የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ትውልዱ በስፋት ሊያስቀጥለው እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለፁ።
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በተካሄደው የመጀመሪያው የፓን አፍሪካኒዝም ፎረም ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፓንአፍሪካኒዝም በ21ኛው ክፍለዘመን ትርጉሙ የኢኮኖሚ ጥገኝነትን ማስቀረት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ለመቻልና የበለፀገች አገር እንድትሆን በርትታ እየሰራች መሆኑን የገለፁት አቶ ደመቀ፤ ባለፉት ዓመታት ለአረንጓዴ አሻራ ትኩረት ሰጥታ መስራቷን ገልፀዋል።
እንደ አቶ ደመቀ ገለፃ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ አለው፡፡
አፍሪካ የመሬት መሸርሸር እንዲሁም ድርቅና ርሀብ የጋራ ችግሮቿ ናቸው ያሉት አቶ ደመቀ፤ ለዚህም ትውልዱ የአረንጓዴ አሻራን ጥቅም ተገንዝቦ በስፋት ሊያስቀጥለው እንደሚገባ መክረዋል።
በመድረኩ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ የደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር አደፍርስ ወርቁ፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የካርቦን ልቀትን በመቀነስ የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ጠቅሰዋል።
መርሃ ግብሩ ጎረቤት ሀገራት ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ እንዲሰሩ ለማድረግ አስፈላጊ ነው ያሉት ዶክተር አደፍርስ፤ የግጦሽ መሬት፣ የውሃና የደን ሃብት እጥረት ችግሮችን ለመፍታት አስችሏል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በተካሄደው የፓን አፍሪካኒዝም ፎርም የተሳተፉ የሀገራት መሪዎች፤እንዲሁም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው ልኡክ በአካዳሚው ችግኞችን ተክሏል፡፡

ትኩረቱን ፓን አፍሪካኒዝም ላይ ያደረገ የውይይት መድረክ ተካሄደ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በፓን አፍሪካኒዝም ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ ተካሄደ።
በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ህይወት አለማየሁ እንደገለፁት አካዳሚው በዋናነት ከሚሰራቸው የስልጠና፤ የምርምርና የማማከር ስራዎች ጎን ለጎን ሀገራዊና አህጉራዊ ፋይዳ ያላቸውን የውይይት መድረኮች በማዘጋጀትና አለምአቀፍ ሙሁራንን በመጋበዝ ግንዛቤን የማዳበርና ዕውቀትን የማስጨበጥ ስራ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው የፓን አፍሪካኒዝም ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የፅሁፍ ስራዎች መታተማቸውን አስረድተዋል።
በመድረኩ ላይ እውቁ ፕሮፌሰር ሀኪም አሊ “የአፍሪካ ዳያስፖራ እና የአፍሪካ እድገት” በሚል ርእስ ፅሁፍ አቅርበዋል። ፕሮፌሰር ሀኪም በፅሁፋቸው ላይ የፓን አፍሪካኒዝምን ምንነት እና ታሪክ አንስተዋል።
ፕሮፌሰር ሀኪም አፍሪካውያን ዳያስፖራዎች ለአህጉሪቱ እድገት የሚኖራቸው ሚና የሚናቅ ባለመሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠቅሰዋል።
መድረኩን የመሩትና ያስተባበሩት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የፕሮግራም ዘርፍ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብሩክ ሀይሉ ሲሆኑ የቀረበው ፅሁፍ አፍሪካውያን ያላቸውን እምቅ የተፈጥሮና የሰው አቅም ያሳየ እና ለመለወጥ በጋራ መስራት እንዳለባቸው የሚጠቁም መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሚዘጋጁ መሰል መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተገልጿል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሀገራችንና ለአህጉሪቱ አመራር አስተዋፅኦ የሚያበረክት ተቋም እንዲሆን የቦርዱ አመራር መስራት አለበት ተባለ፡፡
የአካዳሚው የቦርድ ስብሰባ በተካሔደበት ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ እንደተናገሩት ለአካዳሚው የሚጠቅሙ አዳዲስ ሀሳቦችን በማምጣት ተቋሙ የተቋቋመበትን ተልዕኮ በማሳካት ለሀገራችንና ለአፍሪካ አመራር አስተዋፅኦ የሚያበረክት ተቋም እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ አያይዘውም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሰፊ ተልዕኮ እና ከባድ ሃላፊነት የተሰጠው ተቋም በመሆኑ ተልዕኮውን ሊፈፅም የሚችልበትን አሰራር በማሳደግ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገርም ይገባል ብለዋል፡፡
የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ አካዳሚው እንደ አዲስ ከተቋቋመ ጀምሮ ያከናወናቸውን ተግባራት ለቦርዱ ያስረዱ ሲሆን ከቦርድ አባላቱ ለቀረበላቸው ጥያቄና አስተያየትም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ቦርዱ በሶስት አጀንዳዎች ላይ የተወያየ ሲሆን ተገቢውን አቅጣጫ በማስቀመጥም የዕለቱን ስብሰባ አጠናቋል፡፡
ሰባት አባላት ያሉት የቦርድ አመራር የተቋቋመውም በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

ተከታዮቹን ሊንኮች በመወዳጀት የአካዳሚያችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
ድረ ገጽ፦ https://aflexacademy.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aflexacademy.gov.et
ትዊተር፦ https://twitter.com/Afleexacademy
ቴሌግራም፦ https://t.me/afleexac
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/african-leadership-excellence-academy-aflex-918830240/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/watch?v=OxdPGdqyLXA&t=23s
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/explore/locations/1011950041/african-leadership-excellence-academy/
ኢሜይል፡- info@aflexacademy.gov.et
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን!! ሊንኮቹን በማጋራትም መልዕክታችን ለሌሎች እንዲደርስ ስላደረጉ እናመሰግናለን፡፡

POSTER DRAFT for News Paper 03.pdf
32.3 MB
Call for expression of interest international master plan design competition for AFLEX