የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአፍሌክስ የአመራር ልማት ቅጥር ውስጥ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ለመገንባት ወሰነ።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ክቡር ሚኒስትሩ ገብረ መስቀል ጫላ ውሳኔውን ያሳወቁት ከአፍሌክስ ጋር በምን መልኩ መስራት እንደሚቻል ጥናት እንዲያደርግ የተቋቋመው ቴክኒካል ኮሚቴ ያቀረበውን መነሻ ሀሳብ ከተመለከቱ በኋላ ሲሆን የንግዱን እና የቀጠናዊ ትስስር ስራዎችን ለማጎልበት የሚያግዝ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል በአፍሪካ አመራር ልህቀት ቅጥር ውስጥ ለመገንባት ተቋማቸው እንደወሰነ ተናግረዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው በአመራር ልማት ዘርፍ የራሱን አሻራ ማሳረፍ እንደሚፈልግ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትሩ የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ለመደገፍ፤ በንግድ ዘርፍ እና በቀጠናዊ ትስስር የተሰማሩ ባለሀብቶችን በማስተባበር በርካታ አገልግሎትን በአንድ የያዘ ዘመናዊ የጥናት እና ምርምር ማዕከል በመገንባት፤ ሳይንሳዊ እና ችግር ፈች ሀሳቦችን ማፍለቅ እንደሚቻል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። የሚገነባው ማዕከልም የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራን ጨምሮ ሁሉንም መሰረታዊ አገልግሎቶች የሚሰጥ እንዲሆን እንደሚፈልጉ ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በአፍሌክስ የሽልማት መስክም ቴክኒካል ኮሚቴው ካቀረበው መነሻ ጥናት በተጨማሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲካተቱ የሚፈልጋቸው የአፍሌክስ የአመራር የሽልማት ዘርፎች እንዳሉ የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ በተለይም ምርጥ ተመራማሪ፤ የንግድ ባለሙያ፤ የንግድ መሪ፤ የተቋም መሪ፤ ጅምላ ነጋዴ፤ ችርቻሮ ነጋዴዎች ተወዳድረው የሚሸለሙበት እንዲሆን ሀሳብ አቅርበዋል።
በሚኒስትር ዲኤታ የሚመራ የሀብት አፈላላጊ እና አሰባሳቢ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን የቴክኒክ ኮሚቴውም የተሰጡትን ተግባራት አጠናቆ በአስራ አምስት ቀናት ይዞ እንዲቀርብ ክቡር ሚኒስትሩ ገብረ መስቀል ጫላ ተናግረዋል።

የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአፍሪካ አመራር ልህቀትን የአመራር ልማት ፕሮግራም እና የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ለመደገፍ ያሳለፈውን ውሳኔ አድንቀው ለስራው መሳካት ከአፍሌክስ የሚጠበቀውን ሁሉ በማድረግ ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩ አምባሳደሮች ተናገሩ።
ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለሚሰሩ አምባሳደሮች፤ ሚሲዮኖች እና ዲፕሎማቶች ስለ አፍሌክስ የአመራር ልማት ፕሮግራም እና የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለአምባሳደሮች፤ ለሚሲዮኖች እና ለዲፕሎማቶች ስለ አፍሌክስ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች እና የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ሰፊ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎችም አብራርተዋል።
አቶ ዛዲግ አፍሌክስ የጀመረውን የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳካት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አስታውሰው፤ በተለይም ከአውሮፓ እና አሜሪካ፤ ከእስያ፤ ከመካከለኛው ምስራቅ፤ ከላቲን አሜሪካ እና ከአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራሎች ጋር በመሆን አፍሌክስን የማስተዋወቅ እና ሀብት የማፈላለጉ ተግባር ውጤት እያመጣ እንደሆነ ገልጸው፤ በስራው ላይ ትብብር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን በመወከል በመላው ዓለም የሚሰማሩ አምባሳደሮች፤ ሚሲዮኖች እና ዲፕሎማቶችም የአፍሌክስን ተልእኮ እና ራዕይ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በማስተዋወቅ የቴክኒክ፤ የዕውቀት እና የገንዘብ ድጋፍ የሚገኝበትን መንገድ እንዲያመቻቹ አቶ ዛዲግ አብርሃ ጥሪ አቅርበዋል።
ገለጻውን የተከታተሉ አምባሳደሮች፤ ዲፕሎማቶች እና ሚሲዮኖች በበኩላቸው አፍሌክስ ይዞ የተነሳውን ራዕይ አድንቀው፤ አዲስ የተቀረጸውን የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ለመደገፍ በየተመደቡበት ሀገራት ያለውን ሁኔታ በማጥናት እና ለአፍሌክስ የሚሆኑትን በመለየት ስትራቴጂያዊ አጋርነት እና ሀብት የሚገኝበትን መንገድ እንደሚያመቻቹ ተናግረዋል።
በተለይም የፓኪስታን፤ የጀርመን፤ የዩናይትድ ኪንግደም፤ የመካከለኛው ምስራቅ እና የሞሮኮ አምባሳደሮች እንደተናገሩት አፍሌክስ ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እንደ ድልድይ ሆኖ ለማገናኘት የጀመረውን ጥረት ለማገዝ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን-ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ያለው በበኩላቸው ስለ አፍሌክስ በተደረገላቸው ማብራሪያ አመስግነው በሌሎች ሀገራት የሚገኝ የአመራር ማሰልጠኛ ማዕከል እና መሰረተ ልማት አይነት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለመስራት መታቀዱ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው አፍሌክስ የጀመረው ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ኢትዮጵያን እና አፍሪካን የሚያጎላ በመሆኑ በወጣቶች ስራ ፈጠራ እና ልማት፤ በሴቶች አቅም ግንባታ፤ በሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ዙሪያ ከፋውንዴሽኑን ተልዕኮ እና ዓላማ ጋር በተናበበ መልኩ ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የአፍሪካ አመራር ለህቀት አካዳሚ እና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን-ኢትዮጵያ በጋራ ሊሰሩ በሚችሉባቸው መስኮች ዙሪያ ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለማስተር ካርድ ፋውንዴሽን-ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ያለው የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች እና የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ሰፊ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎችም አብራርተዋል።
ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን-ኢትዮጵያ በወጣቶች ልማት እና ስራ ፈጠራ ዙሪያ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ዛዲግ በአፍሌክስ ጠቅላላ እና ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ ተተኪ እና ሴት አመራሮችን አቅም ለመገንባት በተያዘው ዕቅድ ውስጥ ፋውንዴሽኑ በፕሮግራም ቀረጻ እና በቴክኒክ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እንደ ስሙ አፍሪካዊ ቅርጽ እና ይዘት እንዲኖረው በተሰራው ሪፎርም ውስጥም አፍሪካውያን ወጣቶች የሚገናኙበት እና ስለ አህጉሪቱ ልማት በሰፊው ተወያይተው የስራ ፈጠራ ችሎታቸውን የሚያዳብሩበት ተቋም እንዲሆን ፋውንዴሽኑ የመሰረተ ልማት፤ የማስተርስ ትምህርት እና የአመራር ልማት ፕሮግራም ዲዛይን ላይ ከአፍሌክስ ጋር ሊሰራ የሚችልበት መንገድ እንዳለ የጠቆሙት አቶ ዛዲግ የፋውንዴሽኑ ጉባኤዎችም በአፍሌክስ ማዕከል ውስጥ በሚደረጉበት ሁኔታ ላይ ሀሳብ አቅርበዋል።