አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
our discussion will start soon.....👁‍🗨
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
መልስ ያላገኘው የ ህግ ት/ት መውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ጉዳይ፣

መመሪያውን ተከትላችሁ ቅሬታችሁን በዩኒቨርሲቲያችሁ አቅርቡ በተባልነው መሰረት መንግስትን አምነን ቅሬታችን በፎርሙ መሰረት በግልጽ አስገብተናል። ሆኖም ጥያቄያችንን መመሪያውን ተከትለን በላክነው አግባብ ታይቶ ምላሽ አልተሰጠም ይላሉ።
ድምፅ ለህግ ተማሪዎች
#Ale_Hig #አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በአውሮፓ ህብረት የወንጀል ፍትህ ስርዓት ማሻሻያ በኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስር ከዚህ በታች ተያይዞ በቀረበው የጋዜጣ እትም ላይ በተጠቀሱት የስራ መስኮች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ ማስታወቂያው ከወጣበት መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በመገናኛ ብዙሃን በቀረበ ዘገባ መልካም ሥሜና ክብሬ በሃሰት ወይም በአሉታዊ ጎኑ ተጎዳብኝ ያለ ሰው ምን መብት አለው?

በዛሬው “ከነጋሪት ገጾች” አምዳችን በአዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ውስጥ ከመገናኛ ብዙሃን መብቶች እና ግዴታዎች መካከል አንዱን ነቅሰን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

በዚሁም መሰረት በመገናኛ ብዙሃን በቀረበ ዘገባ መልካም ሥሙና ክብሩ በሃሰት ወይም በአሉታዊ ጎኑ ተጎዳብኝ ያለ ማንኛውም ሰው በተመሳሳይ ሚዲያ፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ በግልፅ እና ያለክፍያ እርማት የመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን ዘገባው የቀረበው በቴሌቪዠን ወይም በሬዲዮ ፕሮግራም ላይ የነበረ ከሆነ እርማቱ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ባሉ 5 ቀናት ውስጥ መተላለፍ አለበት። ይህ ካልሆነ የእርማት መብቱን የተነፈገ ማንኛውም ሰው የፕሮግራሙ አዘጋጅ ተገዶ መልሱን እንዲያወጣለት ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል፡፡ ይሁንና የእርማት ጥያቄው ነገሩ ከተሰራጨበት ቀን ጀምሮ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የቀረበ እንደሆነ ብቻ የሚስተናገድ ስለመሆኑ አዋጁ ይደነግጋል፡፡

ዋቢ፡- የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 48
ባልና ሚስት በባህል ተጋብተው በ 1989 አመተ ምህረት አንዲት ሊጅ ወልደው ተፋትተዋል። ሚስት ልጇን ብቻዋን አሳድጋለች፤ ባልም ሌላ ትዳር መስርቶ ልጆችን አፍርቷል። እናት ልጇን ስታሳድግ በጥረቷ ንብረት አፍርታ ቤትም ሰርታለጭ። በ 2008 አመተ ምህረት ይህ ሰው ያኛዉን ትዳሩን አፍርሶ እና በጠና ታሞ ከመጀመሪያ ባለቤቱ ጋ እርዳታሽን እፈልጋለሁ በማለት ከቤቷ ይገባል፤ የጋራ ልጅ ስለነበረቻቸዉ በርህራሄ ያስጠጉትና አስታመዉት ከዳነ በኋላ አብረው ሲኖሩ ሶስት አመታትን አሳለፉ። እናም አባት ሁልጊዜ ከቤቱ ባለኩል አድርጊኝ የሚል ጥያቄ ያቀርብላት፤ እሷም ባለመስማማት ትመልሰው ነበር። ቆይተዉ ትርፍ ቦታ ስለነበረዉ ጥቂት ዶርሞችን አብረዉ እያሉ ሰርተዋል። ሁልጊዜ ባለ እኩል ካላደረግሽኝ እያለ ፤ ካልተስማምሽም እያለ ያስፈራራትም ነበር። ከዚህ በኋላ ጥያቄዉን አልቀበለዉ ስትል፤ ከእርሷ እዉቅና ዉጪ የራሱ የሆኑ ሰወችን ይዞ ፤ ገንዘብ እንዳጋባላት እና ከቤቱ ባለቤትነት እንዳስገባችዉ የሚገልጽ ዉል ጽፎ እነዚያን ሰወች ከቤት ይዞ በመምጣት እንድትፈርምለት ይጠይቃታል። ነገር ግን በሃሳቡ ባለመስማማቷ ሳትፈርም ቀረጭ። በዚህ የተናደደዉ ሰዉየዉ ሌሊት በ ተተኳሽ መሳሪያ ያስፈራራታል። ከዚያም ቤቷን ጥላ ወደቤተሰቦቿ ትሄዳለች። ከዚያም የቤት እቃዉን ሁሉ አዉጥቶ ከወሰደ በኋላ ክስ ይመሰርትባታል። ክሱም እሱ በሌለበት ቤቱን እንደዘረፈችዉ ያስረዳል።
አሁን አብረው ያፈሩትን ሃብት ሳይቆጥር ጥራ ግራ የሰርችዉን ቤት እኩል ታካፍለኝ ብሎ ከሷት ይገኛል።
ከሙያ አንጻር የሆነ ነገር በሉኝ።
በዚህ ጉዳይ ጥብቅና የሚቆምልኝም ሰው እፈልጋለሁ!
አመሰግናለሁ
https://www.abyssinialaw.com/discussions/2022-11-12-14-03-47
*የዳኛን ክብር መልሱ
ከችሎቱ ፊት አትርከሱ*‼️
ሰ/መ/ቁ 201427 4 ለ 3 በሆነ አብላጫ ድምጽ የተሰጠ

በተሻሻለው የአማራ ብ/ክ/መ/ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/09 ስለ ይርጋ የሚደነግገዉ አንቀጽ 55 ላይ የገጠር መሬትን በወረራ /invasion/ ወይም በሌላ በማናቸውም ህገወጥ መንገድ /in any illegal means/ ይዞ በመገልገል ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው መሬቱን እንዲለቅ በማንኛውም ሰው ወይም ስልጣን ባለው የመንግስት አስተዳደር አካል ሲጠየቅ ወይም በመደበኛ ፍርድ ቤት ሲከሰስ የይርጋ ጊዜ ገደብን በመቃወሚያነት ሊያነሳ እንደማይችል ይደነግጋል። በተያዘው ጉዳይም ክሱ በይርጋ እንደማይታገድ በአብላጫው ድምጽ አቋም ተይዞበታል።

አነስተኛው ድምጽ የተለየው በሰ/መ/ቁ 178927 ቅጽ 24 የተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም መቀየር አለበት/የለበትም በሚለው ላይ ነው።
በሰ/መ/ቁ 178927 ቅጽ 24 አዋጅ ቁጥር 252/09 አንቀጽ 55 አስመልክቶ በተሰጠው ትርጉም በገጠር መሬት ይዞታ ይገባኛል ክርክር ተከሳሽ የሆነ ወገን የይርጋ መቃወሚያ ለማንሳት መሬቱን በሕግ መሠረት በሚመለከተው የአስተዳደር አካል ተፈቅዶለት በሕጋዊ መንገድ ወይም በከሳሽ ፈቃድ የያዘው ስለመሆኑ አስቀድሞ የማስረዳት ኃላፊነት አለበት ተብሏል።
አነስተኛው ድምጽ ይህ የህግ ትርጉም መቀየር እንዳለበት አቋም የያዘ ሲሆን አብላጫው ድምጽ ግን ትርጉሙ ይጣጣማል እንጂ አይጋጭም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል።
በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀኑት አደጋዎች ምን ምን ናቸው
የዳኞች እና የአቃቤ ህጎች ፍልሰትና  ምክንያት ምንድን ነው

አስተያየታችሁን አጋሩን
ሰ-መ-ቁ 219306.pdf
268.4 KB
ሰ-መ-ቁ 219306
አንድ ይዞታዬ ያለአግባብ ተነጥቆብኛል የሚል ሰው ይዞታው እንዲመለስለት ክስ ሲያቀርብ የቀረበው ጉዳይ የክስ ምክንያት የለውም ሊያሰኝ የሚችልበት የህግ አግባብ የለም።
አጠቃላይ_20_80_አዲስ_የቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_1.pdf
988.2 KB
አጠቃላይ የ20/80 አዲስ የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር !

Credit : Mayor Office of AA
@tikvahethiopia
አጠቃላይ_20_80_ነባር_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
4.8 MB
አጠቃላይ የ20/80 ነባር የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር !

Credit : Mayor Office of AA
@tikvahethiopia
አጠቃላይ_40_60_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
1.3 MB
አጠቃላይ የ40/60 የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር !

Credit : Mayor Office of AA
@tikvahethiopia