African Leadership Excellence Academy
2.33K subscribers
2.51K photos
96 videos
6 files
118 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
“አፍሌክስ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር፤ የአመራር ልማት ተግባሩን ለማስፋት በሩ ሁልጊዜም ክፍት ነው።” ወ/ሮ መሰረት ደስታ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ

#ፖላር_ፕላስ_ኤክሰለንስ_ሃብ እና #አጋሮቹ አፍሌክስን ጎበኙ

ታህሳስ 14/2017 (ሱሉሉታ- አፍሌክስ) - የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል ዛሬ ከፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሃብ እና አጋር ድርጅቶች የተወጣጡ ልዑካንን አስተናግዷል።

ሱሉልታ በሚገኘው የአመራር ልማት ማዕከል ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት የፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሃብ እና አጋር ድርጅቶቹ የሆኑት #የዌብ_አክሰስ#የሻላ_ዌልነስ_ሴንተር እና #የአፔክስ_ቬንቸርስ አመራሮች ናቸው።

ልዑካኑ በማዕከሉ የሚገኙ ዘመናዊ የሲኒዲኬትስ ክፍሎችን እና ጂምናዚየምን ጨምሮ ሌሎች ዘመናዊ መገልገያዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም እንዲህ ያለ የተሟላ የአመራር ልማት ማዕከል በኢትዮጵያ መገኘቱ ትልቅ እመርታ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ አፍሌክስ ለአመራር ልማት ምቹ አካባቢን ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት አጉልቶ ያሳያል ብለዋል።

ጉብኝቱን ተከትሎ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ ከልዑኩ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም ላይ "አፍሌክስ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ትብብር፤ ለሁለንተናዊ እድገት ያለውን አስፈላጊነት በመገንዘብ በትብብር ለመስራት በሩን ክፍት አድርጎ እየጋበዘ ነው።" ብለዋል።

በውይይቱ አፍሌክስ እና ልዑካኑ የጋራ የትብብር አቅጣጫዎችን ለይተው አጋርነት መፍጠር ስለሚችሉበት ሁኔታ የተነጋገሩ ሲሆን፣ ከትብብር መስኮቹ መካከል የጤናው ዘርፍ እና የስትራቴጂክ ኮሙዩኒኬሽን ሊካተቱ የሚችሉ እንደሆኑ ተጠቁሟል።
👍7