አምራች እና ህግ አክባሪ ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ በአጠቃላይም የወንጀል ህግ አላማ የሆት የጠቅላላውን ሰላም፣ ደህንነት፣ ስርአት፣ መብትና ጥቅም ያስጠብቃል፡፡

ይህ የይቅርታ አዋጅ የተፈፃሚነት ወሰኑ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች በተሰጡ የመጨረሻ የወንጀል ቅጣቶች ላይ እንዲሁም በማናቸውም የፌዴራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ውሳኔ ላይ ነው፡፡

ይህም ማለት የክልል ፍርድ ቤቶች በህገመንግስታችን በውክልና የተሰጣቸው የፌዴራል ፍርድ ቤት ስልጣን ስር በሚወድቁ ጉዳዮችን ላይ የሚሰጡዋቸውን የመጨረሻ ውሳኔዎች ይጨምራል፡፡ የይቅርታ አይነቶችን ስንመለከት ይቅርታ ለተጣለው ቅጣት በሙሉ ወይም ከፊል ሊሰጥ የሚችል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በቅድመ ሁኔታ የተመሰረተ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ የሚሰጥ ይቅርታ ናቸው፡፡ በቅድመ ሁኔታ የሚሰጥ ይቅርታ ማለት ቅጣቱ ቀሪ ተደርጎ የሚቆየው ተቀጪው ተወስነው የተገለፁለትን ቅድመ ሁኔታዎች (በአብዛኛው የመልካም ጠባይ አመራር) እንዲያከብር ሲጠበቅበት ነው፡፡

ይቅርታ ለማግኘት በቅድሚያ የተጣለበት የፍርድ ቅጣት የመጨረሻ መሆን ያለበት መሆኑ ሲሆን ይህም ማለት በይግባኝ እየታየ ከሆነ ይህው እልባት ማግኘቱ ወይ ይግባኝ ያልተባለ ወይም የማይባል ከሆነ የይግባኝ ጊዜው ያለፈ መሆኑ ናቸው፡፡ አንድ የይቅርታ ጥያቄ የቅጣት ውሳኔው የመጨረሻ እንደሆ መቅረብ የሚችል ሲሆን ጥያቄው ታይቶ በተለያየ ምክንያት ውድቅ ከተደረገ ደግሞ ከስድስት ወር በኋላ በድጋሚ ሊቀርብ ይችላል፡፡

ይቅርታው በከፊል ከተሰጠ ደግሞ ለቀሪው ቅጣት ከአንድ አመት በኋላ በድጋሚ ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ይህ ጊዜ ሳይጠበቅ የይቅርታ ጥያቄ እንዲታይ ካስፈለገ የይቅርታ ቦርዱ በ¾ኛ ድምፅ በማናቸውም ጊዜ እንዲታይ ሊፈቅድ ይችላል፡፡

በአዋጁ መሰረት ይቅርታ የሚሰጠው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፕሬዚዳንት ብቻ ነው፡፡ ለእርሳቸው ጥያቄዎችን አደራጅቶ እና ከአስተያየት ጋር ለውሳኔ የሚያቀርብላቸው በአዋጁ የተደራጀው የይቅርታ ቦርድ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የይቅርታ ቦርድ 11 አባላት ያሉት ሲሆን የፍትሕ ሚኒስትሩ ሰብሳቢ፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ዴኤታ ምክትል ሰብሳቢ ሲሆኑ አባላቱ ደግሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል እና አብዛኛውን ህብረተሰብ ክፍል ከሚወክሉ አደረጃጀቶች በፍትሕ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፕሬዚዳንት የሚሰየሙ ሁለት አባላት ናቸው፡፡ ይህ ቦርድ የይቅርታ ጥያቄዎችን መርምሮ የውሳኔ ሀሳብ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፕሬዚዳንት የሚያቀርብ ነው፡፡

የቦርድ አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ የሚሟላ ሲሆን፣ ውሳኔ በተገኙ አባላት አብላጫ ድምፅ ያልፋል፣ ድምፅ እኩል በኩል በተከፈለ ጊዜ ሰብሳቢው ያለበት ውሳኔ ያልፋል፣ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ደንብ ስነስርአት የሚያወጣ ሲሆን፣ በወር አንድ ጊዜና እንደአስፈላጊነቱ ይሰበሰባል፣ በየስድስት ወሩ ሪፖርት ለክብርት ፕሬዚዳንት ያቀርባል፡፡

የይቅርታ ቦርዱ ደግሞ በፍትሕ ሚኒስቴር ውስጥ የተደራጀ የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት አስተዳደራዊ ስራው የሚታገዝ ነው፡፡ ጽ/ቤቱ የይቅርታ ማመልከቻዎችን ይቀበላል፣ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ለቦርድ ውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ የቦርድ መዛግብት ይይዛል፣ ውሳኔዎች ይይዛል፣ ይቅርታዎችን በመዝገብ ያሰፍራል፣ አግባብነት ባለው ህግ መሰረት ለህዝብ ክፍት ያደርጋል፣ ስታትስቲክስ ያዘጋጃል፣ ውሳኔዎችን ያሳውቃል፣ የይቅርታ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይቅርታ ውሳኔ ዋጋ ማጣትና የቅጣት ፍርድ አፈፃፀም መቀጠል በሚመለከት የቦርድ ውሳኔ ለሚመለከታቸው አካላት ያስተላልፋል፡፡

የይቅርታ ጥያቄ በአንድ የፍርድ ተቀጪ በራሱ፣ በወኪሉ፣ በጠበቃው በኩል ሊያቀርብ ይችላል፡፡ በባለቤቱ ወይም በቅርብ ዘመዱ ደግሞ እርሱ የፈረመበትን ጥያቄ ሊያቀርቡለት ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል እንደ አስፈላጊነቱ የፍትሕ ሚኒስቴር ወይም ማረሚያ ቤቱ ለታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄ ለቦርዱ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ በስሙ የቀረበለት የይቅርታ ጥያቄ ለታራሚው በቅድሚያ መድረስ ያለበት ሲሆን፣ እርሱም በ15 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ በፅሁፍ ካልተቃወመ እንደተስማማ ይቆጠራል፡፡

አለመስማማቱን ለመግለፅ ከአቅም በላይ ችግር ከገጠመው ይህ ችግር እንደተወገደ በ15 የስራ ቀን ውስጥ ተቃውሞ ካለው ማስታወቅ አለበት፡፡

የይቅርታ ጥያቄ የሚከተሉትን የያዘ መሆን አለበት፡-
– የአመልካች ሙሉ ስም፣ የእናት ሙሉ ስም፣ እድሜ፣ ፆታ፣ ዜግነት፣ ብሔር፣ የበፊት ስራ፣ አድራሻ፣ ከመታሰሩ ቀድሞ ያለ አምስት አመት የመኖሪያ አድራሻ፣ የተከሰሰበት ወንጀል፣ ጥፋተኛ የሆነበት ወንጀል፣ የተወሰነበት ቅጣት፣ የፈረደው ፍርድ ቤት፣ የፍርድ መዝገብ ቁጥሩ፣ የፍርዱ አፈፃፀም ደረጃ፣
– ቀድሞ ተፈርዶበት ከሆነ የወንጀሉ አይነት፣ የተወሰነው ቅጣት፣ የፍርዱ አፈፃፀም ደረጃ፣ የፈረደው ፍርድ ቤት፣
– ያለበት ማረሚያ ቤት ስም፣ የይቅርታ ጥያቄው ምክንያት፣ የስነምግባር አስተያየት ከማረሚያ ቤቱ፣ ከቅጣት ፍርዱ በፊት ስላለው ስነምግባር ሊመሰክሩ የሚችሉ የስጋ የጋብቻ ወይም የጥቅም ግንኙነት የሌላቸው 3 ምስክሮች ሙሉ ስምና አድራሻ፣
– የወኪሉ ውክልና ወይም የዝምድና ማስረጃ፣
– የማረሚያ ቤት አስተያየት ከምክንያት ጋር፣
– መቀጮ ወይም ካሳ እንዲከፍል ተወስኖበት ከሆነ ስለመክፈሉ፣ ካልከፈለ ምክንያቱ፣
– ቀደም ሲል ይቅርታ ተደርጎለት ከነበረ ወይም ጥያቄ ቀርቦ ውድቅ ተደርጎበት ከነበረ ውሳኔው የተሰጠበት ቀንና ዓመተ ምህረት፣
– ለጥያቄው ደጋፊ ማስረጃውን፣ ሰነዶች ካሉ፣ በእጁ የሌሉ ደጋፊ ሰነዶች ካሉ የሚገኙበት ቦታ የሚያለክት ሊሆን ይገባል፡፡

በዚህ መሰረት ጥያቄ የቀረበለት የይቅርታ ቦርድ ምስክር ሊሰማ ይችላል፣ የዓቃቤ ህግ እና የፍርድ ቤት መዝገብ ሊመለከት ይችላል፡፡ የይቅርታ ጥያቄዎችን ከመንግስትና ህዝብ ጥቅም አንፃር ይመዝናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቦርዱ ባወጣው የይቅርታ አሰራር ስነስረአት መመሪያ መሰረት የሚከተሉት ጉዳዮች ከግምት እንደሚገቡ ይጠበቃል፡-
• የአመልካቹ አደገኛነት፣
• የወንጀሉ ክብደት፣
• የማረሚያ ቤት ቆይታ ጊዜ፣
• ከቀድሞ መስሪያ ቤት፣ ከመኖሪያ አካባቢ ማህበረሰብ፣ ከቤተሰብ፣ ከሐኪም፣ ከሌሎች የተሰበሰቡ መረጃዎች፣
• ለወደፊት በሰላም ለመኖር የሚያሳየውን ባህሪ፣
• ጥፋተኝነቱን አምኖ በመቀበል የተፀፀተ መሆኑ፣
• ከተጎጂ/ቤተሰብ ጋር ለመታረቅና ለመካስ ያደረገው ጥረት፣ የተወሰነበትን ካሳ ለመክፈል ያለውን አቅምና ፍላጎት፣ (ማህበራዊ ፍርድ ቤት ድህነት ማስረጃ)
• ተጎጂ/ቤተሰብ ለማግኘት ከተቻለ በጥያቄው ላይ ያላቸው አስተያየት፣
• የማረሚያ ቤት ፀባይና ስነምግባር፣
• የአመልካች የቤተሰብ፣ የጤንነት (ለመታረም አስቸጋሪ ያደረገ በቦርድ የተረጋገጠ)፣ እድሜ ሁኔታ፣
• የህዝብና መንግስት ጥቅም ልዩ ሁኔታ፣
• እድሜ ልክ ፍርደኛ ከሆነ 12 አመት እስር መጨረሱን፣ ሌሎች ፍርደኞች 1/3ኛ እስር መጨረሳቸውን፣ የግዴታ ስራ ካለበት ይህን መጨረሱን፣ ናቸው፡፡

ቦርዱ የሙስና፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሽብር፣ በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሀሰተኛ ገንዘብ መስራት ማዛወር፣ አደገኛ እፅ፣ ሴቶችና ህፃናት መድፈር ወይም መጥለፍ፣ መሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀም ወንጀል የፈፀሙ ፍርደኞችን ጉዳይ በጥንቃቄ በልዩ ሁኔታ ካልሆነ እደሌሎች ወንጀሎች አያይም፡፡

በዚህ መልክ ታይቶ የሚፈቀድ የይቅርታ ውሳኔ ውጤትን ስንመለከት ውሳኔው በግልፅ በከፊል መሆኑ ካልተመለከተ በቀር ይቅርታው የፍርድ ቅጣቶችን በሙሉ ያስቀራል፡፡ ሆኖም ይቅርታ ከወንጀል ፍርዱ የሚመነጩ የፍትሐብሔር ሀላፊነቶችን አያስቀርም፡፡ በተጨማሪም በፍትሐብሔር የጠፋውን እንደነበር ለመመለስ እና በተበዳይ ላይ ለደረሰ ጉዳት የሚከፈል ካሳና ኪሳራ አያስቀርም፡፡ ሆኖም በተለይ ካልተገለፀ በቀር ለመንግስት ሊከፈል የሚገባ ወይም ያልተከፈለ ኪሳራ ቀሪ ይሆናል፡፡ ይቅርታው ከመሰጠቱ ቀድሞ የተፈፀሙ ቅጣቶች ደግሞ የፀኑ ይሆናሉ፡፡ ይቅርታ በተሰጠበት ወንጀል በአጥፊው ላይ የተያዘው የወንጀል ሪከርድ በወንጀለኞች መዝገብ ላይ ተመዝግቦ ይኖራል፡፡
ይቅርታ የተሰጠው በሀሰተኛ ወይም በተጭበረበረ ማስረጃ ተመስርቶ ከሆነ ይቅርታው ዋጋ አይኖረውም፡፡

በቅድመ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ የተሰጠ ይቅርታ ቅድመ ሁኔታው ከተጣሰ ዋጋ ያጣል፡፡ በዚህም መሰረት አጥፊው ቀሪ ቅጣቱን እንዲፈፅም ለማድረግ እንዲቻል ቦርዱ ይቅርታው እንዲሰረዝ ክብርት ፕሬዚዳንት ትእዛዝ እንዲሰጡ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ ይህ ተቀባይነት እንዳገኘ ትእዛዙ ለአጥፊው እንዲደርሰው ይደረግና ቅሬታ ካለው ትእዛዙ በደረሰው በአስራ አምስት ቀን ለቦርዱ ማቅረብ አለበት፡፡ ቅሬታው ተቀባይነት ካጣ የይቅርታ ምስክር ወረቀቱን እንዲመልስ ይደረጋል፣ በዚህም መሰረት የመያዣ ትእዛዝ እንዲሰጥ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥያቄ ቀርቦ ቀሪ ቅጣቱን እንዲፈፅም ይደረጋል፡፡

በአጠቃላይ የይቅርታ አላማ ከላይ እንደተመለከትነው አጥፊዎች ከጥፋታቸው ታርመውና ተፀፅተው ህግ አክባሪና መልካም ዜጋ ሆነው መኖር እዲችሉ ለማድረግ የሚሰጥ እድል ነው፡፡ የወንጀል ቅጣታቸው የመጨረሻ የሆነ፣ አንድ ሶስተኛ እስራታቸውን የጨረሱ፣ በማረሚያ ቤት በመልካም ባህሪ የቆዩ፣ ከጥፋታቸው የተፀፀቱና በቀጣይም ህግን አክብረው ለመኖር የሚችሉ ሰዎች የሚያገኙት ሁለተኛ እድል ሲሆን ይቅርታ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ብሎም ከወንጀል የተጠበቀ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ይቅርታ የሚሰጣቸው ሰዎችም ይህን ተገንዘበው ህብረተሰቡን በመካስ በህግ አክባሪነትና በመልካም ስነ ምግባር መመራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ሠ/መ/ቁጥር 211841 ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ/ም
በአንድ ወገን ብቻ የሚደረግ ዉል መሠረዝ (Unilateral cancellation of contract) ተግባራዊ ሊሆን የሚችለዉ በፍ/ብ/ሕጉ ከቁጥር 1786 እስከ 1889 ከተደነገጉት አራት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ተሟልቶ ሲገኝ ነዉ፡፡እነዚህም ቅድመ ሁኔታዎች፡-(1) የዉል ማፍረሻ የሚሆኑ የዉል ቃሎች በዉሉ ተገልጸዉ ሲገኙና ይሄዉ ሁኔታ ተፈጽሞ ሲገኝ ፤(2) ቁርጠኛ የሆነ የዉል መፈጸሚያ ጊዜ በዉሉ ከተመለከተ፣በማስጠንቀቂያዉ ላይ በተሰጠዉ ጊዜ ወይም በፍርድ ቤት በተሰጠ የችሮታ ጊዜ ዉስጥ ተዋዋዩ ግዴታዉን ካልተወጣ ፤(3) ከተዋዋዮቹ አንደኛዉ ወገን የገባበትን ግዴታ ለመፈጸም የማይቻለዉ ሆኖ ከተገኘና በዚህ ምክንያት የዉሉ መሰረታዊ ስምምነት ከተነካ ፤ እንዲሁም (4) ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን የዉል ግዴታዉን የማይፈጽም ስለመሆኑ ግልጽ በሆነ መንገድ ሲያሳዉቅ የሚሉ ናቸዉ፡፡ሕጉ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በመስፈርትነት ያስቀመጠዉ በተቻለ መጠን በሕግ አግባብ የተደረጉ ዉሎች እንዲፈጸሙ ጥበቃ ለማድረግና በተናጠል የሚደረገዉ የዉል መሰረዝ የመፍትሄ አማራጭ በልዩ ሁኔታ በተወሰኑ ሁኔታዎች ብቻ ተፈጻሚ እንዲሆን በመፈለግ ነዉ፡፡ ስለሆነም አንደኛዉ ተዋዋይ ወገን ሌላዉ ወገን ግዴታዉን ባለመወጣቱ ዉሉን በተናጠል ሰርዣለሁ በማለት በተከራከረ ጊዜ ከተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ቢያንስ አንዱ መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
ታክስን/ግብርን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

ታክስዎን/ግብርዎን በወቅቱ ሲከፍሉ ከብዙ እንግልት ከመዳንዎ በተጨማሪ አላስፈላጊ ቅጣት ከመቀጣት ይድናሉ፡፡ ግብርን በወቅቱ ከከፈሉ ደግሞ ለሀገርዎ እና ለእርስዎ የሚጠቅመውን በወቅቱ እና በአስፈላጊው ወቅት እንዳደረጉ ይቆጠራል፡፡

ታክስዎን በተለያየ ምክንያት ሳይከፍሉ ካዘገዩ ከሚደርስብዎት ውጣ ውረድ በተጨማሪ ቅጣቶችንም ለማስተናገድ ይገደዳሉ፡፡ ከነኚህ ቅጣቶች ውስጥ ለእርስዎ ለግንዛቤ ይረዳዎት ዘንድ የሚከተሉት ተቀንጭበው ቀርበዋል፡፡

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ፦
1. ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ)፤ እና
2. ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ)፤ ቅጣት ይከፈላል፡፡
I. የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ ዕዳ መብለጥ የለበትም፡፡
II. መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል፡፡
III. ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ የሚጣል ቅጣት በሚመለከተው ያልተከፈለ ታክስ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
222680.pdf
869 KB
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ላይ የሚገኘው parol evidence rule በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ በሚታመንበት ጊዜ ተፈጻሚነት የለውም። የውሉ ይዘት ለምሳሌ የገንዘቡ መጠን፡ በውሉ ላይ ያለው ቀን ወዘተ በሌላ ውጫዊ ማስረጃ ሊስተባበል ይችላል።
በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ ታምኖ የውሉ ይዘት ፊርማን ጨምሮ በአከራከረ ጊዜ በምን አይነት ማስረጃ ሊረጋገጥ ይገባል? የሚለው ጥያቄ በተመለከተ የሰበር ችሎት የሚከተለውን የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
የቤት ሽያጭ ውል በሕግ ሥልጣን በተሰጠው ውል አዋዋይ ፊት መደረግ አለበት በሚል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገበት አንዱ አላማ ውሉ በጽሁፍ በሰፈረው አግባብ በእርግጥ የተደረገ ስለመሆኑ እና ይዘቱም እምነት የሚጣልበት መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡በመሆኑም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ስር በጽሑፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ የተጻፈው ቀን በፈራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው የሚለው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678/ሐ፣1719/2 እና 1723/1 ስር በተደነገገው መሰረት በሕግ የታዘዘውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ ለተደረገ ውል እንጂ ለማንኛውም ውል አይደለም፡፡
🔹The Commercial Bank of Ethiopia New Vacancy

Position :1 Senior Attorney
Position :2 Senior Legal Advisor
Position :3 Legal Surveillance Officer

Education  : LLM/LLB Degree in Law , Banking, Financial Institutions or other Business Organizations.Diploma in police science or Diploma in social science fields

Date March 27, 2023 - April 05, 2023.

How to Apply
   👇👇👇
https://ethiolatestjobs.com/job/commercial-bank-of-ethiopia/

Share for your friends
     👇👇👇
https://t.me/shegarjob
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት Ricky Jackson ይባላል። Cleveland, Ohio ነዋሪ ሲሆን ገና በ18 አመቱ በለጋ እድሜው ባልሰራው ወንጀል የሞት ፍርድ ተፈርዶበት 39 አመት ከታሰረ በኋላ (አብዛኛውን ግዜ የሞት ፍርድ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ካላፀደቁት ወደ እድሜ ልክ ይለወጣል)፣ ትክክለኛው ወንጀል ፈጻሚ በመገኘቱ ዳጎስ ያለ ካሳ ተከፍሎት በነፃ የተለቀቀ ሰው ነው።

እናም ልክ ከእስር ቤት ተለቆ ሲወጣ ያሳሰረውን ሰው አገኘውና ... «ይቅር ብዬሃለው» .... ብሎ አቀፈው።

ቃለ መጠይቅ ላደረጉለት ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲ ሲል ተናገረ :-

....«እስር ቤት ውስጥ ነህ ማለት እስረኛ ነህ ማለት አይደለም»....

ነጻነት ያለው ያላችሁበት ስፍራ ላይ ሳይሆን አይምሯቹ ውስጥ ነው። የቂምና የጥላቻ እስረኛ እንዳትሆኑ ይቅር በሉ!!
ይቅር በሉ፣ መራመድ አታቁሙ ፣ ጉዳታችሁ ላይ አትቆዩ! ህይወት ሰፊና ፣ ብዙ ደርዝ ያላት የጉዞ ሃዲድ ናት!!


ይቅርታ ለራስ የሚሰጥ ድንቅ ስጦታ ነው ሰው ይቅር ማለት ሲጀምር ህይወት ይጀምራል።
የበደለንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሣይሆን ፍቅርን ማስተማር ፣ ቀንነትን መዝራት ፣ ህይወትን ማደስ ነው።

ፈጣሪ ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበትና ይቅር የሚል ብሩህ ልብ ይስጠን!
ምንጭ ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
Urgent Vacancy
                                              
1. Driver
Full time

Work station: Addis Ababa

👉Having experience is advisable.

          👉 How to Apply 👈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
consultantentrust@gmail.com

Deadline
March, 30/2023


Share for your friends
     👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
ህግ ፣ኅግ ወይስ ሕግ?
Anonymous Poll
33%
ህግ
2%
ኅግ
65%
ሕግ
የመገናኛ ብዙኃን በችሎት ዘገባ ጊዜ ሊከተሏቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች
የመገናኛ ብዙኃን በችሎት ዘገባ ጊዜ ሊከተሏቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

መገናኛ ብዙኃን ዘርፈ ብዙ መረጃዎችን ለህዝብ የሚያቀርቡ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ለህዝብ ከሚያቀርቧቸው መረጃዎች መካከል የፍርድ ቤት ክርክሮችን የተመለከቱ መረጃዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በህግ መሰረት እንይገለፁ ከተከለከሉ ወይም የፍርድ ቤት ነፃነትን የሚጋፉ ካልሆነ በቀር የሚሰጡ ውሳኔዎች፣ ትእዛዞች እንዲሁም ሌሎች ሂደቶች ለህዝብ ግልፅ በመሆናቸው መገናኛ ብዙህን መረጃዎቹን ለህዝብ ያደርሳሉ፡፡ መገናኛ ብዙኃን እነዚህ ግልፅ የሆኑ የችሎት ሥራዎች እና የክርክር ሂደቶች ሲዘግቡ ግን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የመገናኛ ብዙኃን ምንነት፣ መገናኛ ብዙኃን በችሎት ዘገባ ጊዜ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች እና የሥነ ምግባር ሁኔታዎች ይዳሰሳሉ፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ምንነት
በመገናኛ ብዙኃን በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀፅ 2(1) መሠረት መገናኛ ብዙኃን ማለት በየጊዜው የሚወጣ ህትመትን የብሮድካስት አገልግሎትን እና የበይነመረብ የመገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም የዜና እና የፕሮግራም አገልግሎት ለሕዝብ ለማቅረብ የተቋቋሙ አካላት ሲሆኑ ይህም መፃሕፍትን፣ ማኅበራዊ መገኛኛ ብዙኃንን፣ ጦማሮችን እና በየጊዜው የሚወጣ ህትመት አካል ያልሆኑ ፎቶ፣ ስዕልና ካርቱን ሳይጨምር የዜና አገልግሎት ድርጅቶችን የሚያካትት ነው፡፡
በችሎት ዘገባ ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
1. የተከሳሽን ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት ማክበር
ማንኛዉም ተከሳሽ የጥፋተኝነት ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት ከወንጀል ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት እንዳለው በህግ መንግስቱ አንቀፅ 20/3/ ስር ተመላክቷል፡፡ ምክንያቱም ከክርክር በኋላ ተከሳሹ ነፃ ሆኖ ሊገኝም ስለሚችል ነው፡፡ በመሆኑም ጋዜጠኖች የችሎት ዘገባዎችን ሲሰሩ የጥፋተኝት ፍርድ ያልተሰጠበትን ተከሳሽ ጥፋተኛ አድርጎ ከመዘገብ መቆጠብ አለባቸው፡፡
2. ሚዛናዊ መሆን
መገናኛ ብዙኃን በክርክር ላይ ባለ እና ውሳኔ ባልተሰጠው ጉዳይ ላይ አንዱ ወገን አሸናፊ በሚያስመስል መልኩ ወይም ለአንዱ ተከራካሪ ወገን በማዳላት ሚዛናዊ ባልሆነ አግባብ መዘገብ የለባቸውም፡፡ የሚያቀርቧቸው ዘገባዎችና ትንተናዎች ፍርድ ቤት አከራክሮ ውሳኔ ሊሰጥበት በሚገባው ጉዳይ ከፍርድ ቤቱ አስቀድሞ ውሳኔ መስጠት በሚመስል መልኩ የሚቀርቡ መሆን የለባቸውም፡፡
3. የምስክሮች ከጥቃት የመጠበቅ መብት
ማንኛውም ምስክር ለፍትህ እርዳት የመስጠት ህጋዊ ግዴታ አለበት፡፡ ጥቆማ ወይም ምስክርነት በመስጠቱ ምክንያት በምስክሮችና በቤተሰቦቻቸው ህይወት ወይም ንብረት ላይ አደጋ የሚፈጠር ከሆነ የምስክሮች ማንነት፣ አድራሻ፣ ንብረት እንዳይገለፅ በማድረግ የህግ ጥብቃ ይደረግላቸዋል፡፡ በመሆኑም መሰል ሁኔታዎች ሲኖሩ የምስክሮች ህይወት ወይም ንብረት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በችሎት የተገኙ ምስክሮችን ማንነት በመገናኛ ብዙኃን ከመግለፅና በዘገባ ዉስጥ ከማካተት መቆጠብ ይገባል፡፡
4. የጉዳዩን ፍሬ ነገር እንዳይዛባ መጠንቀቅ
መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ሲሰሩ በችሎት ሂደት የነበረውን ሁኔታ ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ በመዘገብ የጉዳዩ ፍሬ ነገሮች እንዳይዘቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ ጊዜ ህግ የራሱ የሆኑ ልዩ ባህሪያት ያሉት በመሆኑ ዘገባዎች የተዛቡ እንዳይሆኑ ከህግ ባለሞያ ማብራሪያ በመጠየቅ ቢሰሩ ተሻለ ይሆናል፡፡
5. ችሎት ማክበር
ችሎት የራሱ ሥነ ሥርአት አለው፡፡ ማንኛውም በችሎት የሚገኝ ሰው ይህን የችሎት ሥርአት ማክበር ያለበት በመሆኑ ዘጋቢዎች ዘገባ ለመስራት በችሎት ሲገኙ የፍርድ ቤትን የችሎት ሥነ ሥርአት ጠንቅቆ ማወቅ እና ችሎት ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. የግል ህይወት መብትን ማክበር
የግል ህይወት መከበር በህገ መንግስቱ አንቀፅ 26 መሠረት በህግ ጥበቃ የተደረገለት ሰብዓዊ መብት ነው፡፡ ይህም መብት የአንድ ሰው የግል ሕይወት፣ ሰዉነት፣ ንብረት እንዲሁም የሚፃፃፋቸው ድብዳቤዎች የተጠበቁ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ይህ መብት ለሀገር ሰላም፣ ወንጀልን ለመከላከል፣ ለህዝብ ጤና እና ሞራል ሲባል በልዩ ሁኔታ በህግ መሰረት ብቻ ሊገደብ የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚሰሩ ዘገባዎች የተከራካሪ ወገኖችንም ሆነ የማንኛውንም ዜጋ የግል ነፃነትና መብት የሚጋፉ መሆን የለባቸውም፡፡
7. ሥነ ምግባር
እያንዳንዱ ሙያ የሚጠይቀው የራሱ የሆነ ሥነ ምግባር አለ፡፡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያ መሆንም የሚጠይቀው የራሱ የሆነ የሙያ ሥነ ምግባር አለው፡፡ ለአብነትም ከአድሎ የፀዳ እና የተለያዩ ሀሳቦችን በእኩል የሚያስተናግድ ሊሆን ይገባል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የችሎት ዘገባ የሚሰራ ባለሞያ የሙያ ሥነ ምግባሩን በጥብቅ ማክበር ይጠበቅበታል፡፡
ማጠቃለያ
መገናኛ ብዙኃን የችሎት ዘገባዎችን ጨምሮ ሌሎች መረጃዎችን ለዜጎች በሚያደርሱበት ወቅት ሊከተሏቸው የሚገቡ የሥነ ምግባር ደንቦችን ማክበር ይገባቸዋል፡፡ በተለይ ችሎት ውስጥ መረጃ ሲሰበሱቡም ሆነ ሲዘግቡ በፍርድ ቤት የተቀመጡ የችሎት መመሪያዎችንና የችሎት ሥነ ሥርአት በጥንቃቄ ሊያከብሩ የሚገባ ከመሆኑም በተጨማሪ ለህዝብ የሚደርሱ ዘገባዎች የተከራካሪ ወገኖችን መብትና ነፃነትን የሚያከብሩ፣ የምስክሮችን ደህንነት የሚያስጠብቁ እንዲሁም የፍርድ ቤትን ነፃነት የማይጋፉ መሆን ይገባቸዋል፡፡

FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች

/ክፍል ሁለት/

ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎችን በተመለከተ ክፍል አንድ መረጃ አቅርበን ነበር የመረጃውን ቀጣይ እና የመጨረሻ ክፍል እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

የሚከተሉት ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ይሆናሉ፡-¬

ልብ ይበሉ:- ሚኒስትሩ በዚህ ፊደል ተራ በቁጥር (1) ፣(2) ፣(3) እና (5) በተመለከቱት ላይ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 1/2011 መሰረት ያደረገው ገደብ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለተቀጣሪው የሚከፈሉ የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ ግብር ነፃ ናቸው፡-

1. በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤
2. በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፤
3. ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፤
4. የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፤
5. የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፤
6. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፤
7. ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15 % (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤
8. በተቀባዩ ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤
9. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 59 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ስጦታው የመቀጠር፣የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
10. ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፤
11. ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፤
12. በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፤
13. ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤
14. በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ፡፡
15. ለሠራተኛ የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤ በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት የሚከፈል አበል፤ ሠራተኛው ከመደበኛ የሥራ ቦታ ውጪ ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፣ የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ ከግብር ነጻ የሚሆነው የገንዘብ መጠን ልክ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡
16. የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ለኢኮኖሚ፣ ለአስተዳደራዊ ወይም ለማህበራዊ ምክንያቶች አንድን ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ገቢዎች