African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የዕውቀት እና የልህቀት ማዕከል ለመሆን የጀመራቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች አበረታች መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ገለጹ።
አካዳሚው በሪፎርም (Reform)፤ በማስፋት (Scaling Up) እና በሽግግር (Transformation) ዘርፎች ላይ ሊሰራ ያቀዳቸው ስራዎች ለክቡር ሚኒስትሩ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ አብርሃ የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች በተመለከተ ባቀረቡት ገለጻ ላይ እንደጠቀሱት አካዳሚው በትምህርት አመራር ልማት ፕሮግራሙ የዘርፉን አመራርና ባለሙያዎች ለማሰልጠን ማቀዱን ገልጸው በፕሮግራም ቀረጻ እና ትግበራ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው አካዳሚው የዕውቀት እና የልህቀት ማዕከል ለመሆን ያቀዳቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው በስፔሻላይዝድ የአመራር ልማት ፕሮግራም ስር ያሉ ስልጠናዎችን ውጤታማ ለማድረግ ከከፍተኛ የትምህርት እና የምርምር ተቋማት ጋር መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም አካዳሚው የዕውቀት፤ የሀሳብ ማመንጫ እና የማሰላሰያ ማዕከል ለመሆን ዓለምአቀፍ ተሞክሮን እንደመነሻ መውሰዱን አድንቀው በተለይም ሱሉልታን እንደ ዳቮስ በሚለው የማስፋት ዕቅድ ውስጥ የተለያየ አመለካከት ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የራሳቸውን አሻራ እንዲያኖሩ ያግዛል ብለዋል።
የፈጠራ ሰዎችን አቅም ለመገንባት እና በሀሳብ የበላይነት የሚያምን አመራር ለመቅረጽም ቅድሚያ የሚሰጣቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል።
ለመላው የአካዳሚያችን አመራሮች እና ሰራተኞች እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ!!
በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ::
ዛዲግ አብርሃ
ርዕሰ አካዳሚ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም (Reform)፤ በማስፋት (Scaling Up) እና በሽግግር (Transformation) ዘርፎቹ ላይ ያቀዳቸው ስራዎች በቢዝነሱ መስክ ያለውን የታለንት ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ኢድ ገለጹ።
አቶ ዛዲግ አብርሃ አካዳሚው በሪፎርም (Reform)፤ በማስፋት (Scaling Up) እና በሽግግር (Transformation) ዘርፎች ላይ ሊሰራ ያቀዳቸውን ስራዎች ለሆልዲንጉ ስራ አስፈጻሚዎች ገለጻ አድርገውላቸዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ አብርሃ የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች በተመለከተ ባቀረቡት ገለጻ ላይ እንደጠቀሱት አካዳሚው በቢዝነስ አመራር ልማት ፕሮግራሙ የዘርፉን አመራርና ባለሙያዎች ለማሰልጠን ማቀዱን ገልጸው በፕሮግራም ቀረጻ እና ትግበራ የኢንቨስትመንት ሆልዲንጉ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ኢድ በበኩላቸው አፍሌክስ የአመራር ለውጥ ባደረገ በአጭር ጊዜ ውስጥ የቀረጻቸው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች የሚያስገርሙ እና መዳረሻውን የሚያመላክቱ መሆናቸውን ጠቅሰው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከቢዝነስ አመራር ልማት ጋር በተያያዙ ያሉበትን ክፍተቶች ለይቶ እንዳስቀመጠና አፍሌክስ የያዛቸው ዕቅዶች የዘርፉን ክፍተት ለመሙላት የሚያግዙ በመሆናቸው ጠቀሜታቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ተናግረዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከኢንዶኔዥያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
በውይይቱ ላይ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም (Reform)፤ በማስፋት (Scaling Up) እና በሽግግር (Transformation) ዘርፎች ላይ ያቀዳቸውን ስራዎች ለኢንዶኔዥያ አምባሳደር አል ቡስይራ ባስኑር Al Busyra Basnur ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በሱሉልታ የሚገኘውን የአመራር ልማት ማዕከልንም ጎብኝተዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ አካዳሚው በሪፎርም፤ በማስፋት እና በሽግግር ሂደት ውስጥ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተቀመጠው ግብ ላይ ለመድረስም ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር መስራት ተገቢ በመሆኑ፤ ለክቡር አምባሳደሩ ጥሪ ተደርጎ እንደነበር አስታውሰው ክቡር አምባሳደሩም ግብዣውን ተቀብለው ከአፍሌክስ ጋር ለመወያየት በመምጣታቸው አመስግነዋል።
ክቡር አምባሳደር አል ቡስይራ ባስኑር Al Busyra Basnur ስለ አፍሌክስ የአመራር ልማት ፕሮግራም ሪፎርም ማስፋትና ሽግግር ማብራሪያ ካገኙ በሁዋላ በሰጡት አስተያየት ኤምባሲያቸው በኢትዯጵያ ውስጥ የሚደረጉ የልማት ስራዎችን በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው በአመራር ልማት ፕሮግራም ዘርፍም ከአፍሌክስ ጋር በትብብር ለመስራት እና የአካዳሚውን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተለይም አፍሌክስን የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ለማድረግ በተያዘው ሪፎርም ውስጥ የኢንዶኔዥያ ኤምባሲ በምርምር እና ጥናት መስክ ሰፊ ልምድ ያላቸውን ምሁራንና ተመራማሪዎችን በመጋበዝ በትብብር መስራት እንደሚቻል አስታውሰው የምርምር ውጤቶችን ተደራሽ ለማድረግም አፍሌክስ በያዘው የህትመት ሪፎርም አማካይነት ለማሰራጨት እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
በኢንዶኔዥያ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመነጋገርም የአመራር ልማት ፕሮግራሙን የሚደግፉ ምሁራንን እንደሚጋብዙ አምባሳደር አል ቡስይራ ባስኑር Al Busyra Basnur ገልጸዋል።
ክቡር አምባሳደሩ አያይዘውም የአፍሌክስን የሪፎርም የማስፋትና የሽግግር ስትራቴጂ ለኢንዶኔዥያውያን የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፤ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፤ ለምሁራን እና ለንግዱ ማህበረሰብ እንደሚያስረዱ የገለጹ ሲሆን ኤምባሲውና አፍሌክስ በትብብር የሚሰሩባቸውን ጉዳዮች በአጭር ጊዜ ለይተው ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸውም ስምምነት ላይ ተደርሷል። ክቡር አምባሰደሩ የጻፏቸውን ሶስት መጽሐፍትንም ለአቶ ዛዲግ በስጦታ አበርክተዋል።
የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራም፤ ተጠቃሚዎች እና መሰረተ ልማቱን በማስፋት ወደ ሽግግር ለማምራት በሚደረገው ሂደት ውስጥ የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አዎንታዊ ሚና እንዳለው ተገለጸ።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም (Reform)፤ በማስፋት (Scaling Up) እና በሽግግር (Transformation) ዘርፎች ላይ አስራ ሶስት የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ለይቶ ለስምንቱ ቅድሚያ በመስጠት ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስራ ሀላፊዎች ገልጸዋል።
ርዕሰ አካዳሚው እንደገለጹት አፍሌክስን ሪፎርም ለማድረግ፤ ለማስፋትና ለማሸጋገር አስራ ሶስት የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን በሶስት ዓመት ውስጥ ለመተግበር የሚረዳ ከ2500 በላይ ገጽ ያለው የስትራቴጂ ሰነድ መዘጋጀቱን ጠቅሰው ለስምንቱ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ቅድሚያ በመስጠት ወደ ስራ እንደገቡ እና የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራም፤ ተጠቃሚዎች እና መሰረተ ልማቱን በማስፋት ወደ ሽግግር ለማምራት በሚደረገው ሂደት ውስጥ የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አዎንታዊ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በበኩላቸው አፍሌክስ ያቀዳቸውን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ለመደገፍ እና አብሮ ለመስራት ተቋማቸው ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም አፍሌክስን የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ በሚሰራው ስራ ውስጥ ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ እና የአፍሪካ የፀረ-ሙስና ኤጀንሲ አባል በመሆኗ በቀጣይ የአስተናጋጅነት ሚናውን ስትወስድ በአፍሌክስ ውስጥ ሊሆን የሚችልበት ሰፊ ዕድል አለ ብለዋል።