African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
“This academy would no longer be for Ethiopians only and it would recruit other African professionals and deliver training for senior and emerging leaders from all corners of the continent. This transformational expansion will be realized soon.” Zadig Abreha, Chief of AFLEX
"Russia is collaborating with the Ethiopian government in leadership development and is eager to further share their experiences with Ethiopia in institutional building."
Yevgeny Terekhin
Russia’s Ambassador to Ethiopia
“Welcomed AFLEX’s appeal to support; reaffirming our government’s backing to the
academy’s transformational expansion.”
Shen Qinmin
Minister Counselor of the Chinese Embassy
አፍሌክስ - በታህሳስ
***********************
 የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ የቻይና አካዳሚ ኦፍ ገቨርናንስ (CNAG) ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል። ስለ አካዳሚው ሪፎርምና የሽግግር ስትራቴጂ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
 መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአፍሪካ፤ የእስያ፣ የአውሮፓ፤ የመካከለኛው ምስራቅ እና የላቲን አሜሪካ አምባሳደሮች ዲፕሎማቶችና ቆንስላዎች ስለ አካዳሚው አጠቃላይ የሪፎርም ስራ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
 የአፍሪካ ፣የአውሮፓ ፣የእስያ የመካከለኛው ምስራቅ እና የላቲን አሜሪካ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በሱሉልታ የስልጠና ማዕከል ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል፡፡
 ለኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ስለ አካዳሚው የሪፎርም ስራዎችና የሽግግር ስትራቴጂ ገለፃ ተደርጓል።
 ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች አካዳሚው እየሰራቸው ስላሉ ተግባራትና ወደፊት ለመሰራት ስላቀዳቸው ትልሞች ገለፃ ተደርጓል፡፡
 ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመራሮች ስለ አካዳሚው ሽግግር እና ሪፎርም ገለፃ ተደርጓል።
 ለትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አመራሮች ስለ አካዳሚው አገልግሎትና የሽግግር ስትራቴጂ ገለፃ ተደርጓል፡፡
 ለደቡብ ሱዳን የብሔራዊ ደህንነት ቢሮ አመራር ስለ አካዳሚው የሽግግር ስትራቴጂ ገለፃ ተደርጎላቸው በአካዳሚው ለመሰልጠን ፍላጎታቸውን ገልጸዋል፡፡
 JICA Ethiopia (Japan International Cooperation Agency) ከፍተኛ ተወካይ ሺንታሮ ታካኖ እና ሌሎች አመራሮች ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሽግግር ስትራቴጂ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ከአካዳሚው ጋር ለመስራትም ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
 በአዲስ አበባ ለሚገኙ 14 አለም አቀፍ ድርጅች ጋር ለመወያየትና የአካዳሚውን የሪፎርም ስራዎች ለማብራራት ጥያቄ ቀርቦ ከተወሰኑት ጋር ውይይት ለማድረግ ተችሏል፡፡ ከቀሩት ጋርም ለመወያየት ቀጠሮ ተይዟል፡፡
 ከኢጋድ ጋር ለመስራት በተያዘው ዕቅድ መሰረት ከከፍተኛ የሥራ ኃላፊው ጋር ውይይት ተደርጎ በጋራ በሚያሰሩ ጉዳዮች ላይ መግባት ተደርሷል፡፡
 ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በጋራ ለመስራት ጥያቄ ቀርቦ ክቡር አምባሳደሩን ለማግኘት ቀጠሮ ተጠይቋል፡፡
 ከተመረጡ የአውሮፓ፣ የአፍሪካ፣ የእስያ እና የላቲን አሜሪካ አገራት ጋር በጋራ ለመስራት ጥቄ ቀርቦ በውይይት ላይ ይገኛል፡፡
 ለጤና ሚኒስቴር አመራሮች ገለፃ ለማድረግና የአካዳሚውን የሽግግር ስራዎች ለመግለጽ ተችሏል፡፡
 ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተውጣጡ ከፍተኛ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ስለ አካዳሚው የሽግግር ስትራቴጂና ሪፎርም ገለፃ ተደርጎላቸው በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መስኮች ዙሪያ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
 ለሸገር ከተማ ከንቲባ ፅቤት ኃላፊዎችና አመራሮች ስለ አካዳሚው ሽግግርና ሪፎርም ገለፃ ተደርጓል፡፡
 ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አመራሮች የአፍሌክስን ሪፎርምና ሽግግር በተመለከተ ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
 ለፈረንሳይ የልማት ድርጅት (AFD) ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ስለ አፍሌክስ የሽግግር ስትራቴጂ እና ሪፎርም ገለጻ ተደርጎላቸው በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አሳውቀዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር ፍሬያማ ውይይት አደረጉ።
ርዕሰ አካዳሚው ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሪፎርም እና ሽግግር ስራዎች ለጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ለተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ገለጻ አድርገዋል። ሁለቱም ተቋማት በጋራ ሊሰሩ በሚችሉባቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በትብብር በሚሰሩ ስራዎች ላይም መግባባት ላይ ተደርሷል።
ገለጻውን ተከትሎ አስተያየት የሰጡት ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም እና በሽግግር ስራዎቹ ውስጥ ያስቀመጣቸው ሀሳቦች እና ግቦች የሀገራችንን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸው በተለይም በህብረተሰብ እና በክሊኒካል ጤና የአመራር ዘርፎች በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ሁሉ አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ጤና ሚኒስቴር የአካዳሚውን ሪፎርምና ሽግግር ከዳር ለማድረስ አብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ክብርት ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።