African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አከዳሚ አመራርና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው የስልጠና ማዕከል 500 ሚሊዮን በአንድ ጀንበር የሚለው መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡
በችግኝ ተከላው ላይ የአካዳሚው አመራሮችን ጨምሮ በአካዳሚው ውስጥ በጸጥታ ስራ ላይ የተሰማሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
የአፍሪካ መሪዎችን በማሰልጠን የወደፊት ምጡቅ አፍሪካዊ መሪዎችን ለማፍራት ራእይ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አስታወቀ
************
የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ አንዳሉት፥ ባለፉት 2 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በተለያዩ ደረጃ ለሚገኙ አስር ሺህ አመራሮች ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው በዋናነት ለፌደራል ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች፣ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ለድፕሎማቶች፣ ለፌደራልና ለክልል ካቢኔዎች፣ ለየሴክተር አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ነው።
አካዳሚው በፓንአፍሪካኒዝም፤ በኢትዮጵያ ስኬታማ በሆኑ እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሉ ተቋማት እና ከአመራር ጋር በተያያዙ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥናት እየሰራ ይገኛል ተብሏል።
ኢትዮጵያ የምትገኝበት ጂኦግራፊዊ አቀማመጥ፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗ፣ ነፃነቷን አስጠብቃ የቆየች ሀገር መሆኗ፣ ጥንታዊ ታሪክ ያላት ሀገር መሆኗ፣ በሀገረ መንግሥት ምስረታ ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር መሆኗ በአፍሪካ ጉዳይ ልዩ ኃላፊነት እንድትሸከም አድርጓታል ነው ያሉት።
AFLEX Signed a Partnership Agreement with the Multi-disciplined Leadership Institution in China
African Leadership Excellence Academy (AFLEX) and Shanghai Administration Institute (SAI) signed a partnership agreement at a ceremony held at the head office of the academy.
The purpose of the memorandum is to strengthen exchanges and cooperation procedures among the two sides in areas of training, scientific research, and public management.
During the signing ceremony, Mrs. Hiwot Alemayehu, Vice Chief of AFLEX, indicated that the agreement provides an opportunity for AFLEX to get its best practices, particularly in professionalism, training technologies, human development, and research. She affirmed that the potential partnership and cooperation areas are sharing experiences in training, governance, leadership building, and other related fields, and conducting academic workshops.
for more...
www.aflexacademy.gov.et
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአካዳሚውን ማስተር ፕላን ንድፍ /Master plan Design/ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሰራት ጨረታ አውጥቶ ያወዳደረ ሲሆን 14 ተጫራቾች የየራሳቸውን ንድፍ አቅርበው የመጨረሻ ማጣሪያው ላይ ደርሰዋል።
አሸናፊው የሚለይበት መርሀ-ግብር ነሀሴ 20/2015 በሱሉልታ በሚገኘው በተቋሙ ማሰልጠኛ ማዕከል የአካዳሚው የቦርድ አመራሮች፤ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፤ የተቋሙ አመራሮችና የማስተር ፕላን ንድፍ ባለሙያዎች በተገኙበት የማስተር ፕላን ንድፍ የውድድር የማጠናቀቂያ እና እውቅና የመስጠት መርሀ ግብር እንደተዘጋጀ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የ Shanghai Administration Institute (SAI) ልዑክ ቡድን ጉብኝት በፎቶ
" በአካዳሚው በመጪዎቹ አምስት አመታት በርካታ የአፍሪካ አገራት አመራሮችን ማሰልጠን የሚያስችል ሥራዎች ይሰራሉ" ዶክተር ምህረት ደበበ ገለፁ።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አቅም በማሳደግ በመጪዎቹ አምስት አመታት በርካታ የአፍሪካ አገራት አመራሮችን ለማሰልጠን የሚያስችል ሥራዎች ይሰራሉ ሲሉ ርዕሰ አካዳሚ ዶክተር ምህረት ደበበ ገለፁ።
የአካዳሚውን የማስተር ፕላን ዲዛይን ውድድር የማጠናቀቂያና እውቅና የመስጠት መርሐግብር ተከናውኖ ታይሎን ኢንጂነሪንግ አሸናፊ ሆኗል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶክተር ምህረት ደበበ እንደገለጹት፣ የአካዳሚውን አቅም በማሳደግ በመጪዎቹ አምስት አመታት በርካታ የአፍሪካ አገራት አመራሮችን ለማሰልጠን የሚያስችል ሥራዎች ይሰራሉ ብለዋል፡፡
እንደ ዶክተር ምህረት ገለጻ የአካዳሚውን የማስተር ፕላን ንድፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሰራት ውድድር ተዘጋጅቷል።
በጨረታው 14 ዓለም አቀፍ ተጫራቾች የራሳቸውን ንድፈ ያቀረቡ ሲሆን የመጨረሻ አሸናፊ ልየታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
አካዳሚው በ50 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ዘመናዊና በአይነቱ ለየት ያለ የአመራር ማሰልጠኛ ነው፡፡ በአካዳሚው 300 ደረጃቸውን የጠበቁ መኝታ ክፍሎች ይገኛሉ ያሉት ዶክተር ምህረት የመመገቢያና ሥልጠና አዳራሾች ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ይገኙበታል ብለዋል፡፡
በመርሃግብሩ የኢትዮጵያ አርክቴክት ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሀብታሙ ጌታቸው የተገኙ ሲሆን የአካዳሚው የአዳሚው አመራሮችን ጨምሮ የማስተር ፕላን ንድፍ ባለሞያዎች ተገኝተዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን በአፍሪካ እሴቶች የተቃኘ አህጉራዊ ተቋም ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን በአፍሪካ እሴቶች የተቃኘ አህጉራዊ ተቋም ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አካዳሚው አስታወቀ።
አካዳሚው ስሙን የሚመጥን በፓን-አፍሪካኒዝም የተቃኘ አህጉራዊ ተቋም መሆን የሚያስችል አዲስ ተቋማዊ የማስተር ፕላን ንድፈ ሃሳብ ይፋ አድርጓል።
በአካዳሚው ማስተር ፕላን ንድፈ ሃሳብን ለማቅረብ ከተወዳደሩ 14 የኪነ-ሕንፃ ባለሙያዎች መካከል ለአሸናፊው እና ለተሳታፊዎቹ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የአካዳሚው ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ዶክተር ወንድዬ ለገሰ፤ አካዳሚው በፓን አፍሪካኒዝም ይዘት ለትውልድ ተሻጋሪ ተቋም የመሆን ግብ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
አዲሱ መሪ ፕላን ተቋማዊ ገጽታውን መገንባት እንደሚያስችለው ነው የጠቆሙት።
አካዳሚው ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ለውጥ የሚበጁ አመራሮች የሚፈልቁበት የሀሳብ ልዕልና ማዕከል በመሆኑ፤ የአካዳሚው ገጽታ የአፍሪካን እሴቶች ያንፀበረቀ እንዲሆን የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ማስተር ፕላኑ አካባቢያዊ ሁኔታውን ታሳቢ ያደረገ፣ የመሬት ሀብቱን በቅጡ የተጠቀመ፣ አፍሪካዊ ገፅታ ያለው ዘመን ተሻጋሪ ሕንፃ ለመገንባት እንደታቀደም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ጌታቸው በበኩላቸው፤ ማስተር ፕላኑ የአካዳሚውን አህጉራዊ የልህቀት ተቋም የመሆን እንቅስቃሴን ለማሳካት የራሱ ድርሻ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
የማስተር ፕላን ሀሳቡ በውድድር መደረጉ በምህንድስና መስፈርቶችን ያሟሉ ግንባታዎችን ለማካሔድ ብሎም ተቋማዊ ገፅታ በመገንባት ሁነኛ ፋይዳ እንደሚኖረው በመጠቆም። (ኢዜአ)
አሁን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች የሳይንስ ሙዝየምን እየጎበኙ ነው