አለሕግAleHig ️ pinned «ሰላም አለ ህጎች እንዴት ናችሁ ነፃ የህግ ማማከር አገልግሎት እንሰጣለን የሚል ማስታወቂያ አይቼ ነው ፍቃደኛ ከሆናችሁ .... ፍቺ በንብረት ላይ ስላለው consequence ነው! እንደሚታወቀው በእኛ ህግ መሰረት personal property ብሎ ያስቀመጣቸው ነገሮች በፍቺ ግዜ የባለ ንብረቱ እንደሚሆን ያስቀምጣል! ነገር ግን የኔ ጥያቄ personal property ላይ በጋራ እያሉ ተጨማሪ…»
🔴Exit Exam🙏የሕግ መዉጫ ፈተና✅
ሠላም እንዴት ናችሁ ዉድ የ2014 የሕግ መዉጫ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ፣
ፈተናው 🔴 ከግንቦት 29 እስከ ሠኔ 5 ✅ የሚሠጠዉ ፈተና እስካሁን ምንም ለዉጥ ያልተደረገ መሆኑን አዉቃችሁ ዝግታችሁን እንድትቀጥሉ እየገለጽን ለውጥ የሚኖር ከሆነ የምናሳዉቅ መሆናችንን እንገልፃለን።
መሥፍን እሸቱ የ ሕግ ት/ ቤቶች አስተባባሪ
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties

#Update
.
የ2014አም መውጫ ፈተና አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግንቦት ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ ይታመናል።ከዚህ በፊት በፃፍኩት ፅሁፍ ላይም ተፈታኞች መዘናጋት እንደሌለባችሁና ጥናታችሁን በአግባቡ ልታጠኑ እንደሚገባ አሳውቄ ነበር።በግል መስመር እጅግ በጣም ብዙ ተፈታኞች በእርግጥም ፈተናው ግንቦት ወር ላይ ይሰጣል ወይ እያላችሁኝ ነው።እኔም በተደጋጋሚ እንደምገልፀው አድስ ነገር እስካልተፈጠረ ድረስና ባለድርሻ አካላቱ ተራዝሟል እስካላሉ ድረስ ሳትዘናጉ ጥናታችሁን ተከታተሉ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታም ፈተናው ግንቦት ወር እንደሚሰጥ እናምናለን ብለዋል የELSA ፕሬዝደንትና የኮንሰርቲየሙ ዋና ፀሃፊ።
.
.
#Ahmed.M

Forwarded from Qualitymovbot
የተለያዩ ጠቃሚ የህግ የቴሌግራም ቻናሎች መካከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስሞች በመንካት ቤተሰብ ይሁኑ❗️🙏
<<<<<<<<<<<<#ፍትሃዊው_ዳኛ!!>>>>>>>>>>
#አሜሪካ ውስጥ የ15 አመት ታዳጊ ሱቅ ሲሰርቅ ከዛም ሊያመልጥ ሲል አንዱን መደርደሪያ ሰበረ ይህ ፍትሃዊ ዳኛ የሰጠው ፍርድ!!
ዳኛው የክስተቱን ዝርዝር ሁኔታ ከሰማ በኋላ ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው።
"በእርግጥ የሆነ ነገር ሰረቅክ? ዳቦና አይብ ሰርቀህ መደርደሪያ ሰባበርክ?"
ልጁም አንገቱን ደፍቶ በአፍረት መለሰ፡-
አዎ.
ዳኛ፡ "ለምን ሰረቅክ?"
ታዲጊው ልጅ: በጣም ፈልጌው ነው
ዳኛ፡ ከመስረቅ ይልቅ መግዛት አልቻልክም ነበር?
ልጅ፡ ምንም ገንዘብ አልነበረኝም።
ዳኛ፡ ወላጆችህን ገንዘብ ልትጠይቅ ትችላለህ።
ልጅ፡ እኔ ያለኝ፣ አልጋ ላይ የተኛች እና ስራ የሌላት የታመመች እናቴን ብቻ ነው... ለሷ ስል ዳቦና አይብ ሰርቄያለሁ።
ዳኛ፡ እና አንተ... ምን እየሰራህ ነው? ሥራ የለህም?
ልጅ፡- የመኪና ማጠቢያ ሆኜ እሰራ ነበር። እናቴን ለመርዳት አንድ ቀን ዕረፍት ወሰድኩ፣ ለዚህም ነው ያባረሩኝ።
ከልጁ ጋር የነበረው ውይይት ካለቀ በኋላ ዳኛው ፍርዱን አስታወቁ፡-
“ሌብነት በተለይም #ዳቦ መስረቅ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው።
ለዚህ የስርቆት ወንጀል ሁላችንም ተጠያቂ ነን። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ዛሬ እኔ ራሴን ጨምሮ እዚህ ክፍል ውስጥ የተገኘ ሁሉ ተጠያቂ ነው” አለ።
በመቀጠልም ሁሉም ተሰብሳቢዎች አሥር ዶላር ይቀጣሉ እና ማንም ሰው #10_ዶላር ሳይከፍል ከአዳራሹ አይወጣም.
ዳኛው ከኪሱ የ10 ዶላር ቢል አንሥቶ እስክሪብቶ አወጣና እንዲህ ብሎ መጻፍ ጀመረ።
"በተጨማሪም የተራበውን ልጅ ለፖሊስ ያደረሰው ሱቅ ባለቤት 1,000 ዶላር እንዲቀጣ አዝዣለሁ እና ቅጣቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ካልተከፈለ ሱቁ ተዘግቶ ይቆያል."
በአዳራሹ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ለልጁ ይቅርታ ጠይቀው ሙሉ ገንዘቡን ሰጡት። ዳኛው እንባውን ለመደበቅ እየሞከረ ከችሎቱ ወጣ።
ተሰብሳቢዎቹ የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ ዓይናቸው በእንባ ተሞላ።
ዳኛው አክለውም “አንድ ሰው ዳቦ ሲሰርቅ ከተያዘ መላው የዚች ሀገር ህዝብና ህብረተሰብ ሊያፍር ይገባል” ሲሉም አክለዋል።
Source:- FB

✅✅✅ #ፍትሃዊው_ዳኛ❗️❗️
#አሜሪካ ውስጥ የ15 አመት ታዳጊ ሱቅ ሲሰርቅ ከዛም ሊያመልጥ ሲል አንዱን መደርደሪያ ሰበረ ይህ ፍትሃዊ ዳኛ የሰጠው ፍርድ!! #አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties

የቅድመ ዝግጅት ማስታወቂያ
የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመፈተን በዝግጅት ላይ ለምትገኙ ተፈታኞች (Exit Exam)
የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና ቀደም ሲል በተገለፀው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመሰራት ላይ እንገኛለን፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተፈታኞች ምዝገባ አንዱ እና ዋንኛው የቅድመ ፈተና አሰጣጥ ዝግጅት ተግባር ሲሆን ተፈታኞች ከታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች ትኩረት በመስጠት ግንዛቤ እንዲጨብጡ እናሳስባለን፡፡
የምዝገባ ቀናት ማስታወቂያ - የተፈታኞች የምዝገባ ቀናት ከጥቂት ቀናት በኋላ ሲወሰን ለሁሉም አስፈታኝ ዩኒቨርሲቲዎች በደብዳቤ እና ለተፈታኞች “ አለ ” በሚለው የቴሌግራም ቻናል ይፋ ይደረጋል፡፡
የምዝገባ ቀናት ጊዜ ሰሌዳ ቆይታ - ከተፈታኞች ምዝገባ መጠናቀቅ በኋላ የፈተና ህትመት የሚካሄድበት ወቅት በመሆኑ እና ፈተናውን በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ለመስጠት ያለው ጊዜ አነስተኛ በመሆኑ የተፈታኞች ምዝገባ ቀናት ቆይታ የተፈታኞች ምዝገባ መጀመሩ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
ተፈታኞች ለምዝገባ እና ለመፈተን ሲመጡ በተጨማሪ ግንዛቤ የሚያስፈልጋቸው ሁኔታዎች -
በሚማርበት ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን ለመውሰድ የተፈቀደለት እና የተመዘገበ መሆን አለበት፣
ለምዝገባ የተወሰነውን ክፍያ በዩኒቨርሲቲው ባንክ ሂሳብ ቁጥር ብቻ ገቢ ያደረገ መሆን አለበት፣ ከዩኒቨርሲቲው ባንክ ሂሳብ ቁጥር ውጭ በሌላ ተቋም ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ማቅረብ ወይም ከምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ ውጪ ለዩኒቨርሲቲውም ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፣ ፈተና ላይ ለመቀመጥም አያስችልም፣
ለመፈተን የተመዘገበ ስለመሆኑ በዩኒቨርሲቲው በኩል ስሙ ለኢንስቲትዩቱ የተላከ መሆን አለበት፣ በምዝገባ ጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ ስሙ በዩኒቨርሲቲው መዝጋቢነት እና በኢንስቲትዩ ማረጋገጫ ያልተላለፈ ተመዝጋቢ ፈተና ላይ መቀመጥ አይችልም፣
ወደፊት በሚገለፀው የምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ ብቻ የሚፈተንበትን ዩኒቨርሲቲ ምርጫ እንዲሁም በኤግዘምሽን ምክንያት የማይፈተናቸው ፈተናዎች ካሉ ማሳወቅ አለበት፣ ከምዘገባ ጊዜ ሰሌዳው ውጭ የሚቀርብ ኤግዘምሽን መረጃ እና የዩኒቨርሲቲ ለውጥ ተቀባይነት የለውም፣
በምዝገባ ወቅት የሚፈተንበትን ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ሲመርጥ ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ ርቆ የሚገኝ ከሆነ ህጋዊ ምክንያት (የመስሪያ ቤት መታወቂያ፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ አስገዳጅ የስራ ወይም የፀጥታ ሁኔታ መረጃ፣ የሆስፒታል መረጃ፣ ሌሎች) ማሳየት / ማቅረብ አለበት፣ ጉዳዩም ለኢንስቲትዩቱ በደብዳቤ መድረስ ይገባዋል፣ በፈተና አሰጣጥ ወቅት የተፈታኞች መረጃ ማጣራት ሲደረግ ስህተት ሆኖ ከተገኘ ፈተናው ይሰረዝበታል፣
ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ ውጭ ተመዝግቦ የተገኘ ተፈታኝ ወይም ያላስተማረውን ተማሪ መዝግቦ መረጃ ያስተላለፈ ዩኒቨርሲቲ የምዝገባው መረጃ ውድቅ የሚደረግበት ሲሆን ኃላፊነቱን ተፈታኙ / ዩኒቨርሲቲው የሚወስድ ይሆናል፣ ፈተና ላይ ለመቀመጥም አያስችልም፣
በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች የተመዝጋቢዎች ዝርዝር እና የተሰበሰበ ገንዘብ ገቢ ካላደረጉ ምንም ተፈታኝ እንዳልመዘገቡ ይቆጠራል / ኃላፊነት ይወስዳሉ፣
በፈተና አሰጣጥ ወቅት ማንነትን የሚገልጽ ህጋዊ መታወቂያ፣ እስክሪቢቶ እና የተፈቀዱ ማጣቀሻዎችን ብቻ ይዞ መገኘት ይገባል፣
በፈተና አሰጣጥ ወቅት ከተፈቀዱ ማጣቀሻዎች ውጪ ማንኛውንም ዓይነት ፅሑፍ ያለበት ወረቀትም ሆነ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ፣ የእጅ ሰዓት፣ ተፈታኙ ከስራ መደቡ አንፃር ህጋዊ የሆነ ሆኖም በፈተና ጣቢያ የማይፈቀድ ነገር ይዞ መገኘት እንዲሁም ሌሎች በፈተና አሰጣጥ ወቅት የማይፈቀዱ ነገሮችን ይዞ መገኘት አይቻልም፣ በአራተኛው የፈተና ቀናት ማንነትን ከሚገልጽ ህጋዊ መታወቂያ እና ከእስክሪቢቶ በስተቀር ምንም ነገር ይዞ መምጣት አይፈቀድም፡፡ በቅድመ ፈተና ፍተሻ ወቅት በፈተና መስጫ ግቢ እና ክፍል ውስጥ ይህ ሆኖ ከተገኘ ሙሉ የፈተና ውጤት ይሰረዛል፣
በፈተና አሰጣጥ ወቅት ምንም ዓይነት ነገር መቀያየር እና መዋዋስ የማይቻል በመሆኑ ሁሉም ተፈታኝ በግሉ የሚጠቀምበትን ነገር ይዞ መገኘት ይገባዋል፣
የፈተና አሰጣጥ ከተጀመረ በኋላ በተለያየ ህጋዊም ሆነ ህጋዊ ባለሆነ ምክንያት ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ አርፍዶ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተና ግቢም ሆነ ክፍል ውስጥ መግባት አይፈቀድም፣ በመሆኑም ለፍተሻ ሂደት እና ለቅድመ ዝግጅት ሲባል ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከሚሰጥበት ሰዓት አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ ወደ ፈተና ጣቢያ ጊቢ እንዲደርስ ይመከራል፣
ውጤትን በተመለከተ ቅሬታ ካለ በዩኒቨርሲቲ በኩል በደብዳቤ ለኢንስቲትዩቱ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
ኢንስቲትዩቱ -
መልካም የቅድመ ዝግጅት ጊዜ!
ማስታወሻ:- በቀጣይ ባሉት ቀናት እና ሳምንት ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ማስታወቂያዎችን ይከታተሉ / ለሌሎች ያሳውቁ፡፡
በ #አለ_ህግ #Ale_Hig via @Lawsocieties

#በጋራ አብሮ የመስራት ውል (joint Venture Agreement)
በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 234 መሰረት የአሽሙር ማህበር ማለት “ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸው በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት የሚያቋቁሙት በሦስተኛ ወገኖች የማይታወቅ የሕግ ሰውነት የሌለው የንግድ ማኅበር ነው፡፡” በማለት ይገልጸዋል፡፡
በዚህ አንቀጽ መሰረት ይህ አይነት ማህበር ስለሌሎች የንግድ ማህበሮች የተደነገጉት የማስመዝገብ ስርዓቶች በዚህ ማህበር ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆኑ ይገልጻል፡፡
በመሆኑም ተገልጋዮች በጋራ አብሮ የመስራት ውል(የአሽሙር ውል) ለመዋዋል ወደ መስሪያ ቤታችን ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡
. በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
. የተዋዋይ ወገኖች ወገኖች የተናጠል ወይም የየግላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣
. ተዋዋይ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረጃ ጽሁፍ፣ የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፣
. በውል ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የተገለጸና ማስረጃ የሚያስፈልገው የባለቤትነት ወይም የመብት ማጣቀሻ ካለ ይህንኑ የሚያረጋግጣ ማስረጃ፣
. የተዋዋይ ወገኖች የታደሰ መታወቂያ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተገልጋዮች የተባሉትን ዝርዝር ነገሮች አሟልተው ሲቀርቡ ለዚህ አገልግሎት የሚወስደው ጊዜ 25 ደቂቃ ነው፡፡
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ( share ) በማድረግ ብልሹ አሰራር እና ሙስናን ይከላከሉ፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig via @Lawsocieties
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የብሔራዊ የምስለ ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆኗል።
ከ19 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተወከሉ የሕግ ተማሪዎች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ በቆየው የምስለ ችሎት/Moot Court የመጨረሻ ዙር ውድድር ተካፍለዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪዎች መካከል የመጨረሻ ውድድር ተካሂዶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲ ሦሥተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
ብሔራዊ ውድድሩ "በስደተኞች ሕግ" ላይ ትኩረት ያደረገ እንደነበር ተገልጿል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ የሕግ ትምህርት ቤት ከሲቪል ሶሳይቲ ሪሶርስ ሴንተር (Civil Society Resource Center) ጋር በመተባበር ውድድሩን ማዘጋጀታቸው ተመላክቷል።

Forwarded from አለሕግ🔵AleHig
የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባሕል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የማኅበረሰብ-አቀፍ ጤና መድኅን ለመደንገግ የወጣውን ረቂቅ አዋጅ የውሳኔ ሐሳብ እና ሪፖርት መርምሮ 1273/2014 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።
የብሄራዊ ደኅንነትና መረጃ አገልግሎት ሠራተኞች የማናቸውም ፖለቲካ ፓርቲ አባላት እንዳይሆኑ የሚያዝ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል።
የሚንስትሮች ምክር ቤት መጋቢት ላይ የመራው ረቂቅ አዋጅ፣ የብሄራዊ ደኅንነትና መረጃ ተቋምን እንደገና ለማዋቀር የቀረበ ነው። ረቂቅ አዋጁ የተቋሙ ሠራተኞች በማንኛውም የፖለቲካ ቅስቀሳ እና ገቢ በሚያስገኝ ሌላ ተጨማሪ የሥራ መስክ እንዳይሰማሩ ጭምር ይከለክላል። የተቋሙ ሠራተኞች ከሥራው ባህሪ ጋር የሚመጣጠን በቂ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም እንዲከፈላቸው ለመንግሥት ጥያቄ እንደሚቀርብ የሚገልጠው ረቂቁ፣ የሠራተኛ ምልመላ፣ ቅጥር፣ ሙያዊ ስነ ምግባርና የስንብት ደንቦችን ጭምር አካቷል።ኢትዮ-መረጃ