ሆን ሊመረጥ የሚችለው እራሱ ካልሆነ በቀር ተጨማሪ ሌላ ሰው አልያም እራሱን ሁለት ጊዜ እንዲመረጥ የንግድ ሕግ ቁጥር 347(1) አይፈቅድም፡፡ይህ ደግሞ በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው ማህበሮች (ድርጅቶች) ሲሆኑ ከሌላው ባለአክሲዮን በተለየ መልኩ በአክሲን ማህበር የቦርድ አባልነት ከአንድ ሰው በላይ ተወክሎ እንዲገባ መፍቀድ የአክሲዮን ማህበሩ አስተዳዳሪነት ከባለአክሲዮኖች ውጪ በሦስተኛ ወገን እንዲተዳደር መፍቀድ መሆኑ ከንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻል ነው፡፡
ተከሳሽ አክሲዮን ማህበር በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው ማህበሮች ከአንድ በላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ እንዳያስመርጡ የሚከለክል ሕግ የለም፣ ለአክሲዮን ማህበሩም የሚያስከትለው ጥቅም ካልሆነ በቀር ጉዳት የለውም ይበሉ እንጂ በአንድ በኩል አክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የአስተዳዳሪው ምክርቤት አባላት ሲመርጥና ሲሾም እያንዳንዱ ባለአክሲዮን ባለው የአክሲዮን ድርሻ መጠን የድጋፍ እና የተቃውሞ ድምፅ እየሰጠ አብላጫ የአክሲዮን ይዞታ ያለው ባለአክሲዮን የሚፈልገው የዳይሬክተሮች ቦርድ መምረጥ የሚያስችልና አነስተኛ የአክሲዮን ይዞታ ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ሳይወከሉ የሚቀሩበት ሁኔታ እንዲኖር የሚያስችል የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ሥርዓት መኖሩ በሌላ በኩል የአክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች ከአንድ ሰው በላይ ተወካይ ለዳይሬክተሮች ቦርድ ማቅረብ እንዲችሉ መፍቀዱ የአክሲዮን ማህበሩ የውስጥ እና የውጭ ግንኙነቱን የመምራት እና የማስተዳደር ኃላፊነት አብላጫው የአክሲዮን ይዞታ ባላቸው ጥቂት ባለአክሲዮኖች እጅ እንዲገባ እና የእነሱን ፍላጎት መፈፀሚያ እንጂ የአክሲዮን ማህበሩ (የኩባንያው) ተወካይ በመሆን ሥራቸውን ለመከወን እንዳይችሉ የሚያደርግ ተግባር መሆኑ ከቀረበው የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ መገንዘብ የሚቻል ነው፡፡
ሲጠቃለልም በተከሳሽ አክሲዮን ማህበር በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች ፒፒሲ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ሊሚትድ (ፒ.ፒ.ሲ) እና ኢንዱስትሪያል ዴቨሎፕመንት ኮርፖሬሽን (አይ.ዲ.ሲ) በዳይሬክተሮች ቦርድ በአራት አባላት ተወክለው እንዲመረጡ ውሳኔ ላይ በመድረስ የአክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በሚያዝያ 26 ቀን 2011 ዓ/ም በያዘው ቃለ-ጉባኤ ሁለቱም ድርጅቶች በጋራ ፒ.ፒ.ሲ/አይ.ዲ.ሲ በሚል ስያሜ አንድ ተጨማሪ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሚሆን አንድ ተወካይ እንዲወክሉ ድምዳሜ ላይ መድረሱ በንግድ ሕጉ 347(1) እና በተከሳሽ አክሲዮን ማህበር መመስረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 8(1) ሥር የአክሲዮን ማህበሩ የአስተዳዳሪነት ኃላፊነት ከባለአክሲዮኖቹ ውጪ ተላልፎ ሊሰጥ አይችልም በሚል የተቀመጠው ድንጋጌን የሚጥስ በመሆኑ በፒ.ፒ.ሲ/አይ.ዲ.ሲ በሚል ስያሜ በጋራ አንድ ተወካይ እንዲኖራቸው ወይም እንዲመርጡ የተሰጠው ውሳኔ ሊሰረዝ ይገባል በማለት ፍርድ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል የተከሳሽ አክሲዮን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሚያዝያ 26 ቀን 2011 ዓም ባደረገው ስብሰባ ሰባት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ውስጥ አንዱ የንግድ ሕጉን በተከተለ መልኩ የተመረጠ ባለመሆኑ ከአባልነት መሰረዛቸው የማህበሩ የዳይሬክተሮች ብዛት ወደ ስድስት ስለሚያወርደው በማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ አንቀጽ 8(8) መሰረት ከአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች መካከል መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እስከሚደረግ ጊዜ ድረስ በምትክነት ከሚመርጡ በቀር አክሲዮን ማህበሩ ሚያዝያ 26 ቀን 2011 ዓ/ም በነበረው ስብሰባ ከተወዳደሩት ባለአክሲዮኖች ውስጥ ቀጥለው ከፍ ያለውን የጉባኤተኛውን ድምጽ ያገኘ ባለአክሲዮን እንዲተካም ሆነ የሰጠው ውሳኔ ሙሉ በሙሉ የሚሰረዝበት አግባብ አይኖርም፡፡
ስለሆነም በፒ.ፒ.ሲ/አይ.ዲ.ሲ በሚል ስያሜ በጋራ አንድ ተወካይ አንደኖራቸው ወይም እንዲመርጡ የተሰጠው ውሳኔ እንዲሰረዝ ፍርድ ቤቱ ድምዳሜ ላይ ስለደረሰ የተሰረዘው አንድ የቦርድ ዳይሬክተር የሚተካ የቀሩት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ከአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች መካከል ምትክ የዳይሬክተር ቦርድ ሊመርጡ ይገባል ተብሏል፡፡
ሌላኛው ነጥብ ፕሮፕሪታሪ ሊሚትድ(ፒፒሲ) ከተከሳሽ ማህበር ጋር የንግድ ግንኙነት ስላለው የቦርድ አባል መሆኑ የጥቅም ግጭት ስላለ አግባብ አይደለም በሚል የቀረበውን መከራከሪያ የተመለከተ ሲሆን ከአንድ አክሲዮን ማህበር ጋር ውል የሚገባ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሆነ ሰው ከዳይሬክተሮች ቦርድ ይሁንታ ሊያገኝ እንደሚገባው፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሉን ያፀደቀው እንደሆነ ለኦዲተር ደርሶት ለማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ልዩ ሪፖርት ሊያቀርብ እንደሚገባ በንግድ ሕግ ቁጥር 356 ሥር ተመልክቷል፡፡ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው የአክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሆነ የተፈጥሮም ሆነ ሕጋዊ ሰውነት ያለው አካል የሥራ ውል ማድረጉ ብቻውን የጥቅመም ግጭት ሊፈጥር የሚችል ነው የሚል የሕግ ግምት አለመቀመጡ ነው፡፡ ተከሳሽ ሀበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት በቁጥር ተ/ሐ/ሲ/ለ-136-2012 በቀን መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም በሰጠው የሰነድ ማስረጃ ተከሳሽ ማህበር ከፕሮትሪታሪ (ከፒ.ፒ.ሲ) ግሩፕ ሊሚትድ ጋር የተደረገ የኮንሰልቲንግ እና የቴክኒካል ሰርቪስ ስምምነት የሌለ መሆኑን ገልጸው ልከዋል፡፡ ከሳሾች ፒ.ፒ.ሲ ሊሚትድ ከተከሳሽ ማህበር ጋር የንግድ ግንኙነት እንዳለ ከማስቀመጥ ባለፈ ያቀረቡት ማስረጃ የሌለ ሲሆን ከማህበሩ በኩል በቀረበው ማስረጃ ግን የኮንሰልቲንግ እና የቴክኒካል ሰርቪስ ስምምነት የሌለ መሆኑን የሚገልጽ ሰነድ የቀረበ በመሆኑ በዚህ ረገድ በከሳሾች በኩል የቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
ው ሳ ኔ
1. ሀበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር በሚያዝያ 26 ቀን 2011 ዓ/ም ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዲሁም በፒ.ፒ.ሲ/አይ.ዲ.ሲ በሚል ስያሜ በጋራ አንድ ተወካይ አንደኖራቸው ወይም እንዲመርጡ የተሰጠው ውሳኔ የንግድ ሕግ ቁትር 347(1) እና የማህበሩ መመስረቻ ፅሑፍ 8(1) የተከተለ ባለመሆኑ እንዲሰረዝ ተወስኗል፡፡
2. የተከሳሽ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የተሰረዘው አንዱ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ምትክ ከአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች እንዲመርጥ ተወስኗል፡፡
3. ተከሳሽ አክሲዮን ማህበሩ በሚያዝያ 26 ቀን 2011 ዓ/ም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በመምረጥ በሰጠው ውሳኔ ላይ ሕብረት ባንክ አክሲዮን ማህበር ከቦርድ አባልነት እንዲሰረዝ ከሳሾች ያቀረቡት ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘውም፡፡
4. ተከሳሽ አክሲዮን ማህበሩ በሚያዝያ 26 ቀን 2011 ዓ/ም በነበረው ስብሰባ ከተወዳደሩት ባለአክሲዮኖች ውስጥ ቀጥለው ከፍ ያለውን የጉባኤተኛውን ድምጽ ያገኘ ባለአክሲዮን እንዲተካም ሆነ የሰጠው ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ ከሳሾችያቀረቡት ጥያቄ መመስረቻ ፅሑፉን የተከተለ ሆኖ ፍርድ ቤቱ አላገኘውም፡፡
5. በዚህ ችሎት በተደረገው ክርክር ምክንያት ከሳሾች ያወጡት ወጪና የደረሰባቸው ኪሳራ የሚያሳይ ዝርዝር በተከሳሽ ላይ የማቅረብ መብታቸው ተጠብቋል፡፡፡
ት ዕ ዛ ዝ
ይግባኝ ለጠየቀ መዝገቡ ተገልብጦ ይሰጠው፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነብ የዳኛ ፊርማ አለበት፡፡
-----------------------------------------------------------------------
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

በወንጀል ጉዳዮች ይርጋ በኢትዮጵያ ህግ
የይርጋ ምንነት
ይርጋ ማለት አንድ ሰው በጉዳዩ ላይ መብት ያለው ቢሆንም ይህንን መብቱን ለመጠየቅ የማይችልበትን ገደብ የሚመለከት ሲሆን ይህም በህግ ተለይቶ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ በአንድ ጉዳይ ክስ ለማቅረብ የሚከለከልበት የህግ ፅንሰ-ሃሳብ ነው፡፡ ይርጋ በወንጀል እና በፍትሀ ብሄር ህጎች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን በወንጀል ጉዳይ ላይ ይርጋን በመቃወሚያነት አንስቶ ለመከራከር የሚችለው ተከሳሽ፣ ዐቃቤ ሕግና ፍርድ ቤቶች ስለመሆናቸው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 130/1/ሐ እና በወንጀል ሕግ 216(2) ላይ ተመልክቷል፡: በወንጀል ጉዳዮች ላይ ተከሳሹ ባያነሳውም ዳኞች በይርጋ የታገደ የወንጀል ክስ ሲቀርብላቸው ማየት አይችሉም፡፡ስለሆነም ክሱ በይርጋ ስለመታገዱና ክሱን ለመቀበል የማይገባ ስለመሆኑ ተከሳሽ ባያመለክትም ዐቃቤ ሕጉ ወይም ፍርድ ቤቱ በማናቸውም ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡
በተመሳሳይ ቅጣቱ ሳይፈፀም የይርጋው ጊዜ ካለፈ አጥፊው ራሱ ባያነሳውም እንኳ አስፈፃሚው አካል ሊያነሳው እንደሚገባ በወንጀል ህግ አንቀፅ 216(2) እና 223 (2) ተገልጿል፡፡ለይርጋ የተወሰነ ጊዜ ካለፈ የጥፋተኝነት ውሳኔ ወይም ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ ሊወሰን አይችልም፡፡በፍትሀ ብሄር ጉዳዮች ግን ይርጋን እንደመቃወሚያነት ማንሳት የሚችለው ተከሳሽ ብቻ ሲሆን ይህንንም ማድረግ የሚችለው በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክሱ መሰማት ከመጀመሩ እና ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር በተከሳሽ በኩል ተፈፅሟል አልተፈፀመም የሚለው ላይ ክርክር ከመደረጉ በፊት ነው፡፡ይርጋ በተከሳሹ ካልተነሳ ለማንሳት እንዳልፈለገ ስለሚቆጠር ዳኛው በራሱ ተነሳሽነት እንዲያነሳ ሕጉ አይፈቅድም፡፡
በይርጋ የማይታገዱ ጉዳዮች
በመርህ ደረጃ የወንጀል ድርጊቶች ከተፈፀሙ በኋላ ክስ ለማቅረብ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ ያለ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ በሌላ ህግ ከተደነገገ በይርጋ የማይታገዱ ወንጀሎች እንዳሉ ከወንጀል ህጉ እንቀፅ 216/1 መገንዘብ ይቻላል፡፡በይርጋ የማይታገዱ የወንጀል ድርጊቶችን ከሚያስቀምጡ የህግ ድንጋጌዎች የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት ቀዳሚው ነው፡፡በህገ መንግስቱ አንቀፅ 28/1 ስር እንደተደነገገው ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና በሌሎች ሕጎች የሰው ልጅ ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑ ወንጀሎች ፣የሰው ዘር ማጥፋት፣ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈፀሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም፡፡
በዓለም አቀፍ ሕግና ልምድ መሠረት በተለይም ይርጋ በጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ እንዳይፈፀም ለማስቀረት በተደረገው ስምምነት እና በሮም የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ መሰረት የዘር ማጥፋት፣ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲሁም የጦር ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሰዎች ላይ የሚቀርቡ ክሶች በይርጋ የማይታገዱ ናቸው::
ይርጋ ያስፈለገባቸው ምክንያቶች
የይርጋ ፅንሰ ሃሳብ እንዲኖር ያስፈለገባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች ከሳሽ በተገቢ ትጋትና በቂ ምክንያት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል፣ተከሳሽ በጣም ዘግይተው ለሚመጡ ክሶች የመከላከያ ማስረጃዎች እንዳያጣ ለማድረግ እና ሰዎች መብታቸውን የሚጠቀሙበትን የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ህብረተሰቡን ከስጋት በማዳን የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ ማስቻል ናቸው፡፡ይርጋ በዋናነት ጠቀሜታ የሚኖረው ለተከሳሽ መሆኑን ከህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡በመሆኑም ተከሳሽ በይርጋ በታገደ ጉዳይ ላይ ክስ ከቀረበበት በመቃወሚያ በማንሳት ክሱ ቀሪ እንዲሆንለት መጠየቅ ይችላል፡፡
በወንጀል ህግ ውስጥ የወንጀል ይርጋ በሁለት የተከፈለ ነው፡፡ ይኸውም የክስ ይርጋና የቅጣት ይርጋ ናቸው፡፡የክስ ይርጋ ዐቃቤ ህግም ሆነ የግል ተበዳይ (ወንጀል የተፈፀመበት ሰው) ወንጀል ፈጽሟል በተባለው ሰው ላይ ክስ ሊያቀርቡ የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ የሚያስቀምጥ ሲሆን ዝርዝር አሰራሩ በወንጀል ህግ አንቀጾች 216-222 ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል የቅጣት ይርጋ ከቅጣት አፈፃፀም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አንድ ሰው ጥፋተኛ ነው ተብሎ ቅጣት ከተወሰነበት በኋላ ቅጣቱ ሳይፈፀም ቢቀር በሕግ የተመለከተው ጊዜ ካለፈ ቅጣቱን የማስፈፀም መብት እንደሚቀር የወንጀል ህግ አንቀፅ 223 ስር ተቀምጧል፡፡እንዲሁም የዋነኛው ቅጣት የይርጋ ዘመን የተጨማሪ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እር
ምጃዎች መፈፀምንም ያስቀራል፡፡እንደ ወንጀሉ ክብደትና ቀላልነት የቅጣት ይርጋ በስላሳ ፣ በሃያ፣ በአስርና በአምስት ዓመት ሊወሰን እንደሚችል የወንጀል ህግ አንቀፅ 224(1) ዘርዝሮ ያስቀምጣል፡፡
ይርጋን አስመልክቶ በህግ ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎች በዋናነት የሚያመላክቱት ክስ ለማቅረብ ወይም መብት ለመጠየቅ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ እንደመሆኑ ይህን ለማድረግ እንዲቻል በህግ የሚጠየቀው የጊዜ ገደብም እንደ ጉዳዩ ክብደት፣ባህሪይና ሁኔታ የተለያየ ሲሆን ለሁሉም ጉዳዮች የተቀመጠ ተመሳሳይ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ የለም፡፡በመሆኑም ህግ አውጪው እንደ ጉዳዩ ዓይነት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ክስ ለማቅረብ እንደሚቻል የተለያዩ የክስ ማቅረብያ ጊዜያት በህጎች ውስጥ አካቷል፡፡
መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ወንጀሎች በሚያስቀጡት የቅጣት አይነት ላይ በመመስረት በስድስት ተከፍለው ይገኛሉ፡፡ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 217/1 ስር እንደተደነገገው መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በወንጀል ተግባር ክስ የማቅረብ የይርጋ ዘመን የሚፀናው ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ነው፡-
1. የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል ሃያ አምስት ዓመት፣
2. ከአስር ዓመት በላይ እስከ ሃያ አምስት ዓመት ለመድረስ የሚችሉ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ሃያ አመት፣
3. ከአምስት ዓመት በላይ እስከ አስር ዓመት ለመድረስ የሚችል ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ አስራ አምስት አመት፣
4. ከአምስት አመት ለማይበልጥ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አስር ዓመት፣
5. ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አምስት ዓመት፣
6. እስከ አንድ ዓመት በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወይም በመቀጮ ብቻ ለሚያስቀጣ ወንጀል ሦስት ዓመት፡፡”
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 217/2 ስር ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመው ሲገኙ፡- የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች ተመሳሳይ በሚሆኑበት ጊዜ የአንዱ ወንጀል የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በሁለቱም ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆንና የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች የተለያዩ በሚሆንበት ጊዜ ከሁሉም ከባድ የሆነው ወንጀል የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን በሌሎች ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ስለዚህ በመደበኛ የወንጀል ክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ጊዜ ቢያንስ 3 ዓመት ቢበዛ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ 25 ዓመት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡
ይሁንና በወንጀል ህጉ አንቀጽ 213 ድንጋጌ መሰረት የግል ተበዳይ ሆኖ የግል አቤቱታ ማቅረብ የሚችል ማንኛውም ግለሰብ የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመበት ወይም የወንጀል አድራጊውን ማንነት ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሶስት ወር ውስጥ ካላቀረበ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንዳልፈለገ ተቆጥሮ ወይም የህግ ግምት ተወስዶ አቤቱታው ቀሪ ይሆናል፡፡ የግል አቤቱታ ማቅረብ ያልቻለው በበቂ ምክንያት ከሆነ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ያጋጠመው ችግር ከተወገ

ደበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ይህ እንዳለ ሆኖ ልዩ የግል አቤቱታ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን የወንጀል ህጉ አንቀጽ 218 ስር እንደተደነገገው ሁለት ዓመት ነው፡፡ ማንኛዉም የግል አቤቱታ ጉዳዩ ከተፈፀመ ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ ጉዳዩ ፍርድ ቤት የማይቀርብና ቀርቦም ከሆነ ጉዳዩን ፍርድ ቤት በዳኝነት ማየት አይችልም፡፡
የይርጋ ዘመን አቆጣጠር
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 219 /1 የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማክበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ሳይገቡ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሠረት በማድረግ እንደሆነ ተቀምጧል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል በተለዋጭ ወይም በተደራራቢ ተፈፃሚነት በሚኖራቸውም ቅጣቶች የሚያስቀጡ ሲሆኑ የይርጋ ዘመኑ የሚታሰበው ከሁሉም ከባድ ለሆነው ወንጀል በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡
የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀሉን ድርጊት ከፈጸመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ የወንጀሉ ድርጊት እየተደጋገመ ተፈፅሞ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ እንዲሁም የወንጀሉ ድርጊት ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ድርጊት ካቆመበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ወንጀሉ ተደርጓል ለማለት የሚቻለው ከፀባዮቹ አንዱ የወንጀሉ ውጤት የሆነ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ውጤት ከተገኘበት ግዜ ጀምሮ ነው፡፡
የይርጋ ዘመን መታገድ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 220/1 በሕጉ ወይም በፍሬ ነገር ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል የሚያግድ መሰናክል እስካለ ድረስ የይርጋ ዘመን መቆጠሩ ታግዶ ይቆያል፡፡ እንዲሁም ክስ ቀርቦ ነገሩ በዳኝነት በመታየት ላይ እንደሆነ ወይም በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ክስ ላይ ውሳኔ ሊሰጥ የማይገባ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር ታግዶ ይቆያል፡፡ መስናከሉም እንደተወገደ ወዲያውኑ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር ይቀጥላል፡፡
በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ስለክሱ መከታተል አቤቱታ እንዲቀርብ ማስፈለጉ በሕግ ተመልክቶ በተገኘ ጊዜ አቤቱታ አለማቅረብ የይርጋውን መቆጠር አያግድም፡፡ እንዲሁም ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል ጥፋተኛው በራሱ ፍላጎት የሚፈፀመው ተግባር የይርጋ ጊዜውን መቆጠር አያግደውም፡፡
የይርጋ ዘመን መቋረጥ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 221 የይርጋ ዘመን መቋረጥ ከወንጀሉ ወይም ከወንጀለኞቹ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምርመራ እንዲካሄድ ፣ብርበራ እንዲደረግ ፣መጥሪያ እንዲሰጥ ወይም ክስ እንዲቀርብ የሚሰጥ ትዕዛዝ፣ የሚፈፀም ድርጊት ወይም የሚሰጥ ውሳኔ የይርጋ ዘመኑን መቆጠር ያቋርጣል፡፡ የይርጋ ዘመን በተቋረጠ ቁጥር እንደገና እንደ አዲስ መቆጠር ይጀምራል፡፡ የይርጋ ዘመኑ መቋረጥ ፍፁም የሆነ ውጤት አለው፡፡ በወንጀሉ ተካፋይ መሆናቸው ለታወቀውም ሆነ ላልታወቀው ሁሉ መቋረጡ ይፀናባቸዋል፡፡ ይህ ማለት የወንጀል ተካፋይ መሆናቸው ወንጀሉ በተከሰተበት ጊዜ ያልታወቁ ሰዎች ያኔ ባለመታወቃቸው ምክንያት የይረጋ መቋረጥ አስመልክቶ ሊኖረው የሚችል ልዩነት እንደሌለ መረዳት ይቻላል፡፡
ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 222 ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን፣ በማናቸውም ምክንያት መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን /አንቀጽ 217/ አጠፌታ ጊዜ (እጥፍ) ካለፈ ወይም ልዩ የግል አቤቱታ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን ሲሆን /አንቀጽ 218/ ከዚሁ ዘመን በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ አልፎ እንደሆነ በወንጀሉ ላይ የሚቀርበው ክስ ወይም የሚደረገው መከታተል በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡እንዲሁም ሕጋዊ ቅጣት ከተወሰነው የይርጋ ዘመን/224/በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ ካለፈ ጥፋተኛው በዚህ ጊዜ ውስጥ ቢያብስ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል አስቦ በመፈፀም አደገኛ መሆኑን ካላሳየ በቀር የቅጣት ወይም የጥንቃቄ ተግባር አፈፃፀም ውሳኔ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ቀሪ ይሆናል፡፡

የዐቃብያነ ህግም የደመወዝ ማሻሻያ ፀድቋል!!
======/////////=====
የአማራ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ህዳር 19 ቀን 2013ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ዓመት መደበኛ ስብሰባ በአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የቀረበለትን የዐቃቤያነሕግና የስራ ኃላፊዎች የደመወዝ ማሻሻያ ጥያቄ መርምሮ የቀረበውን ማሻሻያ ጥያቄው በቀረበበት ልክ ከሐምሌ 1 ቀን 2012ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ወስኗል፡፡
@የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ መ/ቤት

የግብረ ሰዶም ጥቃት የፈፀመዉ ወጣት በ15 አመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡
-----------------------------------
ተከሳሽ አዲስ ተስፋዬ እድሜዉ 19 ዓመት ሲሆን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 631/1/ለ ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ በመተላለፍ በፈፀመዉ ለአካለ መጠን ባልደረሱ ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ሰዶም ጥቃት ወንጀል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሁለት ክሶችን መስርቶበታል፡፡
ተከሳሹ ከእርሱ ጋር አንድ አይነት ፃታ ካላቸዉና ለአካለ መጠን ካልደረሱ ልጆች ላይ የግብረ ሰዶም ጥቃት ለማድረስ አስቦ በቀን 11/10/2012 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል ልዩ ቦታዉ መሪ ጤና ጣቢያ አካባቢ 11 አመትና 9 አመት የሆናቸዉን ህፃናት ጥበቃ ቤት ዉስጥ በማስገባትና አፋቸዉን በካልሲዉ አፍኖ የግብረ ሰዶም ጥቃት ፈፅሟል ሲል በማስረጃ በማስደገፍ ዓቃቤ ህግ ክስ መስርቶበት ቆይቷል፡፡
ከሳሽ ዓቃቤ ህግ ተከሳሽ ተግባሩን መፈፀሙን የሚያስረዱ 4 የሰዉ ምስክሮችንና ከዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የተፃፈ የሀክምና ማስረጃን ጨምሮ ሁለት የፅሁፍ የማስረጃ ዝርዝሮቹን አያይዞ ለፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡
በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ የወንጀል ችሎትም ምስክሮቹን ካደመጠና የፅሁፍ ማስረጃዎችን ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ አዲስ ተስፋዬ ጥፋተኛ ነዉ ሲል የቅጣት ዉሳኔዉን አስተላልፏል፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ እድሜዉ የበሰለ አለመሆኑና ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን በቅጣት ማቅለያት ይዞለት በቀን 17/3/2013 ዓ.ም ባስቻለዉ 6ተኛ ችሎት ወንጀለኛዉ በ15 አመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

“ከዋልድባ ገዳም የመጣሁ ባህታዊ ነኝ” በማለት ሲያታልል የነበረው ተከሳሽ እና የግብረአበሩ ሴራ ሲጋለጥ
--------------------------------------
ነገሩ እንዲህ ነው ተበዳይ አትጠገብ መኮነን የእራሷን እና የቤተሰቦቿን ኑሮ ለማሻሻል ወደ አረብ ሃገር በመሄድ ጥቂት ገንዘብ አፍርታ ወደ ምትወዳት ሃገሯ ኢትዮጵያ ከተመለሰች ሰነባብታለች ። አረብ ሃገር በነበረችበት ወቅትም ከተከሳሽ ሱራፌል ደሴ ጋር አብሮ አደግ እና ወዳጅ ስለነበሩ በማህበራዊ ሚዲያ እና በስልክ አልፎ አልፎ ይጠያየቃሉ በሂደት ተከሳሽ ሱራፌል ለአትጠገብ መኮንን የፍቅር ጥያቄ ቢያነሳም አጥጋቢ መልስ ሳያገኝ ይቀራል ተከሳሽ ሱራፌል የ28 ዓመት ወጣት ነው ።
ታድያ አንደ ቀን በድልበር መድሐኒአለም ቤተክርስቲያን እንደአጋጣሚ ሆኖ ሱራፌል እና አትጠገብ ነጠላቸውን ለብሰው ይገናኛሉ። በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ጊቢ ውስጥም ተቀምጠው መጫዋወት ይጀምራሉ። ተከሳሽ ሱራፌልም አብሮ አደጉ ሆነችውን ተበዳይ አትጠገብን ከውጭ ሃገር ከመጣሽ እኮ ብዙ ጊዜ ሆነሽ ለምን ስራ አትጀምሪም ሲል ይጠይቃታል አትጠገብም በእጄ ላይ ያለው ገንዘብ ስራ ለመጀመር ስለማያስችለኝ ሌሎች አማራጮችን እያየሁ ነው ስትል ትመልስለታለች። ይሄኔ ነው እንግዲህ ተከሳሽ ሱራፌል ሲያስበው እና ሲመኘው ለነበረው የማታለል ሴራው መንገዱ ወለል ብሎ የተከፈተለት።
እናም ሱራፌል የማሳመን እና የማታለል ሴራውን እኔም እኮ እንደአንች ነበርኩኝ እጄ ላይ የነበረውም ጥቂት ገንዘብ ነበር እጅግ በጣምም ከጭንቀት ብዛት እያመመኝ እቸገር ነበር፤ አንዱ ጓደኛዬ ነው ከዋልድባ ገዳም የመጡ አባት አገናኝቶኝ ጤናዬ ተመለሰ ያለኝን ገንዘብ፣ ወርቅና ብሮቼን ለእሳቸው አስባርኬ ገንዘቤም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ሆነልኝ አንችንም ከእሳቸው ጋር ላገናኝሽ እና ንብረትሽን አስባርኪ እኔም ሁለት መቶ ሺህ ብር እጨምርልሽና የፈለግሽውን አይነት ሥራ ትሰሪበታለሽ አላት።
በአብሮአደጓ የፍቅር ጥያቄ ባነሳላት እና በቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ውስጥ መሆኑ እምነት እንድትጥል ያሳደራባት አትጠገብ ፍቃደኝነቷን ታሳውቃለች።
ተከሳሽም ከዋልድባ ገዳም የመጡ አባት ናቸው ወደተባሉት አባት ወይም ተከሳሽ ንብረቱ ግዛቸው ሱራፌል በራሱ ስልክ ይደውል እና “አባን” አናግሪያቸው ብሎ ስልኩን ለተበዳይ ይሰጣል፤ ተበዳይም የዋልድባ አባት ለተባለው ሰው ያለውን ነገር በሙሉ በዝርዝር መናገሯን ለዐቃቤ ህግ በዝርዝር ስታስረዳ ከዋልድባ ገዳም የመጡ አባት ናቸው የተባሉት አባት ወይም ተከሳሽ ንብረቱ ግዛቸው 4 ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ነገ 4፡00 ሰዓት ላይ አብራችሁ እንድትመጡ አሱ ያለሁበትን ቦታ ስለሚያውቀው እሱ ይዞሽ ይምጣ ተባልኩኝ ትላለች አትጠገብ።
ከዋልድባ የመጡት አባት የተባሉት ወይም ተከሳሽ ንብረቱ ግዛቸው ገና የ29 ዓመት ወጣት ነው።
በተባልነው ጊዜ እና ቦታ ስንደርስ የተባሉትን አባት ማግኘት ባለመቻላችን ስልክ ደውለን አባባ መጥተን እኮ አጣንዎት ስንላቸው አይ ልጆቼ ስትዘገዩብኝ እኮ እንደእናንተ የሚፈልጉኝ ሰዎች ነበሩ ወደ እነርሱ ሄጀ ነው መቼም ለመልካም ነገር መድከም ጥሩ ነው፤ በል ልጄ ሱራፌል ወደ ጎላ ሚካዔል ይዘሃት ና ሲሉን ተያይዘን ጎላ ሚካዔል ሄድን በቦታውም ስንደርስ የባህታዊ ልብስ የለበሱ መስቀል የያዙ አባት አገኘን ጉልበታቸውን ተንበርክኬ ስሜ መስቀል ተሳልሜ ተቀመጥን ።
የ29 ዓመት ወጣት የሆነው ተከሳሽ ንብረቱ ድርሳነ ገብርዔል በእጃቸው ይዘዋል ትላለች ተበዳይ ለዐቃቤ ህግ ክሱን ስታስረዳ በመቀጠልም ምንድን ነው ፍላጎትሽ ተብዬ ተጠየቁኩ ስራ መስራት እፈልጋለሁ ወደ ውጭ ሃገር መሄድም እፈልጋለሁ አልኳቸው በይ ሂጅ እና ሁለት ቅጠል ይዘሽ ነይ ሲሉኝ ሁለት ቅጠል በማምጣት ሰጠኋቸው ቅጠሉንም በመፅሐፉ ውስጥ አስቀምጠው አስር ብር እንድሰጣቸው ጠየቁኝ ሰጠኋቸው ብሩንና ቅጠሉን በመፅሐፉ ውስጥ አንድ ላይ አድርገው የኔ ልጅ ይሄ ከተቀየረ ህይወትሽ ይቀየራል ካልተቀየረ ግን እንደዚህ ሆነሽ ነው የምትቀሪ ስለት ግን መሳል አለብሽ ስለትሽ ከሰመረ ለሚካዔል ሃምሳ ሺህ ለገብርዔል ሃምሳ ሺህ ብር ታስገቢያለሽ ተባልኩኝ እሽ ብዬ መፅሀፉን ስገልጠው ሁለቱ ቅጠል ሁለት መቶ ብር ሆኖ አገኘሁት።
እጅግ በጣም ስለደነገጥኩ ከመቀመጫዬ ብድግ ብዬ ስቆም ተቀመጭ ሕይወትሽ ከዚህ በኋላ ተቀይሯል ተባልኩ።
አባ ወይም ተከሳሽ ንበረቱ እኔ እግዛብሔር በሰጠኝ ፀጋ ሰዎችን አገለግላለሁ እንጅ ከአንች ምንም አልፈልግም አሁን እቤትሽ ሄደሽ ነገ ማለትም የካቲት 25/2012 ዓ.ም መሆኑ ነው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ ለዘቢብ እና ለሽቶ መግዣ የሚሆን ስድስት ሺህ ብር እንዲሁም እንዲፀለይበት እና እንዲባረክ የምትፈልጊያቸውን ጥሬ ገንዘብ እና ንብረቶችሽን በሙሉ ይዘሽ ነይ ስባል በአጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው ከአራባ ሰባት ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ ጥሬ ገንዘብ፣ የወርቅ ብራስሌት እና የአንገት ሐብሌን ከታናሽ ወንድሜ ጋር በመሆን ይዘን ሄድን ትላለች ተበዳይ አትጠገብ ስታስረዳ ።
በቦታውም ስንደረስ ግቡ ተብለን ሁለት ሻማ አብሪ ተባልኩ አበራሁ ነጠላሽን ልበሽ ተባልኩ ለበስኩ ታናሽ ወንድሜም ከውጭ እንዲቆይ ተነገረው እና ከቤት ውጭ እንዲጠብቅ ተደረገ ያለኝን ንብረት ከሰጠሁ በኋላ አሁን አይንሽን ጨፍኝ እና አንችም እኔም እንፅልያለን ተባልኩኝ ያለማቋረጥ እያነባሁ ፀለይኩ።
ልጄ በይ በቃሽ አሁን ይሄን ገንዘብ ሳትከፍች ወስደሽ ትራስሽ ውስጥ ታሳድሪው እና ነገ ባንክ ወስደሽ አስቀምጭው ብለው በቤተክርስቲያን ጨርቅ የተጠቀለለ የታሸገ ገንዘብ መሳይ ነገር ሰጡኝ እሽ አመሰግናለሁ አባ ብዬ ስወጣ ታናሽ ወንድሜ ወዲያውኑ የታሸገውን ገንዘብ ከእኔ ቀምቶ ተቀብሎኝ ከፍተው ስናየው የተጠቀለለ ወረቀት ብቻ ሆኖ አገኘነው።
ወንድሜም እኔ ሳላውቅ በዙርያችን ፖሊሶችን አዘጋጅቶ ስለነበር ከዋልድባ ገዳም መጣሁ ባህታዊ ነኝ ባዩ ንብረቱ እና አብሮአደጌ ሱራፌል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደረገ ትላለች ተበዳይ አትጠገብ ።
የክስ መዝገቡ የመጣለት ዐቃቤ ህግም ተከሳሾቹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ) እና 692 (1) ተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፋቸው ዝርዝር የሰው፣ የሰነድ እና የኢግዚቪት ማስረጃዎችን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በማቅረቡ ፍርድ ቤቱ ህዳር 18/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾችን ያርማል መሰል አጥፊዎችንም ያስተምራል በሚል ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል።

የወንጀል ፍትህ አስተዳደር እና የሕግ የበላይነት በህብረተሰቡ የላቀ ተሳትፎ እውን ይሆናል!
____________
መንግሥት የአገርን ብሔራዊ ደህንነትና የሕዝቡን ሰላም ማረጋገጥ ተቀዳሚ ኃላፊነት ቢሆንም ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚፈለገውን ውጤት ማረጋገጥ እና እውን ማደረግ አይቻልም፡፡
ህዝብ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም የወንጀል ፍትህ ሥርዓቱ አፈፃፀም ብቃት ለማሳደግ የሰላ ጫፍ ነው፡፡
ውድ እንባቢያን! የአገራችን ህዝብ ብሂል መሰረት መሬት እና ጎጆ በአንድ በሬ ብሎም በላ እይቆምም እንደሚባለው ሁሉ ወንጀልን ለመከላከል፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ፍትህ ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ የፍትህ አካላት በሚሰሩት ሕግ የማስከበር የለውጥ እንቅስቃሴ በህዝብ ተሳትፎ የተደገፈ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
በአገራችን የረጋና ሰላማዊ ሁኔታ ለመፍጠር ህብረተሰቡ ስለሕግ፣ ፍትህ እና ወንጀል ያለው በጎ አመለካከት መያዝ ሕግና ሥርዓት ለማስከበር እና ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል መሆኑን ለማረጋገጥ የእድል የሚፈጥር ነው፡፡
ህዝብ ዋነኛ የፍትህ ተጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር፣ በሂደቱ ለሚፈለጉ መረጃዎች ዋነኛው ምንጭም ሲሆን በፍትህ ሥርዓቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየትና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማመላከት የማይተካ ሚና አለው፡፡
ቀልጠፋና ውጤታማ የሆነ የፍትህ ሥርዓት መኖር የተፋጠነ ልማትን ለማምጣት ሰላምንና መረጋጋትን ለመፍጠር ህግና ስርዓት በአስተማማኝ ደረጃ ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡
ስለሆነም ህብረተሰቡ ከወንጀል ስጋት እና ከማህበረሰባዊ ጠንቆች ነፃ ሆኖ በልማት ተግባሩ ላይ ብቻ እንዲሳተፍ አስተማማኝ ደህንነት እንዲሰማው ማድረግ ለአንድ ወገን የተሰጠ ተግባራ ሳይሆን የሁሉም ኃላፊነት ነው፡፡
በመሆኑም መንግስት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ ሕጋዊ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባሻገር የህዝብ እና የመንግስትን ጥቅም ብሎም ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ እየተወሰደ ያለው ሕጋዊ እርምጃ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሕግን አክብሮ መሥራት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሕግን አክብረው መስራታቸውን መከታተልና ሕግን ጥሰው የሚገኙትን በቅንጅት ለፍርድ ማቅረብ ከመልካም እና አገር ወዳድ ዜጋ የሚጠበቅ በመሆኑ ለአገር ሰላም እና ለሕግ የበላይነት በአንድነት እንቁም መልዕክታችን ነው፡፡
____________
መንግሥት የአገርን ብሔራዊ ደህንነትና የሕዝቡን ሰላም ማረጋገጥ ተቀዳሚ ኃላፊነት ቢሆንም ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚፈለገውን ውጤት ማረጋገጥ እና እውን ማደረግ አይቻልም፡፡
ህዝብ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ብሎም የወንጀል ፍትህ ሥርዓቱ አፈፃፀም ብቃት ለማሳደግ የሰላ ጫፍ ነው፡፡
ውድ እንባቢያን! የአገራችን ህዝብ ብሂል መሰረት መሬት እና ጎጆ በአንድ በሬ ብሎም በላ እይቆምም እንደሚባለው ሁሉ ወንጀልን ለመከላከል፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ፍትህ ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ የፍትህ አካላት በሚሰሩት ሕግ የማስከበር የለውጥ እንቅስቃሴ በህዝብ ተሳትፎ የተደገፈ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
በአገራችን የረጋና ሰላማዊ ሁኔታ ለመፍጠር ህብረተሰቡ ስለሕግ፣ ፍትህ እና ወንጀል ያለው በጎ አመለካከት መያዝ ሕግና ሥርዓት ለማስከበር እና ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል መሆኑን ለማረጋገጥ የእድል የሚፈጥር ነው፡፡
ህዝብ ዋነኛ የፍትህ ተጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር፣ በሂደቱ ለሚፈለጉ መረጃዎች ዋነኛው ምንጭም ሲሆን በፍትህ ሥርዓቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየትና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማመላከት የማይተካ ሚና አለው፡፡
ቀልጠፋና ውጤታማ የሆነ የፍትህ ሥርዓት መኖር የተፋጠነ ልማትን ለማምጣት ሰላምንና መረጋጋትን ለመፍጠር ህግና ስርዓት በአስተማማኝ ደረጃ ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡
ስለሆነም ህብረተሰቡ ከወንጀል ስጋት እና ከማህበረሰባዊ ጠንቆች ነፃ ሆኖ በልማት ተግባሩ ላይ ብቻ እንዲሳተፍ አስተማማኝ ደህንነት እንዲሰማው ማድረግ ለአንድ ወገን የተሰጠ ተግባራ ሳይሆን የሁሉም ኃላፊነት ነው፡፡
በመሆኑም መንግስት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ ሕጋዊ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባሻገር የህዝብ እና የመንግስትን ጥቅም ብሎም ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ እየተወሰደ ያለው ሕጋዊ እርምጃ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሕግን አክብሮ መሥራት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሕግን አክብረው መስራታቸውን መከታተልና ሕግን ጥሰው የሚገኙትን በቅንጅት ለፍርድ ማቅረብ ከመልካም እና አገር ወዳድ ዜጋ የሚጠበቅ በመሆኑ ለአገር ሰላም እና ለሕግ የበላይነት በአንድነት እንቁም መልዕክታችን ነው፡፡
በወንጀል ጉዳዮች ይርጋ በኢትዮጵያ ህግ
የይርጋ ምንነት
ይርጋ ማለት አንድ ሰው በጉዳዩ ላይ መብት ያለው ቢሆንም ይህንን መብቱን ለመጠየቅ የማይችልበትን ገደብ የሚመለከት ሲሆን ይህም በህግ ተለይቶ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ በአንድ ጉዳይ ክስ ለማቅረብ የሚከለከልበት የህግ ፅንሰ-ሃሳብ ነው፡፡ ይርጋ በወንጀል እና በፍትሀ ብሄር ህጎች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን በወንጀል ጉዳይ ላይ ይርጋን በመቃወሚያነት አንስቶ ለመከራከር የሚችለው ተከሳሽ፣ ዐቃቤ ሕግና ፍርድ ቤቶች ስለመሆናቸው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 130/1/ሐ እና በወንጀል ሕግ 216(2) ላይ ተመልክቷል፡: በወንጀል ጉዳዮች ላይ ተከሳሹ ባያነሳውም ዳኞች በይርጋ የታገደ የወንጀል ክስ ሲቀርብላቸው ማየት አይችሉም፡፡ስለሆነም ክሱ በይርጋ ስለመታገዱና ክሱን ለመቀበል የማይገባ ስለመሆኑ ተከሳሽ ባያመለክትም ዐቃቤ ሕጉ ወይም ፍርድ ቤቱ በማናቸውም ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡
በተመሳሳይ ቅጣቱ ሳይፈፀም የይርጋው ጊዜ ካለፈ አጥፊው ራሱ ባያነሳውም እንኳ አስፈፃሚው አካል ሊያነሳው እንደሚገባ በወንጀል ህግ አንቀፅ 216(2) እና 223 (2) ተገልጿል፡፡ለይርጋ የተወሰነ ጊዜ ካለፈ የጥፋተኝነት ውሳኔ ወይም ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ ሊወሰን አይችልም፡፡በፍትሀ ብሄር ጉዳዮች ግን ይርጋን እንደመቃወሚያነት ማንሳት የሚችለው ተከሳሽ ብቻ ሲሆን ይህንንም ማድረግ የሚችለው በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክሱ መሰማት ከመጀመሩ እና ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር በተከሳሽ በኩል ተፈፅሟል አልተፈፀመም የሚለው ላይ ክርክር ከመደረጉ በፊት ነው፡፡ይርጋ በተከሳሹ ካልተነሳ ለማንሳት እንዳልፈለገ ስለሚቆጠር ዳኛው በራሱ ተነሳሽነት እንዲያነሳ ሕጉ አይፈቅድም፡፡
በይርጋ የማይታገዱ ጉዳዮች
በመርህ ደረጃ የወንጀል ድርጊቶች ከተፈፀሙ በኋላ ክስ ለማቅረብ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ ያለ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ በሌላ ህግ ከተደነገገ በይርጋ የማይታገዱ ወንጀሎች እንዳሉ ከወንጀል ህጉ እንቀፅ 216/1 መገንዘብ ይቻላል፡፡በይርጋ የማይታገዱ የወንጀል ድርጊቶችን ከሚያስቀምጡ የህግ ድንጋጌዎች የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት ቀዳሚው ነው፡፡በህገ መንግስቱ አንቀፅ 28/1 ስር እንደተደነገገው ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና በሌሎች ሕጎች የሰው ልጅ ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑ ወንጀሎች ፣የሰው ዘር ማጥፋት፣ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈፀሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም፡፡
በዓለም አቀፍ ሕግና ልምድ መሠረት በተለይም ይርጋ በጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ እንዳይፈፀም ለማስቀረት በተደረገው ስምምነት እና በሮም የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ መሰረት የዘር ማጥፋት፣ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲሁም የጦር ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሰዎች ላይ የሚቀርቡ ክሶች በይርጋ የማይታገዱ ናቸው::
ይርጋ ያስፈለገባቸው ምክንያቶች
የይርጋ ፅንሰ ሃሳብ እንዲኖር ያስፈለገባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች ከሳሽ በተገቢ ትጋትና በቂ ምክንያት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል፣ተከሳሽ በጣም ዘግይተው ለሚመጡ ክሶች የመከላከያ ማስረጃዎች እንዳያጣ ለማድረግ እና ሰዎች መብታቸውን የሚጠቀሙበትን የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ህብረተሰቡን ከስጋት በማዳን የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ ማስቻል ናቸው፡፡ይርጋ በዋናነት ጠቀሜታ የሚኖረው ለተከሳሽ መሆኑን ከህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡በመሆኑም ተከሳሽ በይርጋ በታገደ ጉዳይ ላይ ክስ ከቀረበበት በመቃወሚያ በማንሳት ክሱ ቀሪ እንዲሆንለት መጠየቅ ይችላል፡፡
በወንጀል ህግ ውስጥ የወንጀል ይርጋ በሁለት የተከፈለ ነው፡፡ ይኸውም የክስ ይርጋና የቅጣት ይርጋ ናቸው፡፡የክስ ይርጋ ዐቃቤ ህግም ሆነ የግል ተበዳይ (ወንጀል የተፈፀመበት ሰው) ወንጀል ፈጽሟል በተባለው ሰው ላይ ክስ ሊያቀርቡ የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ የሚያስቀምጥ ሲሆን ዝርዝር አሰራሩ በወንጀል ህግ አንቀጾች 216-222 ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል የቅጣት ይርጋ ከቅጣት አፈፃፀም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አንድ ሰው ጥፋተኛ ነው ተብሎ ቅጣት ከተወሰነበት በኋላ ቅጣቱ ሳይፈፀም ቢቀር በሕግ የተመለከተው ጊዜ ካለፈ ቅጣቱን የማስፈፀም መብት እንደሚቀር የወንጀል ህግ አንቀፅ 223 ስር ተቀምጧል፡፡እንዲሁም የዋነኛው ቅጣት የይርጋ ዘመን የተጨማሪ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እር
ምጃዎች መፈፀምንም ያስቀራል፡፡እንደ ወንጀሉ ክብደትና ቀላልነት የቅጣት ይርጋ በስላሳ ፣ በሃያ፣ በአስርና በአምስት ዓመት ሊወሰን እንደሚችል የወንጀል ህግ አንቀፅ 224(1) ዘርዝሮ ያስቀምጣል፡፡
ይርጋን አስመልክቶ በህግ ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎች በዋናነት የሚያመላክቱት ክስ ለማቅረብ ወይም መብት ለመጠየቅ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ እንደመሆኑ ይህን ለማድረግ እንዲቻል በህግ የሚጠየቀው የጊዜ ገደብም እንደ ጉዳዩ ክብደት፣ባህሪይና ሁኔታ የተለያየ ሲሆን ለሁሉም ጉዳዮች የተቀመጠ ተመሳሳይ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ የለም፡፡በመሆኑም ህግ አውጪው እንደ ጉዳዩ ዓይነት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ክስ ለማቅረብ እንደሚቻል የተለያዩ የክስ ማቅረብያ ጊዜያት በህጎች ውስጥ አካቷል፡፡
መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ወንጀሎች በሚያስቀጡት የቅጣት አይነት ላይ በመመስረት በስድስት ተከፍለው ይገኛሉ፡፡ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 217/1 ስር እንደተደነገገው መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በወንጀል ተግባር ክስ የማቅረብ የይርጋ ዘመን የሚፀናው ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ነው፡-
1. የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል ሃያ አምስት ዓመት፣
2. ከአስር ዓመት በላይ እስከ ሃያ አምስት ዓመት ለመድረስ የሚችሉ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ሃያ አመት፣
3. ከአምስት ዓመት በላይ እስከ አስር ዓመት ለመድረስ የሚችል ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ አስራ አምስት አመት፣
4. ከአምስት አመት ለማይበልጥ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አስር ዓመት፣
5. ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አምስት ዓመት፣
6. እስከ አንድ ዓመት በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወይም በመቀጮ ብቻ ለሚያስቀጣ ወንጀል ሦስት ዓመት፡፡”
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 217/2 ስር ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመው ሲገኙ፡- የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች ተመሳሳይ በሚሆኑበት ጊዜ የአንዱ ወንጀል የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በሁለቱም ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆንና የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች የተለያዩ በሚሆንበት ጊዜ ከሁሉም ከባድ የሆነው ወንጀል የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን በሌሎች ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ስለዚህ በመደበኛ የወንጀል ክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ጊዜ ቢያንስ 3 ዓመት ቢበዛ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ 25 ዓመት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡
ይሁንና በወንጀል ህጉ አንቀጽ 213 ድንጋጌ መሰረት የግል ተበዳይ ሆኖ የግል አቤቱታ ማቅረብ የሚችል ማንኛውም ግለሰብ የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመበት ወይም የወንጀል አድራጊውን ማንነት ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሶስት ወር ውስጥ ካላቀረበ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንዳልፈለገ ተቆጥሮ ወይም የህግ ግምት ተወስዶ አቤቱታው ቀሪ ይሆናል፡፡ የግል አቤቱታ ማቅረብ ያልቻለው በበቂ ምክንያት ከሆነ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ያጋጠመው ችግር ከተወገ
የይርጋ ምንነት
ይርጋ ማለት አንድ ሰው በጉዳዩ ላይ መብት ያለው ቢሆንም ይህንን መብቱን ለመጠየቅ የማይችልበትን ገደብ የሚመለከት ሲሆን ይህም በህግ ተለይቶ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ በአንድ ጉዳይ ክስ ለማቅረብ የሚከለከልበት የህግ ፅንሰ-ሃሳብ ነው፡፡ ይርጋ በወንጀል እና በፍትሀ ብሄር ህጎች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን በወንጀል ጉዳይ ላይ ይርጋን በመቃወሚያነት አንስቶ ለመከራከር የሚችለው ተከሳሽ፣ ዐቃቤ ሕግና ፍርድ ቤቶች ስለመሆናቸው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 130/1/ሐ እና በወንጀል ሕግ 216(2) ላይ ተመልክቷል፡: በወንጀል ጉዳዮች ላይ ተከሳሹ ባያነሳውም ዳኞች በይርጋ የታገደ የወንጀል ክስ ሲቀርብላቸው ማየት አይችሉም፡፡ስለሆነም ክሱ በይርጋ ስለመታገዱና ክሱን ለመቀበል የማይገባ ስለመሆኑ ተከሳሽ ባያመለክትም ዐቃቤ ሕጉ ወይም ፍርድ ቤቱ በማናቸውም ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡
በተመሳሳይ ቅጣቱ ሳይፈፀም የይርጋው ጊዜ ካለፈ አጥፊው ራሱ ባያነሳውም እንኳ አስፈፃሚው አካል ሊያነሳው እንደሚገባ በወንጀል ህግ አንቀፅ 216(2) እና 223 (2) ተገልጿል፡፡ለይርጋ የተወሰነ ጊዜ ካለፈ የጥፋተኝነት ውሳኔ ወይም ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ ሊወሰን አይችልም፡፡በፍትሀ ብሄር ጉዳዮች ግን ይርጋን እንደመቃወሚያነት ማንሳት የሚችለው ተከሳሽ ብቻ ሲሆን ይህንንም ማድረግ የሚችለው በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክሱ መሰማት ከመጀመሩ እና ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር በተከሳሽ በኩል ተፈፅሟል አልተፈፀመም የሚለው ላይ ክርክር ከመደረጉ በፊት ነው፡፡ይርጋ በተከሳሹ ካልተነሳ ለማንሳት እንዳልፈለገ ስለሚቆጠር ዳኛው በራሱ ተነሳሽነት እንዲያነሳ ሕጉ አይፈቅድም፡፡
በይርጋ የማይታገዱ ጉዳዮች
በመርህ ደረጃ የወንጀል ድርጊቶች ከተፈፀሙ በኋላ ክስ ለማቅረብ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ ያለ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ በሌላ ህግ ከተደነገገ በይርጋ የማይታገዱ ወንጀሎች እንዳሉ ከወንጀል ህጉ እንቀፅ 216/1 መገንዘብ ይቻላል፡፡በይርጋ የማይታገዱ የወንጀል ድርጊቶችን ከሚያስቀምጡ የህግ ድንጋጌዎች የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት ቀዳሚው ነው፡፡በህገ መንግስቱ አንቀፅ 28/1 ስር እንደተደነገገው ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና በሌሎች ሕጎች የሰው ልጅ ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑ ወንጀሎች ፣የሰው ዘር ማጥፋት፣ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈፀሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም፡፡
በዓለም አቀፍ ሕግና ልምድ መሠረት በተለይም ይርጋ በጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ እንዳይፈፀም ለማስቀረት በተደረገው ስምምነት እና በሮም የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ መሰረት የዘር ማጥፋት፣ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲሁም የጦር ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሰዎች ላይ የሚቀርቡ ክሶች በይርጋ የማይታገዱ ናቸው::
ይርጋ ያስፈለገባቸው ምክንያቶች
የይርጋ ፅንሰ ሃሳብ እንዲኖር ያስፈለገባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች ከሳሽ በተገቢ ትጋትና በቂ ምክንያት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል፣ተከሳሽ በጣም ዘግይተው ለሚመጡ ክሶች የመከላከያ ማስረጃዎች እንዳያጣ ለማድረግ እና ሰዎች መብታቸውን የሚጠቀሙበትን የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ህብረተሰቡን ከስጋት በማዳን የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ ማስቻል ናቸው፡፡ይርጋ በዋናነት ጠቀሜታ የሚኖረው ለተከሳሽ መሆኑን ከህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡በመሆኑም ተከሳሽ በይርጋ በታገደ ጉዳይ ላይ ክስ ከቀረበበት በመቃወሚያ በማንሳት ክሱ ቀሪ እንዲሆንለት መጠየቅ ይችላል፡፡
በወንጀል ህግ ውስጥ የወንጀል ይርጋ በሁለት የተከፈለ ነው፡፡ ይኸውም የክስ ይርጋና የቅጣት ይርጋ ናቸው፡፡የክስ ይርጋ ዐቃቤ ህግም ሆነ የግል ተበዳይ (ወንጀል የተፈፀመበት ሰው) ወንጀል ፈጽሟል በተባለው ሰው ላይ ክስ ሊያቀርቡ የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ የሚያስቀምጥ ሲሆን ዝርዝር አሰራሩ በወንጀል ህግ አንቀጾች 216-222 ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል የቅጣት ይርጋ ከቅጣት አፈፃፀም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አንድ ሰው ጥፋተኛ ነው ተብሎ ቅጣት ከተወሰነበት በኋላ ቅጣቱ ሳይፈፀም ቢቀር በሕግ የተመለከተው ጊዜ ካለፈ ቅጣቱን የማስፈፀም መብት እንደሚቀር የወንጀል ህግ አንቀፅ 223 ስር ተቀምጧል፡፡እንዲሁም የዋነኛው ቅጣት የይርጋ ዘመን የተጨማሪ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እር
ምጃዎች መፈፀምንም ያስቀራል፡፡እንደ ወንጀሉ ክብደትና ቀላልነት የቅጣት ይርጋ በስላሳ ፣ በሃያ፣ በአስርና በአምስት ዓመት ሊወሰን እንደሚችል የወንጀል ህግ አንቀፅ 224(1) ዘርዝሮ ያስቀምጣል፡፡
ይርጋን አስመልክቶ በህግ ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎች በዋናነት የሚያመላክቱት ክስ ለማቅረብ ወይም መብት ለመጠየቅ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ እንደመሆኑ ይህን ለማድረግ እንዲቻል በህግ የሚጠየቀው የጊዜ ገደብም እንደ ጉዳዩ ክብደት፣ባህሪይና ሁኔታ የተለያየ ሲሆን ለሁሉም ጉዳዮች የተቀመጠ ተመሳሳይ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ የለም፡፡በመሆኑም ህግ አውጪው እንደ ጉዳዩ ዓይነት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ክስ ለማቅረብ እንደሚቻል የተለያዩ የክስ ማቅረብያ ጊዜያት በህጎች ውስጥ አካቷል፡፡
መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ወንጀሎች በሚያስቀጡት የቅጣት አይነት ላይ በመመስረት በስድስት ተከፍለው ይገኛሉ፡፡ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 217/1 ስር እንደተደነገገው መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በወንጀል ተግባር ክስ የማቅረብ የይርጋ ዘመን የሚፀናው ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ነው፡-
1. የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል ሃያ አምስት ዓመት፣
2. ከአስር ዓመት በላይ እስከ ሃያ አምስት ዓመት ለመድረስ የሚችሉ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ሃያ አመት፣
3. ከአምስት ዓመት በላይ እስከ አስር ዓመት ለመድረስ የሚችል ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ አስራ አምስት አመት፣
4. ከአምስት አመት ለማይበልጥ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አስር ዓመት፣
5. ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አምስት ዓመት፣
6. እስከ አንድ ዓመት በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወይም በመቀጮ ብቻ ለሚያስቀጣ ወንጀል ሦስት ዓመት፡፡”
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 217/2 ስር ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመው ሲገኙ፡- የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች ተመሳሳይ በሚሆኑበት ጊዜ የአንዱ ወንጀል የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በሁለቱም ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆንና የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች የተለያዩ በሚሆንበት ጊዜ ከሁሉም ከባድ የሆነው ወንጀል የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን በሌሎች ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ስለዚህ በመደበኛ የወንጀል ክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ጊዜ ቢያንስ 3 ዓመት ቢበዛ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ 25 ዓመት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡
ይሁንና በወንጀል ህጉ አንቀጽ 213 ድንጋጌ መሰረት የግል ተበዳይ ሆኖ የግል አቤቱታ ማቅረብ የሚችል ማንኛውም ግለሰብ የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመበት ወይም የወንጀል አድራጊውን ማንነት ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሶስት ወር ውስጥ ካላቀረበ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንዳልፈለገ ተቆጥሮ ወይም የህግ ግምት ተወስዶ አቤቱታው ቀሪ ይሆናል፡፡ የግል አቤቱታ ማቅረብ ያልቻለው በበቂ ምክንያት ከሆነ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ያጋጠመው ችግር ከተወገ
ደበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ይህ እንዳለ ሆኖ ልዩ የግል አቤቱታ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን የወንጀል ህጉ አንቀጽ 218 ስር እንደተደነገገው ሁለት ዓመት ነው፡፡ ማንኛዉም የግል አቤቱታ ጉዳዩ ከተፈፀመ ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ ጉዳዩ ፍርድ ቤት የማይቀርብና ቀርቦም ከሆነ ጉዳዩን ፍርድ ቤት በዳኝነት ማየት አይችልም፡፡
የይርጋ ዘመን አቆጣጠር
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 219 /1 የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማክበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ሳይገቡ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሠረት በማድረግ እንደሆነ ተቀምጧል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል በተለዋጭ ወይም በተደራራቢ ተፈፃሚነት በሚኖራቸውም ቅጣቶች የሚያስቀጡ ሲሆኑ የይርጋ ዘመኑ የሚታሰበው ከሁሉም ከባድ ለሆነው ወንጀል በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡
የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀሉን ድርጊት ከፈጸመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ የወንጀሉ ድርጊት እየተደጋገመ ተፈፅሞ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ እንዲሁም የወንጀሉ ድርጊት ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ድርጊት ካቆመበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ወንጀሉ ተደርጓል ለማለት የሚቻለው ከፀባዮቹ አንዱ የወንጀሉ ውጤት የሆነ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ውጤት ከተገኘበት ግዜ ጀምሮ ነው፡፡
የይርጋ ዘመን መታገድ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 220/1 በሕጉ ወይም በፍሬ ነገር ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል የሚያግድ መሰናክል እስካለ ድረስ የይርጋ ዘመን መቆጠሩ ታግዶ ይቆያል፡፡ እንዲሁም ክስ ቀርቦ ነገሩ በዳኝነት በመታየት ላይ እንደሆነ ወይም በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ክስ ላይ ውሳኔ ሊሰጥ የማይገባ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር ታግዶ ይቆያል፡፡ መስናከሉም እንደተወገደ ወዲያውኑ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር ይቀጥላል፡፡
በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ስለክሱ መከታተል አቤቱታ እንዲቀርብ ማስፈለጉ በሕግ ተመልክቶ በተገኘ ጊዜ አቤቱታ አለማቅረብ የይርጋውን መቆጠር አያግድም፡፡ እንዲሁም ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል ጥፋተኛው በራሱ ፍላጎት የሚፈፀመው ተግባር የይርጋ ጊዜውን መቆጠር አያግደውም፡፡
የይርጋ ዘመን መቋረጥ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 221 የይርጋ ዘመን መቋረጥ ከወንጀሉ ወይም ከወንጀለኞቹ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምርመራ እንዲካሄድ ፣ብርበራ እንዲደረግ ፣መጥሪያ እንዲሰጥ ወይም ክስ እንዲቀርብ የሚሰጥ ትዕዛዝ፣ የሚፈፀም ድርጊት ወይም የሚሰጥ ውሳኔ የይርጋ ዘመኑን መቆጠር ያቋርጣል፡፡ የይርጋ ዘመን በተቋረጠ ቁጥር እንደገና እንደ አዲስ መቆጠር ይጀምራል፡፡ የይርጋ ዘመኑ መቋረጥ ፍፁም የሆነ ውጤት አለው፡፡ በወንጀሉ ተካፋይ መሆናቸው ለታወቀውም ሆነ ላልታወቀው ሁሉ መቋረጡ ይፀናባቸዋል፡፡ ይህ ማለት የወንጀል ተካፋይ መሆናቸው ወንጀሉ በተከሰተበት ጊዜ ያልታወቁ ሰዎች ያኔ ባለመታወቃቸው ምክንያት የይረጋ መቋረጥ አስመልክቶ ሊኖረው የሚችል ልዩነት እንደሌለ መረዳት ይቻላል፡፡
ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 222 ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን፣ በማናቸውም ምክንያት መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን /አንቀጽ 217/ አጠፌታ ጊዜ (እጥፍ) ካለፈ ወይም ልዩ የግል አቤቱታ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን ሲሆን /አንቀጽ 218/ ከዚሁ ዘመን በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ አልፎ እንደሆነ በወንጀሉ ላይ የሚቀርበው ክስ ወይም የሚደረገው መከታተል በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡እንዲሁም ሕጋዊ ቅጣት ከተወሰነው የይርጋ ዘመን/224/በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ ካለፈ ጥፋተኛው በዚህ ጊዜ ውስጥ ቢያብስ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል አስቦ በመፈፀም አደገኛ መሆኑን ካላሳየ በቀር የቅጣት ወይም የጥንቃቄ ተግባር አፈፃፀም ውሳኔ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ቀሪ ይሆናል፡፡
የይርጋ ዘመን አቆጣጠር
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 219 /1 የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማክበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ሳይገቡ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሠረት በማድረግ እንደሆነ ተቀምጧል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል በተለዋጭ ወይም በተደራራቢ ተፈፃሚነት በሚኖራቸውም ቅጣቶች የሚያስቀጡ ሲሆኑ የይርጋ ዘመኑ የሚታሰበው ከሁሉም ከባድ ለሆነው ወንጀል በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡
የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀሉን ድርጊት ከፈጸመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ የወንጀሉ ድርጊት እየተደጋገመ ተፈፅሞ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ እንዲሁም የወንጀሉ ድርጊት ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ድርጊት ካቆመበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ወንጀሉ ተደርጓል ለማለት የሚቻለው ከፀባዮቹ አንዱ የወንጀሉ ውጤት የሆነ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ውጤት ከተገኘበት ግዜ ጀምሮ ነው፡፡
የይርጋ ዘመን መታገድ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 220/1 በሕጉ ወይም በፍሬ ነገር ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል የሚያግድ መሰናክል እስካለ ድረስ የይርጋ ዘመን መቆጠሩ ታግዶ ይቆያል፡፡ እንዲሁም ክስ ቀርቦ ነገሩ በዳኝነት በመታየት ላይ እንደሆነ ወይም በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ክስ ላይ ውሳኔ ሊሰጥ የማይገባ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር ታግዶ ይቆያል፡፡ መስናከሉም እንደተወገደ ወዲያውኑ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር ይቀጥላል፡፡
በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ስለክሱ መከታተል አቤቱታ እንዲቀርብ ማስፈለጉ በሕግ ተመልክቶ በተገኘ ጊዜ አቤቱታ አለማቅረብ የይርጋውን መቆጠር አያግድም፡፡ እንዲሁም ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል ጥፋተኛው በራሱ ፍላጎት የሚፈፀመው ተግባር የይርጋ ጊዜውን መቆጠር አያግደውም፡፡
የይርጋ ዘመን መቋረጥ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 221 የይርጋ ዘመን መቋረጥ ከወንጀሉ ወይም ከወንጀለኞቹ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምርመራ እንዲካሄድ ፣ብርበራ እንዲደረግ ፣መጥሪያ እንዲሰጥ ወይም ክስ እንዲቀርብ የሚሰጥ ትዕዛዝ፣ የሚፈፀም ድርጊት ወይም የሚሰጥ ውሳኔ የይርጋ ዘመኑን መቆጠር ያቋርጣል፡፡ የይርጋ ዘመን በተቋረጠ ቁጥር እንደገና እንደ አዲስ መቆጠር ይጀምራል፡፡ የይርጋ ዘመኑ መቋረጥ ፍፁም የሆነ ውጤት አለው፡፡ በወንጀሉ ተካፋይ መሆናቸው ለታወቀውም ሆነ ላልታወቀው ሁሉ መቋረጡ ይፀናባቸዋል፡፡ ይህ ማለት የወንጀል ተካፋይ መሆናቸው ወንጀሉ በተከሰተበት ጊዜ ያልታወቁ ሰዎች ያኔ ባለመታወቃቸው ምክንያት የይረጋ መቋረጥ አስመልክቶ ሊኖረው የሚችል ልዩነት እንደሌለ መረዳት ይቻላል፡፡
ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 222 ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን፣ በማናቸውም ምክንያት መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን /አንቀጽ 217/ አጠፌታ ጊዜ (እጥፍ) ካለፈ ወይም ልዩ የግል አቤቱታ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን ሲሆን /አንቀጽ 218/ ከዚሁ ዘመን በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ አልፎ እንደሆነ በወንጀሉ ላይ የሚቀርበው ክስ ወይም የሚደረገው መከታተል በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡እንዲሁም ሕጋዊ ቅጣት ከተወሰነው የይርጋ ዘመን/224/በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ ካለፈ ጥፋተኛው በዚህ ጊዜ ውስጥ ቢያብስ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል አስቦ በመፈፀም አደገኛ መሆኑን ካላሳየ በቀር የቅጣት ወይም የጥንቃቄ ተግባር አፈፃፀም ውሳኔ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ቀሪ ይሆናል፡፡
አለሕግAleHig ️
what your short answer❓❓ 🔴Refresh your mind‼️ you can send us you answer via @Alemwaza or share to group @ALE_lawsocieties please, indicate the relevant law that you used to answer.
XZY Plc has the right to sue.
B/c of......
- Since they were two Plc's (XYZ &ABC) Plc's that signed contract from the beginning.
- the managers also signed the contract on behalf of the Plc' s and not for their own interests.
- The manager of the XYZ Plc testified that at the time of the
Lawsuit the libres of the excavator belonged to XYZ Plc in the contract.
#therefore it is XYZ Plc that can sue for the reason i mentioned above and b/c the matter is directly related to the XYZ Plc & affects its interests.‼️‼️
via Mebratu G.

1. Who is entitled to sue? The manager or XYZ PLC?
XYZ PLC is entitled to sue.
2. Why?
This will take us to attributes of personality. One of the attributes of legal personality is to sue or be sued. Because according to what we have learned in class, PLC is one of the business organization which has its own legal personality, has the attribute to sue or be sues. Therefore, the XYZ PLC is entitled to sue ABC PLC.

For the fact that the evidence (the title deed/libre) presented by the General Manager of XYZ PLC shows the excavator belongs to the XYZ PLC but not to the manager. The manager has no right to sue the ABC PLC as a separate person from XYZ PLC, in his own name, which will lead us to a conflict of interest since he is claimed that the excavator is his own excavator. But, again for the fact that the general manager represents the XYZ PLC, the manager will continue to sue the ABC PLC in the name of XYZ PLC but not in his own name.
Furthermore, one of the controversial issue in this case is, We do not have a ground how the court ordered the release of the attached excavator. But, one thing is clear for us the contract concluded concerning 264,000.00birr was between the XYZ PLC and DEF PLC but not between the manager as a person and DEF PLC. This is also another ground which will support our answer; the XYZ PLC is entitled to sue as a PLC which has a legal personality.
Our group has tried his best to answer the question based on the case, according to its scope of business law understanding.

ያለ ህጋዊ ፈቃድ ሰዎችን ወደ ውጭ ሀገር ሲልክ የነበረው ግለስብ ተቀጣ
___________
በህገ ወጥ መንገድ ኢትዮዽውያንን ወደ ውጭ አገር በመላክ ወንጀል የተከሰሰዉ ተከሳሽ ሀሰን ሙሀመድ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በጽኑ እስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ::
የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 598/1/ የተመለከተዉን በመተላለፍ ወደ ዉጭ አገር ለመላክ የሚያስችል ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው የግል ተበዳይን ሙስጠፋ ጣሂርን የባለቤቴ ወንድም ዱባይ ሀገር ስላለ እልክሀለሁ ብሎ በማግባባት መጀመሪያ ለሂደት (ለፕሮስስ) ማስጀመሪያ በሚል 20 ሺ ብር ከተቀበለ በኃላ በተለያዩ ጊዚያት ለጉዳይ ማስፈጸሚያ እና ለቪዛ ማሰሪያ በሚል በአጠቃላይ 83 ሺ ብር ተቀብሎ ወደ ዱባይ እንዲሄድና እንግልት እንዲደርስበት በማድረጉ በፈጸመው ህጋዊ የስራ ፈቃድ ሳይኖር ሰዎችን ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገቡ ያስረዳል ፡፡
ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ የሰዉ እና የሰነድ ማስረጃዎች በማደረጀት ለችሎቱ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሽ የቀረበበት ክሱ ግልጽ ነው፤መቃወሚያ የለኝም በማለቱ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከደመጠና መዝገቡን ከመረመረ በኃላ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ባለመከላከሉ ጥፋተኛ ተብሏል፡፡
ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እና 2000 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኗል::

Forwarded from Esmael Seid
Please send ye wul hig meserete hasaboch by professor tilahun teshome Amharic version