African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የሥራ ባህል ሽግግር ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ::

#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የሥራና_ክህሎት_ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል ተፈራርመዋል።


ሁለቱ ተቋማት በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በቅንጅት ለመስራት የተስማሙ ሲሆን የዘርፉን የአመራር ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል የአመራር ልማት ፕሮግራም፣ የሥራ ባህል ሽግግር ለመፍጠር የሚያግዝ ማከል ግንባታ፣ ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት እና ከስር ያሉትን የሚያተጋ የልህቀት ሽልማት እና በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት እንዲቻል የጋራ ምርምር ሥራዎችን ለመስራት ተስማምተዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝደንት ዛዲግ አብርሃ በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ስምምነቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራና ክህሎት ለመፍጠር የሚያደርገውን ተግባር የሚያግዝና ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እንደሆነ ጠቅሰው በስምምነቱ መሰረት የአመራሮችን ብቃት የማሳደግ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።

የዘርፉ ምሁራን እና ተመራማሪዎች ሀሳብ የሚያፈልቁበት የስራ ባህል ሽግግር ማዕከል ግንባታ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበትም የመሰረት ልማት ግንባታው የስምምነቱ አንድ አካል እንዲሆንና በቅርቡም የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነስርዓት እንደሚፈፀም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል::
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የሥራና_ክህሎት_ሚኒስቴር ያደረጉትን የጋራ መግባቢያ ስምምነት አዲስ ዋልታ ቴቪ እንዲህ ዘግቦታል፦