አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ALE (Alternative Legal Education) All in one, All Law Societies. federal & regional Judges, Prosecutors, Advocates, consultants & law school heads, instructors, deans, Law graduates, Students & other NGO and PLC employees..
etc.

Contact Us Via @Alemwaza
https://t.me/lawsocieties
አለሕግAleHig ️
Tena yestelegn esti ketechale sele election yehone neger belun mebt nw weys gedeta?
A response to the question, is election a right or duty?

In the Ethiopian context, election has not long history. The concept comes after coming into effect of the 1995 FDRE Constitution. Having saying that, look Article 38 sub 1 of the FDRE Constitution, it clearly states The right to vote and elected are right. Now relate Article 38 and 54 of the FDRE Constitution at least there is no any Clouse, phrase, or pragraph that shows election is duty. In addition bear in mind, the last five elections.

But, now a day some countries of the world observing election as duty. These countries came up with new philosophy of election. They have minmam age requirement, then any one who attain that age is fully duty bound to participate in election, unless s/he is subject to the provided election laws.

Thank you!!
via Adam H
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን የበሰለ ዳኝነትና የበሰለ ተቋም ያስፈልጉናል›› ሲሉ ተናገሩ፡፡

የበሰለ ዳኝነት ወይም ተቋም ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ያብራሩት ወ/ሮ መዓዛ፣ ሕግን ማዕከል አድርጎ የሚሠራ፣ ከየትኛውም አቅጣጫ ለሚመጣ ግፊት እጅ የማይሰጥ ዳኛና ተቋም ለኢትዮጵያ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ ሦስቱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ለግማሽ ቀን ተዘጋጅቶ በነበረው የአመራሮችና ዳኞች ውይይት ላይ በተገኙበት ወቅት በአገሪቱ በተከሰቱ ወቅታዊ ሁኔታዎች በዳኞች ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል ስለመባሉ ተጠይቀው እንዳብራሩት፣ በዳኞች ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥረው መንግሥት ወይም አስፈጻሚ ብቻ አይደሉም፡፡ ተፅዕኖ ከመገናኛ ብዙኃን፣ ከሕዝቡና ከራሱ ከዳኛውም ይፈጠራል፡፡ ነገር ግን አንድ ዳኛ እነዚህን ተፅዕኖዎች ተቋቁሞና ተጨባጭ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ውሳኔ ይሰጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ የዳኞች ውሳኔ ሁለት ወገኖችን እንደማያስደስት የገለጹት ወ/ሮ መዓዛ፣ የተወሰነለት ደስተኛ ቢሆንም የተወሰነበት ደግሞ ‹‹ፍርድ ቤቶች ነፃ አይደሉም›› እንደሚል አስረድተዋል፡፡ ይህንን ምንም ማድረግ ስለማይቻል ያለው አማራጭ ሕዝቡ የሕግ ግንዛቤው የሰፋ እንዲሆን ማስተማር ብቻ መሆኑን አክለዋል፡፡

ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ ሆነው እስከሚገኙና በፍርድ ቤት ‹‹ወንጀለኛ›› የሚል ውሳኔ እስከሚሰጥባቸው ድረስ፣ እንደማንኛውም የኅብረተሰብ አካል ነፃ ሆኖ የመገመት መብት እንዳላቸው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20(3) ተደንግጎ ስለሚገኘው መብትና አስፈጻሚ አካላት ደምድመው ‹‹ወንጀለኛ›› ስለማለታቸው የተጠየቁት ወ/ሮ መዓዛ፣ ማንም ሰው ከውሳኔ በፊት ንፁህ ሆኖ የመገመት መብት እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በአሠራር ሒደት ላይ ደምድሞ የመናገር ሁኔታ መኖሩን አረጋግጠው፣ መደረግ እንደሌለበት ገልጸዋል፡፡ የሕዝብን ትኩረት የሚስቡና የሚከታተላቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ ነገሮች ሲገጥሙ ዳኞች ሕጉንና ህሊናቸውን ብቻ ተከትለው መሥራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ከፍርድ ቤት ዳኞች ጋር ውይይት በማድረግና ሥልጠናዎችንም በመስጠት ስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁመው፣ እስካሁን በተለይ እሳቸው ወደ አመራር ከመጡ ጀምሮ በቀጥታም ይሁን በማንኛውም ሁኔታ በዳኞችም ላይ ይሁን በፍርድ ቤት አመራሮች ላይ የደረሰ ተፅዕኖ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ ሕዝቡ በተቋሞች ላይ እምነት ማሳደር እንዳለበት ጠቁመው፣ ተቋማት ገና እየተገነቡ በመሆኑና ለረዥም ዓመታት እምነት አጥቶ የከረመ ተቋም በአጭር ጊዜ ውስጥ እምነት ማምጣት ስለሚያስቸግር ቀስ በቀስ እንደሚስተካከል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ መዓዛ ውይይቱን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፣ የፍርድ ቤቶችን ችግር ለመፍታት በርካታ የማሻሻያ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ ከአገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር የአሠራርና የአደረጃጀት ለውጦች ለማድረግ የሚያግዙ የሕግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተዋል፡፡ የመምራትንና የመፈጸምን አቅም የሚያጎለብቱ ትምህርትና ሥልጠናዎች፣ አስተዳደራዊ ችግሮችን ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የተለያዩ ጥናቶች መሠራታቸውን አስረድተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ተይዘው ከነበሩ ግቦች መካከል የዳኝነት ነፃነት፣ ገለልተኝነትና ተጠያቂነት በማጎልበት፣ የዳኝነት ቅልጥፍና፣ ጥራትና ተደራሽነትን ማሻሻልና ለዳኞች አቅርቦቶችን ማሟላት እንደነበሩ አስታውሰው፣ እነዚህን ግቦች ለማሳካት የሚያስፈልጉ የአደረጃጀት ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በተደረጉ ማሻሻያዎችና የአደረጃጀት ለውጦች የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሚሰጧቸው የዳኝነት አገልግሎቶች በመሻሻላቸው የመዛግብት አፈጻጸም መጨመሩን ውዝፍ መዛግብት በከፍተኛ ደረጃ መቀነሳቸው፣ በኮሮና ምክንያት የተፈጠሩ ችግሮችን በመቋቋም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዙ የተፈጠሩ የወንጀልና አጣዳፊ የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን በማስተናገድ የዳኝነት አገልግሎት እንዳይቋረጥ መደረጉን በምሳሌነት ጠቁመዋል፡፡

በጠቅላይ ፍርድ ቤት 15,576፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት 17,049 እና በመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት 100,834 በአጠቃላይ 133,459 መዛግብቶች ዕልባት ማግኘታቸውን ወ/ሮ መዓዛ ተናግረዋል፡፡ ይህም በበጀት ዓመቱ የሥራ አፈጻጸማቸውን 98.2 በመቶ ማከናወን መቻሉን አክለዋል፡፡

ሌላው ወ/ሮ መዓዛ በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ሥራዎች ውስጥ ከፍተኛ ስኬት ነው ያሉት የፍርድ ቤቶች በጀት በቀጥታ እንዲመደብላቸው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ማፀደቅን ነው፡፡ በመሆኑም በ2009 በጀት ዓመት 74 ሚሊዮን ብር፣ በ2010 እና 2011 በጀት ዓመቶች ከነበረው 98 ሚሊዮን ብር በላቀ ሁኔታ በ2012 በጀት ዓመት 138 ሚሊዮን ብር በማድረስ 40 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ሥራዎች ውስጥ የጾታ ጥቃቶች መኖራቸውን ጠቁመው፣ በ302 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህ ውሳኔዎች ውስጥ 44ቱ በኮሮና ወቅት የተሰጡ ውሳኔዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ምንጭ፡- ሪፖርተር
@lawsocieties @lawsocieties
የ ቀበሌ ቤቶችን ስለመውረስ የሚያወራ ድንጋጌ pdf klhe lakelgn
መመሪያ memann kalh
“በፍ/ቤት ማሻሻያ ስራዎች ትኩረት ከሚሰጥባቸው ስራዎች መካከል አንዱ የዳኞችን ዓቅም በዕውቀትና በክህሎት ማሳደግ ነው” ሲሉ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ገለጹ፡፡

ክብርት ፕሬዝደንቷ ይህን የገለጹት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የስድስት ቀን ስልጠና መርሃ ግብር ለመክፈት ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ዳኞች በየጊዜው በህግ አውጪው አካል የሚወጡ አዲስ ህጎችን ወይም ማሻሻያዎችን ተረድተው የመተርጎም መሰረታዊ ክህሎት አላቸው ያሉት ክብርት ፕሬዝደንቷ፤ አንዳንድ ህጎች ዓለም ዓቀፍ እንድምታ ያላቸው እና እያደጉ የሚሄዱ የህብረተሰቡን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስተጋብሮችን የሚነኩ በመሆኑ በህጎቹ ዙሪያ መነጋገር እና ሃሳብን ማዳበር አስፈላጊ መሆኑን በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡

ነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም የጀመረው የስልጠና መርሃ-ግብር የኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ካወጣቸው ህጎች መካከል የተሻሻለው የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1176/2012፤ የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012፤ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጨትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1185/2012 እና ምክር ቤቱ ዓለምአቀፍ ስምምነቶችን በማጽደቅ ስልጣኑ መሰረት የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች እውቅና የመስጠት እና የመፈጸም ስምምነት (New York Convention) ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር 1184/2012 ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ስልጠናው ዳኞች በአዋጆቹ ላይ ወሰረታዊና ወጥ የሆነ ግንዛቤን በመጨበጥ ለዳኝነት በሚቀርቡላቸው ተመሳሳይና ተቀራራቢ ጉዳዮች ላይ ተገማች ዳኝነት መስጠት የሚያስችላቸውን አቅም መፍጠር ዓላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በስልጠናው መጀመሪያ ቀን የጥላቻ ንግግርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ ዓዋጅን በማርቀቅና ግብአት በመስጠት ሂደት ተሳትፎ ያደረጉት አቶ ሰለሞን ጎሹ የዓዋጁን ዓላማ፣ አስፈላጊነት፤ አመክንዮ እና በማርቀቅ ሂደት በተካሄዱ የውይይት መድረኮች የተሳታዎችን ግብረመልስ ይዘት አብራርተዋል፡፡

የስልጠናው ዘዴ የአዋጁን ይዘትና መነሻ ሃሳብን በገለጻ እንዲሁም በመወያያ ጥያቄዎች ላይ የቡድን የሃሳብ ልውውጥ ማካሄድ ሲሆን በየስልጠና ርዕሱ የሚሳተፉ ዳኞች ተዛማጅ ጉዳዮችን በሚያዩ ችሎቶች ተመድበው የሚሰሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በስድስቱ ቀን ስልጠና በአጠቃላይ 200 የሚሆኑ ዳኞች እንደሚሳተፉ ስልጠናውን ከሚያስተባብረው ከፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
የፍ/ቤቱን ሴት ሰራተኞች ማብቃትና ሃላፊነታቸዉን በብቃት መወጣት የሚያስችሉ ድጋፎችን ማመቻቸት እንዲሁም ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር አስፈላጊነት ተጠቆመ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፍ/ቤቱን ሴቶች ባለሙያዎች ማብቃትና ኃላፊነታቸዉን በከፍተኛ ብቃት እንዲወጡ የሚያስችል አሰራሮችን ለማመቻቸት ከሴት ዳይሬክተሮች፣ የቡድን መሪዎች፣ ከፍተኛ ባለሙያዎች እና የፅዳት ሰራተኛ ተወካዬች ጋር ነሐሴ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ዉይይት አድርገዋል፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የሚገኙ ሴት ባለሙያዎችን አቅም በማጠናከርና ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር ፍርድ ቤቱን የተሻለ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በማድረግ በተገልጋይ ዘንድ መልካም ገፅታ ለመፍጠር በጋራ መስራት ይገባል ያሉት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ውይይቱ ያሉንን ሃብቶች በአግባቡ በመጠበቅና በመጠቀም ለቀጣጥ ትዉልድ የሚተርፍ ስራ ለመስራት በአስተሳሰብ የተቀየረ ማህበረሰብ በፍርድ ቤታችን የመፍጠር ዓላማ ያነገበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአዲሱ የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 ላይ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በፌደራል ደኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት ከሶስቱም ፍርድ ቤቶች ለተዉጣጡ 50 ለሚሆኑ ዳኞች የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 ዙሪያ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሽብርተኝነት በአለም አቀፍ ደረጃ ስላለው ሁኔታ ላይ ስልጠናዉን ከአዉስትራሊያ በበይነ መረብ (Virtual Training) አማካኝነት የሰጡት ዶ/ር ወንድወሰን ደምሴ ሲሆኑ በስልጠናቸዉም የሽብርተኝነት በተለያዩ ግዜያቶች የነበረው ባህሪ እና መንግስታት ሲወስዱት የነበረውን የሕግ እርምጃ ያቀረቡበት ነው፡፡ በተለይም የጸረ-ሽብር እርምጃን ከሰብአዊ መብት አጠባበቅ ጋር በተያያዘ ያሉትን ሁኔታዎ ሰፋ ባለ መልኩ አስቀምጠዋል፡፡
ስልጠናውን በመቀጠል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አመሀ መኮንን አዲሱ አዋጅ ማውጣት ያስፈለገበት ምክንያቶች፣ በረቂቅ ሂደቱ ላይ ታሳቢ የሆኑ ጉዳዮችን በገለጻቸው አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም ህጉ ቀድሞ ከነበረው የጸረ-ሽብር ህግ የሚለይባቸውን ጉዳዮች ፣ የሽብር ወንጀል እና ተያያዥ የወንጀል ድርጊቶችን ገልጸዋል፡፡
በዚሁ በጠዋቱ የስልጠና መድረክ ላይ ሕጉን በማርቀቁ ሂደት ላይ ተሳትፎ የነበራቸው አቶ ደሞዝ አማን ድርጅትን በሽብርተኝነት ስለመሰየም የሚመለከቱ የአዋጁ ክፍል እና አንቀጾች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በከሰዓቱ መርሃ ግብርም በዚሁ ርዐሰ ጉዳይ ላይ በተሳታፊዎች በሚደረግ የቡድን ዉይይት የሚቀጥል ሆኖ በነገው እለትም በአዋጁ በተለያዩ ክፍሎች ላይ ስልጠናው የሚቀጥል ይሆናል፡፡
Federal Judicial Administration Council Secretariat
Please criminal code ena le criminal course yemiredu materialoch kalu lakulgn
Attorney
#visionfund_micro_finance
#legal_services
#law
#attorney
Oromia, Shashemene
Diploma in law & with relevant work experience in law
Local language knowledge, communication skill & computer skill is advantageous.
Minimum Years Of Experience: #2_years
Deadline: September 8, 2020
How To Apply: Send your resume through: VFE_vacancy@wvi.org or in person to Shashemene Branch & South West area Operations Office

via @Ethiopian_Legal_Advocate
የፍ/ቤቱን ሴት ሰራተኞች ማብቃትና ሃላፊነታቸዉን በብቃት መወጣት የሚያስችሉ ድጋፎችን ማመቻቸት እንዲሁም ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር አስፈላጊነት ተጠቆመ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፍ/ቤቱን ሴቶች ባለሙያዎች ማብቃትና ኃላፊነታቸዉን በከፍተኛ ብቃት እንዲወጡ የሚያስችል አሰራሮችን ለማመቻቸት ከሴት ዳይሬክተሮች፣ የቡድን መሪዎች፣ ከፍተኛ ባለሙያዎች እና የፅዳት ሰራተኛ ተወካዬች ጋር ነሐሴ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ዉይይት አድርገዋል፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የሚገኙ ሴት ባለሙያዎችን አቅም በማጠናከርና ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር ፍርድ ቤቱን የተሻለ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በማድረግ በተገልጋይ ዘንድ መልካም ገፅታ ለመፍጠር በጋራ መስራት ይገባል ያሉት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ውይይቱ ያሉንን ሃብቶች በአግባቡ በመጠበቅና በመጠቀም ለቀጣጥ ትዉልድ የሚተርፍ ስራ ለመስራት በአስተሳሰብ የተቀየረ ማህበረሰብ በፍርድ ቤታችን የመፍጠር ዓላማ ያነገበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=1878900975593299&id=265784033571676
5ኛው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
LabourLawcomparison.pdf
417.1 KB
በቀድሞ አሠሪና ሠራተኛ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 377/1996) እና በአዲሱ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1156/2011) መካከል የተደረጉ ማሻሻያዎችን ወይም እንደአዲስ የተጨመሩትን የሚያሳይ ሰንጠረዥ
የተዘጋጀው፡ በእሥራኤል በጋሻው
የፌ.መ.ደ.ፍ.ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የአድራሻ ለውጥ ስለማሳወቅ
****************************************************
የፌ.መ.ደ.ፍ.ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀድሞ ለረጅም ዓመታት ለዳኝነትና አስተዳራዊ ስራዎች ምቹ ባልሆነና በተከፋፈለ በሁለት ቦታዎች ማለትም ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ፅ/ቤት አጠገብ እንዲሁም ፒያሳ ብሪቲሽ ህንፃ ላይ የዳኝነት አገልግሎት ሲሰጥ ከነበረበት ከጳግሜ 1/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከጊዮርጊስ አደባባይ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ከሶራምባ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው አዲሱ ህንፃ በመግባት የዳኝነት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ለክቡራን የፍርድ ቤታችን ተገልጋዮች እናሳውቃለን፡፡
ፍርድ ቤቱ
Hi ALE do you have info about Federal justice professional traning entrance exam date
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ 5ኛ ዓመታዊ ጉባዔ የአቋም መግለጫ
****************************
ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ በፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ 25/88 ከአንቀጽ 31-34 በተደነገገው መሰረት የተቋቋመና በዳኝነት ሥራ አስተዳደር ረገድ በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ ተወያይቶ መፍትሔ የመስጠት፤ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አሰራርን ለማሻሻል የሚረዱ መመሪያዎችና ውሳኔዎችን የማሳለፍ፤ አዳዲስ ሕጎች እንዲወጡ ወይም ነባር ሕጎች እንዲሻሻሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሃሰብ የማቅረብ፤ የዳኝነት ስራ አካሄድን ለማቀላጠፍና ለማጠናከር የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን የማከናውን እና ለጉባዔው ስራ አፈጻጸም አስፈላጊውን ደንብ የማውጣት ስልጣንና ተግባር የተሰጠው ጉባዔ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ 5ኛውን ዓመታዊ ጉባዔ ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች ተቋማዊና ዳኝነታዊ ነጻነት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
ጉባዔው ባካሄደው ውይይት የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች በነጻነትና በገለልተኝነት ዳኝነት የመስጠት ህገመንግስታዊ ሃላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት መሆናቸው በውይይቱ ተገልጿል፡፡ የዳኝነት ተጠያቂነት የዳኝነት ነጻነት ዋስትና መሆኑንም ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ነው፡፡ በሃገራችን ከመጣው የለውጥ እንቅስቃሴ በኋላ በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቀሴዎች መኖራቸውንና የተወሰኑትም ቢሆኑ ተግባራዊ መሆን መጀመራቸውን መገንዘብ ተችሏል፡፡
የዳኝነት ነጻነትን ለማረጋገጥ ከተሰሩ ስራዎች መካከልም የፍርድ ቤቶች አደረጃጀትና የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አዋጆችን የማሻሻል ስራዎች በሂደት ላይ መሆናቸው፤ በዚህም አስተዳደራዊ እና የበጀት ነጻነት መጎናጸፍ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች መካተታቸው፤ እንዲሁም የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነት ለማስጠበቅም ያለመከሰስ መብት የህግ ድጋፍ እንዲኖረው መደረጉ፤ ከዚህ ጎን ለጎን የዳኝነት ነጻነት ዋስትና የሆነው የዳንነት ተጠያቂነት ስርዓት መዘርጋት የሚያስችሉ አንቀጾች እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነት ከሚያስጠብቁ ጉዳዮች መካከልም በፌዴራልና በተወሰኑ ክልሎች የደሞዝ ማሻሻያ መደረጉ፡፡ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ መደረጉ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲጠበቁላቸው ጥረቶች መደረጉ ታይቷል፡፡
ይሁን እንጂ ዳኞች ከህግ አውጪውም ሆነ ከአስፈጻሚው አካል ሊደርስ ከሚችል ተጽእኖ ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸው ውሳኔዎችም መከበርና መፈጻም አለባቸው፡፡ ዳኞች ከሚሰጣቸው ውሳኔዎች ጋር ተያይዞ ከማንኛውም ስጋት ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር በአንዳንድ ክልሎች ፍርድ ቤቶች የበጀት፤ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ከማስተዳደር አንጻር ችግሮች ያሉባቸው መሆኑ ተነስቷል፡፡ በምክር ቤቱ የተፈቀደ በጀትን የመከልከል ችግሮችም እንዳሉ ተነግሯል፡፡ በተወሰኑ ክልሎች ደግሞ በበጀት እጥረት ምክንያት የደሞዝ ማሻሻያ አለመደረጉ እና ተመጣጣኝ ክፍያ መርህን ያልተከተለ የደሞዝ ማስተካከያ መደረጉም ከተነሱ ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ከዳኞች ግለሰባዊ ነጻነት ጋርም ተያይዞ በተወሰኑ ክልሎች ዳኞች በሰጡት ውሳኔ በፖሊስ የመታሰር፤ ባልታወቁ ሰዎች የመደብደብ፤ በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ ተኩስ በመክፈት ጫና ለማሳደር መሞከር፤ በማህበራዊ ሚዲያ ዳኞች ከህግ ውጪ እንዲወስኑ በተለያዩ ግለሰቦችና ኢ-መደበኛ ቡድኖች ጫና ማሳደር እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ተስተውለዋል፡፡ እነዚህን በፈጸሙ ግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ምርመራ አድርጎ ወደ ህግ በማቅረብ በኩል ክፍተቶች ታይተዋል፡፡
በተጨማሪም ቁጥጥር ሊደረግባቸው የማይችሉ ሚዲያዎች የሚያሰራጯቸው አሉታዊ ይዘት ያላቸው መረጃዎች በፍርድ ቤትና በዳኞች ላይ ተጽዕኖ መፍጠራቸውም እንደዚሁ ተጠቁሟል፡፡
ከዚህ በመነሳት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ 5ኛ ዓመታዊ ጉባዔ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ በማውጣትም ስብሰባውን አጠናቋል፡፡
1. የዳኝነት ነጻነት መኖር በህግ ማዕቀፍ ብቻ የሚረጋገጥ ባለመሆኑ የዳኝነት ነጻነት መከበር በተግባርም ጭምር መታየት ይኖርበታል፡፡ ለዚህም የህግ አውጪውም ሆነ የአስፈጻሚው አካል በህገ መንግስትና ተያያዥ ህጎች መሰረት ለዳኝነት ነጻነት መረጋገጥ እና አገልግሎት መሻሻል አስቻይ የሆነ በጀት የሃገሪቱ አቅም በሚፈቅደው መጠን መመደብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. የዳኝነት ነፃነትን ማስጠበቅ በዋነኝነት የዳኞች ኃላፊነት ቢሆንም የመንግስት አስፋፃሚ አካል፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ ሲቪል ማህበራት እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት፤ የህግ የበላይነትን ለማስከበርና የመንግስትን ቀጠይነት ለማረጋገጥ እንዲያስችል የዳኝነት ነጻነት እንዲከበር የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡
3. የዳኝነት ነጻነት በዳኞች የሚሰጡ ውሳኔዎች በህገመንግስቱ ከተቋቋመ የመንግስት ተቋም የሚሰጡ ውሳኔዎች በመሆናቸው ትእዛዛቸውና ውሳኔያቸው መከበርን ግድ ይላል፡፡ የዳኝነት ነጻነትን የተመለከቱ የህግ ማዕቀፎች መኖር አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የመንግስት አካላትን ጨምሮ ሌሎች ወገኖች በፍርድ ቤት የሚሰጡ ውሳኔዎችን በማንኛውም አካል ምርመራ ሳይደረግባቸውና ሳይሸራረፉ ማክበር እና ተግባራዊ ማድረግም ይኖርባቸዋል፡፡
4. በህገመንግስታችን መግቢያ እንደተገለጸው በሃገራችን አንድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመመስረት የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች ወሳኝ ድልድዮች ናቸው፡፡ በስራ ረገድም በበርካታ ሁኔታዎች ይገናኛሉ፡፡ የሚመሩበት የሙያ መርህና የስራ ባህሪያቸውም እጅግ ተመሳሳይ በመሆኑ የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ፓኬጆች ምክንያታዊና ነባራዊ ሁኔታውን ከግምት ያስገባ እንዲሆኑ አመራሩ በቀጣይነት በልዩ ትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ ይሆናል፡፡
5. የዳኝነት እና የዳኞች ነጻነት የህግ የበላይነት ቁልፍ ማዕዘን ነው፡፡ በየትኛውም ቦታ የሚያገለግሉ ዳኞች የስራ ነጸነት መከበር አለበት፡፡ በዚህ ረገድ ዳኞች ሁሉ በጋራ መቆምና ሙያዊ መደጋገፍን ማሳየት ሃላፊነታችን ነው፡፡ የዳኞች በባለጉዳይም ሆነ በመንግስት አካላት መደፈር በፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ መንግስት የዳኝነት ነጻነትን ለማረጋገጥ ያለውን ፍላጎትና ቀርጠኝት በተለያየ ሁኔታ ቢያሳይም በመንግስት የታችኛው መዋቅር ያሉ ግሰቦች የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባልተገባ መንገድ በመጠቀም በዳኝነት ነጻነት ላይ የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተጽእኖ በጋራ የምንታገለው ይሆናል፡፡ መንግስትም በህግ የበላይነት መከበር ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየተስፋፉ እንዳይሄዱ ከላይ በተጠቀሱትና መሰል ተግባራት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን ምርመራ በማድረግ ለይቶ ወደ ህግ በማቅረብ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡
👍1
6. የዳኝነት ተጠያቂነት የዳኝነት ነጻነት ዋስትና ነው፡፡ ዳኞች ስህተት ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ውሳኔያቸው በይግባኝ ሊሻር ይችላል፡፡ ከዚህ አልፎ የተሰጣቸውን የዳኝነት ስልጣን ባልተገባ መልኩ በመጠቀም የዲሲፕሊን ጥፋት የሚፈጽሙ ዳኞች ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት አለ፡፡ የዳኝነት ነጻነትን ሚዛን መጠበቅ የሚያስችል የተጠያቂነት ስርዓት መዘርጋት በፍርድ ቤቶች በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም በአንድ ሃሳብ የተቀበልነው ጉዳይ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ደረጃንና መስፈርትን የጠበቀ የዳኝነት ተጠያቂነት ስርዓት ለመዘርጋት የጀመርናቸውን ጥረቶች አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፡፡
7. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያስከተለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ይታወቃል፡፡ መንግስት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚወስዳቸው ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በፍርድ ቤቶች በኩል ወረርሽኙ ያለመገታቱን በመገንዘብ የተጀመሩትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መቀጠል ይኖርብናል፡፡
8. ጉባዔው የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት አሰራር ለማሻሻል የሚረዱ መመሪያዎችና ውሳኔዎችን እንዲያሳልፍ የተሰጠውን ስልጣን ተግባራዊ ለማድግ በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች ያሉትን የጋራ ችግር በመለየትና ምክረ ሃሳብ በማቅረብ ድጋፍ የሚያደርግ ኮሚቴ ተቋቁመዋል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ
5ኛ ዓመታዊ ጉባዔ
ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም.
Hi ale is there any new info about exit exam of 2012 years graduation
Hi endat nachehu sil exist exam addis neger lemaggnet tirt bitadergu.....
ALE (Alternative Legal Education) All in one, All Law Societies. federal & regional Judges, Prosecutors, Advocates, consultants & law school heads, instructors, deans, Law graduates, Students & other NGO and PLC employees..
etc.

Contact Us Via @Alemwaza
https://t.me/lawsocieties