አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Lawyer Executive
SARIA
Addis Ababa
Full–time


Requirements Academic qualification

• Bachelor’s degree in LLB
• Professional license/certification is a requirement. Additional qualifications
• Excellent legal drafting and communications skills;
• Sound judgment and ability to analyze situations, facts and information;
• Strong interpersonal and communication skills;
• Excellent knowledge of corporate law and procedure;
• High degree of professional ethics and integrity Years of experience: 5+ years and experience as a law executive Salary: Attractive and Negotiable

Work Place: Addis Ababa

Number of required Position/s: 1 (One)

How to apply

Submission: Interested applicants fulfilling the above requirements can submit their CV and copy of their credentials through our email address job@sariaconsult.com
For more 👇👇👇👇👇
https://etcareers.com/job/27098/lawyer-executive/?utm_campaign=google_jobs_apply&utm_source=google_jobs_apply&utm_medium=organic
Rammis Bank Job Vacancy 2022

Rammis Bank S.C invites qualified applicants for the following job positions.

The current limited number of banking services compared to the country’s population and lack of full-fledged Interest-Free Bank makes the country require many more banks with different financial products, services, and instruments.  
The existing limitations are considered as an entry point to initiate and launch a new interest-free bank – Rammis Bank. 

Position 2: Director Legal

Requirement: LLM/LLB Degree in Law with 8/10 years of related work experience respectively of which 3 years in managerial position preferably
in banking industry
 
Place of Work: Addis Ababa

How to Apply:

Interested and qualified applicants should send their documents via Rammic Bank S.C emails rammisbank@gmail.com and rammisbankho@gmail.com and are required to attach an application, degree document, curriculum vitae, work experience, and other necessary credentials within seven consecutive days from the date of this announcement.
 
• The bank has the full right to cancel or take any other alternative with regard to the vacancy announcement.
 
• Only shortlisted applicants will be communicated for interview.
 
• All documents should be scanned in pdf or Microsoft Word formats only.
https://t.me/lawsocieties
የወንጀል ቅጣት አወሳሰን 
**

በዚህ አጭር ጽሁፍ የወንጀል ቅጣት አላማ እና ግብ፣ በህጋችን የተካተቱ የቅጣት አይነቶች፣ ስለሞት ቅጣት፣ የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ምክንያቶች፣ ስለወንጀሎች መደራረብ እና ደጋጋሚነት እና ህጋዊ ውጤታቸው የሚዳሰሱ ሲሆን በተጨማሪም ቅጣት ስለሚጣልበት ወይም ስለሚወሰንበት ሁኔታ እና የቅጣት አወሳሰን ላይ የዐቃቤ ህግን ሃላፊነት እና ሚናን የሚመለከቱ ገለጻዎች ይቀርባሉ፡፡
መግቢያ
ወንጀልን እና ቅጣቱ አብሮ የሚነሳው የቅጣት አወሳሰኑ እንዲሁም የወንጀል ህጉ አላማ ነው፡፡  ቅጣት ሲጣል ወንጀለኛ ዳግም ወደ ወንጀል እንዳይመለስ እና ሌሎችም ከተቀጪው ተምረው ራሳቸውን ከወንጀል ድርጊት እንዲቆጥቡ በማስተማር እና ማስጠንቀቂያ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ የወንጀል ህግ አላማ ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ሲሆን ይህም ስለወንጀል ድርጊቶች እና ስለሚያስከትሉት ቅጣቶች አስቀድሞ በማሳወቅ ስለወንጀል ያለ ግንዛቤ መጨመር ነው፡፡ ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ ለሌላው ትምህርት እንዲሆን አስተማሪ የሆነ ቅጣትን በመቅጣት አላማውን የሚያሰካ በመሆኑ የሚጣለውም ቅጣት ወጥነት፣ ትክክለኝነት፣ ተገማችነት፣ ምክንያታዊ እና ፍታዊ መሆን አለበት ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ በ1996 የወጣው የወንጀል ህግ ፍርድ ቤቶች ቅጣትን ሲወስኑ በተመሳሳይ ጉዳዮች ተመሳሳይ ቅጣት በመወሰን የፍርድ ተገማችነትን ማምጣት አላማን ከግምት በማስገባት ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የምናየው የቅጣት አወሳሰን ላይ የአቃቤ ህግ ሃላፊነት እና ሚና፣ የቅጣት አወሳሰን መነሻ እና መድረሻ ሃሳቦች፣ የሞት ቅጣት ቀሪ መሆን አለመሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ሀሳብ ነው፡፡
የቅጣት አላማ እና ግብ

በቀደምት ታሪክ የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ18ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን እሱም በባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ኮድ (የሃሙራቢ ህግ/ኮድ)ውስጥ  አይንን ላጠፋ አይኑ ይጥፋ፣እጅ ለቆረጠ እጁ እንዲቆረጥ የሚል ህግ ነው፡፡ አሁን ከወንጀል አድራጊ የወንጀል ማድረግ መነሻ ሀሳብ ተነስተን ከግዜ ወደግዜ የወንጀል ህግ አላማ እና ግብ እያደገ መጥቷል፡፡ በ1996 አ.ም በወጣው የወንጀል ህግ አላማው ለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የሀገሪቱን መንግስት የነዋሪዎችን፣ የህዝቦችን፣ የህብረተሰቡን ሰላም፣ ደህንነት፣ መብት እና ጥቅም ማስጠበቅ እና ማረጋገጥ ነው፡፡ ከዛም ይህንን አላማ ለማሳካት ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከልን ግብ በዋነኛነት የያዘ ነው፡፡ ስለወንጀል ግንዛቤ በመፍጠር እና ማስጠንቀቂያ በመስጠት ከመከላከል ባለፈ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ ደግሞ ወንጀል ፈፃሚውን በመቅጣት ወንጀለኛውን ከሌላ ወንጀል ድርጊት መፈፀም እንዲቆጠብ በማድረግ እና ህብረተሰቡን ከወንጀለኛው እንዲማር ሌላ ተጨማሪ ወንጀል እንዳይፈፀም የማድረግ አላማ ነው፡፡ ወንጀል አድራጊዎች ተቀጥተው ከጥፋታቸው ተምረው እና ታርመው ጥሩ ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡
በቀደምት ታሪክ የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ18ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን እሱም በባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ኮድ (የሃሙራቢ ህግ/ኮድ)ውስጥ  አይንን ላጠፋ አይኑ ይጥፋ፣እጅ ለቆረጠ እጁ እንዲቆረጥ የሚል ህግ ነው፡፡ አሁን ከወንጀል አድራጊ የወንጀል ማድረግ መነሻ ሀሳብ ተነስተን ከግዜ ወደግዜ የወንጀል ህግ አላማ እና ግብ እያደገ መጥቷል፡፡ በ1996 አ.ም በወጣው የወንጀል ህግ አላማው ለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የሀገሪቱን መንግስት የነዋሪዎችን፣ የህዝቦችን፣ የህብረተሰቡን ሰላም፣ ደህንነት፣ መብት እና ጥቅም ማስጠበቅ እና ማረጋገጥ ነው፡፡ ከዛም ይህንን አላማ ለማሳካት ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከልን ግብ በዋነኛነት የያዘ ነው፡፡ ስለወንጀል ግንዛቤ በመፍጠር እና ማስጠንቀቂያ በመስጠት ከመከላከል ባለፈ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ ደግሞ ወንጀል ፈፃሚውን በመቅጣት ወንጀለኛውን ከሌላ ወንጀል ድርጊት መፈፀም እንዲቆጠብ በማድረግ እና ህብረተሰቡን ከወንጀለኛው እንዲማር ሌላ ተጨማሪ ወንጀል እንዳይፈፀም የማድረግ አላማ ነው፡፡ ወንጀል አድራጊዎች ተቀጥተው ከጥፋታቸው ተምረው እና ታርመው ጥሩ ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡
እድሜ አንፃር ስንመለከት፡- ሰዎች በእድሜያቸው መጠን ስለወንጀል ምንነት እና አፈፃፀም ያላቸው አረዳድ በእደሜያቸው ልክ የተለያየ እንደመሆኑ ቅጣትም ለመጣል እንዲሁ ይለያያል፡፡ የወንጀል ህጉ የወንጀል አድራጊን ከማስተማር እና የቅጣት አጣጣል ምጣኔን ለማምጣት ሲባል የወንጀል አድራጊዎችን በእድሜ ለይቶቷቸዋል፡፡ ይኸውም በሶስት የእድሜ ክልል የሚከፍለው ሲሆን፡- ከዘጠኝ (9) አመት በታች የሆኑትን ህፃናት በወንጀል ፍፁም ሊጠየቁ የማይችሉ፣ ከዘጠኝ(9) አመት እስከ አስራአምስት አመት(15) ዕድሜ ያሉት የጥንቃቄ እርምጃ (አንድ ቦታ ተወስነው እንዲቀመጡ፣የፀባይ ማረሚያ ቦታዎች እንዲሄዱ፣የተወሰኑ ቦታዎች ከመሄድ እንዲከለከሉ ማድረግ…) ሲሆን ይህ ቅጣት ውጤት ካላመጣ በስተቀር የገንዘብ ወይም የእስራት ቅጣት ሊቀጡ አይችሉም፣ ከአስራአምስት (15) አስከ አስራ ስምንት (18) አመት የሆኑት በመደበኛ ቅጣት የሚቀጡ ናቸው፡፡
የሞት ቅጣት

የሞት ቅጣት ክቡር የሆነዉን የሰውን ህይወት የሚያሳጣ የቅጣት አይነት ከመሆኑ የተነሳ ሁለት ተቃራኒ አቋሞች ያሉትና በብዙ መንግስታት እና በአለም ዙሪያ ያሉ ሀገራት አከራካሪ ነው፡፡ ከሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪዎች አንጻር የሚነሳ ሲሆን ሀሳባቸውን ሲገልፁ በህይወት የመኖር መብት በተፈጥሮ የተሰጠ የማይገረሰስ መብት እንደመሆኑ በፍርድ ሂደት ሊነፈግ አይችልም፡፡ የወንጀል ህጉ አላማ የወንጀል አድራጊን ማስተማር እና ማረም እንደመነሻ ያስቀመጠ በመሆኑ በሞት ቅጣት ወንጀል አድራጊን የሚያርም ሆነ የሚያስተምር አይደለም፣ በሞት ቅጣት ምክንያት ህብረተሰቡ ከወንጀለኛው ተምሮ ወንጀል ማስቀረት(መቀነስ) ይቻላል ቢባልም ተሟጋቾቹ እንደሚያነሱት የሞት ቅጣት በነበረበት ወቅት እና ባልነበረበት ወቅት ያለው የወንጀል መፈፀም መጠን ያልቀነሰ እና ልዩነት የሌለ በመሆኑ የሞት ቅጣት የሚያመጣው የተሻለ ለውጥ ባለመኖሩ ሊቀር ይገባል፣ ሌላው መከራከሪያ በሞት ቅጣት ከተቀጣ በኋላ ስህተት መሆኑ ቢታወቅ ወደኋላ የሚመለስ ባለመሆኑ የማይስተካከል ስህተት ይሆናል የሚሉ ሃሳቦች ያሉ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ የሞት ቅጣትን የሚደግፉት በሕይወት የመኖር መብት ተፈጥሮአዊ መብት ቢሆንም በከባድ ወንጀሎች አማካኝነት ግን የሞት ፍርድ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ከተፈፀመው ወንጀል አንፃር ተመጣጣኝ ቅጣት እስከሆነ ድረስ የወንጀል ህጉም እንደቅጣት ስካስቀመጠው ድረስ እና ሌሎች ከወንጀል ድርጊት እንዲቆጠቡ እስካደረገ ድረስ ተፈፃሚነት ሊኖረው ይገባል የሚሉ ናቸው፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ በወንጀል ህግ የሞት ቅጣት የሚወሰነው ከባድ ለሆኑ ወንጀሎች እንደሆነ ከድንጋጌው ዝርዝር ሀሳብ ውስጥ አካቷል፡፡ የሞት ቅጣት ከተወሰነ በኋላ እንዲፈፀም በህገመንግስቱ መሰረት ፕሬዝዳነት መፈረም አለበት፡፡ የሞት ቅጣት በወንጀል ህጉ አንቀጽ 117 (1) መሰረት፡-
1. የወንጀል ድርጊቱ በሞት የሚያስቀጣ ስለመሆኑ ወንጀሉን በሚያቋቋመው የህጉ ልዩ ክፍል በግልጽ ተደንግጎ ሲገኝ፣
2. ወንጀሉ ፍፃሜ ያገኘ ማለትም በሙከራ ደረጃ ላይ ያልተገታ ሲሆን፣
3. ቅጣቱን የሚያቀልለት ምንም አይነት ማቅለያ ምክንያት የሌለ እንደሆነ፣
4. የተፈፀመው ወንጀል እጅግ በጣም ከባድና ወንጀለኛው በተለይ አደገኛ ሲሆን እና
5. አጥፊው የቅጣት ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ እድሜው 18 የሞላዉ ከሆነ ነዉ፡፡
=============
በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ(2)
https://t.me/lawsocieties
Ethiopia Commodity Exchange (ECX) በዜሮ ዓመት ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Postion:Junior Investigation and Enforcement Officer

📚የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:
LLB(Law) Degree from recognized University.


🇪🇹 የስራ ቦታ : Addis Ababa

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡እስከ ጥቅምት
8/2015 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/job/junior-investigation-and-enforcement-officer/
Legal Aid

Amhara Bank S.C
Addis Ababa


Full–time
Job Requirements Qualifications: - Diploma/Level IV in Law (COC is mandatory for Level graduates)Experience: - 3 years relevant experience in the banking industry or court.

How To Apply:

Only shortlisted candidates will be communicated
Hard copy or physical applications will not be accepted
The Bank has the right to cancel the post.
Interested applicants fulfilling the above requirements are invited to apply within five (5) consecutive days from October 7, 2022 to October 11, 2022 only via.
Application Form - Legal Aid
For any inquiry contact us on 690.
https://t.me/lawsocieties
Company: Amhara Bank S.C
Job Type: Full Time
Work Place: Addis Ababa

Qualifications:

- LLB in Law. Experience:

- 1 year relevant experience in the banking industry or Court.

- Only shortlisted candidates will be communicated
- Hard copy or physical applications will not be accepted
- The Bank has the right to cancel the post. More Information


- Address Ethiopia
- Experience Level Junior
- Total Years Experience 0-5 Amhara Bank S.C
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from ሕግ ቤት
Deutsche Gesellschaft für Internationale Zusammenarbeit (GIZ) GmbH ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position: - Adminstrative Specialist

📚ትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:-
University degree in economics, law, or another related subject

🇪🇹 የስራ ቦታ ፡ አዲስ አበባ

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ ጥቅምት
08 /2015 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://tikusjobs.com/job/adminstrative-specialist/
ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት/Legal Immunity/
=============== ==========
ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ምንነት
ለህዝብ እና ሀገር ጥቅም ሲባል ለተወሰኑ ሰዎች የሚሰጥ በሁኔታ ላይ የተመረኮዘ የህግ ጥበቃ ሲሆን ይሄንን መብት የተጎናጸፉ ሰዎች በህግ የተደነገጉ ሁኔታዎችን እስካልተላለፉ ድረስ ወይም ከለላው እስካልተነሳ ድረስ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ ይህ ልዩ መብት ወይም (Privilege) ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን የሚሰጥበት አላማ ይህ መብት ወይም ጥበቃ የሚሰጣቸው ሰዎች ባላቸው ሀላፊነት እና ተግባር ምክንያት ስራቸውን በሚያደናቅፍ መልኩ በየምክንያቱ የማሰርና የመክሰስ ተግባር እንዳይኖር በማድረግ የሚያከናውኑትን ተግባር እና የሚወከሉትን ሀላፊነት መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ልዩ መብት ጥፋት ወይም ወንጀል ለመፈፀም ፈቃድ ለመስጠት ወይም ተጠያቂነትን ለማስቆም (impunity) እንዲኖር አይደለም፡፡ ልዩ መብቱ የሚሰጣቸው ሰዎች ይታመናሉ ህግንም ያከብራሉ ከሚል እምነት ነው፡፡ ይህ ልዩ መብት የሚሰጠው በልዩ ሁኔታ እንደመሆኑ በጠባቡ የሚተረጎምና አስፈላጊ መሆኑ በታመነ ጊዜ ብቻ በአዋጅ የሚሰጥ መሆኑ ሌላው ባህሪው ነው፡፡ ከለላው የተሰጣቸው ሰዎች ጥፋት ወይም ከባድ ወንጀል ፈፅመው ሲገኙ ግን ይህን ሁኔታ በምርመራ ክፍሉ በቂ ጥርጣሬ ብቻ ሳይሆን ከለላውን በሚከታተለው አካል የጥርጣሬው ትክክለኛነት ተረጋግጦ በህግ እንዲጠየቁ ይደረጋል፡፡

ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ያላቸው አካላት

1. የምክር ቤት አባላት
ምክር ቤት ማለት የህግ አውጪው የመንግስት አካል ሲሆን የተወሰኑ ሀገራት ባለ አንድ ምክር ቤት (unicameral) ያላቸው ሲሆን ሌሎች ደግሞ ባለ ሁለት ምክር ቤት (bicameral) የሆኑ አሉ፡፡ ስያሜውን ስናይ በኮመን ሎው የህግ ስርዐት የሚከተሉ ሀገራት የላይኛው እና የታችኛው ምክር ቤት እያሉ የሚገልጹት ሲሆን በእንግሊዘኛ አጠራሩ house of lord and house of common ይባላል፡፡

ያለመከሰስ መብት በአብዛኛው ለነዚሁ ለህዝብ እንደራሴዎች የተሰጠ መብት ሲሆን አባላቱ የወከላቸውን ህዝብ ሃሳብ እና ፍላጎት በነጻነት እንዲገልጹ እና በውጤታማነት መወከል እንዲችሉ ለማስቻል ያለመ መብት ነው፡፡

በሀገራችን የስርዐተ-መንግስት አወቃቀር መሰረት በፌዴራል እና በክልል ደረጃ የህግ አውጪ አካላት ያሉ ሲሆን በፌደራል ደረጃ ሁለት ምክር ቤቶች አሉ፡፡ እነሱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ሲሆኑ ክልሎችም የየራሳቸው ምክር ቤቶች አሏቸው፡፡ እነዚህ የምክር ቤት አባላት በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 54 ንኡስ አንቀጽ 4 እና በአንቀጽ 63 መሰረት የሁሉም ህዝብ ተወካይ ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረት ማንኛውም የምክር ቤት አባል በምክር ቤቱ ውስጥ በሚሰጠው አስተያየት ምክንያት አይከሰስም፣ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወሰድበትም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ማንኛውም የምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም በወ/መ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 19 እና 20 መሰረት እጅ ከፈንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም በወንጀልም አይከሰስም፡፡ ሆኖም ይህ መብት ፍጹማዊ መብት አይደለም፡፡ ይልቁንም በሁኔታዎች ላይ የተመረኮዘ መብት ነው።

በመሆኑም የምክር ቤት አባላት አባል የሆኑበት ምክር ቤት ሲፈቅድ ወይም የምክር ቤቱ ፈቃድ ሳያስፈልግ ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ የሚያዙበት እና የሚከሰሱበት የህግ አሰራር ያለ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በክልሎች ህገ-መንግስታት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995(እንደተሻሻለው) አንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ 3 እና 4 እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ቻርተር መሰረት የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮቹ ምክር ቤት አባላት ከላይ በተገለጸው መልኩ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሲሆን ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ ግን የሚያዙበት ሁኔታ በህግ ተደንግጓል፡፡ ለሌላ ወንጀል ጉዳይ ግን የምክር ቤቶቹ ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡ እዚህ ላይ ከባድ ወንጀል ምንድን ነው ለሚለው የአገራችንን የወንጀል ህግ ማየት የሚስፈልግ ሲሆን ህጉ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ያስቀመጠው ነገር የለም፡፡ ሆኖም የወንጀል ህጉ አንቀጽ 106 እና 108 ባስቀመጡት አግባብ ቀላል እስራት እና ጽኑ አስራት የሚያስቀጡ ወንጀሎችን እንደየሁኔታው ከባድ ወንጀልን ለመለየት በመስፈርትነት መጠቀም ይቻላል፡፡

2. የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ
በአለምአቀፍ ህግ መሰረት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የላካቸውን አገር እና አለምአቀፍ ድርጅት ወክለው ባሉበት አገር ፍርድ ቤት በወንጀልም ሆነ በፍትሐብሔር ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ ይህ ያለመከሰስ መብት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በመኖሪያቸው እና በቢሮዎቻቸው ለሚያደርጓቸው እንቅስቃሴም የሚሰጥ መብት/የህግ ጥበቃ ነው፡፡ ይህ ጥበቃ ሀገራችንም ፈርማ ባፀደቀችው የ1961 የቬና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነት መሰረት የሚሰጥ ሲሆን ለውጭ አገራት አምባሳደሮች፣ ቆንስላዎች እና የኢምባሲቸው ሰራተኞች የሚሰራ ነው፡፡ እንዲሁም ለአለምአቀፍ ድርጅት ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች ከስራቸው ጋር በተገናኘ ሀገራችን በፈረመችው የመቀመጫ ሀገር ስምምነት (host country agreement) የሚሰጥ የህግ ጥበቃ ሲሆን ሆኖም ይህ ያለመከሰስ መብት ፍጹም አይደለም፡፡ ወንጀል በሚፈጸምበት ጊዜ የላካቸውን አገር ወይም አለምአቀፍ ድርጅት የበላይ ሀላፊ ያለመከሰስ መብቱን እንዲያነሳ በመጠየቅ ሲነሳ መያዝ እና መጠየቅ የሚቻል ሲሆን ይሄንን ማድረግ ካልተቻለ ግን ተጠርጣሪውን ከአገር እንዲወጣ ማድረግ (persona non grata) የአንድ ሀገር ሉዓላዊ ስልጣን ነው፡፡

3. ዳኞች
በፌደራል የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 34 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት ማንኛውም ዳኛ ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፈንጅ ካልተያዘ ወይም በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያለመከሰስ መብቱ ካልተነሳ በስተቀር ሊያዝ፣ ሊታሰር እና ክስ ሊቀርብበት አይችልም፡፡ ይህ ህግ ዳኞች በህገመንግስቱ አንቀጽ 79 ንኡስ አንቀጽ 2 እና 3 ላይ የተደነገገውን ዳኞች ከማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ወይም ሌላ አካል ነጻ ሆነው በህግ ብቻ እየተመሩ የዳኝነት አገልግሎትን ማከናወን እንዳለባቸው የተደነገገውን ለማስፈጸም የወጣ ህግ ነው፡፡ በዚህም ዳኞች በሚወስኑት ውሳኔ ፍትህን ለማስፈን ከየትኛውም አካል መያዝ፣ እስር እና ክስ ሳይደርስባቸው ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ለማስቻል ሲሆን በዚህም ፍትህ ፈላጊው ማህበረሰብ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህ የህግ ጥበቃ ፍጹም እና ዳኞችም እንደፈለጉት እንዲሰሩ የሚፈቅድ አይደለም፡፡ ዳኞች ከላይ ባነሳነው የወንጀል ህግ እና የወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህግ መሰረት ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ ቀጥታ የሚያዙበት፣ የሚታሰሩበት እና የሚከሰሱበት ሁኔታ ያለ ሲሆን ከባድ ወንጀል ባይሆንም ወንጀል ከፈጸሙ በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ተደርጎ ተይዘው ክስም የሚቀርብባቸው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
4. የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሰረት አገራዊ ምክክሩን እንዲያመቻች በኮሚሽን ደረጃ የተቋቋመ ህጋዊ ሰውነት ያለው አገራዊ ተቋም ሲሆን ይሄንኑ ኮሚሽን እንዲመሩ በኮሚሸነርነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰየሙ 11 ኮሚሽነሮች እንዳሉት ይታወቃል፡፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15(1(ሀ) መሰረት እነዚህ ኮሚሽነሮች ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሲሆን በዚሁ መሰረት ያለመከሰስ መብታቸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልተነሳ ወይም ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ በስተቀር በኮሚሽነርነት በሚያገለግሉበት ወቅት ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ እነዚህ ኮሚሽነሮች ከባድ ሀላፊነት ያለባቸው ሲሆን ስራቸውም ከማንም አካል ተጽእኖ ነጻ ሆኖ መከናወን እንዲችል የዚህ አይነቱ ጥበቃ በህግ ተድርጎላቸው ይገኛል፡፡

5. የምርጫ ስራ አመራር ቦርድ አባላት
በምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 4 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሙሉ ጊዜ የሚያገለግሉ 5 አባላት ያሉት ስራ አመራር ቦርድ ያለው ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 15 ንኡስ አንቀጽ 6 መሰረት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ሃላፊነት ላይ አስካሉ ድረስ ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ በስተቀር ያለ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ ያለመያዝ እና በወንጀል ያለመከሰስ መብት አላቸው፡፡ ይህ መብት ስራ አመራሩ የተጣለበትን ከፍተኛ ሀላፊነት ያለ ተጽኖ በነጻነት አንዲወጣ ለማስቻል ታስቦ የተደነገገ ነው፡፡ ይሄም መብት ጊዜአዊ ሲሆን አባላቱ ሀላፊነታቸውን ሲለቁ ወይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ሲያነሳ የሚያበቃ ነው፡፡

6. ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች
በአትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 42 መሰረት የግልም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩ ተወዳዳሪ /እጩ ተመራጭ/ የሆኑ ሰዎች ከተመዘገቡበት ቀን አንስቶ ምርጫው አልቆ ውጤቱ እስኪገለጽ ድረስ በወንጀል ተጠርጥረው ያለመያዝ መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን ከባድ ወንጀል ፈጽመው እጅ ከፈንጅ ከተያዙ ተይዘው ሊከሰሱ ይችላሉ፡፡ የፈጸሙት ወንጀል እጅ ከፈንጅ ባይሆንም የህግ እርምጃ የሚወሰድባቸው ምርጫው አልቆ ውጤቱ ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡ ተጠርጣሪው በምርጫው ያሸነፈ ከሆነ በዚሁ ህግ መሰረት ሊያዝ እና ሊታሰር የሚችለው ያለመከሰስ መብቱ በተወከለበት ምክር ቤት ከተነሳ በኋላ ነው፡፡ የዚህ ከለላ ዋነኛ አለማ የምርጫ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግ እና ተወዳዳሪዎች ያለምንም እስር እና ክስ እና ሌሎች እንቅፋቶች የሚወክሉትን መራጭ የህብረተሰብ ክፍል ሀሳብ እና ፍላጎት እንዲገልጹ ወይም እንዲያራምዱ ለማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን ከለላውን ሽፋን በማድረግ ወንጀል ከፈጸሙ ከላይ በተገለጸው አግባብ ከተጠያቂነት አያመልጡም፡፡

7. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 210/2002 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) በአንቀጽ 35 መሰረት የኮሚሽኑ ከፍተኛ ሀላፊዎች እና መርማሪዎች ያለመከሰስ መብታቸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልተነሳ ወይም ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ በስተቀር አይከሰሱም፡፡ እነዚህ የስራ ሃላፊዎችም በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ዋና ኮሚሽነር፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነሮች እና የልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ የተሾሙ ኮሚሽነሮችን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም በአዋጅ ቁጥር 210/2002 አንቀጽ 2 (10) እና አንቀጽ 35 መሰረት በዋና ኮሚሽነሩ የተሰየሙ የሰብአዊ መብት ጥሰት መርማሪዎችም የዚህ መብት ተጠቃሚ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ የህግ ከለላ ያላቸው ሰዎች ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፈንጅ ከተገኙ በቀጥታ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የሚችሉ መሆኑን አይተናል፡፡ በሌላ በኩል የህግ ከለላ የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስቀር ሳይሆን ከለላው የተሰጣቸው ሰዎች ካለባቸው የስራ ሀላፊነት ልዩ ባህሪ አንጻር ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ታስቦ የተደነገገ ሲሆን በወንጀል ከተጠረጠሩ ግን ይህ ከለላ በህጋዊ ሂደት ተነስቶ የሚጠየቁ ይሆናል፡፡
በዚህም መሰረት ከባድ ወንጀል ከእጅ ከፈንጅ ውጭ በሆነ ሁኔታ ወይም ቀላል ወንጀል ፈጽመዋል ተብሎ ከተጠረጠሩ በህግ የተሰጣቸው ያለመያዝ እና ያለመከሰስ ከለላቸው እንዲነሳ በሚመለከተው አስፈጻሚ የመንግስት አካል ጥያቄ ሲቀርብ ጉዳዩ የቀረበለት የሚመለከተው ምክር ቤት በምክር ቤቱ አሰራር እና የአባላት የስነ ምግባር ደምብ መሰረት ማመልከቻ የቀረበበትን የምክር ቤት አባል ወይም የስራ ሀላፊ ያለመከሰስ መብት መነሳት አሳማኝ ሆኖ ሲያገኘው ያነሳል፡፡

ተጠርጣሪው ዳኛ ከሆነ በተመሳሳይ ሁኔታ በፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጉዳዩ ታይቶ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብቱ የሚነሳ ይሆናል፡፡ ከለላው በዚህ መልኩ ከተነሳ በ|ላ የሚመለከተው ህግ አስከባሪ መርማሪ አካል ተጠረጣሪውን የሚይዝ ዓቃቤ ህግም ክስ የሚያቀርብበት ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የሚቀጣበት የህግ አሰራር መኖሩን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህም መረዳት እንደሚቻለው የህግ የበላይነት በማንኛውም ሰው ላይ በእኩልነት የሚረጋገጥ እና የሚፈጸም መሆኑን ነው፡፡
በዮሃንስ ግርማ
ከፍትህ ሚኒስቴር ንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት