አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በክርክርና በቀጠሮ ላይ ያሉ የክስ መዛግብት ለሚቀጥለው ዓመት እንዲቀጠሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ

 

ምንጭ: ሪፖርተር ጋዜጣ

በዳኝነት ነፃነት ላይ ጣልቃ መግባት እንዳይሆን ተሠግቷል

የፍትሐ ብሔር ውሳኔዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጽ እንዳይገለጹ ታገደ

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ከሚታዩ የክስ መዝገቦች ውስጥ በክርክርና በቀጠሮ ላይ ያሉ መዛግብት፣ ከመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ ባሉት ጊዜያት እንዲቀጠሩ ለየምድብ ችሎቶቹ ማሳሰቢያ መሰጠቱ ተጠቆመ፡፡ ማሳሰቢያው የተሰጠው በፍርድ ቤቱ አመራሮች በመሆኑ፣ በዳኝነት ነፃነት ላይ ጣልቃ መግባት እንዳይሆን የሕግ ባለሙያዎች ሥጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ በክርክር ላይ ያሉ ወይም ክርክራቸው የተወሰነ ጊዜ የሚወስድ መዛግብት ለቀጣዩ ዓመት ከመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ እንዲቀጠሩ አመራሩ የገለጸ ቢሆንም፣ የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ያለው ሥርጭት ከተቃለለ፣ የቀጠሮ ጊዜ ተሰብሮ በነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም. ሊሠራ እንደሚችልም አማራጭ ሐሳብ አስቀምጧል፡፡

የፍርድ ቤቱ አመራር ያስተላለፈውን ማሳሰቢያ በሚመለከት አስተያየታቸውን የሚሰጡ የሕግ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ አመራሩ የሰጠውን ማሳሰቢያ በሁለት ከፍለውታል፡፡ የመጀመርያው ከተከሳሹ የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብት አንፃር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሠራጭቶ ከሚገኘው ኮሮና ቫይረስ አደገኛ ሁኔታ አንፃር ነው፡፡ በእስር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ቤተሰቦችና ሌላ የችሎት ታዳሚዎች በሌሉበት ርቀታቸውን በጠበቀ ሁኔታ ክርክር በማድረግ አንድ ደረጃ ላይ መድረስ እየቻሉ፣ ሙሉ በሙሉ መከልከል ግን የመብት ጥሰት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል የፍርድ ቤቱ አመራር በወረርሽኙ ይከሰታል ብሎ የሚሠጋበትን ጉዳት የሚያሳይ በመሆኑ፣ ማሳሰቢያው ተገቢ መሆኑንም የሚደግፉ የሕግ ባለሙያዎች አሉ፡፡ በሌላ በኩል አንድ ዳኛ በያዘው መዝገብ ላይ የመወሰንና የማዘዝ ሥልጣኑ የዳኛው ሆኖ ሳለ፣ ‹‹ይህንን አድርግ›› ማለት በዳኝነት ነፃነት ላይ ጣልቃ መግባት በመሆኑ እንዳሳሰባቸውም ገልጸዋል፡፡

የሕግ ባለሙያዎቹ ከመብት ጥሰትና በዳኞች ነፃነት ላይ ጣልቃ መግባት ላይ ባነሱት ጥያቄ፣ ፍርድ ቤቱ የክርክርና የቀጠሮ መዛግብትን ከመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ ለምን መቅጠር እንደፈለገ ምላሽ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ መስቀል ዋጋሪ፣ ፍርድ ቤት አልተዘጋም ብለዋል፡፡ ‹‹ሕዝብ ፍትሕ ማግኘት አለበት፡፡ ፍትሕ እንደ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ውኃና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች ነው፡፡ ነገር ግን ዓለም አቀፉ ኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያም በመከሰቱ፣ የሕዝብ መሰባሰብን ማለትም ችሎት ለመከታተል፣ ዋስ ለመሆን፣ ለዋስትና ያስያዙትን ገንዘብ ለመውሰድ፣ የውሳኔ ግልባጭ ለመውሰድና ለሌሎች ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት የሚመጣውን ማኅበረሰብ ለማስቀረት ፍርድ ቤት በከፊል እንዲዘጋ ተደርጓል፤›› ብለዋል፡፡

ለወረርሽኙ መስፋፊያ ከሆኑት ምክንያቶች አንዱ መሰባሰብ በመሆኑ፣ ያንን ለማስቀረትና የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለው አክለዋል፡፡ በጣም አስፈላጊና አስቸኳይ የሆኑ የወንጀልም ሆነ የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች በተረኛ ችሎቶች እንደሚታዩ ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡ የወንጀል ክስ ኖሮባቸው በማረሚያ ቤት ያሉ ተጠርጣሪ ታሳሪዎች ጉዳይ ባሉበት ቦታ በቴሌ ኮንፈረንስ ለማከራከር ዝግጅቶች እየተሟሉ መሆኑን፣ አቶ ብርሃነ መስቀል ተናግረዋል፡፡ እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ፍርድ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የሚዘጉበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ መታሰብ ያለበት ግን ሲከፈት ምን ያህል ባለጉዳይ ፍርድ ቤቶችን ሊያጥለቀልቅ እንደሚችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ፍርድ ቤቶቹ ሙሉ በሙሉ ሳይዘጉ እንዴት መቀጠል እንዳለባቸው ከችሎት አስተባባሪ ዳኞች ጋር በተደረገ ውይይት አንድ የውሳኔ  ሐሳብ ላይ መደረሱን ጠቁመው፣ የችሎት አስተባባሪ ዳኞች ከችሎት ዳኞች ጋር በመወያየትና የዳኞቹን ውሳኔ በማወቅ፣ ችሎቶች ሳይሠሩ የሚቀጥሉበትን ማመቻቸት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የችሎት ዳኞችን ባገኙት መገናኛ ዘዴ ያነጋገሩት የችሎት አስተባባሪዎች ያገኙት ምላሽ፣ ሰኔ መጨረሻና ሐምሌ መጀመርያ አካባቢ ወረርሽኙ በስፋት ይሠራጫል የሚል ሥጋት ስላለ፣ እስከዚያው ድረስ የክርክርና የቀጠሮ መዝገቦችን ረዘም አድርጎ በመቅጠር ጊዜው በሰላም ካለፈ፣ ነሐሴ 2012 ዓ.ም. እና መስከረም ወር 2013 ዓ.ም. ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የሚያዩዋቸው ጉዳዮች ከባድና ትልልቅ በመሆናቸው፣ እንዲሁም ዳኞቹ ከፍተኛ የሆነ ልምድ ያላቸው ስለሆኑ እነሱ ያልመከሩበት ውሳኔ ሊተላለፍ እንደማይችል የገለጹት አቶ ብርሃነ መስቀል፣ አንድ ዳኛን እንኳን ‹‹ይህን መዝገብ ሥራ፣ ያንን መዝገብ ተው›› ብሎ ጣልቃ በመግባትና ማዘዝ ቀርቶ ስለያዘው መዝገብ እንኳን ማንሳት እንደማይቻል አስታውቀዋል፡፡ ማንም አካል በዳኝነት ነፃነት ላይ ሊገባ እንደማይችልም አክለዋል፡፡

የፍርድ ቤቱ አመራር ባደረገው ውይይት የደረሰበት ስምምነት፣ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅ ጋር ተያይዞ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚቀርቡ ጉዳዮችን የማየት ሥልጣን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑን የፍርድ ቤቱ አመራሮች ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የተረኛ ችሎት ዳኞችን ቁጥር በመጨመር በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም በሌሎች መዝገቦች ማለትም ለውሳኔ፣ ለብይንና ለትዕዛዝ የተቀጠሩ በርካታ የወንጀል መዛግብትና ውስን የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን ሥራ ማቃለል እንደሆነም በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

የፍርድ ቤቱ አመራር ሌላው ያስተላለፈው ሐሳብ፣ ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ ከተደረገ በኋላ የፍትሐ ብሔር የውሳኔ መዝገቦች በፍርድ ቤቱ ማኅበራዊ የትስስር ገጽ ላይ እንዲወጡ የተወሰነ ቢሆንም፣ አመራሩ እንዲቆም ወስኗል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተወሰነበት ወገን በወቅቱ ይግባኝ ማለት ስለማይችልና የፍርዱን ግልባጭ ማግኘት ስለሚቸገር፣ ሁሉም ሰው ማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ማግኘት ስለማይችል፣ የተወሰነለትም በወረርሽኙ ምክንያት ማስፈጸም ስለማይችል መታገዱን አቶ ብርሃነ መስቀል አስረድተዋል፡፡

ውሳኔ ያረፈባቸው መዛግብት በዳኞች እጅ በመሆናቸው ሰብስቦ ወደ መረጃ ቋት (ዳታ) ማስገባትም ስለማይቻል መሆኑን፣ በርካታ ምክንያቶች እንዳሉም አክለዋል፡፡ ነገር ግን በልዩ ሁኔታ የልጅ፣ የቤተሰብ ቀለብ፣ የአሠሪና የሠራተኛ ጉዳይ፣ የጉዳት ካሳ፣ የሜጋ ፕሮጀክቶች፣ የንግድና ኢንቨስትመንት፣ በአጠቃላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አንድምታ ያላቸው ጉዳዮችና አስቸኳይ ጉዳዮች ከሆኑ ሊታዩ እንደሚችሉ የፍርድ ቤቱ አመራር ስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡

በማረሚያ ቤት ሆነው የጥፋተኝነት ፍርድም ሆነ ወይም የቅጣት ውሳኔ፣ በነፃ የሚለቀቁ ወይም እንዲከላከሉ ብይን የመሥራት ሥራ በሚገባ እንዲሠራና ውጤቱ እንዲነገራቸውም አመራሩ ተስማምቷል፡፡ በክርክር ሒደት ላይ ያሉት ደግሞ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ክርክር እንዲያደርጉና ፍትሕ እንዲያገኙ ለማድረግ አመራሩ ተስማምቷል፡፡ ስምምነቱ በቂሊንጦ፣ ቃሊቲ፣ ድሬዳዋና በክልል ያሉ ተዘዋዋሪ ችሎቶችን ያካተተ ነው፡፡ ከማረሚያ ቤት ውጪ በዋስትና ያሉ መደበኛ ችሎቶች እስከሚጀምሩ ድረስ ባሉበት እንደሚቆዩም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ መዛግብት በትብብር ተሠርተው እንዲጠናቀቁ፣ ለግንቦት ወር 2012 ዓ
.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበሩ በከፊል ዝግ መሆኑን ያልሰሙ ባለጉዳዮችን፣ ዳኞች ከቻሉና ከፈለጉ ርቀታቸውን ጠብቀው ፍርዱን መንገር እንደሚችሉም ሐሳብ ሰጥተዋል፡፡ የዋስትና ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ በሚመለከት በጣም የተቸገሩ ከሆነ እንደ ሁኔታው ዳኞች በሚሰጡት ትዕዛዝ እንዲፈጸምላቸው ተስማምተዋል፡፡ የየራሳቸውን ውዝፍ መዝገብ ሠርተው ያጠናቀቁ ዳኞች በፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ፊት ዕውቅና እንደሚሰጣቸው፣ ያላጠናቀቁ ደግሞ የየራሳቸው ምክንያት ስለሚኖራቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ አመራሩ መስማማቱ ታውቋል፡፡

Ethiopian Legal Brief

A BLOG ABOUT ETHIOPIAN LAW

https://telegram.me/lawsocieties
ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች በሙሉ
________
የጥብቅና ፈቃድ በኦንላየን/online/ማደስ እንድትችሉ የኢ-አገልግሎት የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ስራ የገባን በመሆኑ የአጠቃቀም መመሪያውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከታች የተመለከተውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ


shorturl.at/nJ048


https://telegram.me/lawsocieties
Never cease to do this! Your heart❤️ is the essence of your existence, listen to it, cherish it and protect It!❤️

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!!

via Christina Mishell:
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ጊዜያቶች በንፋስ ስልክ ለፍቶ ምድብ ችሎት የተሰጡ ውሣኔዎች ከፊል መግለጫ

************************************************************

1. መ.ቁ 161652 ……….. ተከሳሽ ኃላፊነት የለም ተብሎ ተወሰነ፡፡

2. መ.ቁ 162380 ……….. ስንብቱ ሕጋዊ ነው፣ ተከሳሽ ለከሳሽ የ11 ቀን ደሞዝ፣

የ62 ቀን የአመት ዕረፍት ክፍያና 1500.00 ኪሳራ

ይክፈል፣ የስራ ምስክር ወረቀት ይስጥ ተብሎ ተወሰነ፡፡

3. መ.ቁ157065 ……….. በተከሣሽ የተፈፀመ ሕገወጥ ድርጊት የለም፡፡

የአገልግሎት የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ

ለከሣሾች እንዲከፈለ ተወሰነ፡፡

4. መ.ቁ149066 ……….. ስንብቱ ሕገወጥ ስለሆነ ተከሳሽ ለከሳሽ የሁለት ወር

የማስጠንቀቂያ ጊዜና የካሳ ክፍያ እንዲከፍል ተወሰነ፡፡

5. መ.ቁ163948 ……….. ስንብቱ ሕጋዊ ነው፣ ተከሳሽ ለከሳሽ የሁለት ወር

የማስጠንቀቂያ ጊዜ፣ የአገለግሎት የአመት ዕረፍት ክፍያ

እንዲከፍል ተወሰነ፡፡

6. መ.ቁ161318 ……….. ለከሳሽ የሚከፈል ክፍያ የለም ተብሎ ተወሰነ፡፡

7. መ.ቁ160779 ……….. የከሳሾች የዳኝነት ጥያቄ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ

ተደረገ፡፡

8. መ.ቁ163057 ……….. የከሳሽ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ የዚህ ፍ/:ት ስልጣን አይደለም፣

የቦነስ ጥያቄ በይርጋ ውድቅ ተደረገ፣ ከሳሽ 1000 ኪሳራ

ለተከሳሽ ይክፈል ተብሎ ተወሰነ፡፡

9. መ.ቁ163115 ……….. አደጋው በከሳሽ ምክንያት አልደረሰም፣ ጣልቃ ገብ ካሳ

ስለከፈለ በድጋሚ ተከሳሽ ሊከፍል አይገባም፣ ለህክምና እና

ለመድሀኒት ተከሣሽ ለከሳሽ 15000.00 ይክፈለው ተብሎ

ተወሰነ፡፡

10. መ.ቁ152984 ……….. ሕገወጥ ስንብት የለም ተብሎ ለተከሰሽ ተወሰነ፡፡

11. መ.ቁ154966 ……….. የስራ ውሉ የተቋረጠው በሕጋዊ መንገድ ነው ተብሎ ተወሰነ፡፡

12. መ.ቁ162127 ……….. የስራ ውሉ የተቋረጠው በሕገወጥ መንገድ ነው፣ የወር ደሞዝ

8500፣ የአግልግሎት፣ የማስጠንቀቂያ፣ የሁለት ወር ደሞዝና የካሳ ክፍያ ለከሳሽ ይከፈለው ተብሎ ተወሰነ፡፡

13. መ.ቁ163046 ……….. ስንብቱ ሕጋዊ ስለTነ የሚከፈል ክፍያ የለም ተብሎ ተወሰነ፡፡

14. መ.ቁ163286 ……….. ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም ተብሎ ተዘጋ፡፡

15. መ.ቁ163781 ……….. የሚፈፀም ፍርድ የለም ተብሎ ተዘጋ፡፡ስንብቱ ሕጋዊ ስለሆነ

የሚከፈል ክፍያ የለም፡፡

16. መ.ቁ160838 ……….. ሕገ ወጥ የስራ ውል መቋረጥ አልተደረገም፣ የከሳሾች የአመት

ዕረፍት በገንዘብ ተለውጦ እንዲከፈላቸው ተወሰነ፡፡

17. መ.ቁ100885 ……….. 245870.00 ተከሳሽ ለከሳሽ ከ9% ወለድ ጋር እንዲከፍል

ተወሰነ፡፡

18. መ.ቁ130629 ……….. ወጪና ኪሳራ ለከሳሽ ተወሰነ፡፡

19. መ.ቁ149428 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

20. መ.ቁ160338 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

21. መ.ቁ108882 ……….. አመልካች የቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ ውድቅ ተደርጓል፡፡

22. መ.ቁ164086 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

23. መ.ቁ47163 ……….. ለከሳሽ በከፊል ተወስኗል፡፡

24. መ.ቁ163771 ……….. አመልካቾች በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

25. መ.ቁ163356 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

26. መ.ቁ115972 ……….. ተከሳሽ የቀረቡት የዳግም ዳኝነት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡

27. መ.ቁ157525 ……….. የከሳሽ የሞግዚትነት ማስረጃ በፍ/:ት የታገደ ስለሆነ መዝገቡ

ተዘጋ፡፡

28. መ.ቁ158450 ……….. በድጋሚ የቀረበ ክስ ስለሆነ በብይን ተዘጋ፡፡

29. መ.ቁ153958 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

30. መ.ቁ157995 ……….. ፍርድ :ቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም ተብሎ ተዘጋ፡፡

31. መ.ቁ163133 ……….. ክሱ በይርጋ ታግዷል ተብሎ ተዘጋ፡፡

32. መ.ቁ162014 ……….. የአመልካቾች የክልከላ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡

33. መ.ቁ157809 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

34. መ.ቁ156037 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

35. መ.ቁ134072 ……….. የንብረት ክፍፍል ውሣኔ ተሰጠ፡፡

36. መ.ቁ150205 ……….. የልጅነት ውሣኔ ተሰጠ፡፡

37. መ.ቁ162732 ……….. የፍቺ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

38. መ.ቁ163737 ……….. የቀለብ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

39. መ.ቁ163080 ……….. የፍቺ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

40. መ.ቁ159116 ……….. የልጅነት ውሣኔ ተሰጠ፡፡

41. መ.ቁ157951 ……….. የቀለብ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

42. መ.ቁ163011 ……….. ፍቺና የልጅ ቀለብ ውሳኔ ተሰጠ፡፡

43. መ.ቁ166929 ……….. የቀለብ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

44. መ.ቁ163359 ……….. የልጅነት ውሣኔ ተሰጠ፡፡

45. መ.ቁ158817 ……….. የፍቺ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

46. መ.ቁ163410 ……….. የፍቺ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

47. መ.ቁ162108 ……….. የከሳሽ ክስ ውድቅ ተደረገ፡፡

48. መ.ቁ151719 ……….. የአመልካች አ:ቱታ ላይ በከፊል ተወሰነ፡፡

49. መ.ቁ153968 ……….. ስምምነት ተሻሽሎ ፀደቀ፡፡

50. መ.ቁ155813 ……….. አመልካች ድርቸው እንዲሰጣቸው ተወሰነ፡፡
በአሰራር ሂደት የሚከሰቱ ስህተቶች ለዳኝነት ነጻነት አለመኖር ማሳያ ተደርገው ሊወሰዱ እንደማይገባ የፍርድ ስራ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ገለጸ፡፡
ሰሞኑን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር አጣሪ ችሎት በቀረበ አንድ የፍትሐ-ብሔር ጉዳይ ላይ በአመራሩ ጣልቃ ገብነት ሁለት ጊዜ የተለያየ ውሳኔ እንደተሰጠ ተደርጎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ በፍርድ ቤቱ ዳታ ቤዝ ባለሙያዎች በተፈጠረ የአሰራር ስህተት ምክንያት መሆኑን ጉዳዩን ያጣራው የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፍርድ ስራ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ገልጿል፡፡
በፍርድ ቤቱ አመራር ጣልቃ ገብነት የዳኝነት ነጻነት አደጋ ላይ ወድቋል እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ጥቆማ የደረሰው የጠቅላይ ፍ/ቤቱ የፍርድ ስራ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ጉዳዩን ለማጣራት ባካሄደው ምርመራ የዳታ ቤዝ ባለሙያዎች የሰበር አጣሪው ችሎት በአምስት ዳኞች ውሳኔ የሰጠበትን ጉዳይ ቀደም ሲል “አያስቀርብም” ለማለት በመዝገቡ ውስጥ ተያይዞ የቀረበን ቅጽ በመመልከት ውሳኔ እንደሰጠ የሚገልጽ የተሳሳተ መረጃ በመረጃ ቋት (Database) ውስጥ በማስገባታቸው ምክንያት የተፈጠረ ችግርን መነሻ በማድረግ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የፍርድ ቤቱ የፍርድ ስራ ምርመራና የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ችግሩን የፈጠሩት ባለሙያዎችንና የችግሩን ስረ ነገር ለመለየት የማጣራት ስራውን የቀጠለ ሲሆን በዚህ ያልተገባና ሃላፊነት በጎደለው ተግባር ላይ ድርሻ ያላቸው ባለሙያዎች ለተፈጠረው ስህተት በዲሲፕሊን እንዲጠየቁና በፍርድ ቤቱ በተዘረጋው የተጠያቂነት ስርዓት ተገቢው አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡
ህብረተሰቡም የዳኝነት ነጻነት የለም፤ የዳኝነት አካሉ አሁንም ከጣልቃ ገብነት ነጻ አልወጣም እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚተላለፈው መረጃ ከእውነት የራቀና መሰረት የሌለው መሆኑን ተረድቶ በዳኝነት አካሉ ላይ የሚሰነዘሩ ማናቸውም አስተያየቶችና የሚቀርቡ ትችቶችን በጥንቃቄ እንዲመዝናቸው ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቶች ዜጎች ፍትህ ለማግኘት ጠንካራ ተስፋ የሚጥሉባቸው ተቋማት ናቸው ያለው ዳይሬክቶሬቱ የፍ/ቤቶች መልካም ገጽታን የማጠልሸትና የህዝቡን አመኔታ በመሸርሸር አሉታዊ ውጤት ያላቸው መረጃዎችን በማንጨት የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ቆም ብለው ጥቅምና ጉዳቱን እንዲያመዛዝኑም መክሯል፡፡ የምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት የደረሰበትን የምርመራ ውጤትም እንዲህ አብራርቷል፡፡
ጉዳዩ በጀ ፎር ኮንስትራክሽን እና አስማማው ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ የውል ክርክር ሲደረግበት የቆየ ነው፡፡ አመልካች ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ባቀረበው አቤቱታ የፍርድ ቤቱ ይግባኝ ችሎት ዳኝነት በጠየቁበት ጉዳያቸው ላይ የሰጠው ውሳኔ የህግ ትርጉም ስህተት ያለው መሆኑን ጠቅሰው የሰበር ችሎቱ ጉዳዩን አይቶ እንዲያርምላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የአቤቱታውን ተገቢነት እንዲያጣራ በመዝገብ ቁጥር 185837 ጉዳዩ የቀረበለት 1ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት ጥር 8 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጉዳዩን ሰምቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በጉዳዩ ላይ የችሎቱ ሁለቱ ደኞች የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡበት እና አንድ ዳኛ ግን በጉዳዩ ላይ እንነጋገርበት ማለታቸውን የሚያሳይ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የተሞላ የውሳኔ ቅጽ ተያይዟል፡፡ በዚህም ምክንያት ችሎቱ ውሳኔ ያልሰጠ መሆኑን መዝገቡ ያስረዳል፡፡
አቤቱታ አቅራቢው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ጉዳያቸው ውሳኔ ሳይሰጠው ረጅም ጊዜ መውሰዱን፤ መዝገባቸውም ቀጠሮ ሳያገኝ መቆየቱንና በዚሀም ምክንያት ጉዳያቸው በምን ደረጃ ላይ እንደለ መረጃ ማግኘት ያልቻሉ መሆኑን ጠቅሰው መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በጽሁፍ አቤቱታ ያቀርባሉ፡፡ የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንትም ችሎቱ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ያደርጋሉ፡፡ ከችሎቱ ዳኞች ጋርም ባካሄዱት ውይይት ክብርት ፕሬዝደንቷ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 21 (1) በተሰጣቸው ስልጣንና በችሎቱ ዳኞች ስምምነት ጉዳዩ በሶስት ዳኞች ከሚታይ ይልቅ በአምስት ዳኞች እንዲታይ የስራ መመሪያ ይሰጣሉ፡፡
አምስቱ ዳኞችም መዝገቡን መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም አስቀርበው ጉዳዩን መርምረዋል፡፡ በመጨረሻም ሰበር ችሎቱ ይግባኝ ሰሚው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ላይ ሊያያቸው የሚገቡ ዝርዝር ጉዳዮች ያሉበት ነው በማለት “ያስቀርባል” የሚል ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ያሳልፋል፡፡
በዚህ ሂደት መዝገቡ ሚያዚያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ዳታ ቤት በመሄዱ የዳታ ቤዝ ባለሙያዎች መጀመሪያ የውሳኔ ሃሳብ የቀረበበትን ነገር ግን ውሳኔ ያላረፈበትን ቅጽ በመመልከት ጉዳዩ “አያስቀርብም” ተብሎ መወሰኑን የሚገልጽ መረጃ መረጃ ቋት (Database) ውስጥ በስህተት ያስገባሉ፡፡ ይህም መረጃ ለባለጉዳዮች በ992 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ይደርሳቸዋል፡፡ ባለጉዳዮቹም ውሳኔውን ተቀብለው በዝምታ ያልፋሉ፡፡ በሌላ በኩል በበችሎቱ ውሳኔ መሰረት በሪጂስትራር በኩል የአመልካች የሰበር አቤቱታ ከፍርድ ቤቱ መጥሪያ ጋር ለተጠሪ እንዲደርስ በታዘዘው መሰረት መጥሪያው እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
የተፈጠረውን ስህተት ለማረም በመረጃ ቋት (Database) በገባው ትክክለኛ መረጃ መሰረት ለባለጉዳዮቹ መዝገቡ ያስቀርባል ተብሎ መወሰኑን እንዲሁም ለምርመራ እና የመልስ መቀባበያ ቀጠሮ መሰጡተን የሚገልጽ መረጃ በ992 አጭር የጽሁፍ መልእክት በድጋሚ ይደርሳቸዋል፡፡
በአንድ ጉዳይ ላይ አንድ ችሎት በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ እንዴት ሊሰጥ ይችላል የሚል ተገቢነት ያለው ጥያቄ ምናልባትም ከግራና ቀኝ ተከራካሪ ባለጉዳዮች መካከል አንዱ ያነሳሉ፡፡ ለዚህም ጥያቄ አሁን ላይ ማንነታቸው ተለይቶ ያልታወቁ አካላት ያልተገባና እውነታነት የሌለው ምክንያት በመስጠት የዳኝነት ነጻነት በአመራሩ ጣልቃ ገብነት መጣሱንና የውሳኔ ለውጥ መደረጉን የሚገልጽ መረጃ መሰራጨት መጀመሩን የምርመራ ክፍሉ አመልክቷል፡፡ ነገር ግን አቤቱታ አቅራቢው ባለጉዳይ ከላይ እንደተገለጸው ለፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ውሳኔ ዘገየብኝ፤ መዝገቡም ቀጠሮ ባለመያዙ ጉዳያቸው ያለበትን ደረጃ ማወቅ አለመቻላቸውን የሚገልጽ መሆኑን ከመዝገቡ ጋር የተያያዘው ማስረጃ ያሳያል፡፡
ይህን አይነት የተለመደ አቤቱታ የመቀበልና አስተዳደራዊ መፍትሄ የመስጠት አሰራር በተሳሳተ ግንዛቤ ዓላማውን እንዲስት በማድረግ አቤቱታው ውሳኔ እንዲሻሻል የቀረበ በማስመሰልና ከእውነት የራቀ መረጃ በማሰራጨት ላይ መሆናቸውን የምርመራ ክፍሉ ጠቁሟል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ በዲሲፕሊን የሚጠየቁ አካላትን ለይቶ ተገቢው አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ መሆኑን በማረጋገጥ ጉዳዩን ለማጣራት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም የመዝገቡን ሙሉ ግልባጭ በማግኘት ማጣራት እንደሚችል ጨምሮ ገልጿል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሰበር መረጃ

#Ethiopia : ግብፅ ከኢትዮጵያና ሱዳን ተቋርጦ የነበረውን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሚደረገውን ድርድር ለመቀጠል የቀረበላትን ጥያቄ መቀበሏን የሀገሪቱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠቅሶ Daily News Egypt ዘግቧል።

via Natnael Mekonnen:
‹‹ …. ጤነኛ የሆንን እና የገቢ ምንጭ ያለን ስዎች እስኪ በአካባቢያችን ቢያንስ አንድ የተቸገረ ሰው እንርዳ። በየአካባቢያችን እንደዚህ ያሉ የእኛን እርዳታ የሚሹ ብዙ ናቸው። አይኖቻችንን ከፍተን በፍቅር እና በርህራሄ እንያቸው፣ እንርዳቸው! ..››

ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
ለአገራችን ህዝብ ሰላም እና ደህንነት ሽብርተኝነትን በጋር እንከላከል
_______________

አገራችን የሰላም እና የልማት እንጅ የጦርነት አውድማ አይደለችም፡፡ ትልልቅ አገራዊ የለውጥ እና የልማት ሀሳብ ይዘን በትንንሽ ጉዳዮች የለውጥ ጊዜን አናባክን፡፡

የሰከነ ሀሳብ ለአገራችን ለውጥ መደሃኒት በመሆኑ ዛሬን ከነገ የተሻለ ለማድረግ አስተውለንና በአንድነት ተባብረን መራመድ ይገባል፡፡
አንድ ስንሆን ስንተባበር ካሰብነው እና ካቀድነው አላማ እንደርሳለን፡፡ ውድ አንባቢያን!! ሽብርተኝነት በመላው አለም በሰው ልጆች ላይ ጻታ፣ ሀይማኖት፣ ዘርና አካባቢ ሳይለይ የተቃጣ ግልፅ ጦርነት ነው፡፡

በመሆኑም ከአሁን በፊት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ወጥቶ የነበረው የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2009 በይዘትና አፈጻጸም ክፍተቶች የነበሩበት መሆኑ ይታወቃል፡፡

አጥፊዎች ከድርጊታቸው ጋር ተመጣጣኝና አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ የሚያስችል፣ የግለሰቦችን መብቶችና ነፃነቶች በበቂ ሁኔታ ሊያስጠብቅና የሕግ አሰፈጻሚ አካላትን ተጠያቂነት የሚያሰፍን ሕግ መተካት በማስፈለጉ እና የሽብር ድርጊት ተጎጂዎች የህክምና፣ መልሶ ማቋቋምና መሰል ተግባራት ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል ሥርዓት ለመፍጠር የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሸሽሎ የወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

በአዋጁ ድንጋጌ መሰርት ማንኛውም ሰው የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የርዕዮተ ዓለም ዓላማን ለማራመድ በማሰብ ህዝብን ወይም የተወሰነ የህብረተሰብን ክፍል ለማሸበር ወይም መንግስትን፣ የውጭ አገር መንግስትን ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅትን ለማስገደድ፡-በሰው አካል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤ የሰውን ሕይወት ለአደጋ ያጋለጠ፤ ሰውን ያገተ ወይም የጠለፈ፤ በንብረት፣ በተፈጥሮ ሃብት ወይም አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤ ወይም የሕዝብ ወይም ማህበራዊ አገልግሎት እንዳይሰጥ በከፍተኛ ሁኔታ ያስተጓጎለ እንደሆነ ከ15 እስከ 18 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ያስቀምጣል፡፡

በሽብር ድርጊቱ የተፈጸመው ተግባር ሰውን መግደል፣ በታሪካዊና የባሕል ቅርስ ወይም የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ እንደሆነ ከ15 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ ጽኑ እስራት ወይም በሞት ይቀጣል፡፡

በመሆኑም ወቅታዊ የኮሮና ወረርሽኝ እና ምርጫ ጋር በተያያዘ ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት የሽብረተኝነት ተግባር የተጠናወታቸው አካልት ሰላማችን እንዳይነጥቁን ነቃትን መጠበቅና ሕግን ማስከበር የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆን አለበት፡፡

https://telegram.me/lawsocieties
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 83ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ #ውሳኔ አሳልፏል!

#PMOEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ 1441ኛውን የኢድ - አል - ፊጥር በዓል ምክንያት በማደረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፋል።
******************************
ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመልዕክታቸው ይህ በዓል ምስጋና፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ ይቅርታ የተሞላበት እንዲሆን በመመኘት በዓሉን ስናከብር አቅም ለሌላቸው ወገኖቻችንን በመርዳት እና የደስታችን ተካፋይ በማድረግ ደስታ እና በዓል የማያውቀውን የኮሮና ወረርሽኝ ሳንረሳ ለእራሳችን እና ለቤተሰቦቻችን ከፍተኛውን ጥንቃቄ ማድረግ እና ህጎቹን ማክበር እንዳንዘናጋ አደራ በማለት አሳስበዋል።

በሌላ በኩልም በትላንትናው ዕለት ምሽት በአዲስ አበባ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኮቪድ 19 ለይቶ ማቆያ ስፍራ በመገኘት በልይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዩች እና ይህን ውረርሽኝ ለመከላከል በግንባር ቀደምነት ለተስለፉ ህክምና ባለሙያዎች ና የጽጥታ አካላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ በስፍራው ለሚገኙ አካላት የበአል ስጦታ በጎችን አስረክቧል።
ኢድ ሙባረክ!
ለእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎች እንዲሁም ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊያት በሙሉ እንኳን ለ1441ኛው ኢድ-አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ ... አደረሠን!!! ኢድ- ሙባረክ!!!
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች በተለያዩ ምድብ ችሎቶች በመዘዋወር የመስክ ምልከታ አድረገዋል

………………………………………………………………

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች ግንቦት 13/2012 ዓ.ም የተለያዩ ምድብ ችሎቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በከፍል ዝግ በሆነበት በአሁኑ ወቅት አመራሮቹ በአዲስ ከተማ፤አራዳ፤መናገሻ እና ልደታ ምድብ ችሎቶች በመገኘት ዳኞች እና ሰራተኞች እራሳቸዉን ከወረርሽኙ እየጠበቁ በአግባቡ ባለጉዳዮችን እያሰተናገዱ መሆኑን ተመልክተዋል፡፡ በመስክ ምልከታዉ ወቅትም በየምድብ ችሎቶቹ ከሚገኙ ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እና ሰራተኞች ጋር የተወያዩ ሲሆን በዚህም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በፍርድ ቤቱ በኩል እሰከ አሁን የተወሰዱ እርምጃዎች የሚበረታቱ መሆናቸው ተገልጷል፡፡

በቀጣይነትም ወረርሽኙን ለመከላከል እንዲያስችል በቂ አቀርቦት እና የስርጭት ስርዓት ሊኖር የሚችልበት አግባብ ላይ የፍርድ ቤቱ አመራሮች ከዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እና ሰራተኞች ጋር ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

በሌላ በኩል የወረርሽኙን መስፋፋት ለመቀነስ ሁሉም ወደ ፍርድ ቤቱ የሚመጡ ባለጉዳዮች የመግብያ በር ላይ እጃችዉን በአግባቡ በዉሃ እና ሳሙና በመታጠብ ፣ አካላዊ ሪቀታቸዉን በመጠበቅ እና የአፍ መሸፈኛ ማስክ በማድረግ እየተስተናገዱ የሚገኙ መሆናቸውን መመልከት ተችሏል፡፡

የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ክፍል
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀምን በማጥበቅ ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል አለብን ።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

-------------------------------

የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ስርጭት አኳያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ማጥበቅና ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም በተመለከተ እንደገለጹት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ከጊዜ ወደጊዜ ወጥነት ባለው መልኩ እየተሻሻለ ኮሮናቫይረስን እንዳይስፋፋ የራሱን ሚና እየተጫወተ ነው።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየታየ በመሆኑና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ዜጎች ቫይረሱ እየተገኘባቸው መሆኑ የተሰጠውን ትኩረት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል።

“በመሆኑም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያወጣቸውን ዝርዝር ደንቦች በትክክል እንዲተገበሩ በጥብቅ መከታተል ያስፈልጋል” ብለዋል።

“በተለይ በትራንስፖርትና ሌሎች ዘርፎች ላይ የአዋጁን ደንቦች በሚገባ ለማስፈፀም እንዲያስችል ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ አዋጁን ማየት እንዳለብን ተመልክተናል” ሲሉ ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል።

“አዋጁን በትክክል ተረድቶ ከመፈፀምም ይሁን ከማስፈፀም ስህተቶች ሊገጥሙ ይችላሉ” ያሉት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጓ፤ የአዋጁ አስፈፃሚዎች የሚያደርጉት ክልከላዎች የዜጎችን ህይወት ለማዳን እንደሆነ በመገንዘብ ደንቦቹን መተግበር ከሁሉም እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

በተለይም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ከማድረግና ካለማድረግ ጋር ሰዎች ያለ አግባብ ይታሰራሉ ከሚለው ቅሬታ ጋር አያይዘውም “ህዝቡ ሰዎች በሚበዛባቸው ቦታዎች ብቻ ሳይሆን በማናቸውም ቦታዎች ማስክ ቢያደርግ ይጠቀም እንደሆን እንጂ አይጎዳም” ሲሉ መክረዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማስከበር ሽፋን ውስጥ የሙስና ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ መንግስት እንዴት ይከላከላል? ለሚለው ጥያቄም “ህዝቡ ህይወቱን አስይዞ መደራደር የለበትም” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ግን ወደ አላስፈላጊ ድርድር የሚገባ ህግ አስከባሪ ካለ ጥቆማ በመስጠት የዜጎችን ህይወትና የሙስና ወንጀልንም ከመንግስት ጎን ሆኖ እንዲከላከል ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።