የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በኢንዱስትሪ አመራር ልማት ፕሮግራም ላይ ለመስራት ያቀደው ሪፎርም እና ሽግግር የዘርፉን ክፍተት ለመድፈን ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ክቡር መላኩ አለበል ገለፁ::
የአካዳሚውን ሪፎርም ሽግግር እና ማስፋት በተመለከተ ለክቡር ሚኒስትሩ እና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ገለፃ ተደርጓል::
የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ እንደገለፁት ከሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ውስጥ የኢንዱስትሪ አመራር ልማት አንዱ በመሆኑ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል::
አቶ ዛዲግ አያይዘውም አካዳሚው በሪፎርም እና ማስፋፋት እቅዶቹ ውስጥ ከያዛቸው ስራዎች መካከል አስራ ሁለት የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ስራ ላይ እንደሚውሉ እና ከኢንዱስትሪ ጋር የሚገናኘውን በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል::
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ክቡር መላኩ አለበል በበኩላቸው አፍሌክስ የጀመረው ሪፎርም እና ማስፋፋት የኢንዱስትሪ ዘርፉን የአመራር ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ጠቅሰው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የልማት አጋሮች እና ባለሀብቶች ጋር በመሆን የአካዳሚውን ተልእኮ ለማሳካት እንደሚሰሩ እና አፍሌክስን ለባለ ድርሻ አካላት በማስተዋወቅ አለም አቀፍ ጉባኤዎች በአካዳሚው እንዲደረጉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይሰራል ብለዋል::
ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል::

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በተቋሙ የሪፎርም፤ የሽግግርና የማስፋት ስራዎች ዙሪያ ለክቡር ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እና ለከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ገለጻ አድርገዋል።
አፍሌክስ አራት ጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ነድፎ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ዛዲግ አብርሃ፤ በውሀና ኢነርጂ ዘርፍ ውስጥ ያሉ የስልጠና፤ የጥናት እና የምርምር ስራዎች ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመለየት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመሆን ለመስራት ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ካለው ሰፊ ልምድና አቅም አንጻር በተመረጡ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ቀረጻ እና ለፕሮግራሞቹ የሚያስፈልገውን ሀብት መሸፈን ላይ ትኩረት አድርጎ ቢሰራ የተቋሙን የመፈጸም አቅም ማሳደግ እንደሚቻል የጠቀሱት አቶ ዛዲግ አፍሌክስም ለዚሁ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ከፍተኛ የስልጠና ፍላጎት እንዳለው ጠቅሰው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም፤ በሽግግር እና በማስፋት የያዛቸውን ስራዎች ለማገዝ አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም አካዳሚው በጥናትና ምርምር ማዕከሉ አህጉር አቀፍ የውሀ እና ኢነርጂ ጉዳዮችን አካቶ ለመስራት ማቀዱ በዘርፉ ያለውን ክፍተት እና ውስንነት ለማረምና ለማስተካከል እንደሚያግዝ ጠቅሰው ለዚሁ እንዲረዳ በአጭር እና በረጅም ጊዜ የሚከናወኑ ተግባራትን የሚያመላክት የመግባቢያ እና የተግባር ማስፈጸሚያ መነሻ እንዲዘጋጅ ሀሳብ አቅርበዋል።

ሌሎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸው በዘርፉ የሚዘጋጁ ዓለምአቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጉባኤዎች እና ወርክሾፖች በአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ እንዲካሔዱ የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 28 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.