African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር ፍሬያማ ውይይት አደረጉ።
ርዕሰ አካዳሚው ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሪፎርም እና ሽግግር ስራዎች ለጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ለተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ገለጻ አድርገዋል። ሁለቱም ተቋማት በጋራ ሊሰሩ በሚችሉባቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በትብብር በሚሰሩ ስራዎች ላይም መግባባት ላይ ተደርሷል።
ገለጻውን ተከትሎ አስተያየት የሰጡት ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም እና በሽግግር ስራዎቹ ውስጥ ያስቀመጣቸው ሀሳቦች እና ግቦች የሀገራችንን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸው በተለይም በህብረተሰብ እና በክሊኒካል ጤና የአመራር ዘርፎች በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ሁሉ አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ጤና ሚኒስቴር የአካዳሚውን ሪፎርምና ሽግግር ከዳር ለማድረስ አብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ክብርት ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጀኔራሎች ጋር ተወያዩ።
ርዕሰ አካዳሚው ተቋሙ በሪፎርምና በሽግግር ስራዎቹ ውስጥ ሊሰራቸው ስላቀዳቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ገለጻ አድርገዋል። አካዳሚው በሪፎርም ስራዎቹ ውስጥ አስራ ሶስት የትኩረት መስኮችን ለይቶ እየሰራ እንደሆነና ከእነዚህ ውስጥ ለስምንቱ ቅድሚያ በመስጠት ወደ ስራ እንደገባ አቶ ዛዲግ አብራርተዋል።
ተቋሙ እንደ ስሙ አፍሪካዊ እንዲሆን የሚያስችሉ የሪፎርም ስራዎች እንደተሰሩ የገለጹት አቶ ዛዲግ፤ በዋናነትም በምክትል ፕሬዚደንት የሚመራ የአፍሪካ ጉዳዮች ዘርፍ ለማቋቋምና ወደ ስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።
በሱሉልታ የሚገኘው የአመራር ልማት እና የስልጠና ማዕከል አፍሪካዊ ቅርጽና ይዘት እንዲኖረው እየተሰራ እንደሆነና አፍሪካውያን ወንድሞችንና እህቶችን በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ለማስተማር ካሪኩለም መቀረጹን ርዕሰ አካዳሚው አስታውሰው፤ ለፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብ መስረጽ አካዳሚው የድርሻውን ለማበርከት እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰዋል። የሀገራችንን እና የአፍሪካ አመራሮችን በስልጠና ለማብቃትም አራት ጠቅላላ ፕሮግራሞችና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች እንደተቀረጹ አቶ ዛዲግ ተናግረዋል።
በሌሎች ስምንት የአመራር ልማት ፕሮግራሞችና የሪፎርምና ስራዎች ላይ ገለጻ የተደረገላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጀኔራሎች አስተያየትና ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በርዕሰ አካዳሚው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በኢንዱስትሪ አመራር ልማት ፕሮግራም ላይ ለመስራት ያቀደው ሪፎርም እና ሽግግር የዘርፉን ክፍተት ለመድፈን ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ክቡር መላኩ አለበል ገለፁ::
የአካዳሚውን ሪፎርም ሽግግር እና ማስፋት በተመለከተ ለክቡር ሚኒስትሩ እና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ገለፃ ተደርጓል::
የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ እንደገለፁት ከሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ውስጥ የኢንዱስትሪ አመራር ልማት አንዱ በመሆኑ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል::
አቶ ዛዲግ አያይዘውም አካዳሚው በሪፎርም እና ማስፋፋት እቅዶቹ ውስጥ ከያዛቸው ስራዎች መካከል አስራ ሁለት የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ስራ ላይ እንደሚውሉ እና ከኢንዱስትሪ ጋር የሚገናኘውን በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል::
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ክቡር መላኩ አለበል በበኩላቸው አፍሌክስ የጀመረው ሪፎርም እና ማስፋፋት የኢንዱስትሪ ዘርፉን የአመራር ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ጠቅሰው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የልማት አጋሮች እና ባለሀብቶች ጋር በመሆን የአካዳሚውን ተልእኮ ለማሳካት እንደሚሰሩ እና አፍሌክስን ለባለ ድርሻ አካላት በማስተዋወቅ አለም አቀፍ ጉባኤዎች በአካዳሚው እንዲደረጉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይሰራል ብለዋል::
ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል::