African Leadership Excellence Academy
2.35K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነምግባር ኮሚሽን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዛሬው እለት #በአፍሪካአመራርልህቀትአካዳሚ ተጀምሯል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የስነ-ምግባር ሰብሳቢ፣ዶ/ር ደስታ ተስፋው የኢንስፔክሽንና የሥነምግባር ኮሚሽን ም/ሰብሳቢ፣ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የኮሚሽኑ ዋና ፅ/ቤት ሀላፊ፣የኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የክልልና ከተማ አስተዳደሮች ኮሚሽን አባላትና የፌዴራል ተቋማት ኮሚሽን አባላት ተገኝተዋል።
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይም የአፍሌክስ የለውጥ የማስፋት እና ሽግግር ስትራቴጂ ቀርቧል። አፍሌክስ በሶስት ዓመታት ውስጥ ሊሰራቸው ያቀዳቸው ስራዎች ለተሳታፊዎች ገለጻ የተደረገ ሲሆን ከመድረኩም አስተያየትና ጥያቄ ቀርቦ በቂ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
መድረኩን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የስነ-ምግባር ኮሚሽን ሰብሳቢ ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት #ለአፍሪካአመራርልህቀትአካዳሚምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#በአፍሪካአመራርልህቀትአካዳሚ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚካሄደው አራተኛው ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በፓርቲው እና በኮሚሽኑ የፀደቁ አዳዲስ መመሪዎች ላይ እንዲሁም “በፓርቲ የሀብት አስተዳደር መመሪያዎች እና በኮሚሽኑ ሚና” የሚሉ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግበት ታውቋል።
👍1