African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከሜሊንዳ እና ቢልጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን ለሚሰጠው የሴቶች አመራር ልማት ስልጠና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር ተከናወነ፡፡ ሰልጣኞችም የእርስ በእርስ ትውውቅ አድርገዋል፡፡
የትውውቅ መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የአካዳሚው የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ እንደተናገሩት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እንደ አዲስ በህግ ከተቋቋመ ጀምሮ በስልጠና እና በምርምር የሰራቸውን ስራዎች የገለፁ ሲሆን የከፍተኛ አመራር ስልጠናን በመስጠት ላይ እንደሆነና ለፖሊሲ አውጭውና ለስልጠና ፕሮግራሙ ግብዓት የሚውሉ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል፡፡
የስልጠናውን መስፈርት አሟልተው ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ሴት የስልጠና ተሳታፊዎችን አቅም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ አካዳሚው የራሱን ሚና እንደሚጫወትና ስልጠናውን ተከታትለው በቁርጠኝነት የሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎችም በሀገር ግንባታ ውስጥ የራሳቸውን የአመራር ድርሻ እንዲያበረክቱ ድጋፍና እገዛ እንደሚደረግና ሰልጣኞችም ስልጠናውን በተገቢው መንገድ እንዲከታተሉና ለውጤት እንዲበቁ ም/ል ርዕሰ አካዳሚዋ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ገልፀዋል፡፡
የሴቶች አመራር ልማት ፕሮጀክት ማኔጀር አቶ መስፍን በሀይሉ የፕሮጀክቱን ዓላማ በስፋት የገለፁ ሲሆን ሰልጣኞች ወደ ፊት ስለሚሰለጥኑባቸው ርዕሰ ጉዳዮችና ከስልጠናው የሚጠበቀውን ውጤትም አብራርተዋል፡ ስልታዊ አስተሳሰብን ማበልፀግ፤ ችግርን ተረድቶ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መፍታት፤ ውጤታማ የተግባቦት ክህሎትን ማሳደግ፤ የቡድን ስራ ግንባታና የባለድርሻ አካላት ስራ አመራር ከስልጠናው የሚጠበቁ ውጤቶች መሆናቸውንም አቶ መስፍን ጠቅሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ እንደተናገሩት ተቋሙ በተሟላ የስልጠና ማዕከል ውስጥ ከፍተኛ አመራሮችን እያሰለጠነ እንደሆነና ይህንንም በአፍሪካ ደረጃ በማሳደግ የአህጉሩን መሪዎች አቅም በማጎልበት የአፍሪካን ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡
አካዳሚው ከስልጠና በተጨማሪ በምርምርና ማማከር አገልግሎት ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በቅርቡም የፓን አፍሪካኒዝም ፎረም እንደሚያዘጋጅ ተጠቅሷል፡፡
በጉብኝቱ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍስሀ ሻውልን ጨምሮ የአካዳሚው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የራሺያ ፌዴሬሽን አምባሳደር Yevgeny Tarekhin ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ ላይ ዶ/ር ምህረት ደበበ እንደተናገሩት አካዳሚው እንደ አዲስ በሚኒስትሮች ም/ቤት ከተቋቋመ ጀምሮ የመንግስትንና የግል ተቋማትን አመራሮች በተሟላ የስልጠና ማዕከል ውስጥ እያሰለጠነ እንደሆነና ይህንንም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተቋማዊ ሪፎርም እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡
ተቋማዊ ሪፎርሙ ሲጠናቀቅም አካዳሚው ሊያከናውናቸው ያቀዳቸው በርካታ አገር አቀፍና አህጉር አቀፍ ፕሮግራሞች መኖራቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ምህረት ይህንንም ለማሳካት ተቋሙ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ስትራቴጂያዊ አጋርነትን በመመስረትም የአካዳሚውን ተልዕኮ ለማሳካት እየተሰራ እንደሆነ የተናገሩት ርዕሰ አካዳሚው ከራሺያ ፌዴሬሽን ጋር በስልጠና እና በምርምር መስኮች በመስራትም የተቋሙን የመፈፀም አቅም ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላቸውም ገልፀዋል፡፡
አምባሳደር Evgeny Tarekhin በበኩላቸው ከአካዳሚው ጋር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልፀው በቀጣይ በሚደረጉ ውይይቶች የሚዳብር ሀሳብ እንዳላቸው አስታውሰው አካዳሚው ላደረገላቸው መልካም አቀባበልና ግብዣ አመስግነዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ እንደተናገሩት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት የሚደረገው በሁሉም የመንግስትቋማት ውስጥ መሆኑን ገልፀው ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ከሀይማኖት አባቶች የሚተላለፉ መልእክቶች በመንግስት ስራ ውስጥ ክፍተት እንዳይፈጥሩ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሁሉም የአካዳሚው አመራርና ሰራተኛ የበኩሉን ሚና እንዲጫወትም ጠይቀዋል፡፡
የስራ አመራር ዘርፍ ም/ል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው በሀይማኖት አባቶች መካከል የተፈጠረውን ችግር ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው የሚሰሩ ሀይሎች እንዳሉ ጠቅሰው የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ በሰከነ መንገድ ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞችም የተፈጠረው ችግር በሰላም እንዲፈታ መንግስት እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡
Public Lecture on The African Diaspora and Africa’s Development
Date Feb. 22, 2023
Time 4 pm -5:30 pm
Venue A.A.U Mekonnen Hall
Prof. Hakim Adi
organized by :-
African Leadership Excellence Academy
in Collaboration with Addis Ababa University
የፓን አፍሪካዊነት እሳቤ ዳግም እንዲያንሰራራ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እየተካሄደ በሚገኘው የፓን አፍሪካዊነት ፎረም ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው።
ኢትዮጵያ የገነባችው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአፍሪካ ወጣት መሪዎችን ለማፍራት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካ መጠናከር የነበራትን ታሪካዊ የመሪነት ሚና አሁንም አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉ አረጋግጠዋል።
የፓን አፍሪካ ፎረምን በ2063 የአፍሪካ የልማት አጀንዳ 10 ዓመት እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረት ምስረታ ለ60ኛ ዓመት ክብረ በዓል ወቅት ማዘጋጀቷም ለጉዳዩ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፎረሙ ለፓን አፍሪካዊነት መንፈስ እና የአፍሪካ አንድነት እንደ አዲስ ትንሳዔውን እንደሚያበስር ተናገረዋል። የፓን አፍሪካ እንቅስቃሴውን ዕውን ለማድረግ አዲስ አስተሳሰብ፣ አካሄድ እና ጥበብ እንደሚጠይቅም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ሀገራት ከሰው ሰራሽ መልክዓ ምድራዊ የወሰን ሃሳብ መስመሮች እና ከርዕዮተ ዓለም አጥሮች ወጥተው የተባበረች እና የበገለፀገች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ መስራት አለባቸውም ነው ያሉት። በተለይም መሪዎች አጀንዳ የሚቀርጽ፣ ተሻጋሪ ሃሳብ የሚያፈልቅ ችግር ፈች አፍሪካዊ ትውልድ ለመገንባት በአርዓያነት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የፓን አፍሪካዊነት ዳግም ትንሳኤ እንዲያብብ በቁርጠኝነት እንደምትሰራም አረጋግጠዋል።
የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የፓን አፍሪካዊነት ፎረም በአካዳሚው ተከናውኗል፡፡