.....የቀጠለ
1. የኢትዮጵያ ህግ ምንጮች (sources of Ethiopian laws)
በአገራችን ህጎች በፌደራል እና በክልል ደረጃ ወጥተው ስራ ላይ ይውላሉ፡፡ እነዚህም ህጎች በፌደራል እና በክልሎች የተለያዩ ምንጮች አሏቸው፡፡
1.1. የፌደራል የህግ ምንጮች
i. ህገ መንግስት (constitution)
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 9 ህገ መንግስት የሀገሪቱ የበላይ ሕግ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ ማንኛውም ህግ ለምሳሌ አዋጅ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ይህ ማለት ህገ መንግስት የማንኛውም ህጎች መነሻ እና ምንጭ እንዲሁም ህጋዊነታቸውን (validation) የሚያገኙበት መሰረት ነው፡፡
ii. አለም አቀፍ ስምምነቶች (international treaties)
ሀገራት አለም አቀፍ ስምምነት ሲፈርሙ ስምምነቱን እንደ አንድ አለም አቀፍ ህግ እንተቀበሉ ማስረጃ ነው፡፡ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 9 (4) እንደሚደነግገው ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ህግ አካል ናቸው፡፡ እነዚህ ስምምነቶች ስራ ላይ ለመዋል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቅ እና በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትመው መውጣት አለባቸው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገሪቱ ህግ አካል ሆነው ተግባራዊ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡
iii. ኮዶች (codes)
በሀገራችን በ1960ዎቹ አምስት ኮዶች ተዘጋጅተው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ እነዚህም የፍትሀ ብሄር ህግ፣ የንግድ ህግ፣ የባህር ህግ በ1960፣ የወንጀል ስነ ስርዓት ህግ በ1961 እና የፍትሀ ብሄር ስነ ስርዓት ህግ በ1965 ናቸው፡፡ እነዚህም ህጎች በነጋሪት ጋዜጣ በአዋጅ መልክ ታውጀው ስራ ላይ ውለዋል፡፡ ከዚህም በኃላ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ፣ የወንጀል ህግ እና አዲሱ የንግድ ህግ በኮድ መልክ ስራ ላይ የዋሉ የአገራችን የህግ ምንጮች ናቸው፡፡
iv. አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ (proclamations, regulations & directives)
አዋጆች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ደንቦች በሚኒስትሮች ምክር ቤት እና መመሪያዎች ደግሞ በፌደራል ሚኒስትሮች መስሪያ ቤቶች ወይም በሚስትሮች ምክር ቤት መመሪያ እንዲያወጡ በደንብ ውክልና በተሰጣቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ይወጣሉ፡፡ በተጨማሪም የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማወጅ ስልጣን በህገ መንግስቱ ተሰጥቶታል፡፡ እነዚህም የህግ ክፍሎች ወይም አይነቶች የአገራችን የህግ ምንጭ በመሆን የሚያገለግሉ ሲሆኑ በስራ ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ በተመለከተ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ይህም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በሚነስትሮች ምክር ቤት ከታወጁበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ የሚውሉ ወይም በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡
v. አስገዳጅ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች (precedent)
ይህ የህግ ምንጭ አይነት ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ አስገዳጅ ወይም ህግ የሚሆንበት ስርዓት ነው፡፡ በአገራችን ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸው ውሳኔዎች በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ እንደ ህግ እንደሚያገለግሉ እና አስገዳጅ እንደሆነ የሚገልፀው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10/2 ስር እንደተደነገገው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ ባለ የፌደራል እና የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል ይላል፡፡ ይህ ማለት እነዚህ ውሳኔዎች የህግ ምንጭ ሆነው ስራ ላይ ይውላሉ ማለት ነው፡፡
vi. ልማዳዊ ህጎች (customary laws)
ልማዳዊ ህጎች በኢትዮጵያ ህጎች ውስጥ በተለያየ ጊዜ እንደምንጭ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ለምሳሌ የፍትሀ ብሄር ህጉን ያረቀቁት ፕሮፌሰር ሬኒ ዳቪድ በረቂቁ ውስጥ የኦርቶዶክስን ልማዳዊ ህግ ‘ፍትሀ ነገስትን‘ እንደምንጭ እንደተጠቀሙበት ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በህገ መንግስቱ አንቀፅ 34/5 ስር እንደተደነገገው የግል እና የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ፈቃድ በሀይማኖቶች ወይም በባሕሎች ሕጎች መሰረት መዳኘት እንደሚችሉ ያስቀምጣል፡፡ በመሆኑም ባህላዊ ወይም ልማዳዊ ህጎች እንደ አንድ የህግ ምንጭ ያገለግላሉ ማለት ነው፡፡
1.2. የክልል ህግ ምንጮች
i. የክልል ህገ መንግስት(state constitutions)
በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 52/2 ስር እንደተደነገገው ክልሎች የራሳቸው ህጎች ማውጣት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ክልሎች የራሳቸው ህገ መንግስት ከፌደራል ህገ መንግስት ጋር በሚጣጣም መልኩ አውጥተዋል እየተገለገሉበት ይገኛሉ፡፡ የክልል ህገ መንግስት በክልሎቹ ውስጥ የበላይ ህግ ነው፡፡
ii. የክልል አዋጆች (state proclamations)
የፌደራል ህገ መንግስት ክልሎች ለአስተዳደር በሚያመች መልኩ የክልሎቹን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት አዋጅ ማወጅ እንደሚችሉ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ መሰረት ለምሳሌ ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እና የደ/ብ/ብ/ህ ክልል የራሳቸው የቤተሰብ ህግ አውጀዋል፡፡
iii. የክልል ደንቦች እና መመሪያዎች (state regulations & directives)
የፌደራል ህገ መንግስት የክልል አስፈፃሚ ምክር ቤቶች በክልል ወሰን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ እንደሚችሉ እንዲሁም ደንብ እና መመሪያዎችን ማውጣት እንደሚችሉ ስልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡
2. የህጎች ተዋረድ (hierarchy of laws)
የህጎች ተዋረድ (hierarchy of laws) የህጎች የበላይነት ደረጃን ወይም የትኛው ህግ ከየትኛው ህግ የበላይ ህግ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ በአገራችን በህገ መንግስቱ አንቀፅ 9/1 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ ድርጊት እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ይደነግጋል፡፡ ይህ ማለት በሀገሪቱ ውስጥ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ህገ መንግስቱ ነው ማለት ነው፡፡
የፌደራል ህገ መንግስት በፌደራልም ይሁን በክልል ደረጃ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው፡፡ በመቀጠል የአገሪቱ የበላይ የህግ አውጪ አካል ማለትም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያወጣቸው ህጎች ማለትም አዋጆች ይከተላሉ፡፡ የአለም አቀፍ ስምምነቶችን የህግ ተዋረድ በተመለከተ ወጥ የሆነ መግባባት ባይኖርም በህገ መንግስቱ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የአገረቱ ህግ አካል ይሆናሉ ስለሚል ከአዋጅ ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ የሚል ሀሳብ አለ፡፡ በህግ ተዋረድ በመቀጠል የሚመጡት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወጡት ደንቦች እና በሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚወጡት መመሪያዎች በቅደም ተከተል ናቸው፡፡
በሌላ በኩል በተመሳሳይ ተዋረድ (hierarchy) ላይ ባሉ ህጎች መካከል መቃረን ሲኖር ተፈፃሚ የሚሆነው በጊዜ ዘግይቶ የወጣው ህግ (latest prevails) ነው፡፡ ይህ ማለት ዘግይቶ የወጣው ቀድሞ ከወጣው ይልቅ ተፈፃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ልዩ ህግ (special law) ከጠቅላላ ህግ ይልቅ ቅድሚያ ተቀባይነት (special law prevails over general law) ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties

።።።።።።።።።። የወንጀል ተጎጂዎች መብት። ።።።።።።
ወንጀል የግለሰብን እና የህብረተሰብን ጥቅም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መልኩ የሚጎዳ ድርጊት ሲሆን በተጎጂው አእምሯዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካላዊ ደህንነትን ላይ ከባድ ተፅዕኖ ያሳድራል። እንዲሁም የሰው አካል እና ህይወት መጥፋት ሊያስከትል ይችላል፡፡ እንደ ወንጀሉ አይነት የወንጀል ተጎጂዎች የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የወንጀል ተጎጂዎች መጀመሪያ በወንጀል ድርጊቱ ከደረሰባቸው ጉዳት ባሻገር ሌላ ጉዳት እንዳይደርስባቸው እና ለደረሰባቸው ጉዳት መፍትሄ እንዲያገኙ በወንጀል ፍትህ ስርዓት ውስጥ ያላቸው መብት እና ጥበቃ ምን ይመስላል የሚለው ምላሽ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም በዚህ ፅሁፍ የወንጀል ተጎጂዎች መብት በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን እውቅና እና ጥበቃ እንዲሁም በኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት ውስጥ ያለውን ቦታ እንመለከታለን፡፡...........

የወንጀል ተጎጂ ምንነት
ለወንጀል ተጎጂ በተለያዩ ፀሀፍት/ምሁራን፣ መዝገበ ቃላት እና የህግ ድንጋጌዎች የተለያዩ ትርጉሞች ተሰጥቶታል፡፡ ከእነዚህም ትርጉሞች መካከል የህግ መዝገበ ቃላት በሆነው በብላክስ ሎው ዲክሽነሪ መሰረት የወንጀል ተጎጂ ማለት በወንጀል ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ሰው (“victim is a person who has been harmed by a crime”) ነው፡፡ በሌላ በኩል ለወንጀል ተጎጂዎች ጥበቃን የሚያደርገው በ1985 የወጣው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለወንጀልና በሥልጣን አላግባብ መጠቀም ተጎጂዎች መሰረታዊ የፍትህ መርሆዎች መግለጫ (UN Declaration of Basic Principles of Justice for Victims of Crime and Abuse of Power, 1985) እንዳስቀመጠው የወንጀል ተጎጂ ማለት በአባል ሀገራት ውስጥ የሚሰሩ የወንጀል ህጎችን ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ወንጀል ጨምሮ በሚጥሱ ድርጊቶች ወይም ግድፈቶች ምክንያት በግልም ሆነ በቡድን በአካል ወይም በአእምሮ ጉዳት፣ በስሜታዊ ስቃይ፣ በኢኮኖሚ መጥፋት ወይም በመሠረታዊ መብቶቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በተጨማሪ መግለጫው እንደሚያስቀምጠው “ተጎጂ” የሚለው ቃል አግባብነት ባለው ጊዜ፣ ቀጥተኛ ተጎጂ፣ የቅርብ ቤተሰብ ወይም ጥገኞች እና በችግር ውስጥ ያሉ ተጎጂዎችን ለመርዳት ወይም ተጎጂዎችን ለመከላከል ጣልቃ በመግባት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ያጠቃልላል።
በወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ ከሳሽ በመሆን ተሟጋች ሆኖ መቅረቡ በአንድ የወንጀል ድርጊት አጠቃላይ ተጎጂው ማህበረሰቡ በጠቅላላው መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይኸውም ለአብነት አንድ የግድያ ወንጀል ቢፈፀም የሟች ቤተሰቦች ላይ የደረሰው ጥቃት በማህበረሰቡ ሰላማዊ ኑሮ ላይ ከሚደርሰው ጥቃትና ተፅዕኖ ተለይቶ ሊታይ የማይችል ይሆናል፡፡
የወንጀል ተጎጂ መብት በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው ሽፋን
የወንጀል ተጎጆዎችን መብት በተመለከተ ከቅርብ አስርት አመታት ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ክርክሮችን ያስነሳ እና መደበኛ የወንጀል ፍትህ ስርዓቱን ጥያቄ ውስጥ የከተተበት ሁኔታ ተስተውሏል፡፡ እ.ኤ.አ ከ1970ዎቹ ጀምሮ እየሰፋ የመጣው የወንጀል ተጎጂዎች መብቶች እንቅስቃሴ (victims’ right movement) በመደበኛ የወንጀል ፍትህ ስርዓት ላይ ከሚሰነዘሩት ትችቶች ዋነኛው መደበኛው የወንጀል ፍትህ ስርዓት ለወንጀል ተጎጂዎች ምን ይደረግ ከሚለው ይልቅ አፅኖት ሰጥቶ የሚቆመው ተጠርጣሪው ወይም አጥፊው ምን ይደረግ የሚለው ነጥብ ላይ ነው የሚል ነው፡፡ በመሆኑም እንደ እንቅስቃሴው እምነት መደበኛው የወንጀል ፍትህ ስርዓት ለወንጀል ተጎጂዎች ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ፍላጎቶች መልስ የሚሰጥ ባለመሆኑ በወንጀል ፍትህ ሂደት ውስጥ የወንጀል ተጎጂዎች ለዳግመኛ ተጎጂነት (secondary victimization) ይጋለጣሉ፡፡ ስለሆነም ለወንጀል ተጎጂዎች መብት ትኩረት እና ጥበቃ የሚሰጡ ህጎች አስፈላጊነት እየጎላ መጥቷል፡፡
በአጠቃላይ የወንጀል ተጎጂዎችን መብት የሚመለከት ዓለም አቀፍ ስምምነት ባይኖርም የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በ1985 እ.ኤ.አ ለወንጀልና በሥልጣን አላግባብ መጠቀም ተጎጂዎች መሰረታዊ የፍትህ መርሆዎች መግለጫን አውጥቷል፡፡ መግለጫው የወንጀል ተጎጂዎች እና ስልጣንን አላግባብ መጠቀም የሚለውን ሀሳብ እና ለተጎጂዎች ሊጠበቁላቸው የሚገቡ የተለያዩ መብቶችን አካቷል፡፡
በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.ኤ.አ. ህዳር 15 ቀን 2000 በጠቅላላ ጉባኤ ያፀደቀው አለማቀፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተዘጋጀው ሥምምነት (United Nations Convention against Transnational Organized Crime) በአንቀጽ 25 ላይ “የተጎጂዎችን እርዳታ እና ጥበቃ” በሚመለከት የተወሰኑ ጉዳዮችን ይዟል፡፡ ከዚህም ወስጥ እያንዳንዱ አባል ሀገር አቅሙ በፈቀደ መጠን ለወንጀል ተጎጂዎች እርዳታ እና ጥበቃ ማድረግ እንዳለበት፣ ለወንጀል ተጎጂዎች ካሳ እና መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆኑ እርምጃዎችን ማመቻቸት እና የሀገራቱን ህግ መሰረት በማድረግ በተጎጂዎች ላይ በተፈፀመ ወንጀል ክስ በተገቢው ደረጃ የተጎጂዎች አስተያየት እና ስጋቶች በወንጀል ፍትህ ሂደት ውስጥ እንዲታዩ ወይም እንዲሰሙ ማድረግን አካቷል፡፡ እንዲሁም የኮንቬንሽኑ/ስምምነቱ ማሟያ የሆነው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና ለመቅጣት የወጣው ፕሮቶኮል በአንቀጽ 6 በተለይም ሴቶች እና ህጻናት በሚመለከት ህገወጥ የሰዎች ማዘዋወር ሰለባዎች እርዳታ እና ጥበቃን በተመለከተ የበለጠ ዝርዝር ህጎች ይዟል፡፡ አትዮጵያም የዚህ ስምምነት ፈራሚ ሀገር እንደመሆኗ እነዚህን ግዴታዎች የሀላፊነት መወጣት ይጠበቅባታል፡፡
በተጨማሪም በአህጉር ደረጃ የአውሮፓ ምክር ቤት አባል ሀገራት እ.ኤ.አ. በ1983 የአውሮፓ ህብረት የወንጀል ጥቃት ሰለባዎች ማካካሻ ስምምነት (European Convention on the Compensation of Victims of Violent Crimes) በየካቲት 1 ቀን 1988 ሥራ ላይ አውለዋል፡፡ ይህ ስምምነት የተረቀቀው ለተጎጂዎች የሚሰጠው እርዳታ በወንጀል ፍትህ ፖሊሲ ውስጥ ቋሚ መሆን አለበት ለሚለው ምላሽ ለመስጠት ነው፡፡ እንደዚህ አይነት እርዳታ የተጎጂዎችን የስነ ልቦና ጭንቀት ለማስታገስ እና ለተጎጂው አካላዊ ጉዳት ማካካሻ ለማድረግ የተነደፉ እርምጃዎችን እንደሚያጠቃልል ተመልክቷል፡፡
ለወንጀል ተገጂዎች ሊጠበቅላቸው የሚገቡ መብቶች
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መግለጫ የተጎጂዎችን ፍላጎት ከተለያዩ መብቶች ጋር ያጣጣመና ያዛመደ ሲሆን የሚከተሉት እንደ ተጎጂዎች መብት እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
• የመከበር እና እውቅና የማግኘት መብት (Respect and Recognition)፡- ተጎጂዎች ከፍትህ አካላት ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት በክብር መያዝ አለባቸው፡፡ ጉዳታቸውም እውቅና ማግኘት አለበት፡፡ በፍትህ ሂደት ውስጥ የተጎጂዎችን ስሜት ለሚነኩ ነገሮች ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
• ጥበቃ የማግኘት መብት (Protection)፡- የወንጀል ተጎጂዎች በወንጀል ጉዳይ ምስክር ሆነው በመቅረባቸው ምክንያት ሊደርስባቸው ከሚችል ጥቃት እና ጉዳት የመጠበቅ መብት አላቸው፡፡
• ፍትህ ማግኘት እና ፍትሃዊ አያያዝ (Access to Justice and fair treatment)፡- ተጎጂዎች ፈጣን፣ ፍትሃዊ፣ ውድ ያልሆነ እና ተደራሽ በሆነ መደበኛ ወይም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ፍትሃዊ ዕርዳታ እንዲያገኙ የሚያስችል የዳኝነት እና የአስተዳደር ስልቶች መዘርጋት እና መጠናከር አለበት። ይህም ሲሆን የተጎጂዎችን ሚና እና የሂደቱን ወሰን፣ ጊዜ እና የጉዳዮቻቸውን ሂደት በተለይም በከባድ ወንጀሎች በሚሳተፉበት ወቅት መረጃዎችን እንዲያገኙ ማድርግ ተገቢ ነው፡፡
• እርዳታ እና ድጋፍ ማግኘት (Support and Assistance)፡- ተጎጂዎች አስፈላጊውን የቁሳቁስ፣ የህክምና፣ የስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ድጋፍ በመንግስታዊ፣ በበጎ ፈቃደኝነት፣ በማህበረሰብ አቀፍ እና በአገር በቀል ዘዴዎች ማግኘት አለባቸው።
• የወንጀል አሉታዊ ተፅእኖዎችን በማካካሻ እና በመመልስ መልክ ማረም (Compensation and restitution)፡- ለደረሰው ጉዳት ሀላፊ የሆኑ ወንጀለኞች ወይም ሶስተኛ ወገኖች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለተጎጂዎች፣ ለቤተሰቦቻቸው ወይም ለጥገኞች ፍትሃዊ ካሳ መስጠት አለባቸው።

የወንጀል ተጎጀዎች መብት በኢትዮጵያ ህግ ስርዓት
የኢፌደሪ ሕገ መንግሥት ፍትህ የማግኘት እና የእኩልነት መብት በአንቀፅ 37 እና 25 ስር እውቅና ሰጥቷል። በዚሁ መሰረት ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅርብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው፡፡ እንዲሁም ህገ-መንግስቱ ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል በመሆናቸው ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ይደነግጋል፡፡ የወንጀል ተጎጂዎችም የህብረተሰብ አካል እንደመሆናቸው መጠን በወንጀል ድርጊት ሳቢያ ለደረሰባቸው ጉዳት ፍትህ የመሻት እና የማግኘት መብት እንዳለቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡
ነገር ግን ህገ መንግስቱ ተጎጂዎች በልዩ ሁኔታ በፍትህ ሂደት ውስጥ ሊጠበቁላቸው የሚገቡ መብቶችን እና በሂደቱ ሊኖራቸው ስለሚገባ ተሳትፎ ለምሳሌ የመደመጥ መብት በግልፅ አላካተተም፡፡ ያካተተ አይደለም፡፡ በተለይ የወንጀል ተጎጂ ሆነው ምስክር የማይሆኑ ሰዎች ለምሳሌ ልጇ የግድያ ወንጀል የተፈፀመባት እና የድርጊቱን መፈፀም ያልተመለከተች እናት በወንጀል ፍትህ ሂደት ውስጥ የምትሳተፍበት፣ የደረሰባትን ጉዳት የምታሰማበት እና ልታስረዳ የምትችልበት እድል የላትም፡፡ እንዲሁም ከተከሰሱ ሰዎች ባልተናነሰ አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት ፍላጎት ያላቸው ቢሆንም ይህ መብት ለወንጀል ተጎጂዎች በህገ መንግስቱ፣ በወንጀል ህጉ እና በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህጉ በበቂ ሁኔታ ጥበቃ አግኝቷል ማለት አይቻልም፡፡
በሌላ በኩል በወንጀል ድርጊት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች መብት በአግባቡ ማስከበር እንዲቻል የተፈፀመው የወንጀል ዓይነት ወይም የተጎጂውን ግላዊ ሁኔታ መሠረት ያደረገ እና ለልዩ ፍላጎቶቻቸውም ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ላይ ያተኮረ አሠራር በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ እንዲዘረጋ እንደሚደረግ የወንጀል ፍትህ ፖሊሲው ያስቀምጣል፡፡ በተጨማሪም በወንጀል ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ሰው በጉዳዩ ላይ በሚደረገው የምርመራ፣ የክስ አቀራረብ እና የፍርድ ሂደት ውስጥ ተሣትፎ የማድረግ፣ ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ በቅርብ የመከታተል እና ስለሚሰጡት ውሣኔዎች ተገቢውን መረጃ የማግኘት እንዲሁም የደረሰበትን የጉዳት መጠን፣ ዕድሜውን፣ ችሎታውን እና የማኀበራዊ ኑሮ መሠረቱን ባገናዘበ መልኩ በክብርና በርህራሄ የመያዝ መብት እንዳለው ያትታል፡፡ በዚህ የፖሊሲ አቅጣጫ ውስጥ የተካተቱ መብቶች እንደ ወንጀል ህግ እና በወንጀል ስነ ስርዓት ህግ ባሉ ህጎች ውስጥ ተካተው ተግባራዊ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡
ከወንጀል ፍትህ ፖሊሲው በተጨማሪ ለወንጀል ተጎጂዎች መብት ሽፋን ሰጥቶ የምናገኘው ህግ በሰው የመነገድ እና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ሲሆን ለተጎጂዎች አስፈላጊው ጥበቃ እና ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና ድጋፉ የተጎጂዎችን ሁኔታ ያማከለ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በአዋጁ አንቀፅ 23/1 እንደተደነገገው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አግባብነት ካላቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመተባበር በውጪ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተጎጂዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የማድረግ ሀላፊነት አለበት፡፡ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በየደረጃው ያሉ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መስሪያ ቤቶች ደግሞ አግባብነት ካላቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመተባበር በሀገር ውስጥ የሚገኙ እንዲሁም ከውጪ ሀገር የተመለሱ ተጎጂዎች እንዳሉበት ሁኔታ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ እንደሚያደርግ አዋጁ ያስቀምጣል፡፡ በተጨማሪም የፌደራል የከተማ የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ እንዲሁም የገጠር የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ እንደ ቅደም ተከተላቸው መኖሪያቸው ከተማ እና ገጠር ለሆኑ ተጎጂዎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመተባበር አስፈላጊውን መልሶ የማቋቋም ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡
በአጠቃላይ በአዋጁ እንደተደነገገው በሰው የመነገድ፣ በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በህገወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጪ አገር መላክ ወንጀል ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ እንደተቋቋመ እና ፈንዱ የተጎጂዎችን የህክምና፣ የስነ-ልቦናና የህግ ምክር፣ የትራንስፖርት ወጪ ለመሸፈን፤ ለተጎጂዎች ቁሳዊ እርዳታ ለማድረግ፣ ለተጎጂዎች ጊዜያዊ መጠለያ ግንባታ ለማከናወን እና ለተጎጂዎች የሙያ እና በኢኮኖሚ እራሳቸውን እንዲችሉ ድጋፍ ለማድረግ አላማ እንደሚውል ያስቀምጣል፡፡
በተጨማሪም የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 የሽብር ድርጊት ተጎጂዎች የህክምና፣ መልሶ መቋቋምና መሰል ተግባራት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ስርዓት እንደሚዘረጋ ይገልፃል፡፡ በዚሁ መሰረት የሽብር ወንጀል ተጎጂዎች ፈንድ በአዋጁ የተቋቋመ ሲሆን ፈንዱ በሽብር ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች የህክምና ወጪ ለመሸፈንና እንዳግባብነቱ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም እንደሚውል በአዋጁ ተደንግጓል፡፡
ይሁንና እነዚህ አዋጆች ለወንጀል ተጎጂዎች ሊደረጉላቸው ስለሚገባ ድጋፍ እውቅና ከመስጠት እና ድጋፉን የሚያገኙበትን ስርዓት ከመዘርጋት ባለፈ የወንጀል ተጎጆዎች በፍትህ ሂደት ውስጥ ስለመሳተፍ ያላቸውን መብት በግልፅ አላካተቱም፡፡
በአጠቃላይ የወንጀል ተጎጂዎች የወንጀል ምስክር ሆነው የፍትህ ስርዓቱን ከማገዝው ውጪ እንደተጎጂነታቸው በወንጀል ፍትህ ስርዓት ውስጥ መብታቸውን ለማስከበር አስፈላጊውን ተሳትፎ እንዲያደርጉ እድል ሊሰጣቸው፣ ጥበቃ ሊያገኙ እና አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል፡፡

የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና
ለመፈተን በዝግጅት ላይ ለምትገኙ ተፈታኞች
የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና አስተዳደር በ 17 / 09 / 2014 ዓ.ም በተገለፀው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዋና እና ዝርዝር ሂደቱ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ በዚህ መሰረት
የተፈታኞች ምዝገባ መረጃ -
የተፈታኞች ምዝገባ ቀናት ከግንቦት 18 - 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ሰባት የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
መደበኛ ተፈታኞች በተመሩበት ዩኒቨርሲቲ የሚመዘገቡ እና የሚፈተኑ በመሆኑ መረጃቸውን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው ኃላፊነት ይወስዳል፣
የቀን መደበኛ ያልሆኑ፣ የግል እና ድጋሚ የሚፈተኑ እና ሌሎች ተፈታኞች በተማሩበት ዩኒቨርሲቲ ብቻ ይመዘገባሉ፣ ኤግዘምሽን ማድረግ የሚፈልጉትን ፈተና መረጃ ይሰጣሉ፣ የሚፈተኑበትን ዩኒቨርሲቲ ይመርጣሉ፣
ተፈታኞች የመፈተኛ ጣቢያ ሲመርጡ ከታች በተጨማሪ ማብራሪያው ላይ የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት ሊፈተኑበት የሚችሉበትን እርግጠኛ የሆኑበት ቦታ መምረጥ ይገባል፣
በልዩ ሁኔታ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተምረውና ተፈትነው የነበረ፣ በድጋሚ መፈተን የሚፈልጉ ከሆነ በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በማመልከት፣ ክፍያ በመፈፀም እና ምርጫቸውን በማሳወቅ ይፈተናሉ፣
አንድ ተፈታኝ በተፈታኝነት ለመመዝገብ ብር 850.00 (ስምንት መቶ ሃምሳ ብር) በዩኒቨርሲቲው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፣ ከዩኒቨርሲቲው ሂሳብ ቁጥር ውጪ ገቢ ማድረግ ተቀባይነት የለውም፣ ለፈተናም አይቀመጥም፣
የፈተና አስፈጻሚዎች እና ተፈታኞች ገለፃ (ኦረንቴሽን) መረጃ
አረንቴሽን ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ፈተና በሚሰጥበት ዩኒቨርሲቲ ብቻ ይሆናል፡፡
ኦረንቴሽን ለመውሰድ ተፈታኙ ስሙ በመፈተኛ ጣቢያ እንዲፈተን የተላለፈ እና የምዝገባ ቁጥር ያለው መሆን አለበት፣
ተፈታኙ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ እና ሌሎች የፈተና አሰጣጥ ሂደት የሚፈቅዳቸውን ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፣
ዓይነ ስውራን ተፈታኞች ከኦረንቴሽን በፊት ፈተናውን የሚያነብላቸው አንባቢ በሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ፈተና ጉዳይ አስተባባሪ በማመልከት በደብዳቤ እንዲገለፅላቸው ማድረግ ይጠበቃል፣ ወይም አንባቢ እንዲመደብላቸው ማመልከት ይጠበቅባቸዋል፣
ተፈታኞች የፈተና ጣቢያ ለውጥ የሚፈልጉ ከሆነ በምዝገባ ወቅት ሊያመለክቱ ይገባል፣ ሆኖም ስማቸው ከተላለፈ በኋላ የፈተና ጣቢያ ለውጥ የሚጠይቁ ወይም በፈተና መስጫ ወቅት በፈተና ጣቢያው ቢገኙ ለመፈተን የማይፈቀድላቸው በመሆኑ የፈተና ደንብ መተላለፍ እንደፈጸሙ ይቆጠራል፣
ለተፈታኞች ፈተና የሚሰጥበት ቀናት
ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ከሰኔ 21 - 24 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ አራት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 - 6፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡
ተፈታኞች ፈተና በሚሰጥበት ቀን ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ፣ ስክርቢቶ እና የተፈቀዱ ማጣቀሻዎችን በመያዝ ማለዳ ከ 1፡00 - 1፡30 ሰዓት ፈተና በሚሰጥበት ግቢ መድረስ አለባቸው፣
ያልተፈቀዱ ማንኛውንም ነገር ይዞ መምጣት አይፈቀድም፣ ይዞ የተገኘ ተፈታኝ የፈተና ደንብ መተላለፍ እንደፈፀመ ተቆጥሮ የፈተናው ውጤት በከፍል ወይም በሙሉ የሚሰረዝበት ይሆናል፣
ዓይነስውራን ተፈታኞች ከላይ የተገለፁት እንደተጠበቁ ሆኖ ፈተናውን የሚያነብላቸው አንባቢ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣ ወይም አንባቢ ባለሙያ ይመደብላቸዋል፣
የፈተና አሰጣጥ ከተጀመረበት ሰዓት ጀምሮ ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ግቢም ሆነ ወደመፈተኛ ክፍል መግባት አይፈቀድለትም፣
ዝርዝር ነጥቦች
ተፈታኞች ከምዝገባ እና ከፈተና አሰጣጥ ሂደት ጋር በተያያዘ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ተጨማሪ ግንዛቤ እንዲጨብጡ እናሳስባለን፡፡
ተፈታኞች ለምዝገባ እና ለመፈተን ሲመጡ በተጨማሪ ግንዛቤ የሚያስፈልጋቸው ሁኔታዎች -
በሚማርበት ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን ለመውሰድ የተፈቀደለት እና የተመዘገበ መሆን አለበት፣
ለምዝገባ የተወሰነውን ብር 850.00 (ስምንት መቶ ሃምሳ ብር) ክፍያ በዩኒቨርሲቲው ባንክ ሂሳብ ቁጥር ብቻ ገቢ ያደረገ መሆን አለበት፣ ከዩኒቨርሲቲው ባንክ ሂሳብ ቁጥር ውጭ በሌላ ተቋም ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ማቅረብ ወይም ከምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ ውጪ ለዩኒቨርሲቲው ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፣ ፈተና ላይ ለመቀመጥም አያስችልም፣
ለመፈተን የተመዘገበ ስለመሆኑ በዩኒቨርሲቲው በኩል ስሙ ለኢንስቲትዩቱ የተላከ መሆን አለበት፣ በምዝገባ ጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ ስሙ በዩኒቨርሲቲው መዝጋቢነት እና በኢንስቲትዩ ማረጋገጫ ያልተላለፈ ተመዝጋቢ እንዲሁም የምዝገባ ቁጥር ያልተሰጠው ተፈታኝ እንዳልተመዘገበ ተቆጥሮ ፈተና ላይ መቀመጥ አይችልም፣
ከላይ በተገለፀው የምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ ብቻ የሚፈተንበትን ዩኒቨርሲቲ ምርጫ እንዲሁም በኤግዘምሽን ምክንያት የማይፈተናቸው ፈተናዎች ካሉ ማሳወቅ አለበት፣ ከምዘገባ ጊዜ ሰሌዳው ውጭ የሚቀርብ ኤግዘምሽን መረጃ እና የዩኒቨርሲቲ ለውጥ ተቀባይነት የለውም፣
በምዝገባ ወቅት የሚፈተንበትን ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ሲመርጥ ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ ርቆ የሚገኝ ከሆነ ህጋዊ ምክንያት (የመስሪያ ቤት መታወቂያ፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ አስገዳጅ የስራ ወይም የፀጥታ ሁኔታ መረጃ፣ የሆስፒታል መረጃ፣ ሌሎች) ማሳየት / ማቅረብ አለበት፣ ጉዳዩም ለኢንስቲትዩቱ በደብዳቤ መድረስ ይገባዋል፣ በፈተና አሰጣጥ ወቅት የተፈታኞች መረጃ ማጣራት ሲደረግ ስህተት ሆኖ ከተገኘ ፈተናው ይሰረዝበታል፣
ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ ውጭ ተመዝግቦ የተገኘ ተፈታኝ ወይም ያላስተማረውን ተማሪ መዝግቦ መረጃ ያስተላለፈ ዩኒቨርሲቲ የምዝገባው መረጃ ውድቅ የሚደረግበት ሲሆን ኃላፊነቱን ተፈታኙ / ዩኒቨርሲቲው የሚወስድ ይሆናል፣ ፈተና ላይ ለመቀመጥም አያስችልም፣
በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች የተመዝጋቢዎች ዝርዝር እና የተሰበሰበ ገንዘብ ገቢ ካላደረጉ ምንም ተፈታኝ እንዳልመዘገቡ ይቆጠራል / ኃላፊነት ይወስዳሉ፣
የፈተና አሰጣጥ ገለፃ (ኦረንቴሽን) ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን ፈተና የሚሰጠው ከሰኔ 21 - 24 ቀን 2014 ዓ.ም ይሆናል፣ በመሆኑም በዚህ ሳምንት ተፈታኞች ማንነትን የሚገልጽ ህጋዊ መታወቂያ፣ እስክሪቢቶ እና የተፈቀዱ ማጣቀሻዎችን ብቻ ይዞ መገኘት ይገባቸዋል፣
በፈተና አሰጣጥ ወቅት ከተፈቀዱ ማጣቀሻዎች ውጪ ማንኛውንም ዓይነት ፅሑፍ ያለበት ወረቀትም ሆነ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ፣ የእጅ ሰዓት፣ ተፈታኙ ከስራ መደቡ አንፃር ህጋዊ የሆነ ሆኖም በፈተና ጣቢያ የማይፈቀድ ነገር ይዞ መገኘት እንዲሁም ሌሎች በፈተና አሰጣጥ ወቅት የማይፈቀዱ ነገሮችን ይዞ መገኘት አይቻልም፣ በአራተኛው የፈተና ቀናት ማንነትን ከሚገልጽ ህጋዊ መታወቂያ እና ከእስክሪቢቶ በስተቀር ምንም ነገር ይዞ መምጣት አይፈቀድም፡፡ በቅድመ ፈተና ፍተሻ ወቅት በፈተና መስጫ ግቢ እና ክፍል ውስጥ ይህ ሆኖ ከተገኘ ሙሉ የፈተና ውጤት ይሰረዛል፣
በፈተና አሰጣጥ ወቅት ምንም ዓይነት ነገር መቀያየር እና መዋዋስ የማይቻል በመሆኑ ሁሉም ተፈታኝ በግሉ የሚጠቀምበትን ነገር ይዞ መገኘት ይገባዋል፣

የፈተና አሰጣጥ ከተጀመረ በኋላ በተለያየ ህጋዊም ሆነ ህጋዊ ባልሆነ ምክንያት ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ አርፍዶ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተና ግቢም ሆነ ክፍል ውስጥ መግባት አይፈቀድም፣ በመሆኑም ለፍተሻ ሂደት እና ለቅድመ ዝግጅት ሲባል ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከሚሰጥበት ሰዓት አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ ወደ ፈተና ጣቢያ ጊቢ እንዲደርስ ይመከራል፣
ውጤትን በተመለከተ ቅሬታ ካለ ወደፊት በሚገለፀው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በአካል በመቅረብ ወይም በዩኒቨርሲቲ በኩል በደብዳቤ ለኢንስቲትዩቱ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
ውጤትን በተመለከተ ቅሬታ ካለ ወደፊት በሚገለፀው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በአካል በመቅረብ ወይም በዩኒቨርሲቲ በኩል በደብዳቤ ለኢንስቲትዩቱ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
Exit Exam
ፈተናው የሚሰጥበት ቀናት ከሰኔ 21 - 24 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ አራት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 - 6፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡

የመብራት ሃይል ሰራተኛው ፍቅረኛውን ለማግኘት መብራት በተደጋጋሚ ሲያቋርጥ ተደረሰበት!
የሴት ጓደኛውን በድብቅ ለማግኘት ሲል በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቋርጠው የመብራት ኃይል ሰራተኛ ድርጊቱ ተደረሰበት።
በህንድ ምስራቃዊ ቢሃር ፑርኒያ ወረዳ በምትገኛው የጋኔሽፑር አነስተኛ መንደር፣ አመሻሽ ላይ ጀምበር ከጠለቀች ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የሚከሰተው ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ነዋሪዎችን ለምንታት ፈትኗል። በመብራት ሃይል መስሪያ ቤቱ ምንም አይነት የኃይል ችግር አለመኖሩን እና በአጎራባች መንደሮች ውስጥ ተመሳሳይ ክስተት አለማጋጠሙ የችግሩ መንስኤ ምን እንደሆነ ለማወቅ እንዳይቻል አድርጓል።
በሁኔታው የተበሳጩት የመንደሩ ነዋሪዎች የኃይል የመቆራረጥ ችግር የተከሰተበትን ጊዜ በትኩረት መከታተል ይጀምራሉ።ሁልጊዜ አመሻሽ ሊጨላልም ሲል በመንደሩ መብራት እንደሚጠፋ ይረዳሉ።
መብራት የሚጠፋው ከ2 እስከ 3 ሰዓት ሲሆን በስተመጨረሻ ድርጊቱን የሚፈፅመው ግለሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰራተኛ እንደሆነ ይደረስበታል።ግለሰቡ ይህንን አሻጥር ፍቅረኛውን ለማግኘት እንደሚፈፅም አምኖ በመቀበሉ ክስ ባይመሰረትበትም በመንደሩ ነዋሪዎች ድብደባ ተፈፅሞበታል።
ስለ ሚስጥራዊው የፍቅር ግንኙነት ያወቁ የመንደሩ ሽማግሌዎች ሁለቱ ፍቅረኛሞች እንዲጋቡ በማስገደዳቸው የመንደሩ ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ጋብቻ ፈፅመዋል።
>ዳጉ ጆርናል
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

New at Commercial Bank of Ethiopia(Call for Written Exam )
🔰 Position: for Legal Trainee
🔰 ሙሉ ዝርዝሩን ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
👇 👇
👉Read Here:- https://bit.ly/3lBopwU
🔰 Position: for Legal Trainee
🔰 ሙሉ ዝርዝሩን ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
👇 👇
👉Read Here:- https://bit.ly/3lBopwU
#Moot_Court
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አዘጋጅነት ላለፉት 4 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የምስለ-ችሎት (Moot Court) ውድድር ግንቦት 20/ 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ በተካሄደው የፍጻሜ ዝግጅት ፍፃሜውን አግኝቷል።
በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ዙርያ ያተኮረው የዘንድሮው ውድድር ፦
➡️ በአዲስ አበባ፣
➡️ አዳማ፣
➡️ ሀዋሳ፣
➡️ ሆሳዕና፣
➡️ ሚዛን፣
➡️ ጋምቤላ፣
➡️ አሶሳ፣
➡️ ሰመራ፣
➡️ ሐረር፣
➡️ ድሬዳዋ፣
➡️ ጅግጅጋ እና ጎንደር ከተሞች የተካሄዱ ሲሆን በ10 ክልሎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ 63 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 130 ተወዳዳሪ ተማሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡
በክልላዊ የቃል ክርክር ውድድሮች 1ኛ እና 2ኛ የወጡ 24 ተወዳዳሪ ቡድኖች የጽሑፍ ክርክራቸውን ለኢሰመኮ በመላክ የተወዳደሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 8 ቡድኖች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከግንቦት 15-20 ቀን 2014 ዓ.ም በሩብ ፍፃሜ እና ግማሽ ፍፃሜ ዙሮች ተወዳድረዋል።
ከነዚህም ውስጥ ከወላይታ ከተማ፣ ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት የመጡት ተማሪ ሳያት ደሳለኝ እና ተማሪ አስቻለው ማቴዎስ እንዲሁም፣ ከጎንደር ከተማ፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኮሙኒቲ ት/ቤት የመጡት ተማሪ ብሌን ሙሉጌታ እና ተማሪ አማኑኤል ዋሴ ግማሽ ፍፃሜ አሸናፊዎች በመሆን ለፍፃሜ ውድድር መቅረብ ችለዋል።
ዛሬ በተደረጉው ውድድር ተማሪ ብሌን ሙሉጌታ እና ተማሪ አማኑኤል ዋሴ #ከጎንደር_ዩኒቨርሲቲ_ኮሙኒቲ_ትምህት_ቤት የ2ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምስለ-ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡
(ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ እና ፎቶዎች ከላይ ተያይዟል)
#EHRC
#tikvahethiopia @lawsocieties

For Women Lawyers........ 🙏👇👇
Dear all,
Greetings from EWLA Head Office!
Nairobi, Kenya Media Defence is calling for applications from women lawyers based in Burundi, Ethiopia, Kenya, (for Media Defence 23 to 25 August 2022)
Kindly find the details using the link below
https://www.mediadefence.org/news/call-for-applications-east-africa-women-litigation-surgery/
Kind regards!
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Dear all,
Greetings from EWLA Head Office!
Nairobi, Kenya Media Defence is calling for applications from women lawyers based in Burundi, Ethiopia, Kenya, (for Media Defence 23 to 25 August 2022)
Kindly find the details using the link below
https://www.mediadefence.org/news/call-for-applications-east-africa-women-litigation-surgery/
Kind regards!
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Media Defence
[NOW CLOSED] Call for Applications: East Africa Women Litigation Surgery - Media Defence
23 to 25 August 2022, Nairobi, Kenya Media Defence is calling for applications from women lawyers based in Burundi, Ethiopia, Kenya, Rwanda, Tanzania and Uganda to participate in a forthcoming litigation surgery on the right to freedom of expression and digital…