African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
እንኳን ወደ አፍሌክስ ቤተ-መጽሐፍት መጡ 📚

በሱሉልታው የአካዳሚያችን የአመራር ልማትና ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ የሚገኘው ቤተ-መፃህፍታችን ለዛሬ እና ለነገ መሪዎች የእውቀት መናኸሪያ ነው! 🌟

ወደ ቤተ-መፃህፍታችን መጥተው ስለ አመራር ልማት በሰፊው ያስሱ! ምን ይፈልጋሉ

🔹ስልታዊ አስተሳሰብ?
🔹የተግባቦት ክህሎቶች?
🔹ወይስ ተቋማዊ አመራር?
ለሁሉም የሚሆኑ መጻህፍትን እኛ ጋር ያገኛሉ!📖

ምን ይሄ ብቻ❗️ ሰፊው ዲጂታል ቤተ-መጻህፍታችን በርካታ መጻህፍትን የያዘ ነው! የQR ኮዱን በስማርትፎንዎ ስካን በማድረግ ብቻ ኢ-ላይብረሪያችንን ይጠቀሙ! 📱

ወደማዕከላችን ሲመጡ በሚያርፉባቸው ምቹ መኝታ ክፍሎች ውስጥ በተገጠሙ ኮምፒዩተሮች አማካኝነት ከዲጂታል ቤተ-መጻህፍቱ መጻህፍትን በቀጥታ ማውረድ ይችላሉ!💻

ከአሜሪካ ኤምባሲ🇺🇸 እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የፈጠርናቸው አጋርነቶች የዲጂታል አቅማችንን እያሰፉ፣ ቤተ-መጻሕፍታችን በአመራር ልማት መስክ ቀዳሚ የእውቀት ምንጭ እንዲሆን በማድረግ ላይ ናቸው።

የአፍሌክስ ቤተ-መጻሕፍት ማንበቢያ ብቻ ሳይሆን፣ ሀሳቦች የሚያብቡበት፣ መሪዎች የሚገኙበት የእውቀት ቤት ነው።

ወደማዕከላችን ለስልጠና ሲመጡ ቤተ-መጻህፍታችን ሁሌም በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቆታል 🌟📚

#AFLEX #Library #LeadeshipDevelopment