በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ በረጅም እና በመካከለኛ ጊዜ ውስጥ የሚሰሩ ስራዎችን በመለየት ወደ ስራ መግባት እንደሚቻል ተናግረዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ክቡር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ስለ አካዳሚው የሶስት ዓመት ስትራቴጂ እና ፕሮግራም ገለጻ አድርገዋል።
አቶ ዛዲግ እንደጠቀሱት አፍሌክስ የአህጉሪቱን እና የሀገራችንን አመራሮች ለማብቃት ስልጠና ብቻውን በቂ እንዳልሆነ በማመኑ አራት ጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ነድፎ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ ተናግረዋል። በእነዚህ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፎች ውስጥም ከፍተኛ አመራሮች አቅማቸውን እንደሚገነቡ እና ሀሳብ እያፈለቁ የምርምር ስራዎችን እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) አፍሌክስ ይዞ የተነሳው የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የሚኖረውን ጥቅም አስታውሰው፤ በተለይም ከመንግስት ልማት አቅጣጫ እና የብልጽግና መስመር ጋር በተናበበ መልኩ የተቀረጹት የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ለሀገር እድገት ግብዓት እንደሚሆን ተናግረዋል። ተቋማቸውም ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ማድረግ የሚችለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ለሀሳብ ማመንጫ ማዕከል የሚሆን የመሰረተ ልማት ግንባታም በአፍሌክስ ውስጥ ለመስራት ውይይት እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ላይ እንደሚደርሱም አሳውቀዋል።

የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ክብርት ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ጋር የአፍሌክስን ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ስትራቴጂ ገለጹ።
የአካዳሚው የሪፎርም የማስፋት እና የሽግግር ስራዎች ላይ ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ጋር አብረው ለመስራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ክብርት ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደተናገሩት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሶስት ዓመታት ውስጥ ሊፈጽም ያቀዳቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች የሀገራችንን አመራር ወደ ታላቅ ከፍታ የሚያሸጋግሩ እና ትውልድን የሚቀርጹ ናቸው ብለዋል።
ክብርት ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የአፍሌክስ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍም ከሀገር አልፎ በአፍሪካ ላይ ተጽእኖ በመፍጠር ከአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑ የሚኒስትር መስሪያ ቤታቸው ድጋፍ ባስፈለገበት ሁሉ አብረው ለመስራት ቃል ገብተዋል።
በአፍሌክስ ውስጥም የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ለመገንባትም ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹት ክብርት ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ሰፊ ውይይት እና ዝርዝር ጥናቶችን በማድረግ ወደ ስራ ለመግባት የቴክኒክ ኮሚቴ አቋቁመዋል።

የሳውዘርን ኮፐሬሽን ኦርጋናይዜሽን ሴክሬተሪ ጄኔራል መንሱር ቢን ሙሳላም Mansssour Bin Mussallam Secretary General of the Organization of Southeren Cooperation በበኩላቸው በቀረቡት ፕሮጀክቶች እና በአመራር ልማት ፕሮግራሞቹ ላይ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራምን በቴክኒክ ለመደገፍ እና በመሰረተ ልማት ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝርዝር ውይይት እንደሚያስፈልግ ተናግረው የቴክኒክ ኮሚቴው በሚያቀርበው ምክረ ሀሳብ መሰረት አጋርነታቸውን እንደሚገልጹ ተናግረዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከሳውዘርን ኮፐሬሽን ኦርጋናይዜሽን ሴክሬተሪ ጄኔራል መንሱር ቢን ሙሳላም Mansssour Bin Mussallam Secretary General of the Organization of Southeren Cooperation (OSC)ጋር ተወያዩ።
ለሴክሬተሪ ጄኔራሉ ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር በርዕሰ አካዳሚው ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ እና በሀገራችን የነበረውን የስልጠና ስርአት ወደ አመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳደግ ሰፊ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ለዚህም የሚሆን አራት ጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
አካዳሚው አፍሪካዊ መልክና ይዘት እንዲኖረውም እየተሰራ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ዛዲግ፤ የታቀደውን ለመፈጸም የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ እና እገዛ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
አፍሌክስን የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግም ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ የሚል ፕሮጀክት መቀረጹን ያስታወሱት ርዕሰ አካዳሚው፤ ሸገር ሲቲን ከዳቮስ ከተማ ጋር በእህትማማች ከተማ ለማገናኘት ስራ መጀመሩንም ተናግረዋል።
ሳውዘርን ኮፐሬሽን ኦርጋናይዜሽን በአፍሪካ ፕሮግራሞች ላይ በዲዛይን እና ፕሮግራም ቀረጻ ፤ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን በአፍሌክስ ውስጥ እንዲያደርጉ እና በሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ ከአፍሌክስ ጋር በትብብር እንዲሰራ አቶ ዛዲግ ግብዣ አቅርበዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በበኩላቸው ክቡር አቶ ዛዲግ በአፍሌክስ ውስጥ በተመደቡ በወራት ውስጥ ታላቅ ሀገራዊ የአመራር ልማት ፕሮግራም እና ፕሮጀክቶችን ቀርጸው ወደ ስራ ለመግባት ያደረጉትን ጥረት አድንቀው፤ ከአመራር ጋር በተያያዘ ያለውን የኢትዮጵያን ፖለቲካል ኢኮኖሚ ስብራት ለመጠገን የአመራር ልማት ፕሮግራሞቹ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።
በአፍሌክስ ውስጥ ውጤታማ አመራር ማፍራት እና ማብቃት ከተቻለ ምርት እና ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ ከአካዳሚው ጋር በመሆን ለአመራር ልማት ዕድገት የበኩላቸውን አሻራ ማሳረፍ እንደሚፈልጉ ተናግረው በዝርዝር በማየት በምን መልኩ ከአፍሌክስ ጋር መስራት እንደሚችሉ መነሻ ጥናት እንዲዘጋጅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ የቴክኒክ ኮሚቴም በሁለት ሳምንት ውስጥ መነሻ ሀሳብ እንዲያቀርብ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ጋር ተወያዩ።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች አብራርተዋል።
አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ለይቶ ለስምንቱ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ዛዲግ፤ አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመታት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
አፍሌክስን የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግም ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ የሚል ፕሮጀክት ተቀርጾ እየተሰራ እንደሆነ ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአፍሌክስ ጋር አብሮ እንዲሰራ አቶ ዛዲግ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ዛዲግ አያይዘውም በአፍሌክስ ውስጥ ከሚገነቡ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል አመራር ማዕከል እንዲገነባ እና የሚኒስቴሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በማእከሉ በመጠቀም በጥናትና ምርምር ስራ ውስጥ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የዋር ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እና ተማሪዎች የአፍሌክስን ፋሲሊቲ ጎበኙ።
ለከፍተኛ አመራሮቹና ተማሪዎቹ አቀባበል ያደረጉት የአፍሌክስ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ሲሆኑ አካዳሚው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ውስጥ እንደሆነ ጠቅሰው ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ልዩ የአርሚ የአመራር ልማት ፕሮግራም ለመቅረጽ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ለልኡካን ቡድኑ የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ገለጻ ያደረጉት አቶ መስፍን በሀይሉ ሲሆኑ አፍሌክስ በአመራር ስርአት ውስጥ ያሉ ስብራቶችን ለመጠገን እንዲችል አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ እንደገባ ጠቅሰው አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ተቀርጸዋል ብለዋል።
ጉብኝት ካደረጉ እና ገለጻውን ከተከታተሉ የዋር ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እና ተማሪዎች ውስጥ አራት ብርጋዴር ጄኔራሎች፤ ሁለት የውጭ ሀገር ጄኔራሎች፤ የረጅም እና የአጭር ኮርስ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።