African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ሴቶችን ወደ ውሳኔ ሰጭነት ለማምጣትና አቅማቸውን ለመገንባት እየተሰራ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ በሴቶች አመራር ልማትና ማብቃት ፕሮጀክት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጓል ፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት አካዳሚው ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን (Bill and Melinda Gates Foundation) ጋር በመተባበር ሴቶችን ለማሳደግ የሚረዳ የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት ሚና ለማሳደግ የሚረዳ የሴቶች የአመራር ልማት ፕሮጀክት (WLDP) ቀርፆ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ሕይወት አያይዘውም ፕሮጀክቱ ሊያሳካ ያቀዳቸውን ውጥኖች የጠቆሙ ሲሆን መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር ሴት አመራሮችን ለማብቃትና በቁልፍ የመካከለኛ አመራር ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ሚና እንዲኖራቸው ይሰራል ብለዋል ፡፡
የምክክር መድረኩም በፕሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ ሴት አመራሮችን ለመምረጥና በቀጣይ በጋራ መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እንደሆነ ም/ርዕሰ አካዳሚዋ ተናግረዋል ፡፡
የፕሮጀክቱ ማናጀር አቶ መስፍን በሃይሉ ስለ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የሚመረጡ የሴት አመራሮችን መስፈርት አብራርተዋል፡፡ በቀረበው ገለፃ ላይም ጥሪ የተደረገላቸው የተቋማት አመራሮች ጥያቄና አሰስተያየት ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ በቂ ምላሽም ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ ከ10 በላይ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በአካዳሚ ደረጃ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሮ እንደሚውል ተገለጸ::
የአካዳሚው የስነምግባር እና ፀረ ሙስና ዳዳይሬክተር ወ/ሮ አልማዝ መኮንን እንደተናገሩት በዓለም አቀፍ ለ19ነኛ ጊዜ እና በአገር አቀፍ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው የፀረ ሙስና ቀን በአካዳሚው በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሁነቶች ለማክበር እየተሰራ እንደነ ገልጸዋል::
አለም አቀፍ የኤድስ ቀን
"ፍትሃዊና ተደራሽ የኤች አይ ቪ/ኤድስ አገልግሎት!
እንዲሁም አለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን"ሴትን አከብራለሁ፤ ጥቃቷንም እከላከላለሁ!" በሚል መሪ ቃል በእግር ጉዞ እና በውይይት እንደሚከበር በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሴቶች፣ ወጣቶች እና ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ ምህረት አስጨ ገልጸዋል::
ሙስና የአገር ነቀርሳ በመሆኑ መንግስት ይህንን ትኩረት አድርጎ እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚበረታታ ነው ሲሉ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ምክትል ርእሰ አካዳሚ ዶክተር ወንድዬ ለገሰ ተናገሩ።
አካዳሚው ግንዛቤ በመፍጠር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ገልጸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በዓለም አቀፍ ለ19ኛ ጊዜ እና በአገር አቀፍ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ ሙስና ቀንን "ሙስናን መታገል በተግባር" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሁነቶች በማክበር ላይ ነው፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ምክትል ርእሰ አካዳሚ ዶክተር ወንድዬ ለገሰ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፣ ሙስና የአገር ነቀርሳ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት ይህንን ትኩረት አድርጐ እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
የአካዳሚው የስነምግባርና ፀረ ሙስና ዳዳይሬክተር ወይዘሮ አልማዝ መኮንን ባቀረቡት ጽሁፍ፣ ሙስና የአገርን ኢኮኖሚ የሚገታ፣ የአለም ስጋት፣ አደገኛና ድንበር ዘለል ወንጀል በመሆኑ በጋራ መታገል እንደሚገባ አመላክተዋል።
ሁሉን አቀፍ እድገትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ሙስናን በተግባር መታገል ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እንደሆነም ተናግረዋል።
መርሐግብሩ በፓናል ውይይት፣ ስነ ጽሁፍ፣ ጥያቄና መልስና መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሁነቶች ተከናውኗል፡፡።
ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የሚያስከትለውን ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንደሚያስፈልጉና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ተግባራዊ ለውጥ ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡

ይኽ የተገለፀው ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት እና የኤድስ ቀን በአካዳሚ ደረጃ ሲከበር ነው፡፡ አለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን "ሴትን አከብራለሁ፤ ጥቃቷንም እከላከላለሁ!" እንዲሁም አለም አቀፍ የኤድስ ቀን "ፍትሃዊና ተደራሽ የኤች አይ ቪ/ኤድስ አገልግሎት! በሚል መሪ ቃል በእግር ጉዞ እና በውይይት በተከበረበት ወቅት ነው፡፡

በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ም/ል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት ፆታዊ ጥቃትንም ሆነ ኤድስን ለመከላከል ተግባራዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ሁሉም የአካዳሚው ማህበረሰብ ከመድረኩ የሚያገኘውን ግንዛቤ ወደ ተግባር በመለወጥ ለሴቶች ያለውን ድጋፍና አጋርነት በተግባር ማሳየት ይገባል ሲሉም አክለዋል፡፡

በአካዳሚው የሴቶች፣ ወጣቶች እና ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ ምህረት አስጨ በበኩላቸው ተቋሙ የፆታ ጥቃትን ለመከላከልና ወላጆቻቸውን በኤድስ ያጡ ህጻናትን ለመደገፍ ያለውን ጥረት አመላክተው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት እና የኤድስ ቀንን በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብሮች ሱሉሉታ በሚገኘው የስልጠና ማዕከል ውስጥ አክብረዋል፡፡
Research Validation workshop at AFLEX
AFLEX holds a workshop on the Pan African Now: Pan Africanism for a changing world
Today, January 20, 2023, the African Leadership Excellence Academy, AFLEX, holds a discussion on Pan Africanism Now: Pan Africanism for a changing world here at Skylight Hotel Addis Ababa.
According to Dr.Shimles, the purpose of the workshop is research output validation.
Dr. Shimles Offered the Source, The argument, the background, significance, objectives, research questions, and what can be done as part of the broadsheet.
After the presentation, a discussion was apprehended on the topic. Participants outstretched their questions and perceptions and the questions were responded.

Finally, the head of the African Leadership Excellence Academy, Dr. Mehret Debebe, gave an explanation of the presentation given on the topic and told the inputs given by the participants are vital.

The presentation was moderated by professor Brook Hailu Senior Advisor of AFLEX.
በትውውቅ መርሀ ግብሩ ላይ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክ፤ ከመከላከያ፤ ከትምህርት፤ ከኢንዱስትሪ፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፤ ከግብርና ሚ/ር መስሪያ ቤቶች፤ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል፤ ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ፤ ከስፔስ ሳይንስ፤ ከምድር ባቡር፤ ከፌዴራል ፖሊስ እና ሌሎችም ተቋማት የመጡ ተሳታፊዎች የተካፈሉ ሲሆን ሱሉሉታ የሚገኘውን የአካዳሚውን የስልጠና ማዕከልም ጎብኝተዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከሜሊንዳ እና ቢልጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን ለሚሰጠው የሴቶች አመራር ልማት ስልጠና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር ተከናወነ፡፡ ሰልጣኞችም የእርስ በእርስ ትውውቅ አድርገዋል፡፡
የትውውቅ መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የአካዳሚው የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ እንደተናገሩት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እንደ አዲስ በህግ ከተቋቋመ ጀምሮ በስልጠና እና በምርምር የሰራቸውን ስራዎች የገለፁ ሲሆን የከፍተኛ አመራር ስልጠናን በመስጠት ላይ እንደሆነና ለፖሊሲ አውጭውና ለስልጠና ፕሮግራሙ ግብዓት የሚውሉ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል፡፡
የስልጠናውን መስፈርት አሟልተው ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ሴት የስልጠና ተሳታፊዎችን አቅም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ አካዳሚው የራሱን ሚና እንደሚጫወትና ስልጠናውን ተከታትለው በቁርጠኝነት የሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎችም በሀገር ግንባታ ውስጥ የራሳቸውን የአመራር ድርሻ እንዲያበረክቱ ድጋፍና እገዛ እንደሚደረግና ሰልጣኞችም ስልጠናውን በተገቢው መንገድ እንዲከታተሉና ለውጤት እንዲበቁ ም/ል ርዕሰ አካዳሚዋ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ገልፀዋል፡፡
የሴቶች አመራር ልማት ፕሮጀክት ማኔጀር አቶ መስፍን በሀይሉ የፕሮጀክቱን ዓላማ በስፋት የገለፁ ሲሆን ሰልጣኞች ወደ ፊት ስለሚሰለጥኑባቸው ርዕሰ ጉዳዮችና ከስልጠናው የሚጠበቀውን ውጤትም አብራርተዋል፡ ስልታዊ አስተሳሰብን ማበልፀግ፤ ችግርን ተረድቶ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መፍታት፤ ውጤታማ የተግባቦት ክህሎትን ማሳደግ፤ የቡድን ስራ ግንባታና የባለድርሻ አካላት ስራ አመራር ከስልጠናው የሚጠበቁ ውጤቶች መሆናቸውንም አቶ መስፍን ጠቅሰዋል፡፡