አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
December 19, 2019
December 19, 2019
December 19, 2019
December 19, 2019
Abiy:
Hi am Abiy, I need the new draft commercial code for my research if anybody have it please attache it on the group.
December 19, 2019
December 19, 2019
የግልግል ዳኝነት ረቂቅ አዋጅን እና ዓለም ዓቀፍ የዕቃዎች ሽያጭ ውሎች ስምምነትን አስመልክቶ ዉይይት እየተካሄደ ነዉ፡፡
-------------------------------------------------------

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የግልግል ዳኝነትን ለመደንገግ ባዘጋጀዉ ረቂቅ አዋጅ ላይ እና የተባበሩት መንግስታት ዓለም ዓቀፍ የእቃዎች ሽያጭ ውሎች ስምምነት አዉደ ጥናት አስመልክቶ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈና ለሁለት ቀናት የሚቆይ ዉይይት እያካሄደ ነዉ፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በሕግ ጉዳዮች አለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ የሱፍ ጀማዉ በዉይይት መድረኩ ላይ እንደተናገሩት አገራችን ኢትዮጵያ የኒዮርክ ኮንቬንሽንን ተቀብላ ለማፀደቅ በሂደት ላይ መሆኗን አዉስተዉ የግልግል ዳኝነት ረቂቅ አዋጅም ኮንቬንሽኑን ለማስፈጸም አገልግሎት ላይ የሚውል እንደ አንድ የማስፈጸሚያ ተግባር ተደርጎ ሊወሰድ እነደሚችል በማንሳት ለረቂቅ አዋጁ ግብአት የሚሆኑ ሀሳቦችን ለመሰብሰብ ታስቦ ዉይይቱ መዘጋጀቱን ለተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

ቀጥሎም የግልግል ዳኝነትን ለመደንገግ የወጣዉን ረቂቅ አዋጅ ያቀረበችዉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህግ ማርቀቅና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ የሆነችዉ ወ/ሮ ትእግስት መሐቤ ረቂቁ ከመዘጋጀቱ በፊት በተለያዩ ጊዜያት የተዘጋጁ ሶስት ረቂቅ አዋጆችን በግብአትነት መጠቀማቸዉን አዉስታለች፡፡ የግልግል ዳኝነት ከዉል ወይም ከውል ዉጭ ባለ ህጋዊ ግንኙነት ሊፈጠር የሚችልን ወይም የተፈጠረን አለመግባባት በሙሉ ወይም በከፊል በግልግል ዳኝነት ለመፍታት የሚፈፀም የዉል ስምምነት ሲሆን የንግድ የኢንቨስትመንት እና የመሳሰሉት አለመግባባቶችን በግልግል ዳኝነት መፍታት አስፈላጊ በመሆኑና አገራችን ተቀብላ ያፀደቀቻቸዉን ዓለም ዓቀፍ የግልግል ዳኝነት ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም ለነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ማደግ አስተዋፅኦ የሚያደርግ በመሆኑ አዋጁ መዘጋጀቱ ተገልጧል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በርካታ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል ጥያቄዎችም ተነስተዉ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ውይይቱ ነገም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን በነገዉ ውሎዉ የተባበሩት መንግስታት ዓለም ዓቀፍ የእቃዎች ሽያጭ ዉል አዉደ ጥናት ቀርቦ በስምምነቱ ይዘትና መፅደቅ አስፈላጊነት ላይ ገለፃ እና ዉይይት ይካሄድበታል፡፡
https://telegram.me/lawsocieties
December 19, 2019
December 19, 2019
የወጣቶች የወንጀል ፍትሕ እና የክስ አጀማመር ህጋዊ አንድምታው ምን ይመስላል
--------------------------------------
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌስቡክ ገጽ ተከታታዬቻችን፤ እንዴት ናችሁ ለዛሬ የወጣቶች የወንጀል ፍትሕ እና የክስ አጀማመር ህጋዊ አንድምታው ምን ይመስላል በሚል አንድ ጥንቅር ልናስነብባችሁ ወደናል ከወዲሁ መልካም ንባብ ተመኘን፡፡

እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች በሕግ የተለየ ጥበቃ ይደርግላቸዋል። ይህ ጥበቃ በሕገ-መንግሥት፣ በቤተሰብ ሕግ፣ በውርስ ሕግ፣ በውል ሕግ፣ በወንጀል ሕግ፣ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ፣ በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ፣ በአለም ዓቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎችም በርካታ የይዘት ሕጎች ተደንግጎ የሚገኝ ነው። እነዚህ ሕጎች ከሞላ ጎደል የሚጋሩት ጉዳይ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑት ሰዎች ይበልጥ በሚጠቅም መርህ የያዙ መሆናቸው ነው። በወንጀል የፍትሕ ሥርዓት ለወጣቶች እንዲሁም ለሕፃናት የሚደረገው ጥበቃ በወንጀል ሕጉ እና በሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋውን ሥርዓት የሚያጠቃልል ነው። የወንጀል ሕጉ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶችን/ሕፃናትን በሦስት የእድሜ ክልሎች ማለትም ከ9 በታች፣ ከ9-15፣ ከ15-18 በመመደብ በተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች እንዲገዙ አድርጓል።

ወጣቶችን የሚመለከተው የሥነ-ሥርዓት ሂደት እንደዚሁ ከመደበኛው በይዘት የተለየ፣ ከሌሎች ታሳቢዎች የሚንደረደርና በሌሎች መርሆች የሚመራ ነው። ይህ ልዩነት ከሞላጎደል በሁሉም የሂደቱ ደረጃዎች የሚንፀባረቅ ነው። ስለሆነም ምርመራው፣ ክሱ፣ የመስማት ሂደቱና የማረም ሥርዓቱ የራሱ ገፅታዎች ያሉት ነው።

የወንጀል ፍትሕ ሂደት የሚመራው በዋናነት በወንጀል የሥነ-ሥርዓት ሕግ ነው። የሥነ-ሥርዓት ሕጉ የወንጀል ጉዳዮችን በማስመልከት ሦስት የተለያዩ ሀዲዶችን አስቀምጧል፤ አንድ መደበኛና ሁለት ልዩ ሥነ-ሥርዓቶችን። ሁለቱ ልዩ ሥነ-ሥርዓቶች የደንብ መተላለፍንና (አንቀጽ 167-180) የወጣቶችን ጉዳይ (አንቀጽ 171-180) የሚመለከቱ ሲሆን ሦስተኛው ከነዚህ ውጭ ያሉትን ሁሉንም የወንጀል ጉዳዮች የሚሸፍነው መደበኛው ሥነ-ሥርዓት ነው።

ሀ የክስ አጀማመር (setting justice in motion)
ወጣቶችን የሚመለከት የወንጀል ምርመራ በልዩ ሥርዓት የሚመራ ነው። እንደሚታወቀው በመደበኛ የወንጀል ጉዳዮች የፍትሕ ሂደት የሚጀምረው ማንም ሰው በሚያቀርበው ክስ ወይም አቤቱታ መነሻነት ነው (አንቀጽ 11) ። አቤቱታ ወይም ክስ ማቅረብ መብት ቢሆንም በፍትሐብሔር ሂደት እንደሚደረገው ክሱን ወይም አቤቱታውን ቀጥታ ለፍርድ ቤት ማቅረብ አይቻልም። ክስ ወይም አቤቱታ ማቅረብ የሚቻለው ለፖሊስ ነው።

በመሆኑም የወንጀል የፍትሕ ሂደት የክስ አቀራረብ፣ ማስረጃ አሰባሰብና አቀርረብ ከፍትሐብሔሩ የተለየ ነው። በፍትሐብሔር የሙግት ሂደት ማስረጃ ማሰባሰብም ሆነ ለፍትሕ ተቋማት የማቅረብ ኃላፊነት በዋናነት የከሳሽና የተከሳሽ ነው። በመሆኑም ግለሰቦች (ከሳሽና ተከሳሽ) የራሳቸውን ጉዳይ የሚመለከት ማስረጃ የማሳባሰብ እንዲሁም ለፍርድ ቤት የማቅረብ የግል ኃላፊነት አለባቸው። የወንጀል የፍትሕ ሥርዓቱ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ማስርጃ የማሰባሰቡም ሆነ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ ከግል ወደ መንግሥት ኃላፊነት በማዘዋወር ግለሰቦች ከዚህ ኃላፊነት ነፃ እንዲሆኑ አድርጓል። በዚህ መሠረት ሕጉ በወንጀል ጉዳዮች ሪፖርት የማቅረብ መብት ለዜጎች ሲሰጥ ሪፖርቱን የመቀበል፣ የመመዝገብ እና የማጣራት ሥልጣንና ኃላፊነት የፖሊስ አካላት እንዲሆን አድርጓል። በመሆኑም የወንጀል ጉዳይ የሚጀምረው ለፖሊስ በሚቀርብ ክስ ወይም አቤቱታ መነሻነት ነው።

"ማናቸውም የወንጀል ክስ (ቁጥር 11) ወይም የክስ አቤቱታ (ቁጥር 13) ለፖሊስ ወይም ለዓቃቤ ሕግ ማቅረብ ይቻላል። አካለመጠን ባላደረሰ ወጣት ላይ የሚቀርብ ክስ ወይም የክስ አቤቱታ በቁጥር 172 መሠረት መቅረብ አለበት"
በማለት የመደበኛውና የወጣችቶ ጉዳይ በተለያየ ሥርዓት እንደሚጀምር ያሳያል። አንቀጽ 172 በሌላ በኩል ወጣት አጥፊዎች በወንጀል ገብተው ሲገኙ ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሳይሆን ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑን ይደነግጋል።
አንቀፁ"አካለ መጠን ያልደረሰ ወጣት በወንጀል ነገር ውስጥ ገብቶ በተገኘ ጊዜ ፖሊሱ፣ ዐቃቤ ሕጉ፣ ወላጁ ወይም ሞግዚቱ በቅርብ ወደሚገኘው የወረዳ ፍርድ ቤት ወድያውኑ ይዞት ይቀርባል" በማለት ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ ይዘት በግልፅ መገንዘብ እንደሚቻለው የወጣቶች ጉዳይ የሚጀምረው ክስን ለፍርድ ቤት በማቅረብ ነው።

በመደበኛው ሂደት ፖሊስ የሚቀርብለትን ክስ ወይም አቤቱታ ተቀብሎ ምርመራውን የመምራት ሥልጣን ሲኖረው በወጣቶች ጉዳይ ላይ ወይም ከ9 አመት በታች፣ ከ9-15፣ ከ15-18 የእድሜ ክልሎች ውስጥ ባሉ ወጣት አጥፊዎች ላይ ይህ ሥልጣን አልተሰጠውም፣ ይህ ሥልጣን የተሰጠው ለፍርድ ቤቶች ነው። ስለዚህ ፖሊስ ገና ከጅምሩ በእነዚህ የእድሜ ክልሎች ውስጥ የሚገኙት የወንጀል ጉዳይ የሚያስተናገድበት እድል የለም።

በአጠቃላይ ፖሊስ ወጣቶቹን ወድያውኑ ወድ ፍርድ ቤት ከመውሰድ ያለፈ ሌላ ተግባር የለውም። ከዚህ ቀጥሎ እንደምንመለከተው ፖሊስ ክሱንም ሆነ አቤቱታውን ተቀብሎ የምርመራ መዝገብ የመክፈት ኃላፊነት ስለሌለበት በጉይዩ ላይ ማንኛውንም አይነት የምርመራ ሥራ የማከናወንም ተግባር አይጠበቅበትም። በመርህ ደረጃ ምርመራ የማከናወን አደራ የተሰጠው ለፖሊስ ተቋም ቢሆንም ሕጉ ወጣቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ይህ ኃላፊነት ለፍርድ ቤት እንዲሆን ይደነግጋል፡፡

ውድ አንባቢያን ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁን ጥንቅር በዚሁ አበቃን በቀጣይ ክፍል በወጣት አጥፊዎች ላይ ማስረጃዎች እንዴት ይሰበሰባሉ የከስ አቀራረብ ሂደት ምን ይመስላል በሚሉና በመሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ጥንቅር ወደ እናንተ እናደርሳለን በቀጣይ እስክንገኛኝ ሰላም፡፡
መረጃውን ያገኘነው ከአቢሲኒያ ሎው ድህረ-ገጽ ነው፡፡
December 19, 2019
December 19, 2019
December 20, 2019
December 20, 2019
December 20, 2019
@lawsocieties
Spend Summer in Germany 🇩🇪

Summer Student Program 2020 Germany (Fully Funded)

100 Students will Participate from all around the world.

Duration: July 21 to September 10, 2020

Who can apply?

Undergraduates & Graduates Students are Eligible.

💰Financial Coverage:

Paid Allowance will be given to cover the Living Expenses. Round Airfare Flight ✈️ Tickets will be Covered.

✍🏿Link: https://bit.ly/2Efxrcy

🔥Deadline: 31st Jan 2020
https://telegram.me/lawsocieties
December 20, 2019
December 21, 2019
December 21, 2019
December 21, 2019
December 21, 2019