African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
# አሁን በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ
የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አመራርና ባለሙያዎች ስልጠና እየወሰዱ ነው::
ስለ አካዳሚው አገልግሎትና ተልዕኮ የአካዳሚው ጽ/ ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀና አጥናፉ ገለፃ አድርገዋል::
እንኳን ለኢትዮጵያዊነት በዓል አደረሳችሁ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
*************

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ለ18ኛ ጊዜ ‹ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት› በሚል ርእስ በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ በጅግጅጋ እየተከበረ ነው። መሪ ቃሉ እንደሚያመለክተው ይህ በዓል የኢትዮጵያዊነት በዓል ነው። ኢትዮጵያዊነት ማለት ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ማዕከል ያደረገ ሀገራዊ ማንነት በመሆኑ። ኢትዮጵያዊነት በአንድ በኩል የብሔር ብሔረሰቦችን ብዝኃነት የሚቀበል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ይሄንን ብዝኃነት አስተሣሥሮ የያዘና ለዘመናት የተሻገረ ጠንካራ አንድነት አለ ብሎ የሚያምን ነው፡፡

ይህ በዓል በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ላይ የተመሠረተውን የብሔራዊነት ትርክት የምንገነባበት በዓል እንደሚሆን እምነቴ ነው። ብሔራዊነት ሀገርን ለመከፋፈልና ለማዳከም ከተገነባው ነጠላ ትርክት የምንወጣበት መንገድ ነው፡፡ ከፖለቲካዊ ታሪካችን ይልቅ ማኅበራዊ ታሪካችንን በማጉላት፣ ከትናንትና ይልቅ በዛሬና በነገ ዕድሎቻችንና ሥራዎቻችን ላይ በመመሥረት፣ በሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ የቆመ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመመሥረት የሚያስችል ገዥ ትርክት ነው።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሀገራት የስትራቴጂክ አጋርነት መገንቢያ ማዕከል ነው
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 01/2016 ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ /አፍሌክስን የአህጉሪቱን ብልጽግና ለማሳካት የሚሰራ የተሟላ ተቋም እንዲሆን የማገዝ ፍላጎት ማሳየታቸው ተገለጸ፡፡
የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዛዲግ አብርሃ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች የአካዳሚውን የሽግግር ስትራቴጂን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አካዳሚው እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2021 እንደገና ተደራጅቶ ሪፎርም ካደረገ በኋላ ተቋማዊ አቅሙን በማስፋት እምርታዊ ለውጥ ለማስመዘገብ 13 ፕሮጀክቶችን መንደፉ ተገልጿል፡፡
አካዳሚው በትብብር ላይ ከተመሰረተው መርሁ በመነሳት ከሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብርና በቅንጅት የሚሰራባቸው ስምንት መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀቱም ተጠቅሷል፡፡
ከእነዚህም መካከል የአመራር ልማት ፕሮግራም፣ አፍሪካዊ ተቋም አድርጎ መገንባት፣ ሱሉልታን እንደ ዳቮስ፣ አዳዲስ እሳቤዎችን ማመንጨት፣ የአመራሮችና ተቋማት እውቅናና ሽልማት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭገኒ ተረክሂን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም እያስመዘገበ ያለው ውጤት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስለ አፍሪካ አመራር አካዳሚ የሽግግር ስትራቴጂ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮች ገለጻ የተደረገበትን ሁነት በፎቶ ይህን ይመስል ነበር