አቶ ዛዲግ አብርሃ ከተባበሩት መንግስታት ረዳት ጄኔራል ሴክሬታሪ ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ Dr. Ramiz Alakbarov, UN Assistant Secretary General and UN Resident and Humanitarian Coordinator ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
አፍሌክስን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የልማት ድርጅቶች እንዲያውቁት እና አብረውን እንዲሰሩ እንፈልጋለን ያሉት አቶ ዛዲግ፤ ለዚህም የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራም በሰፊው በማስተዋወቅ በሀገር ውስጥ ሀብት ብቻ ሊሰሩ የማይችሉ የመሰረተ ልማቶች እና የፕሮግራም ቀረጻዎች ላይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ዶክተር ራሚዝ በበኩላቸው የአፍሌክስን መሰረተ ልማትና የተቀረጸውን የአመራር ልማት ፕሮግራም አድንቀው ለዚሁ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ እና ሽግግር ዕውን መሆን አብረው ሊሰሩ የሚችሉ ተቋማትን በማፈላለግና ከአፍሌክስ ጋር አብረው እንዲሰሩ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም (Reform)፤ በማስፋት (Scaling Up) እና በሽግግር (Transformation) ዘርፎቹ ላይ ያቀዳቸውን ስራዎች ለኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለጻ አደረገ።
ሰንዳፋ በሚገኘው የፖሊስ ዩኒቨርስቲ በመገኘት ገለጻውን ያደረጉት የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ሲሆኑ ከከፍተኛ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም ፌዴራል የፖሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ማዕከሉን በአፍሌክስ ውስጥ ለመገንባት በመወሰኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በማዕከሉ ውስጥም ለሀገራችን እና ለአፍሪካ ሰላም የሚሰሩ ሀሳቦችን በማመንጨት በኩል ሰፊ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ በበኩላቸው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም (Reform)፤ ማስፋት (Scaling Up) እና ሽግግር (Transformation) ስትራቴጂ ከሀገር አልፎ ለአፍሪካውያን የአመራር ልማት ፕሮግራም እና የምርምር ማዕከል ለመሆን በሚያስችል መልኩ የተነደፈ በመሆኑ ዩኒቨርስቲው ከአፍሌክስ ጋር በመስራት ዓላማው እንዲሳካ ያደርጋል ብለዋል።
ፕሬዚደንቱ አያይዘውም የፖሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ማዕከሉም በአፍሌክስ ውስጥ እንዲሆን መወሰኑ ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ ሰላም እና ደህንነት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን ለማሳየት ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር እና አስራ ሁለት የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ባሉበት ስፍራ ላይ መሆኑ ሰፊ ምርምርና ጥናት ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
ሌሎች የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮችም በሰጡት ሀሳብ ማዕከሉ መገንባቱ ለፖሊስ ሙያ የምርምር ስራ ሰፊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ገለጻ አደረጉ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ እንደገለጹት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የአመራር ልማት ፕሮግራም የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
አፍሌክስ ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ጋር በመሆን በዘርፉ ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራም በመቅረጽ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ መሆኑን የገለጹት አቶ ዛዲግ፤ ተቋሙ ያለውን ሰፊ የባለሙያ አቅም እና ልምድ በመጠቀም ከአፍሌክስ ጋር እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል። የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል በመገንባትም በዘርፉ ያለውን የጥናትና ምርምር ስራዎች በማጎልበት ሳይንሳዊ እና ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶችን ማፍለቅ እንደሚገባ ርዕሰ አካዳሚው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ በበኩላቸው አፍሌክስ ይዞ የተነሳውን አህጉር አቀፍ የሪፎርም፤ የማስፋት እና የሽግግር ዕቅድ አድንቀው ለተግባራዊነቱ ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የአመራር ልማት ፕሮግራሙ በአደአ ከተማ ከሚገኘው የአገልግሎቱ የሊደርሺፕ ኢንስትትዩት ጋር በተናበበ መልኩ እንዴት ሊሰራ እንደሚችል ተነጋግረውበታል።

የመሰረተ ልማት ድጋፍን በተመለከተም በአፍሌክስ ውስጥ የሚገነቡ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላትን በመገንባት በኩል የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ፍላጎት እንዳለው ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶክተር በሪሶ አመሎ ገለጹ ሲሆን ለአፈጻጸሙም ከሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች ጋር በመነጋገር ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልጸዋል።
ሌሎች የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችም በአፍሌክስ የሪፎርም፤ የማስፋት እና የሽግግር ዕቅድ ላይ ጥያቄ እና አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ አብርሃ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል።

አቶ ዛዲግ አብርሃ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በውይይቱ ላይ የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎችን አብራርተዋል።
ርዕሰ አካዳሚው ባቀረቡት ገለጻ ላይ እንደጠቀሱት አካዳሚው በልዩ የቢዝነስ አመራር ልማት ፕሮግራሙ የዘርፉን አመራርና ባለሙያዎች ለማብቃት ማቀዱን ገልጸው በፕሮግራም ቀረጻ እና ትግበራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
አቶ ዛዲግ አያይዘውም በአፍሌክስ ውስጥ ከሚገነቡ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የአመራር ማዕከል እንዲገነባ እና የባንኩ አመራሮችና ባለሙያዎች በማእከሉ በመጠቀም በጥናትና ምርምር ስራ ውስጥ የተሻለ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ በበኩላቸው አፍሌክስ ለትውልድ የሚሸጋገር እና ከፍተኛ አመራሩን በተሟላ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ውስጥ ለማብቃት ማቀዱን አድንቀው ከተቋማቸው ጋር በምን መልኩ መስራት እንደሚቻል ሰፋ ያለ የባለሙያዎች ውይይት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ከዲጂታል የአመራር ማዕከል ግንባታ ጋር በተያያዘም ከባንኩ የቦርድ አመራሮች እና ይህንኑ ከሚያጠና የባለሙያ ቡድን ጋር በመነጋገር በሚቀርበው ምክረ ሀሳብ መሰረት ከአፍሌክስ ጋር አብሮ ለመስራት ሀሳብ አቅርበዋል።

አቶ ዛዲግ አብርሃ ከግሎባል ኢነርጂ አሊያንስ ፎር ፒፕል ኤንድ ፕላኔት (The Global Energy Alliance for People and Planet) (GEAPP) ካንትሪ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከካንትሪ ዳይሬክተሯ ኤናስ ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለካንትሪ ዳይሬክተሯ ገለጻ አብራርተዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
አፍሌክስን የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግም ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ የሚል ስትራቴጂ ተቀርጾ እየተሰራ እንደሆነ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን በአፍሌክስ ውስጥ እንዲደረጉ ለዳይሬክተሯ ጥሪ አቅርበዋል።
ለግሪን ኢኮኖሚ የሚሰሩ ተቋማትም በአፍሌክስ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ውስጥ የመሰረተ ልማት ግንባታ በማካሔድ አብረው እንዲሰሩ እና የአፍሌክስ ስትራቴጂያዊ አጋር እንዲሆኑ አቶ ዛዲግ ሀሳብ አቅርበዋል።