አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Lawyer 1
Job Category: Legal

Job Type: Full-Time

Deadline of this Job:&nbsp28 August 2021

Duty Station:&nbspAddis Ababa

Posted: 23-08-2021

Vacancy title:
Lawyer

[ Type: FULL TIME , Industry: Manufacturing , Category: Legal ]

Jobs at:

Waliif Trade And Industry Share Company

Deadline of this Job:
28 August 2021  

Duty Station:
Within Ethiopia , Addis Ababa , Horn of Africa

Summary
Date Posted: Monday, August 23, 2021 , Base Salary: Not Disclosed

JOB DETAILS:
Job Type: Full Time
Location: Waliif Trade & Industry S.C head office, 4 kilo, NIB International Building, 2nd floor, Administration Dep’t 212 Head Office
Category: Legal
Job Overview
Salary Offer: Negotiable
Experience Level: Senior
Total Years Experience: 8
Job Requirement
Qualification: MA/BA in law
Work Experience: Minimum of 8 years, experience in trade and industry share company with is preferable.
Proven ability to write report, to work proactively, organize and manage own work independently
Ability of listening:- speaking, reading, writing Afaan Oromo, Amharic and English is mandatory
Work place: Head office

Work Hours: 8

Experience in Months: 96

Level of Education: Bachelor Degree

 

Job application procedure
Anyone who interested and qualified for the above mentioned posts is invited to submit application letter, CV and other copy credential documents with original for registration
Registration Date: – 5 (five) working days after the vacancy is announced. Registration Place: – Waliif Trade & Industry S.C head office, 4 kilo,NIB International Building, 2nd floor, Administration Dep’t 212
For further information, Telephone:-0118123098
Lawyer II


Bole Medhanialem, Zewdu Bldg 5th Floor Next to Kebe Pastry, Addis Ababa

  0988747248



WORK AT

Ethiopian Wildlife Conservation Authority

JOB TYPE

Employee

JOB STATUS

Full Time

ANNOUNCED

22 August, 2021

JOB TITLE

Lawyer II

JOB LOCATION

Addis Ababa, Ethiopia

JOB PRESENTATION

Ethiopian Wildlife Conservation Authority is looking to hire qualified applicants who fulfill the following requirement 

Level XI

Requirement; First degree in Law

Experience ; 2 years 

Salary: 6,193.00

Required number. 2
Place of work Head office
SALARY 6,193.00 (ETB)

VALID TILL 3 Sep, 2021
Attorney-Wolkite at Metemamen Micro Financing Institution S.C

Company: Metemamen Micro Financing Institution S.C
Location: Ethiopia
State: Debub
Job type: Full-Time
Job category: Legal Jobs in Ethiopia

Job Description

Position: Attorney

– Required No. 1 (One)
– Term of Employment: Permanent
– Place of Work: Wolkite
Qualifications/Skills

• Qualification: Diploma/BA LLB in Law
• Work Experience: 3/0 years of experience in legal practice and must be able to communicate in both in Amharic and Oromifa Languages

Method of Application
Submit your CV and Application to metemamenm@gmail.com
Telephone: 01136982 44 / 0114706866
The email candidates must scan all required documents and compile them into a single PDF Format
Use the title of the position as the subject of the email

Closing Date : 30 August . 2021
Attorney Job at Metemamen Micro Financing Institution S.C - Career Opportunity in Ethiopia New
Metemamen Micro Financing Institution S.C 1 Day Ago

Overview Requirements Job Status Location

Job Category: Legal
Job Type: Full-Time
Deadline of this Job: 31 August 2021
Duty Station: Wolkite
Posted: 23-08-2021
Requirements
Job Status
No of Jobs: 1
Start Publishing: 23-08-2021
Stop Publishing (Put date of 2030): 23-08-2030
Metemamen Micro Financing Institution S.C
Linkedid Twitter Share on facebook
Job Description

Vacancy title:
Attorney
[ Type: FULL TIME , Industry: Finance , Category: Legal ]

Jobs at:
Metemamen Micro Financing Institution S.C

Deadline of this Job:
31 August 2021
Duty Station:
Within Ethiopia , Addis Ababa , Horn of Africa

Summary
Date Posted: Monday, August 23, 2021 , Base Salary: Not Disclosed

JOB DETAILS:
Job Requirement
• Qualification: Diploma/BA LLB in Law
• Work Experience: 3/0 years of Experience in Legal Practice and must be able to communicate in both Amharic and oromifa languages
• Place of Work: Wolkite

Work Hours: 8

Experience in Months: 36

Level of Education: Associate Degree

Job application procedure
Interested and eligible candidates can send their application letter with non-returnable copies of their CVs in 7 working days from the first day of the announcement.
The email candidates must scan all required documents and compile them in to a single PDF format.
Our Address Wolo Sefer area near Picok Park Telephone 011-3-69-82-44/011-4-70-68-66 Metemamen Micro Financing Institution S.C P.O.Box 21304 Code 1000 Email; metemamenm@Gmail.Com
Job Category: Legal
Job Type: Full-Time
Deadline of this Job:&nbsp28 August 2021
Duty Station:&nbspAddis Ababa
Posted: 23-08-2021

Vacancy title:
Lawyer

[ Type: FULL TIME , Industry: Manufacturing , Category: Legal ]

Jobs at:

Waliif Trade And Industry Share Company

Deadline of this Job:
28 August 2021

Duty Station:
Within Ethiopia , Addis Ababa , Horn of Africa

Summary
Date Posted: Monday, August 23, 2021 , Base Salary: Not Disclosed

JOB DETAILS:
Job Type: Full Time
Location: Waliif Trade & Industry S.C head office, 4 kilo, NIB International Building, 2nd floor, Administration Dep’t 212 Head Office
Category: Legal
Job Overview
Salary Offer: Negotiable
Experience Level: Senior
Total Years Experience: 8
Job Requirement
Qualification: MA/BA in law
Work Experience: Minimum of 8 years, experience in trade and industry share company with is preferable.
Proven ability to write report, to work proactively, organize and manage own work independently
Ability of listening:- speaking, reading, writing Afaan Oromo, Amharic and English is mandatory
Work place: Head office

Work Hours: 8

Experience in Months: 96

Level of Education: Bachelor Degree


Job application procedure
Anyone who interested and qualified for the above mentioned posts is invited to submit application letter, CV and other copy credential documents with original for registration
Registration Date: – 5 (five) working days after the vacancy is announced. Registration Place: – Waliif Trade & Industry S.C head office, 4 kilo,NIB International Building, 2nd floor, Administration Dep’t 212
For further information, Telephone:-0118123098
ttorney-Wolkite at Metemamen Micro Financing Institution S.C

Company: Metemamen Micro Financing Institution S.C
Location: Ethiopia
State: Debub
Job type: Full-Time
Job category: Legal Jobs in Ethiopia

Job Description

Position: Attorney

– Required No. 1 (One)
– Term of Employment: Permanent
– Place of Work: Wolkite
Qualifications/Skills

• Qualification: Diploma/BA LLB in Law
• Work Experience: 3/0 years of experience in legal practice and must be able to communicate in both in Amharic and Oromifa Languages

Method of Application
Submit your CV and Application to metemamenm@gmail.com
Telephone: 01136982 44 / 0114706866
The email candidates must scan all required documents and compile them into a single PDF Format
Use the title of the position as the subject of the email

Closing Date : 30 August . 2021
የቅጣት ማክበጃ ምክንያት (aggravating circumstance)
--------------------
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ የፌስቡክ ገጽ ተከታታዮቻችን እንዴት ናችሁ ለዛሬ አንድ ሰው በማወቅም ይሁን ባለማዎቅ በሰራው ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርቦ በሚከራከርበት ሰዓት ዐቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ ምክኒያቶችን አቀረበ ሲባል እንሰማለን ለመሆኑ የቅጣት ማክበጃ ምክኒያቶች ምንድን ናቸው?
የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች በሁለት ይከፈላሉ እነኚህም ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት እና ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ለዛሬ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን በተመለከተ ያዘጋጀንላችሁ አጭር ገለጻ እነሆ….ከወዲሁ መልካም ንባብ ተመኝን፡-
ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች የምንላቸው በወንጀል ህጋችን በአንቀጽ 84 ስር የተዘረዘሩት ናቸው፡፡
የወንጀል ህጋችን አንቀጽ 84(1) ከፊደል ተራ ሀ-ሠን እንደሚከተለው ተመልክተናቸዋል፡፡

ሀ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው በከሀዲነት ወይም በወስላታነት ወይም በወራዳነት ወይም መጥፎ አመልን በሚያሳይ ምቀኝነት፣ጥላቻ፣ ስግብግብነት፣ መጥፎ ነገርን ለመስራት ወይም ሰውን ለመጉዳት ፍጹም ፍቃደኛ በመሆን ወይም በተለየ ክፋት ወይም በጨካኝነት እንደሆነ ይላል
ወንጀል ታስቦ ወይም በቸልተኛነት ሊፈጸም ይችላል፡፡ከላይ የምንመለከተው ወንጀልን አስበው እና ሆነ ብለው የሚፈጽሙ ሰዎች በፈጸሙት ወንጀል ማግኘት ካሰቡት ያልተገባ ብልጽግና በተጨማሪ ወንጀሉን ለማድረግ ካነሳሳቸው ወይም ምክንያት ከሆናቸው ነጥብ አንጻር የወንጀል አድራጊውን አደገኛነት የሚያመላክት እንደሆነ ፍ/ቤቶች ከላይ በተዘረዘሩት የማክበጃ ምክንያቶች መሰረት ቅጣትን ሊያከብዱ ይችላሉ፡፡በዚህ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ስር የተለያዩ ምክንያቶች የተዘረዘሩ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት ቅጣትን ለማክበድ ከመካከላቸው የአንዱ መሟላት በቂ ነው፡፡ይህም ማለት ተከሳሽ ወንጀሉን ያደረገው በከሃዲነት ወይም በወስላታነት ወይም በምቀኝነት ወይም በጥላቻ ከሆነ ከነዚህ መካከል አንዱ በወንጀል አድራጊው ወንጀል አደራረግ ውስጥ ከተገኘ በቂ ነው ማለት ነው፡፡እምነቱን በጣለበት ወዳጁ ላይ፣ በተበዳዩ ላይ ባለው የግል ጥላቻ ወይም በምቀኝነት(ጥቅም ለማግኘት ብቻ ሳይሆን አንድ ሰው ጥቅም እንዳያገኝ በማሰብ) ወዘተ ወንጀልን ማድረግ በአብነት ሊነሱ ይችላሉ፡፡

ለ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው ስልጣኑን፣ ተግባሩን ወይም የተጣለበትን እምነት ወይም ሀላፊነት ያለአግባብ በመገልገል እንደሆነ
ባለስልጣናት ወይም የመንግስትን ስራ ለመስራት ወይም ለመምራት ስልጣን ወይም እምነት የተጣለበት ሰው ስራውን በታማኝነት እና በቅንነት መፈጸም አለበት፡፡በተጨማሪም ይህንኑ ስልጣን ተገን በማድረግ ለራሱም ሆነ ለሌላው ጥቅም ለማስገኘት ወይም በሌላ ሰው ጥቅም ወይም መብት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ አንድን ወንጀል ከፈጸመ ቅጣት ሊከብድበት እንደሚገባ የወንጀል ህጉ ይደነግጋል፡፡ይህ የሆነበት ምክንያት ሰዎች ስራ ፈጻሚዎች የሚነግሯቸውን ወይም እንዲያደርጉ የሚያዟቸውን ነገር ሁሉ ስለሚቀበሉ እና ትዕዛዙን መቀበል ካልቻሉ ደግሞ የሚፈልገውን አገልግሎት ላናገኝ እንችላለን ከሚል የአማራጭ ማጣት ሀሳብ ምክንያት ለጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ወንጀል አድራጊውም እምነት ሲጣልበት እምነቱን ወይም አደራውን በተገቢ መንገድ መወጣት አለበት፡፡

ስራውን የሠጠው ሰው እምነቱን የጣለበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጠባቂ የሌለው በመሆኑ ስልጣኑን ወይም ሀላፊነቱን ለግል ጥቅሙ ለማዋል አይችልም፡፡ሰነዶችን በህገ-ወጥ መንገድ ለማይገባው ሰው የሰጠ የመዝገብ ቤት ወይም የአገልግሎት መስጫ ተቋም ሰራተኛ፣ ሌላውን ሰው ከህጋዊ ቅጣት ወይም ክፍያ ለማዳን ሲል ወንጀልን የፈጸመ የትራፊክ ፖሊስ ወይም መርማሪ ፖሊስ እና የመሳሰሉት በምሳሌነት ሊነሱ ይችላሉ፡፡በመሆኑም ከላይ የጠቀስነውን ሁኔታ ተሟልቶ ሲገኝ እንደ አንድ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ተወስዶ ቅጣትን በአንድ እርከን ከፍ ሊያደርግ የሚችል ምክንያት ነው፡፡

ሐ/ ወንጀለኛው በቀድሞ ጥፋተኛነቱ ወይም ወንጀልን ማድረግ ሙያ ወይም ልማድ አድርጎ መያዙ፣ ወይም የወንጀሉ አፈጻጸም ዘዴ፣ ጊዜ፣ ቦታና የአፈጻጸም አኳሀን፣ በተለይም በሌሊት ወይም በሽብር ወይም በሁከት ለአደጋ ሽፋን ወይም በጦር መሳርያ ወይም በሌላ አደገኛ መሳርያ ወንጀሉን በማድረግ የተለየ አደገኝነቱን አሳይቶ እንደሆነ
በዚህ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ስር ሶስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ እነኚህም፡-ወንጀልን ማድረግ ሙያው ወይም ልማዱ አድርጎ መያዝ ወንጀል አፈጻጸም ዘዴ፣ጊዜ፣ቦታ እና የአፈጻጸም አኳሀን ወንጀልን በጦር መሳርያ ወይም በሌላ አደገኛ መሳርያ መፈጸም ናቸው፡፡

ወንጀል ማድረግን ሙያው ወይም ልማድ አድርጎ መያዝ ማለት ተከሳሹ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት ተመሳሳይ ወይም የተለያዩ ወንጀሎችን በማድረግ የሚታወቅ እና ፍርድ ቤቶች የዚህን ሰው ጉዳይ ተመለክተው በሚሰጡት የመጨረሻ ውሳኔ ጥፋተኛ እያሉት ቅጣት የጣሉበት እና በማረሚያ ቤት ገብቶ የእስር ጊዜውን አጠናቆ ከወጣ በኋላም ወንጀልን ማድረግ ባለማቆም ወንጀልን ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡የወንጀል ህጉ በአንቀጽ 67 ስር ስለደጋጋሚነት ያስቀመጠው ድንጋጌ የተካሳሹን የቀድሞ ባህሪ በቅጣት ማክበጃነት ልንጠቀም እንደምንችል ይደነግጋል፡:

ሌላው ወንጀል አድራጊው ወንጀሉን ለማድረግ አስቀድሞ በማሰብ ተጎጂው እራሱን እንዳይከላከል ወይም ሰው እንዳይደርስለት ወይም ማስረጃ እንዳይገኝበት ለየት ያለ ቦታ በመምረጥ፣ ወይም ሰው በማይንቀሳቀስበት በሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግ የፈጸመው እንደሆነ ወይም የወንጀል አድራጊውን አደገኛነት በሚያሳይ ጨካኝነት ወይም በተለየ ስልት ወንጀልን ከፈጸመ፡፡ሌሊት የሚለው ሀረግ ከስንት ሰዓት ጀምሮ እንደሆነ አሻሚ ቢሆንም በተለምዶ ፍርድ ቤቶች ከሌሊቱ 6፡00-12፡00 ድረስ ያለውን የጊዜ ገደብ በሌሊትነት ወስደው ቅጣት ያከብዱበታል፡፡

ሶስተኛው ምክንያት ወንጀልን ለመፈጸም ወንጀል አድራጊው የተጠቀመባቸው መሳርያዎች ናቸው፡፡ ወንጀልን ለመፈጸም ጥቅም ላይ የሚውል መሳርያ የወንጀል አደራረግን ከባድነት ያሳያሉ፡፡በመሆኑም በእጅ ወይም በዱላ የውንብድና ወንጀልን የፈጸመ ሰው እና የስለት ወይም የጦር መሳርያዎችን ተጠቅሞ ይህንኑ ወንጀል የፈጸመ ሰው የወንጀል ማድረግ አደገኛነቱ እኩል ሊሆን አይችልም፡፡በመሆኑም ተከሳሽ ወንጀሉን ለመፈጸም የተጠቀመው መሳርያ በወንጀል ማቋቋሚያነት በልዩ ህጉ ካልተወሰደ በስተቀር በቅጣት ማክበጃ ምክንያትነት ይወሰዳል፡፡
መ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው ወንጀል ለመፈጸም በተደረገ ስምምነት መሰረት ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን ወይም ወንጀል ለመፈጸም ከተቋቋመ ቡድን ጋር በመስማማት ወይም አባል በመሆን ይልቁንም እንደ ወንጀል ቡድን ሹም ወይም አደራጅ ወይም መሪ በመሆን እንደሆነ
በየትኛውም ምክንያታዊ አስተሳሰብ በአንድ ሰው መብት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በተናጠል እና በቡድን ወይም ከአንድ በላይ በመሆን መፈጸሙ በተጎጂው ስነልቦና ላይ የሚያደርሱት ተጽዕኖ አንድ ሊሆን አይችልም፡፡በመሆኑም ወንጀልን ለመፈጸም ከሌላው ጋር ወይም ለዚሁ አላማ ከተደራጀ ቡድን ጋር በአባልነት በመስማማት ወንጀልን ማድረግ ቅጣትን ሊያከብድ የሚችል በቂ ምክንያት ነው፡፡
ሠ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው በዕድሜው፣ በጤንነቱ፣ በኑሮው ወይም በስራው ሁኔታ ልዩ ጥበቃ በሚያሻው ሰው ላይ በተለይም ለመከላከል አቅም በሌለው፣ መንፈሰ ደካማ፣ በሽተኛ ወይም አካል ጉዳተኛ ፣ እስረኛ ወይም በቅርብ ዘመዱ ላይ ወይም የበላዩ ወይም የበታቹ በሆነ ሰው ላይ፣ በህግ በተቋቋመ ባለስልጣን ወይም የስራ ግዴታውን በማከናወን ላይ በሚገኝ በአንድ የህዝብ አገልጋይ በሆነ ሰራተኛ ላይ እንደሆነ ነው ሲል ይደነግጋል፡፡
ውድ አንባቢያን ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁን አተታ በዚሁ አበቃን በቀጣይ ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክኒያቶች ምንድናቸው የሚለውን ይዘንላችሁ እንቀርባለን ሰላም፡፡
ጠ.አቃቤ ህግ
ሀሰተኛ ወይም አስጠቂ ምስክርነት መስጠት የሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት
ሰላም ጤና ይስጥልን እንደምን አላችሁ የፅሁፋችን አንባቢዎች ዛሬ ደግሞ ስለ ሀሰተኛ /አስጠቂ/ ምስክር ምንነት ላይ ማብራሪያ ልንሰጣቹ ወደናል፡፡
አንድአንድ ሰዎች ያላግባብ ግለሰቦችን ለመጉዳት ወይም ለመጥቀም ሲሉ ሀሰተኛ /አስጠቂ/ ምስክርነቶችን ሲሰጡ ይስተዋላል፤ ታዲያ እኛም ሀሰተኛ ወይም አስጠቂ ምስክርን አስመልክቶ ያላችሁን ግንዛቤ ለማዳበር ጽሁፋችንን አዘጋጅተናል፡፡
በመሆኑም አስጠቂ ምስክር ሲባል ምን ማለት ነው? በሀሰት መመስከርስ ምን ያስቀጣል? የሚሉትን ለናንተ ለማስቃኘት ወደናል፡፡ ሀሰተኛ ወይም አስጠቂ ምስክር ማለት ከቃሉ ትርጓሜ ስንነሳ በሀሰት መመስከር ወይም ይመሰከርልኛል ብለን ካመጣነው ጭብጥ በተለየ እና ክሱን በሚጎዳ መልኩ መመስከር፣ ማስጠቃት፣ መጉዳት የሚለውን ትርጓሜ ይሰጠናል።

በሀገራችን አስጠቂ ወይም ሀሰተኛ ምስክርነትን አስመልክቶ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፊ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 452 ስለ አንድ ተከራካሪ ወገን የሚሰጠው ሀሰተኛ ቃል፡ 453 ስለ ሀሰተኛ ምስክርነት አስተያየት ወይም ትርጉም፡ 454 ላይ ቃልን ስለማቃናትና መለወጥ እያለ በተከታታይ ድንጋጌዎች ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ድንጋጌዎች በወንጀል የሚያስቀጡ ድርጊቶች መሆናቸውን የደነገገ ሲሆን፤ በዋናነትም አሁን ላይ በብዛት የተበራከተ በወንጀል ጉዳዮች ላይ ምስክሮች አንድን ድርጊት አይተው በፖሊስ ጣቢያ ምስክርነታቸውን ከሰጡ በኋላ ችሎት ቀርበው እንዲመሰክሩ ሲጠሩ ግን በተለያየ ምክንያት፦ ተከሳሾችን በመፍራት፣ ከተከሳሽ ጋር በመታረቅ ወይም መደለያ በመቀበል አስቀድመው በፖሊስ ጣቢያ የሰጡትን ቃል በመለወጥ ተከሳሽን ከቅጣት ሲያስመልጡ ይሰተዋላል።

በወንጀል ጉዳይ አንድ ግለሰብ ምስክር ሆኖ ከክስ በፊት ለፖሊስ የሰጠውን ቃል ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ ከሚያውቀው ማስረጃ የቀየረ፣ የቀነሰ ወይም የጨመረ እንደሆነ በዚህ ጊዜ ዐቃቤ ህግ ለዳኛው ምስክሩ አስጠቂ ነው ብሎ ካሰወቀ እና መሪ ወይም መስቀለኛ ጥያቄ እንዲፈቀድለት ከጠየቀ ምስክሩ በፖሊስ ጣቢያ የሰጠውን ቃል አቅርቦ በመመልከት ዐቃቤ ህግ መስቀለኛ ጥያቄ እንዲጠይቀው ይፈቅዳል፤ ይህ መሪ ጥያቄ ምስክር ቀድሞ ለፖሊስ የሰጠውን ቃል መሰረት በማድረግ የሚጠየቅ ይሆናል፤ ይህ የሚረዳው ምስክር ተቃራኒ የሆኑ ነገሮችን እየተናገረ ስለመሆኑ ለፍርድ ቤቱ ለማረጋገጥ እና በመሪ ጥያቄ እውነቱን ለማዋጣት ይጠቅማል ማለት ነው። የሀገራችን የሥነ-ስርዓት ህግ መሪ ወይም መስቀለኛ ጥያቄን አስመልክቶ በግልፅ የተቀመጠ ባይሆንም የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 137 /2/ ላይ በዋና ጥያቄ መሪ ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ከፈቀደ ሊጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ያስቀምጣል ከነዚህም ውስጥ አስጠቂ ምስክርነት አንዱ ነው።

የአስጠቂ ምስክርነት ቃል በራሱ ምስክርነት ተከሳሽን በሚጠቅም መልኩ የተሰጠ እንደሆነ ምስክሩ ልክ እንደመከላከያ ምስክር ስለሆነ አመሰካከሩ መስቀለኛ ጥያቄ በመጠየቅ እውነታውን ለማውጣት ጥረት ያደርጋል።

ከዚህ ድርጊት ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያለው የወንጀል ህግ አንቀፅ 453 ላይ ድርጊቱ ወንጀል ስለመሆኑ የተደነገገ ሲሆን ይኽውም ምስክሮች ማንኛውንም ተከራካሪ ወገን ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት በማሰብ ሀሰተኛ ምስክርነት ከሰጡ እና እውነቱን ከደበቁ ያሰቡት ባይሳካ እንኳን በቀላል እስራት ወይም ከ5 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ሲሆን በዚህ የምስክርነት ቃልም ውጤቱ ተገኝቶ ከሆነ ማለትም ተከሳሹ በአስጠቂው ምስክር ምክንያት ነፃ ቢወጣ ከ10 ዓመት ባልበለጠ ፅኑ እስራት ያስቀጣል፤ በተቃራኒው ደግሞ ተከሳሹ በመስካሪው ድርጊት ምክንያት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈው በንፁህ ሰው ወይም ተከሳሽ ላይ ከ10 ዓመት በላይ ፅኑ እስራት ተፈርዶበት ከሆነ ተከሳሽ በተቀጣው ቅጣት ልክ ሀሰተኛ ምስክሩ ሊቀጣ ይችላል ማለት ነው ።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በወንጀል የተደነገገው ሀሰተኛ የሆነ አስተርጓሚነት ሲሆን በሀሰት መተርጎምም ራሱን ችሎ በወንጀል የሚያስቀጣ ድርጊት ነው ። ሀሰተኛ ወይም አስጠቂ ምስክርነት ዋነኛ ጉዳቱ በተለይም በወንጀል ጉዳዮች ላይ ሰዎች ባልፈፀሙት ወንጀል እንዲቀጡ ወይም ወንጀል ፈፃሚዎች ከቅጣት እንዲያመልጡ በማድረግ ፍትህን ለማዛባት የሚከናወን በመሆኑ በጥንቃቄ የሚታይ ጉዳይ ነው።

የተከበራችሁ የፅሁፋችን አንባቢዎች እንድንጽፍላቹ የምትፈልጉት የህግ ማብራሪያ ካለ በአስተያየት መስጫው ላይ ብታስቀምጡ ምላሻችንን ታገኛላቹ፡፡
ጠ.አቃቤ ህግ