አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
'ከረሜላ ልስጥሽ' በማለት አታሎ የ9 ዓመት ህጻን የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት እስራት ተቀጣ

በይርጋጨፌ ከተማ የ9 ዓመት ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

ግለሰቡ ድርጊቱን የፈጸመው በቀን 10/9/2016ዓ.ም በግምት ከጥዋቱ 4 ሰዓት በይ/ጨፌ ከተማ ካራ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ነው።

የግል ተበዳይ 9 ዓመት ህጻን ተማሪ ስትሆን ሜክ አፕ ተጠርታ ተምራ እየመጣች ባለችበት ቅ/ኪዳነምህረት ት/ቤት ፊት ለፊት ባለው  የመጠጥ ማከፋፈያ ውስጥ ሆኖ እማ ነይ ከረሜላ ልስጥሽ በማለት ደስታ ከረሜላ የመሰለ ነገር እንደበላች እራሷን እንደሳተች የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

በመቀጠልም ወደ ውስጥ በማስገባት በፒላስቲክ ጅባ ላይ አስተኝቶ አሰገድዶ የደፈረ መሆኑንና ተከሳሽ ሆን ብሎ አስቦ በማድረጉ ተገልጿል።

ተከሳሹ፥ 1997 ዓ.ም በሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ዕግ አንቀፅ 627/1 የተደነገገውን በመተላለፍ በፈፀመው በሕፃናት ልጆች ላይ በሚፈፀም በግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

በዚህም ተከሳሹ 14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉን የይርጋጨፌ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
No Fayda no service‼️
ከጥር 2017 አጋማሽ ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ የባንክ አገልግሎት ለማግኘት ግዴታ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያስፈልጋል‼️

-ከሰኔ ወር 2017 መጨረሻ ጀምሮ ደግሞ በሀገሪቱ ባሉ ሁሉም ትልልቅ ከተሞች ባሉ ባንኮች አካውንት ለመክፈት ፋይዳ ግዴታ ነው

-በመላው ሀገሪቱ ያሉ ሁሉም ባንኮች ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፋይዳ መታወቂያን ግዴታ ያደርጋሉ

-በታሕሳስ 2019 ዓ.ም ነባር የባንክ ደንበኞችም ቢሆኑ ፋይዳ ካልያዙ አገልግሎት አያገኙም።
#ዋዜማ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ጨምሮ ስምንት የመንግስት ልማት ድርጅቶች በኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር እንዲተዳደሩ ተወሰነ

ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ተጠሪ የነበሩ የልማት ድርጅቶች ከአሁን ጀምሮ በባለቤትነት የሚተዳደሩትና የሚመሩት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፣ ኢትዮ ፖስት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን እና ለኢትዯ ፋርማ ግሩፐ ተጠሪ የሆኑት ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ተቋምና ሺልድ ቫክስ በኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር እንዲሆኑ የተደረጉት መንግስታዊ ተቋማት ናቸዉ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ ( ዶ/ር) እንደተናገሩት እነዚህ የልማት ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ኢንደስትሪላይዜሽን እና የዕድገት ምኞቶችን ለማሳካት ወሳኝ ናቸው ብለዋል፤ "እኛም ባለን ትኩረት፣ ሙያዊ አስተዳደር እና ንቁ ባለቤትነት እነዚህን ድርጅቶች ወደ አዲስ የስራ አፈጻጸም እና ፈጠራ እንደምናመጣ እርግጠኞች ነን" ሲሉም እርምጃውን አድንቀዉታል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 487/2022 የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን አሁን ላይ አዳዲሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ 25 በላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በባለቤትን እያስተዳደረ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
Source: capitalethiopia
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት እና አገልገሎት
Alternative legal enlightenment and Service
https://linktr.ee/alehig
alehig.com
👆
ረቂቅ አዋጁ ፀደቀ

የህ/ተ/ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ዛሬ በምክር ቤት የፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የሪል ስቴት አልሚ ድርጅት ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ እንደማይችል አስቀምጧል።

በተጨማሪ በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር እንደማይችልም አስቀምጧል።

የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?

👉 የሪል ስቴት አልሚ የቦታና የተናጠል ይዞታ ማረጋገጫ አሰጣጥን በተመለከተ ፦

1) በከተሞች ለሪል ስቴት ልማት የሚውል ቦታ በሚከተለው አግባብ የሚቀርብ ይሆናል፤

ሀ. በአዲስ አበባ ከ5 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፤
ለ. እንደከተሞች ተጨባጭ የቤት ፍላጎትና ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባለ ከተሞች ከ1 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፣
ሐ. ከነዚህ ባነሰ ስፋት ቤት ለሚፈልጉ ከተሞች ደግሞ 500 ቤት በላይ የሚገነባና የሚያስተላልፍ የሪል ስቴት አልሚ መሬት ቅድሚያ ተሰጥቶት በስፋት እንዲቀርብለት ይደረጋል።

2) የሪል ስቴት አልሚው የገነባውን ቤት በተናጠል ለቤት ፈላጊ በሽያጭ ለማስተላለፍ ግንባታው የተፈቀደለትን መስፈርት አሟልቶ 80 በመቶ ሲጠናቀቅ ለየቤቱ የተናጠል የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል፤

👉 የሪል ስቴት አልሚ ግዴታዎች ምንድናቸው ?

የሪልስቴት አልሚ በውል ሰነዱ በህንጻ እዋጁ እና በሌሎች የህግ ማዕቀፎች የተመላከቱ ግዴታዎችን ማክበር እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪነት የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል ፡-

1) ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡

2) በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር አይችልም፡፡

3) ቤቶቹን ለመገንባት የሚያስችለውን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከመረከቡ በፊት ደንበኞችን መመዝገብና ቅድመ ክፍያዎችን መሰብሰብ አይችልም፡፡

4) በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም።

5) የመኖሪያ ቤት ገዢ ደንበኞች ማኀበር እንዲያቋቋም ያበረታታል ፤ የህንጻ መግለጫ ያስረክባል።

6) ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የተሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫ፣ የቤቱ የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት፣ አርክቴክቸራል፤ ሳኒተሪ ፣ ስትራክቸራል እና ኤሌክትሪካል ዲዛይን፤ የግንባታ ፍቃድና የሪል ስቴት ልማት ፍቃዱን ቅጂዎች ከውል ሰነዱ ጋር አያይዞ ለደንበኛው መስጠት አለበት።

7) ደንበኛው ለከፈለው ገንዘብ ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት አለበት።

👉 ዋስትና ስለመስጠት ፦

የአገር ውስጥ አልሚ ቤቱን ሳይገነባ ለቤት ፈላጊዎች በቅድሚያ በሚሽጥበት ወቅት የሚከተሉትን የዋስትና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፡፡

1) የሪል ስቴት አልሚው በቤት ቅድሚያ ሽያጭ ስልት ለመስራት መፈለጉን አግባብ ላለው አካለ አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት፡፡

2) ከቤት ገዥዎች የሚሰበስበውን ገንዘብ አግባብ ካለው አካለ ፈቃድ መሰረት በሚከፈተው የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ፣

3) የሪል ስቴት አልሚው በቅድሚያ መሽጥ የሚፈልገውን ቤት የመስሪያ ቦታ የይዞታ ማስረጃ ቤቱ ለተጠቃሚዎች ተገንብቶ እስከሚተላለፍ ድረስ በሚመለከተው አካል እንዳይሽጥ እንዳይለወጥ እንዲታገድ ማድረግ፤
📌 በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡
አዋጁ ከተች በ PDF ተቀምጧል።
#ቲክቫህ
የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ_1.pdf
1.7 MB
👆
ረቂቅ አዋጁ ፀደቀ

የህ/ተ/ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።