አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from Hailegiorgis Tefera
Please please announce there was exit exam in July 27/ 2013 or post poned
Forwarded from Hailegiorgis Tefera
The time is very short it is difficult to cover all the course that will take in the exam even if the 5th year first semistr course is not end so please notify immediately as mach as possible to prepare for the exam .... please ask the compitent body
ALE (Alternative Legal Education)
All in one, for all.🔴
አለ (አማራጭ የሕግ ትምህርት)
ሁሉም በአንድ፣ ለሁሉም።🔴
There is free legal aid.
ነፃ የሕግ ድጋፍ አለ።

For discussion @ALE_lawsocieties

For more Contact us: @LawsocietiesBot
https://t.me/lawsocieties
የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ እና መስቀለኛ ይግባኝ---የሰበር ችሎት የህግ ትርጉም

የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ
Abrham Yohanes📊
ተከሳሽ የሆነ ወገን በተከሰሰበት መዝገብ ላይ በተራው በከሳሹ ላይ የሚያቀርበው ክስ

ንብረት ለማስመለስ በቀረበ ክስ ላይ ንብረቱ የሚመለስ ከሆነ ተከሳሽ በንብረቱ ላይ ያፈሰሰውን ሀብት /ያወጣውን ወጪ/ መጠየቅ የሚችለው በተከሰሰበት መዝገብ ተገቢውን ዳኝነት ከፍሎ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ /ወይም ሌላ አዲስ ክስ/ በማቅረብ እንጂ በመከላከያ መልሱ ላይ በሚያቀርበው መከራከሪያ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 86454 ቅጽ 15 ፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 234(1) ረ፣ 215(2)

በግልጽ ዳኝነት ተጠይቆበት ውሣኔ ሳይሰጥበት የታለፈ ጉዳይ እንደተነፈገ የሚቆጠር መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ቁ. 5/3/ ላይ የተመለከተ ቢሆንም የዚህ ድንጋጌ ተፈፃሚነት ዳኝነት ከተጠየቀባቸው ነገሮች በተወሰኑት ላይ ውሣኔ ተሰጥቶ በተወሰኑ ላይ ደግሞ ውሣኔ ሳይሰጥ ቢቀር የታለፈው እንደተነፈገ እንደሚቆጠር ሲሆን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ጨርሶ ካልታየ እንደተነፈገ ይቆጠራል ለማለት የሚቻል አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ 24574 ቅጽ 5
መስቀለኛ ይግባኝ
በይግባኝ ክርክር መልስ ሰጪ የሆነው ወገን በቀጥታ ይግባኝ ሳያቀርብ ተገቢውን ዳኝነት ከፍሎ ይግባኝ ባዩ ባቀረበው የይግባኝ ክርክር በመልስ ሰጪነት ከሚያቀርበው ክርክር ጋር በፍርዱ ቅር በመሰኘት የሚያቀርበው ይግባኝ

መስቀለኛ ይግባኝ ስለሚስተናገድበት ስርዓት በሕጉ በተለየ ሁኔታ በግልጽ የተመለከተ ነገር እስከሌለ ድረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 እና 338 ድንጋጌዎች የተመለከተው የክርክር አመራር ስርዓት ለመስቀለኛ ይግባኝም በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጻሚነት የሚኖረው በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 340(2) በተመለከተው መሰረት መልስ ሰጪው ወገን የሚያቀርበው የይግባኝ ማመልከቻ ግልባጭ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ.ቁ. 338 መሰረት ለይግባኝ ባዩ እንዲደርስ ሊደረግ የሚችለው ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/.ቁ. 337 መሰረት ያልተሰረዘ በሆነ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም መልስ ሰጪው ወገን ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ከተሰማ በኋላ የሌላኛውን ወገን ክርክር መስማት ሳያስፈልግ ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት እንዲሰረዝ የሚሰጥ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 340(2) የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት የሚቃረን ነው ለማለት አይቻልም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 92043 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 337፣ 338፣ 340/2/
👍1
Forwarded from 💪 👊
ሰላም ሰላም አለዎች እንዴት ናቹ... ሰላማቹ ብዝት ይበልልኝ... እስኪ የአብክመ ህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 220/2007 ካላቹ እስኪ ተባበሩኝ
የሰ-መ-ቁ 196228 ውሳኔ ግልባጭ.pdf
4 MB
ከፍርድ ቤት ውጪ በአማራጭ የሙግት መፍቻ መንገዶች እልባት የተሰጠ አንድ የፍትሐብሔት ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ በቀጥታ ለአፈጻጸም ሊቀርብ የሚችልበትን ሁኔታ በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 196228 ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ
👍1
ለጊዜው ስለሚሰጡ ማገጃዎችና ሌሎች ትዕዛዞች
=================
1. ከፍርድ በፊት ስለሚሰጥ የእስራት ትዕዛዝ (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 147-150)
1.1. ከሳሹ ወይም ተከሳሹ የተከሳሽ ከሳሽ በሚሆንበት ጊዜ ሌላኛው ወገን ዋስትና እንዲሰጥ ለፍ/ቤቱ ማመልከት ይችላል፡፡
1.2. ማመልከቻው በመኃላ ቃል የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
1.3. ማመልከቻው ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 147 (1) (ሀ) ና (ለ) ሥር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ሲረጋገጡ ነው፡፡ ሁኔታዎቹም ሀ/ ተከሳሹ በማንኛውም ሁኔታ የዳኝነት ሥርዓቱን የሚያስናክል ድርጊት ሲፈጽም ወይም ለ/ ተከሳሹ ከኢትዮጵያ ግዛት ለመውጣት ሲዘጋጅና መውጣቱም ፍርዱን እንዳይፈጽም የሚያደርገው ሲሆን ነው፡፡
1.4. ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ከተቀበለ ተከሳሽ ታስሮ እንዲቀርብ ያዛል፡፡
1.5. ተከሳሹ የሚፈለግበትን ዕዳ በመያዣ ካስቀመጠ የእስር ትዕዛዙ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
1.6. ተከሳሹ መያዣውን ካላስቀመጠ ወይም ፍ/ቤት ቀርቦ በቂ ምክንያት ካልሰጠ በቂ መያዣ እንዲያስቀምጥ ወይም ዋስ እንዲጠራ ይታዘዛል፡፡
1.7. የዋስትናው ወይም የመያዣው ዓይነትና ልክ እንዲሁም ዋስትናው የሚቆይበት ጊዜ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 148(1) መሠረት ይወሰናል፡፡
1.8. ተከሳሹን ለማቅረብ ዋስ የሆነ ሰው ሳያቀርብ የቀረ እነደሆነ ተከሳሹ ሊከፍል የሚገባውን ገንዘብ እንዲከፍል ይገደዳል (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 148(2))፡፡
1.9. በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 149 በተደነገገው መሠረት የዋስትና ግዴታ ሊወርድ ይችላል፡፡ ዋስትናው ሲወርድ ተከሳሹ ሌላ ዋስ ማቅረብ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ መያዣ ማስቀመጥ አለበት፡፡
1.10. ተከሳሹ ይህን ግዴታ ለመፈፀም እምቢተኛ ከሆነ እንደሁኔታው እስከ ስድስት ወር በማረፍያ ቤት እንዲቆይ ለማዘዝ ይቻላል (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 150)፡፡ ተከሳሹ አዲስ ዋስ ለመጥራት ወይም መያዣ ለማስጠት ዓቅም የሌለው ከሆነ ግን ይህ ትዕዛዝ መሰጠት የለበትም፡፡ ተከሳሹ በማንኛውም ጊዜ ትዕዛዙን ከፈፀመ የማሰር ትዕዛዙ መነሳት አለበት፡፡
2. ከፍርድ በፊት ንብረትን ማስከበር (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 151-153)
2.1 በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 151(1) (ሀ) ና (ለ) ሥር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች መኖራቸውን ከሳሹ ወይም የተከሳሽ ከሳሹ በመኃላ ቃል በተደገፈ አቤቱታ ወይም በሌላ ሁኔታ ማስረዳት ይችላል፡፡
2.2 ፍ/ቤቱ አቤቱታውን መርምሮ እውነት መሆኑን ካረጋገጠ ተከሳሹ ዋስትና እንዲሰጥ ወይም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ንብረት ወይም ግምቱ እንዲቀርብ በወሰነው ጊዜ እንዲያመጣ ወይም ደግሞ ከሚያዘው ገንዘብ ወይም ንብረት ላይ ለሚሰጠው ፍርድ ተመዛዛኝ የሚሆን መጠን ያለው ገንዘብ ወይም ንብረት በፍ/ቤቱ እንዲቀመጥ ወይም ይህን መያዣ የማይሰጥበትን ምክንያት ቀርቦ እንዲያስረዳ ያዛል (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 151(1) (ለ)) ፡፡
2.3 የሚያዘው ንብረት የግድ ከሳሹ ያመለከተው ሁሉ ሳይሆን ከክሱ ገንዘብ ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለበት (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 151(3) እና (1))፡፡ እንዲሁም በቁ. 404 እና በሌላ ሕግ እንዳይከበር የተወሰነ ንብረት መያዝ የለበትም፡፡
2.4 ተከሳሹ ዋስ ያልጠራበትን ምክንያት በሚገባ ካስረዳ ወይም የሚፈለግበትን መያዣ ከሰጠ ንብረቱ ይለቀቅለታል፡፡ (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 152 (2) እና 153(4))፡፡
2.5 ንብረቱ በሚከበርበት ጊዜ የሦስተኛ ወገኖች መብት መጠበቅ አለበት (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 153(2)(3)፣ 428-421 እና 443)፡፡
3. ለጊዜው የሚሰጥ የማገድ ትዕዛዝ (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 154-159)
1.1 በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 154 (ሀ) ና (ለ) ሥር የተመለከቱት ሁኔታዎች በመኃላ በተደገፈ ቃል ወይም በሌላ መንገድ ሲረጋገጡ ነገሩ በፍርድ እስኪወሰን ድረስ ወይም ሌላ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ ክርክር የተነሳበት ንብረት እንዳለ እንዲቆይ፣ ከመጥፋት እንዲድን እንዳይበላሽ ለሌላ ሰው ተላልፎ እንዳይሰጥ ወይም ሌላ ስፍራ እንዳይዘዋወር ወይም እንዳይባክን ፍ/ቤቱ አስፈላጊውን ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡
1.2 ውል ወይም ሌላ ግዴታ ተደጋግሞ እንዳይፈርስ ወይም ለማፍረስ የተወሰደው አርምጃ እንዳይቀጥል የሚሰጠው ያማገጃ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 155 መሠረት ይፈፀማል፡፡
1.3 የማገጃ ትዕዛዝ ያለማክበር የፍትሐብሔረና የወንጀል ኃላፊነትን ሊያስከትለ ይችላል (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 156)፡፡
1.4 የማገጃ ትዕዛዝ መሰጠት ያለበት ማመልከቻው ለሌላቸው ወገን ከደረሰው በኃላ ነው፡፡ ከዚህ ወጪ ትዕዛዙ ሊሰጥ የሚችለው መዘግየቱ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል መስሎ ሲታይ ብቻ ነው (ለምሳሌ ንብረቱ የሚጠፋ ወይም የሚበላሽ ሲሆን )
1.5 የማገጃ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 158 በተደነገገው መሠረት ሊነሳ፣ ሊሠረዝ ወይም ሊሻሻል ይችላል፡፡
4. ከፍርድ በፊት ስለሚሰጥ ትዕዛዝ (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 160-165)
1.1 ለክርክሩ መነሻ የሆነው ወይም የተያዘው ንብረት ክርክሩ እስኪሰማ ቢቆይ የሚበላሽ መሆኑን ወይም መቆየቱ ሌላ ጉዳት ያለው መሆኑን ከተረዳው ፍርድ ቤቱ ንብረቱ እንዲሸጥ ማዘዝ ይችላል፡፡
1.2 ክርክር የተነሳበትን ሀብት በአንድ ስፍራ አኑሮ መጠበቅ፣ እንደይበላሽ የሚደረግ ጥንቃቄና የመቆጣጠር ምርምራ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 161 በተደነገገው መሠረት ይፈፀማል፡፡
1.3 በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 160 እና 161 መሠረት በሚቀርበው አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ከመሰጠቱ በፊት ለሌላኛው ወገን ማስታወቂያ መስጠት አለበት (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 162)፡፡
👍1
የውርስ ጉዳይን የተመለከቱ የይርጋ ገደቦች ከተመረጡ የሰበር ውሳኔዎች ጋር በማጠቃስ የቀረበ፤

ኑዛዜን ለመቃወም የተቀመጠ ጊዜ ገደብ
///////
ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በቁጥር 973 ላይ የተመለከተው ተፈጻሚ ሚሆነው ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚለውን ክስ ኑዛዜው ሲነገር በነበሩ ሰዎች የቀረበ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973/1/ ላይ እንደተገለጸው “ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከሉ ሰዎች ኑዛዜው አይጸናም ወይም አንዱ በኑዛዜው የተነገረው ቃል አይጸናም በማለት ክስ ለማቅረብ ያላቸውን ሀሳብ መግለጫ ወይም ስለ ክፍያው በሂሳብ አጣሪው የቀረበውን የድልድል አመዳደብ ሀሳብ ለመቃወም ኑዛዜው ከተነበበት አንስቶ በሚቆጠር የአስራ አምስት ቀን ጊዜ አላቸው”፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ ሰዎች መቃወሚያቸውን መቼ ሊቀርቡ ይችላሉ ለሚለው በፍ/ሕ/ቁ 974/1/ እና 2 ላይ የተገለጸ ሲሆን በዚህም መሰረት “ በኑዛዜ ንባብ ሥነ-ሥርዓት ላልነበሩ ወይም በኑዛዜው ንባብ ሥነ-ሥርዓት በወኪልነት ላልሰሙ ሰዎች እንዲሁም ኑዛዜው በሌሉበት የተነበበ እንደሆነ ከዚህ በላይ የተገለጸው የጊዜ ገደብ ለመቁጠር መነሻ የሚሆነው ሥለ ክፍያው ድልድልና አመዳደብ ሀሳቡን ከተነገራቸው ቀን አንስቶ ነው”፡፡
በፍ/በ/ህ/ቁ 973/2/ ላይ በተገለጸው መሰረት ኑዛዜ ከፈሰሰበት ጊዜ ከአምስት ዓመት በኋላ ወይም ኑዛዜ የሌለ እንደሆነ ሟች ከሞተ ከአምስት ዓመት በኋላ ስለ ኑዛዜው መጽናትና ስለክፍያው አመዳደብ አጣሪው ያቀረበውን የድልድል ሀሳብ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን መቃወሚያ ሊቀርብበት አይችልም፡፡
ከዚህ በላይ ከተገለጹት የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በተያያዘ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 82585 በቅጽ 15 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን በትርጓሜውም “በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ድንጋጌዎች አቤቱታ አቅርቢው ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ ወይም የተወከለ የመሆን አለመሆን መስፈርት መሰረት በማድረግ ይርጋው መቁጠር የሚጀምርበትን ጊዜ እና ፍጹም የሆነ የይርጋ ጊዜ በቁጥር 974/2/ ከመደንገጋቸው በስተቀር ሁለቱም ድንጋጌዎች ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን ስርዓት የሚደነግጉ በመሆቸው ተያያዥነት አላቸው በማለት ኑዛዜ መኖሩን ማወቅ እና የኑዛዜውን ሙሉ ይዘት ማወቅ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው ሲል በፍ/ብ/ህ/ቁ 973/1/ የተመለከተው የ15 ቀን ጊዜ ገደብ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ሳይሆን የመግለጫ ማቅረቢያ ጊዜ ነው፡፡ በመሆኑም ስለ ኑዛዜ መኖር እንጂ ስለድልድሉ የማያውቅ ወራሽ መግለጫ የማቅረብ ግዴታ ስለማይኖርበት ጊዜው መቁጠር የሚጀምረው በኑዛዜው የተደረገውን ድልድል ካወቁበት ቀን ጀምሮ ነው” በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በሟች የተደረገ ኑዛዜ ከውርስ የነቀለኝ በመሆኑ ሊፍርስ ይገባል በማለት ኑዛዜው ሲነበብ በነበረ አመልካች የሚቀርብ የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 መሰረት በተገለጠው የጊዜ ገደብ ነው ወይስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ነው? የሚለው አከራካሪ ጉዳይ በመሆኑ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 152134 በቅጽ 23 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በውሳኔውም መሰረት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ስለ ኑዛዜ መነበብ እንዲሁም ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ኑዛዜው እንዲፈርስ አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ሥርዓትና ጊዜውን በሚመለከት የሚደነግግ ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል /ነቅሎናል/ በማለት ኑዛዜው እንዲፈርስ የሚቀርብን ወይም የቀረበ አቤቱታን የሚመለከት አይይለም፡፡ በመሆኑም ኑዛዜው ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ እንዲፈርስ በሚል የሚቀርብ የዳኝነት ጥያቄ ሊታይ የሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነውእንጂ በአንቀጽ 973 መሰረት አይደለም በማለት አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የሕግ ትርጓሜ መሰረት ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ አንድ ኑዛዜ ፈራሽ ነው በሚል ስለሚቀርብ መግለጫ እና እንዲሁም መግለጫው እና ክሱ ሊቀርብ ስለሚገባው የጊዜ ገደብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ተፈጻሚነት የሚኖረው ኑዛዜ ሲነበብ በነበሩ ወይም በተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ሲሆን በአንቀጽ 974 ድንጋጌ ደግሞ ተፈጻሚነቱ በኑዛዜ ሥነ-ሥርዓት ባልነበሩ ወይም ባልተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ነው፡፡ ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነው፡፡
//////
የወራሽነት ጥያቄ ለማቅረብ የተቀመጠ ጊዜ ገደብ🇪🇹
///////
የወራሽነት ጥያቄን ለማቅረብ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የሚመለከቱ የሕግ ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000 ላይ የተመለከተ ሲሆን ወደዚህ ነጥብ ከመግባቴ በፊት ወራሽነት ጥያቄ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን እደሚከተለው ለመዳሰስ እሞክራለሁ÷
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 996(1) ላይ በተገለጸው መሰረት ወራሽ የሆነ ሰው የሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል በማለት የተገለጸ ሲሆን ይህ ማለት ፍ/ቤቱ የወራሽነት ምስክር እንዲሰጠው ወራሹ ሲፈልግ የሚጠይቀው እንጂ ሟችን ለመውረስ የግድ ከፍ/ቤቱ የወራሽነት ማስረጃ ማምጣት እንዳለበት የሚያስገድድ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በተግባር እንደሚስተዋለው ስመ ንብረቱ ለማዛወር እና ከሌሎች የሟች መብቶች ለመጠቀምና ለመስራት በፍ/ቤቱ የተረጋገጠ የወራሽነት የምስክር ወረቀት መጠየቁ የተለመደ አሰራር ሆኗል፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን መሰረት በማድረግ አንድ ሰው ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ ያደረገ እንደሆነ እውነተኛው ወራሽ ወራሽነቱን እንዲታወቅለትና የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች እንዲመለሱለት በዚህ ሰው ላይ የወራሽነት ጥያቄ ክስ ሊያቀብበት ይችላል በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 999 ላይ ተደንግጓል፡፡ ስለዚህ ይህን መሰል የክስ አቤቱታ አቤቱታ መቼ ሊቀርብ ይገናል ለሚለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ ላይ የጊዜ ገደብ ተቀምጧል፡፡
በዚሁ መሰረት ከሳሽ መብቱንና የውርሱን ንብረት በተከሳሽ መያዛቸውን ካወቅ ሶስት ዓመት ካለፈ በኋላ ስለ ወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም፡፡ በሌላ መልኩ በአንቀጽ 1000(2) ላይ እንደተገለጸው “ሟቹ ከሞተበት ወይም ከሳሹ በመብቱ ለመስራት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት አመት ካለፈ በኋላ ከዘር የወረደ ርስት ካልሆነ በቀር የውርስ ጥያቄ ክስ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን ተቀባይነት አያገኝም የሚለው ተደንግጎ ይገኛል፡፡
👍1