African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል በጊዜ የለንም መንፈስ መስራት ይገባል -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2017(ኢዜአ)፦ በየዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በላቀ ውጤት ለማስቀጠል በጊዜ የለንም መንፈስ በትጋት መስራት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና የዘርፎች ዕቅድ አፈጻጸምን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ከፌዴራል ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር መገምገም ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ በ100 ቀናት የትኩረት ማዕከል የሆኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶች፣ የታዩ ክፍተቶች እና የትኩረት አቅጣጫዎች ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ ታይተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ እና በተለያዩ መስኮች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

በየዘርፉ የተሰሩ ስራዎችን በአግባቡ መለካት፣ ማቅረብ እንዲሁም ለሌላው ማስረዳት እንደሚገባ ገልጸው፤ አሁንም አመራሩ በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።

ሰራተኛውን በአግባቡ የማይመራ፣ የማይመዝን እና የማይከታተል መኖሩንና በጥቂት ታታሪ ሰራተኞችና ኃላፊዎች ተቋማት የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ እንደሚስተዋል ገልጸው፤ ይህንን መፈተሽ እና ማስተካከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከታሰበው በላይ የተሳኩ ድሎች መመዝገባቸውን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁንም ትኩረት የሚፈልጉ አካባቢዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
አገራዊና ዓለም አቀፋዊ አውድን በመገንዘብ እየተገኙ ያሉ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸው የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ከዚህ በላይ መሮጥ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ እና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርምን መፈጸም ውዴታ ሳይሆን ግዴታ መሆኑንም ተናግረዋል።

አገልግሎት አሰጣጥ ሁሉንም ሊያሳስብ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በጠንካራ አመራር እና ሰራተኛ የታጀበ አገልግሎት አሰጣጥ መኖር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ከተገኙ ውጤቶች በላይ ለማሳካት ሁሉም በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በውይቱ ላይ የአፍሌክስ ከፍተኛ አመራሮች፤ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች እና ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል::
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና በኢትዮጵያ የማልታ አምባሳደር በትብብር ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2017 (አፍሌክስ) -
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በኢትዮጵያ የማልታ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ ጋር ቀደም ሲል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል።

በአፍሌክስ ዋና መስሪያ ቤት የተካሄደው ስብሰባ በማልታ እና በኢትዮጵያ መካከል በአመራር ልማት እና ተያያዥ ዘርፎች ዙሪያ ትብብርን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው።

አቶ ዛዲግ በውይይቱ ላይ "በተለዩ የትብብር መስኮች ላይ ስራዎችን በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል" ብለው። የመግባቢያ ሰነዱን ስኬታማነት ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሚካሌፍ በንግግራቸው ኢትዮጵያ እንደ ሃገር አፍሌክስ እንደ ተቋም እያካሄዱ ላለው ለውጥ አድናቆታቸውን ገልፀው፣ "ኢትዮጵያ በጥቂት አመታትውስጥ በተሃድሶው ብዙ ለውጥ አድርጋለች። ይህም በእጅጉ የሚደነቅ ነው" ብለዋል። በተጨማሪም፣ የአረንጓዴ ልማት አጀንዳ፣ ሰውሰራሽ አስተውሎትና የስነምግባር አመራርን ጨምሮ በርካታ የትብብር መስኮችን ጠቁመው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአመራር ክህሎትን በማዳበር ለነዚህ ውጥኖች መሳካት ቁልፍ ተቋም መሆኑን ጠቅሰዋል።

በውይይቱ የመግባቢያ ስምምነቱ የትብብር መስኮች ብሎ የዘረዘራቸው የሥልጠና መርሃ ግብሮችን በጋራ ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች የአመራር ልማትን ለማሳደግ ያለሙ ውጥኖች ተነስተው፣ እንዴት ይተግበሩ በሚለው ላይ ከስምምነት ተደርሷል።

ውይይቱ ሲጠናቀቅ፣ አምባሳደሩ እና የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት የመግባቢያ ሰነዱን ስኬታማ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራር እና ሰራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር እቅድ ሃገራዊ እና ተቋማዊ አፈፃፀም ላይ ውይይት አደረገ::
የእቅድ አፈጻጸም ከተቀመጠው ግብ አንጻር 87.67 % ያሳካ እንደሆነም ተገልጿል።

ሱሉልታ 8/8 2017 ዓ.ም /አፍሌክስ/ የአካዳሚው የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የቀረበውን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ሃገራዊ እቅድ አፈፃፀም ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው የአመራር ልማት ላይ ገለፃ ሰተዋል፡፡

ኃላፊዋ ኢትዮጵያ አንደ ሀገር በበጀት አመቱ 8.4 እድገት ለማስመዝገብ እቅድ የያዘች አንደሆነ እና አለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያና ለኢትዮጵያ ያለው እንድምታ ምን ይመስላል፣ ሀገራችን ላይ እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና መሰረተ ልማት እና ፕሮጀክት አፈፃፀም ላይ የተሰሩ ስራዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 98.66% የተናቀቀ መሆኑ፣ የ ኮሪደር ልማቱ በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና የክልል ከተሞች በአፋጣኝ ሁኔታ እየተገነባ መሆኑ ከተሞቻችንን ከማስዋብ በላይ የቱሪዝም ተደራሽነት እና ትራንስፖርትና ፍሰትን ከማሳለጥ አኳያ ብዙ ስራ እንደተሰራ ተናግረዋል።

ወ/ሮ መሰረት ዘላቂ ልማት ማህበራዊ አካታችነት ላይ ልማቱ ለማህበረሰቡ አንድምታ ያለው ጥቅም፣ በበጀት ዓመቱ የኢነርጂ ተጠቃሚነት በሰፊው ጭማሪ ማሳየቱ፣ የትምህርት ዘርፉን ተደራሽነት ማስፋት፣ የእናቶች እና ህፃናትን ሞት በመቀነስ ላይ ብዙ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ ሃገራችንን ከተረጅነት ለመላቀቅና ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውንም አብራርተዋል።
ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ አውድን በመገንዘብ እየተገኙ ያሉ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡

በአፍሌክስ የስትራቴጂ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ዘሪሁን የአካዳሚውን የ 2017 ዓ. ም የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል ።
መሰረታዊ አገልግሎትን ማቀላጠፍ እና ፋሲሊቲ ማዘመንና አገልግሎት አሰጣጥንና ቅልጥፍና በማሳደግ ረገድ በተሰራው የአገልግሎት እርካታ ዳሰሳ ጥናት የአገልግሎቶች እርካታ የ9ወሩ አማካይ ከ96% በላይ ለማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ላይ ሱሉልታ የሚገኘውን የአስተዳደር ህንጻ የማገባደድ ስራ እየተከናወነ እንደሆነና የአካዳሚው ዋና የስራ ቦታ ወደ ሱሉልታ የሚዞር መሆኑን ተናግረዋል።

በአካዳሚው የሚሰጡ ስልጠናዎች የሥነ ምግባር ግንባታ እና የሞራል ግንባታን ያካተቱ እንዲሆኑ የመከታተል ስራም ተሰርቷል ብለዋል።
በሚዲያና ኮሚኒኬሽን የአካዳሚውን ገጽታ ለማሻሻልና ለመገንባት የተለያዩ የተግባቦት መሳሪያዎችን እና ስልቶችን በመጠቀም የተቋሙን ስራዎች ለማስተዋወቅ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም አብራርተዋል።

በቀረበው ገለጻ ላይ የአካዳሚው ሰራተኞች ሃሳባቸውን አንስተው የተወያዩ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።
በአጠቃላይ እቅዱ አፈጻጸም ከተቀመጠው ግብ አንጻር 87.67 % ያሳካ እንደሆነ ተገልጿል።
አፍሌክስ ከሲዲ ሞሀመድ ቤን አብደላህ ዩኒቨርሲቲ ጋር አጋርነት መሰረተ

አዲስ አበባ/ ሚያዚያ 8/2017 (አፍሌክስ) -
አካዳሚው መገኛውን በፌዝ፣ ሞሮኮ ካደረገው የሲዲ ሞሀመድ ቤን አብደላህ ዩኒቨርሲቲ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።

ትብብሩ በአመራር ልማት እና ተያያዥ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው።

አፍሌክስን በመወከል የአካዳሚው ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ፣ የሞሮኮውን ዩኒቨርሲቲ ወክለው ደግሞ የዩኒቨርሲቲው የሳይንሳዊ ጥናትና ትብብር ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ኤል መስታፋ ኤል ሃድራሚ የመግባቢያ ሰነዱን ፈርመዋል። የፊርማ ስነ ስርዓቱ በአፍሌክስ ዋና መስሪያ ቤት በቨርቹዋል መንገድ ተከናውኗል።

አቶ ዛዲግ አብርሃ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር "ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ብዙ የሚያመሳስላቸው ሁለት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ናቸው። ከሞሮኮ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ስናስብ ቆይተናል እናም የዛሬው ፊርማ ይህን ሃሳብ ወደተግባር የምንቀይርበት ትልቅ ምዕራፍ ነው" ብለዋል። የሚቀጥለው እርምጃ በትብብር መስኮች ላይ የስራ ሂደቱን የሚመራ ኮሚቴ ማቋቋም መሆኑን በመግለጽ ስምምነቱን ለመፈጸም አፍሌክስ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ፕሮፌሰር ኤል ሃድራሚ በበኩላቸው ስለ ትብብሩ ሲናገሩ "ይህ ስምምነት በሁለቱ ተቋማት አልፎም በኢትዮጵያና በሞሮኮ መካከል አካዳሚክ ትብብርን የሚያሳድግ እና ውጤታማ የአመራር ልማትን የሚያስፋፋ ነው“ ብለዋል።

የመግባቢያ ሰነዱ የሁለቱን ተቋማት ግንኙነት ለማጠናከር እና የአመራር ክህሎትን ለማሻሻል የሚረዱ የእውቀትና የልምድ ልውውጥን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ተግባራትን ለመከወን መሰረት የሚጥል መሆኑ ተገልጿል።