አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from Deleted Account
ፀበፍ/ብ/ህ/ቁ 418 እና 358 ሳይከራከር የቀረ መብት አለኝ የምል ሰው በ 421 ክስ ማቅረብ ይችላል ወይ?
Forwarded from Deleted Account
ሠላም ወንድሞች ፣ እባካችሁ አዲሡን የመውጫ ፈተና መመሪያ
Forwarded from Deleted Account
ሠላም ወንድሞች ፣እባካችሁ አዲሱ exit guide line ካላችሁ attach አድርጉልን።
Forwarded from Deleted Account
አዎ ይችላል! በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 41 መጀመሪያ በክርክሩ መግባት የነበረበት ሰው ሳይገባ ከቀረ በ358 መሰረት ፍርዱን ለፈረደው ፍ/ቤት ተቃውሞ ሊያቀርብ ይችላል። ሁለቱንም ያላደረገ ሰው ደግሞ በአፈጻጸሙ ክስ ላይ በ418 መሰረት አፈጻጸሙን ሊቃወም ይችላል። ሆኖም ግን ከዚህ በላይ ባለው መሰረት ተቃውሞ ያላቀረበ ወይም አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ራሱን ችሎ በአዲስ ክስ ከማቅረብ አያግደውም(የመጨረሻ አማራጩ ሊሆን ይችላል) ብየ አስባለሁ።
New Doc 2020-12-18.pdf
265.3 KB
New Doc 2020-12-18
ለዐቃብያነ ሕግ የስብዕና ግንባታ እና የሙያ ብቃት ለማጎልበት ስልጠና ተሰጠ
--------------------------------------

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክተር ከጀስቲክስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ100 ለተቋሙ ለዐቃብያነ ሕግ ስብዕና ግንባታ እና የሙያ ብቃት ማጎልበቻ ዙሪያ ለ2 ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሕግ ጉዳዮች ዘርፍ ም/ል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ተሰፋዬ ደባ እንደተናገሩት ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 10 የለውጥ አጀንዳዎችን በመቅረፅ ተቋማዊ ለውጥን ለመፍጠር ከሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መካከል የባለሙያዎች እና አመራሮች ሙያዊ ብቃት ማጎልበት መሆኑን ጠቁመው ተቋሙ ለ"ሕግ፣ ለፍትህ እና ለርትዕ!" የቆመ የሕዝብ አገልጋይ ተቋም እንዲሆን የተቋም ግንባታ እና ሙያዊ ብቃት ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ተስፋዬ አክለውም ስልጠናው ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ተአማኒነት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም የዐቃብያን ሕግ እና አመራሮች ተገቢ የሆነ የተሟላ ስብዕና፣ ሙያ ብቃት፣ ሥነ- ምግባር ፣ የስራ ተነሳሽነት እንዲኖራቸው የዐቃቤ ሕግ ስብዕና ከፍ ለማድረግ እና ፕሮፌሽናሊዝምን ለማስፈን የስልጠናው ዋና አላማ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ኃለፊው አያይዘውም ሰልጣኞች በሚኖራቸው የስልጠና ቆይታ የዐቃቤ ሕግ ማንነትና ምንነት፣ስብዕና፣ ባህሪ፣ የዐቃቤ ሕግ ስነ-ምግባር፣ ነፃነትና ገለልተኝነት ፣ በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ የዐቃቤ ሕግ ሚና እና ሰብዓዊ መብትን በማስከበር ሂደት የዐቃቤ ሕግ ሚና የሚሉትን ወሰኝ ሙያዊ ጉዳዮችን መሰራት ያደረገ ስልጠና ሲሆን በስልጠናውም ጠቃሚ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቋሟል።

በመጨረሻም የተቋሙን ባለሙያዎች ሙያዊ ብቃት እና ስነ- ምግባር ተላብሰው እንዲሰሩ የሰብዕና ግንባታ ስልጠና በቀጣይነት ተጠናክሮ እንደሚሰጥ የንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ወርቁ በበኩለቸው ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቶች በፀረ-ሙስና ትግሉ ተደራራቢ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገለጸ
**********************************************************
በአገራችን ሙስናን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት ፍርድ ቤቶች ከሌሎች ተቋማት በተለየ ሁኔታ ተደራራቢ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር ገለጹ፡፡

ክቡር ፕሬዚዳንቱ ይህን የገለጹት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ 16ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በፍርድ ቤት ደረጃ ለማክበር ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በሐርመኒ ሆቴል ለግማሽ ቀን በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ፍርድ ቤቶች ከሌሎች ተቋማት በተለየ ሁኔታ በአንድ በኩል በሕግ በተሰጣቸው የዳኝነት ሥልጣን የሙስና ወንጀሎችን የመዳኘት ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ውስጣዊ አገልግሎት አሠጣጣቸው ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳ እንዲሆን የመከታተልና ይህንኑ የማረጋገጥ ኃላፊነትም ያለባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በፍርድ ቤቱ የተከበረው «የትውልድ የሥነምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፒሊን በመምራት፣ ሌብነት እና ብልሹ አሠራርን በመታገል የሕዝብ አመኔታን ያተረፈ የዳኝነት ሥርዓት እንገነባለን» በሚል መሪ-ቃል ሲሆን በውይይት መድረኩ ላይ 150 ያህል የፍርድ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በመድረኩ ላይ «የሙስና መከላከያ ስልቶች እና በሙስና መከላከል ሒደት የፍርድ ቤቶች ሚና» በሚል ርዕስ በፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት በክቡር አቶ ፉአድ ኪያር ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን ይህን ተከትሎም የፍርድ ቤቱ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል የ2012 በጀት ዓመት ሪፖርት እና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ በፍርድ ቤቱ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ኑሀሚን አለሙ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በፍርድ ቤቱ ተዘጋጅቶ ለሕትመት የበቃው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሥነምግባር መተዳደሪያ ደንብን የማስመረቂያ ሥነሥርዓትም በመድረኩ ላይ ተከናውኗል፡፡

አራት ክፍሎችና 30 አንቀጾች ያሉት የሥነምግባር መተዳደሪያ ደንብ የሥነምግባር ጥሰት የሚፈጽሙ ሠራተኞችን እና የሥራ ኃላፊዎችን ተጠያቂ በማድረግ ፍርድ ቤቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የራሱ ድርሻ እንደሚኖረውም በወቅቱ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ላይ ከፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት በተጨማሪ የፍርድ ቤቱ ም/ፕሬዚዳንቶች፣ የየምድብ ችሎቶች ሬጅስትራሮች፣ አስተባባሪ ዳኞች እና የሥነምግባር አውታሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
proclamation-no-881-2015-corruption-crimes-proclamation.pdf
4.7 MB
proclamation-no-881-2015-corruption-crimes-proclamation.pdf
https://t.me/lawsocieties
Ethiopia - Investment Proclamation No1180_2020 (English).pdf
154.1 KB
Ethiopia - Investment Proclamation No1180_2020 (English).pdf
https://t.me/lawsocieties
INVESTMENT-PROCLAMATION.pdf
1.1 MB
INVESTMENT-PROCLAMATION.pdf
Amharic
https://t.me/lawsocieties
ETH85156.pdf
807.7 KB
Environmental impact assessment proclamation
ETH85156.pdf
https://t.me/lawsocieties
የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ "የሕግ የበላይነት ለሀገር ልማት" በሚል ያሳተሙት መጽሐፍ በዛሬው ዕለት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል እየተመረቀ ይገኛል።

በአርቲስት ተፈሪ ዓለሙ ቅንጭብ የመፅሃፉ ገፅ እንዲሁም በአርቲስት ደበበ እሸቱ ምስክርነት ቀርቧል።

ደራሲው ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የህግ በላይነት ይሰፍን ዘንድ በሙያቸው ከመስራት በተጨማሪ ግንዛቤ የሚያሳድግ መፅሃፍ ማዘጋጀት ተገቢ መሆኑን በማመን ማዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

በዲያቆን ዳንኤል ክብረት አጋፋሪነት ሶስት ምሁራን የመፅሃፍ ዳሰሳ አቅርበዋል።

ባለሃብቶች በበኩላቸው ለተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ቤተ መፃህፍት ይዳረስ ዘንድ ከ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የመፅሃፉን ግዥ ለመፈፀም ቃል ገብተዋል።
via ደመቀ ከበደ
Notice for A.A Center examinee - Law Exit Exam - 2013.docx
14.9 KB
Share 'Notice for A.A Center examinee - Law Exit Exam - 2013.docx'