African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ኤናስ አብደላ በበኩላቸው ስለ አፍሌክስ በተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው ከአፍሌክስ ጋር አብረው ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ ያለው የኢነርጂ ሀይል እና አጠቃቀም ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ ሰፊ ስራ እንደሚጠይቅ እና የዓለም አቀፉን ግብ ለማሳካትም ጥናት እና ምርምሮችን ማድረግ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ዘርፍ አፍሌክስ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ለመገንባት ያቀደው ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ካንትሪ ዳይሬክተሯ ኤናስ በፕሮግራም ቀረጻ፤ በመሰረተ ልማት እና በቴክኒካል ድጋፍ መስኮች ከአፍሌክስ ጋር አብረው ለመስራት ተጨማሪ ውይይት እንዲኖር የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። የአካዳሚውን ፋሲሊቲም ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በአፍሌክስ የአመራር ልማት ቅጥር ውስጥ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ለመገንባት ተስማማ።
ኮሚሽኑ ይህን የገለጸው ከአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከክቡር ኮሚሽነሩ ጋር በነበራቸው ውይይት በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን የአካዳሚው የሪፎርም የማስፋት እና የሽግግር ስራዎች ላይ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር አብረው ለመስራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ክቡር ኮሚሽነሩ አቶ ደበሌ ቃበታ እንደተናገሩት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሶስት ዓመታት ውስጥ ሊፈጽም ያቀዳቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች የሀገራችንን አመራር ወደ ታላቅ ከፍታ የሚያሸጋግሩ እና ትውልድን የሚቀርጹ በመሆናቸው አካዳሚው ውስጥ ከሚገነቡ አስራ ሶስት የሀሳብ ማመንጫ ማእከላት ውስጥ አንዱን በመገንባት በጉምሩክ ዘርፍ ጥናትና ምርምር እንዲደረግበት እንደወሰኑ ገልጸዋል።
ክቡር ኮሚሽነሩ አያይዘውም ኮሚሽናቸው ለአገር ልማትና ዕድገት እንደሚሰራ ገልጸው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍም ከሀገር አልፎ በአፍሪካ ላይ ተጽእኖ በመፍጠር ከአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑ የኮሚሽኑ ድጋፍ ባስፈለገበት ሁሉ አብረው ለመስራት ቃል ገብተዋል።

አቶ ዛዲግ በበኩላቸው በጠቅላላ እና በልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ በጋራ ለመስራት እና ክቡር ኮሚሽነሩ ካላቸው ዓለም አቀፍ የሽልማት ልምድ በመነሳት በአፍሌክስ የአመራር ሽልማት ማዕቀፍ ላይ ልምዳቸውን እና ተሞክሮአቸውን እንዲያካፍሉ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከ UNDP, UNIDO, UNESCO, እና UN ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ስለ አፍሌክስ ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ውይይት ያደረጉት ከዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ (Dr. Ramiz Alakbarov, UN Assistant Secretary General and UN Resident and Humanitarian Coordinator) ከአኡሬሊአ ፓትሪዚአ (Aurelia Patrizia Calabro, UNIDO Representative and Director of the Regional Office) ከሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) እና ከዶ/ር ሪታ ቢሶናኡዝ (Dr. Rita Bissoonauth, UNESCO Director of Addis Ababa Liaison Office to AU & UNECA and Representative to Ethiopia) ጋር ነው። የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከUN ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለሀላፊዎቹ አብራርተዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎቹ ስለ አፍሌክስ በተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው ከአፍሌክስ ጋር አብረው ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ሰጥተዋል።
የ UNDP, UNIDO, UNESCO, እና UN ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ካነሷቸው ጥያቄና አስተያየቶች መካከል አካዳሚው አፍሪካዊ ቅርጽ እና ይዘት እንዲኖረው በሚደረገው ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ዙሪያ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ኤምባሲዎች እና ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ጋር አብሮ ለመስራት ስላቀደው ዕቅድ፤ የማስተርስ ዲግሪዎቹን በተመለከተ ስላለው ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና፤ የአመራር ልማት ፕሮግራሙን ወደ ስራ ለመቀየር ያለው ዝግጅት ምን እንደሚመስል፤ እና ከሌሎች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በምን መልኩ ለመስራት እንደታቀደ የጠየቁ ሲሆን አቶ ዛዲግ አብርሃ ማብራሪያ ሰጥተዋቸዋል።
ከ UNDP, UNIDO, UNESCO, እና UN ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከአፍሌክስ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን እና ዝርዝር ጥናት በማድረግ ዽጋፍ በተጠየቁባቸው መስኮች አብረው ለመስራት ተስማምተዋል። የአካዳሚውን ፋሲሊቲም ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች በአፍሪካ አመራር ልህቀት ቅጥር ውስጥ ለሚያሰሩት የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ የመስክ ምልከታ አደረጉ።
በክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተመራው ልዑክ በአፍሌክስ ውስጥ ለሚሰራው Center for Medemer and African Integration ማዕከል ግንባታ የሚሆነውን ቦታ ተመልክተዋል።
በመስክ ምልከታው ላይ ግንባታውን የሚያከናውነው ኮንትራክተርም ተገኝቶ የቦታውን የቀደመ ዲዛይን እና አሁን ያለበትን ሁኔታ ተመልክቶአል።