African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከ UNDP, UNIDO, UNESCO, እና UN ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ስለ አፍሌክስ ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ውይይት ያደረጉት ከዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ (Dr. Ramiz Alakbarov, UN Assistant Secretary General and UN Resident and Humanitarian Coordinator) ከአኡሬሊአ ፓትሪዚአ (Aurelia Patrizia Calabro, UNIDO Representative and Director of the Regional Office) ከሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) እና ከዶ/ር ሪታ ቢሶናኡዝ (Dr. Rita Bissoonauth, UNESCO Director of Addis Ababa Liaison Office to AU & UNECA and Representative to Ethiopia) ጋር ነው። የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከUN ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለሀላፊዎቹ አብራርተዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎቹ ስለ አፍሌክስ በተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው ከአፍሌክስ ጋር አብረው ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ሰጥተዋል።
የ UNDP, UNIDO, UNESCO, እና UN ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ካነሷቸው ጥያቄና አስተያየቶች መካከል አካዳሚው አፍሪካዊ ቅርጽ እና ይዘት እንዲኖረው በሚደረገው ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ዙሪያ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ኤምባሲዎች እና ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ጋር አብሮ ለመስራት ስላቀደው ዕቅድ፤ የማስተርስ ዲግሪዎቹን በተመለከተ ስላለው ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና፤ የአመራር ልማት ፕሮግራሙን ወደ ስራ ለመቀየር ያለው ዝግጅት ምን እንደሚመስል፤ እና ከሌሎች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በምን መልኩ ለመስራት እንደታቀደ የጠየቁ ሲሆን አቶ ዛዲግ አብርሃ ማብራሪያ ሰጥተዋቸዋል።
ከ UNDP, UNIDO, UNESCO, እና UN ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከአፍሌክስ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን እና ዝርዝር ጥናት በማድረግ ዽጋፍ በተጠየቁባቸው መስኮች አብረው ለመስራት ተስማምተዋል። የአካዳሚውን ፋሲሊቲም ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች በአፍሪካ አመራር ልህቀት ቅጥር ውስጥ ለሚያሰሩት የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ የመስክ ምልከታ አደረጉ።
በክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተመራው ልዑክ በአፍሌክስ ውስጥ ለሚሰራው Center for Medemer and African Integration ማዕከል ግንባታ የሚሆነውን ቦታ ተመልክተዋል።
በመስክ ምልከታው ላይ ግንባታውን የሚያከናውነው ኮንትራክተርም ተገኝቶ የቦታውን የቀደመ ዲዛይን እና አሁን ያለበትን ሁኔታ ተመልክቶአል።
የራሺያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ከፍተኛ አመራሮች የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን የአመራር ልማት ፕሮግራም እንደሚደግፉ ገለጹ።
ስለ አፍሌክስ የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስትራቴጂም ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በሱሉልታ የሚገኘውን የአመራር ልማት ማዕከልንም ጎብኝተዋል።
የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስትራቴጂ ላይ ሰፊ ገለጻ ያደረጉት የአፍሌክስ የውስጥና የውጭ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ዮሐንስ ሣሀለማሪያም ሲሆኑ አካዳሚው ከራሺያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የምርምር ማእከላት ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ጠቅሰው የሳይንስ እና ባህል ማዕከሉ በራሺያ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የስልጠና ማዕከላት ጋር ለሚኖረው ስትራቴጂያዊ ትስስር እና ትብብር የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ አቶ ዮሐንስ ጠይቀዋል።
የራሺያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ዳይሬክተር አሌክሳንደር ኤቭጊየስትኔቭ በበኩላቸው አካዳሚው ሊተገብራቸው ያቀዳቸው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስትራቴጂ እቅድ ለአገሪቱ ብቻ ሳይሆን እንደ አህጉር ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን በማመን በራሺያ ከሚገኙ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አመራሮች እና የስራ ክፍሎች ጋር በመወያየት ይህንን ራዕይ እንደሚያስገነዝቡና ለስኬቱም በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገቡ አስረድተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም አሌክሳንደር ኤቭጊየስትኔቭ ራሺያ በተለያዩ ዘርፎች የስመጥር ምሁራንና ተመራማሪዎች መፍለቂያ መሆኗን ገልጸው፤ በአገራቸው ከሚገኙ አንጋፋ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የምርምር ማዕከላት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን እና ከአካዳሚው በሚቀርቡ ክፍተትን መሰረት ያደረጉ የስልጠና፤ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማማከር ፍላጎቶች አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
በተለይም የሱሉልታ የአመራር ልማት ማዕከልን የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ በተያዘው ዕቅድ ላይ ራሺያ የበኩሏን እገዛ እንደምታደርግ በመግለጽ የተለያዩ አለምአቀፍ ፎረሞችና ኮንፈረንሶችን በማዕከሉ ለማድረግ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል፡፡