African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የሴቶች እኩልነት በስራ እና በአመራር ላይ ካልተረጋገጠ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች እንዲሁም ልዩ ድጋፍ ምን እንደሆነና የሚያስፈልግበትን ምክንያት ፣ በሥራ ላይ ትርጉም እና ዓላማ ማግኘት፣ በአመራር ውስጥ የደስታ ኃይል ፣ በመንግስት ዘርፍ ያሉ ሴቶች ወደ ፖለቲካው እንዲገቡ ምን አይነት ቁርጠኝነት ያስፈልጋል፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሴቶች የሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች፣ ሴቶች በራስ መተማመን ራስን ማወቅና የማደግ አመላካከት እንዲኖራቸው ምን ማድረግ አለብን በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከስልጠናው ተሳታፊዎችጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ #ለውጥ_ከሀይሉ_እስከ_መሰረታውያኑ- በሚል ርዕስ ለአመራሮች የሰጡትን ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የዩቱዩብ ቻናል ለመከታተል

ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ👉 https://www.youtube.com/watch?v=5Io3w2WGcmU

በስልጠናው ብዙ እውነታዎች ተዳሰዋል 👇

🔹 ብንፈልገውም ባንፈልገውም ለውጥ አይቀሬ ሁነት ነው!

🔹 ለውጥን አንቀበልም ማለት መጥፋት ነው!

🔹 በተለዋዋጭ አለም ውስጥ ለመቆየታችን ዋስትና የሚገኘው ለውጥን በመቀበል እና ራስን በማላመድ ብቻ ነው!
ብዙ ጥያቄዎች ተመልሰዋል 👇

ለውጥን በምን መልኩ ብንቀበል ይሻላል

ለውጥን የተቀበሉ ኩባንያዎች የት ደረሱ? ያልተቀበሉትስ የት ናቸው

ስኬታማ የለውጥ መሪ ለመሆን ምን እናድርግ

ስልጠናውን ይከታተሉ ብዙ ያተርፉበታል!
ሀገራዊ ልማት የሁሉንም ርብርብ ስለሚጠይቅ ምልዓተ ሕዝቡን አስገንዝቦ ማነሣሣት ላይ ሊተኮር ይገባል - ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ
*************************
ሀገራዊ ልማት እና ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ የሚቻለዉ ቀጣይነት ያለው የምልዓተ ሕዝቡ ተሳትፎ በመሆኑ ሀገራዊ ትልሞችን እና የመዳረሻ ግቦችን ማስገንዘብ ላይ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ እንዲያተኩር የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

“ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለኢትዮጵያ መንሰራራት” በሚል መሪ መልእክት ለክልል እና ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ እየተሰጠ ባለው ሥልጠና ዶ/ር ኢዮብ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መሠረተ ሐሳቦችንና የተመዘገቡ ስኬቶችን አብራርተዋል፡፡
በማብራሪያቸዉም የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ “የሀገር ልማት የሁሉንም ርብርብ ስለሚጠይቅ ምልዓተ ሕዝቡን አስገንዝቦ ለላቀ ተሳትፎ እና ስኬት ማነሣሣት ላይ አተኩሮ መሥራት አለበት” ብለዋል፡፡ ይዘቶቹ የኢትዮጵያን ተስፋዎች፣ የዕድገት መሠረቶች፣ የልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን ፋይዳ፣ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ማመላከት ላይ አተኩረዉ መዘጋጀት እንዳለባቸዉም አመላክተዋል፡፡

የመጀመሪያዉ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ በበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ፣ ድርቅ እና ጦርነት የተፈተነ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ኢዮብ “በበርካታ ችግሮችም ውስጥ በአመራሩ ጥበብ የተሞላበት መሪነት ስኬት ያስመዘገበ ነበር” ብለዋል፡፡ በበርካታ ፈተናዎችም ውስጥ ከፍተኛ ዕድገት መመዝገቡን፣ ኢኮኖሚዉ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ዲጂታላይዜሽን መሸጋገሩን፣ አጠቃላይ ሀገራዊ ዕዳን ከነበረበት ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (GDP) የነበረውን ምጣኔ በመጀመሪያዉ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ወቅት በከፍተኛ መጠን መቀነስ መቻሉን በማሳያነት አንሥተዋል፡፡

የአጠቃላይ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያዉ የተረጋጋ ማክሮ-ኢኮኖሚ መፍጠርን፣ ዘላቂነትና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ማስመዝገብን፣ የወጪ እና ገቢ ንግድን ማመጣጠንን፣ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ገብይት ሥርዐት መፍጠርን፣ የዜጎችን ሕይወት በዘላቂነት ማሻሻልንና የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አኀዝ ማውረድን ታሳቢ ያደረገ መኾኑንም ሚኒስትር ዴኤታዉ አስገንዝበዋል፡፡

ከተያዘዉ በጀት ዓመት መግቢያ ጀምሮ ወደ ተሟላ የትግበራ ምዕራፍ የገባዉ ሁለተኛዉ ምዕራፍ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በርካታ ስኬቶች እንደተመዘገቡበትም ዶ/ር ኢዮብ በገለጻቸዉ አመላክተዋል፡፡ ለአብነትም ባለፉት ዘጠን ወራት ብቻ 5.3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከወጪ ንግድ መገኘቱንና ካለፈዉ በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸም አንጻር የ150% ዕድገት የታየበት መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡ አጠቃላይ የመንግሥት ገቢም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከባለፈዉ በጀት ዓመት አንጻር የ135% ዕድገት አስመዝግቦ ከ926 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ዶ/ር ኢዮብ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሁለተኛዉ ምዕራፍ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተረጋጋ ማክሮ-ኢኮኖሚ ለመፍጠር፣ ምቹ የኢንቨስትመንት እና የገበያ ሥርዐት ለመፍጠር፣ የዘርፎችን ምርታማነትና ውጤታማነት ለማሳደግ እና ብቃት ያለው እና ውጤታማ የሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት እየሠራች ትገኛለች፡፡

ከመጋቢት 29/2017 ዓ/ም ጀምሮ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በየደረጃው ላሉ የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል።
የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል በጊዜ የለንም መንፈስ መስራት ይገባል -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2017(ኢዜአ)፦ በየዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በላቀ ውጤት ለማስቀጠል በጊዜ የለንም መንፈስ በትጋት መስራት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና የዘርፎች ዕቅድ አፈጻጸምን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ከፌዴራል ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር መገምገም ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ በ100 ቀናት የትኩረት ማዕከል የሆኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶች፣ የታዩ ክፍተቶች እና የትኩረት አቅጣጫዎች ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ ታይተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ እና በተለያዩ መስኮች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

በየዘርፉ የተሰሩ ስራዎችን በአግባቡ መለካት፣ ማቅረብ እንዲሁም ለሌላው ማስረዳት እንደሚገባ ገልጸው፤ አሁንም አመራሩ በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።

ሰራተኛውን በአግባቡ የማይመራ፣ የማይመዝን እና የማይከታተል መኖሩንና በጥቂት ታታሪ ሰራተኞችና ኃላፊዎች ተቋማት የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ እንደሚስተዋል ገልጸው፤ ይህንን መፈተሽ እና ማስተካከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከታሰበው በላይ የተሳኩ ድሎች መመዝገባቸውን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁንም ትኩረት የሚፈልጉ አካባቢዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
አገራዊና ዓለም አቀፋዊ አውድን በመገንዘብ እየተገኙ ያሉ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸው የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ከዚህ በላይ መሮጥ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ እና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርምን መፈጸም ውዴታ ሳይሆን ግዴታ መሆኑንም ተናግረዋል።

አገልግሎት አሰጣጥ ሁሉንም ሊያሳስብ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በጠንካራ አመራር እና ሰራተኛ የታጀበ አገልግሎት አሰጣጥ መኖር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ከተገኙ ውጤቶች በላይ ለማሳካት ሁሉም በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በውይቱ ላይ የአፍሌክስ ከፍተኛ አመራሮች፤ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች እና ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል::
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና በኢትዮጵያ የማልታ አምባሳደር በትብብር ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2017 (አፍሌክስ) -
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በኢትዮጵያ የማልታ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ ጋር ቀደም ሲል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል።

በአፍሌክስ ዋና መስሪያ ቤት የተካሄደው ስብሰባ በማልታ እና በኢትዮጵያ መካከል በአመራር ልማት እና ተያያዥ ዘርፎች ዙሪያ ትብብርን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው።

አቶ ዛዲግ በውይይቱ ላይ "በተለዩ የትብብር መስኮች ላይ ስራዎችን በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል" ብለው። የመግባቢያ ሰነዱን ስኬታማነት ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሚካሌፍ በንግግራቸው ኢትዮጵያ እንደ ሃገር አፍሌክስ እንደ ተቋም እያካሄዱ ላለው ለውጥ አድናቆታቸውን ገልፀው፣ "ኢትዮጵያ በጥቂት አመታትውስጥ በተሃድሶው ብዙ ለውጥ አድርጋለች። ይህም በእጅጉ የሚደነቅ ነው" ብለዋል። በተጨማሪም፣ የአረንጓዴ ልማት አጀንዳ፣ ሰውሰራሽ አስተውሎትና የስነምግባር አመራርን ጨምሮ በርካታ የትብብር መስኮችን ጠቁመው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአመራር ክህሎትን በማዳበር ለነዚህ ውጥኖች መሳካት ቁልፍ ተቋም መሆኑን ጠቅሰዋል።

በውይይቱ የመግባቢያ ስምምነቱ የትብብር መስኮች ብሎ የዘረዘራቸው የሥልጠና መርሃ ግብሮችን በጋራ ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች የአመራር ልማትን ለማሳደግ ያለሙ ውጥኖች ተነስተው፣ እንዴት ይተግበሩ በሚለው ላይ ከስምምነት ተደርሷል።

ውይይቱ ሲጠናቀቅ፣ አምባሳደሩ እና የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት የመግባቢያ ሰነዱን ስኬታማ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራር እና ሰራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር እቅድ ሃገራዊ እና ተቋማዊ አፈፃፀም ላይ ውይይት አደረገ::
የእቅድ አፈጻጸም ከተቀመጠው ግብ አንጻር 87.67 % ያሳካ እንደሆነም ተገልጿል።

ሱሉልታ 8/8 2017 ዓ.ም /አፍሌክስ/ የአካዳሚው የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የቀረበውን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ሃገራዊ እቅድ አፈፃፀም ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው የአመራር ልማት ላይ ገለፃ ሰተዋል፡፡

ኃላፊዋ ኢትዮጵያ አንደ ሀገር በበጀት አመቱ 8.4 እድገት ለማስመዝገብ እቅድ የያዘች አንደሆነ እና አለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያና ለኢትዮጵያ ያለው እንድምታ ምን ይመስላል፣ ሀገራችን ላይ እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና መሰረተ ልማት እና ፕሮጀክት አፈፃፀም ላይ የተሰሩ ስራዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 98.66% የተናቀቀ መሆኑ፣ የ ኮሪደር ልማቱ በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና የክልል ከተሞች በአፋጣኝ ሁኔታ እየተገነባ መሆኑ ከተሞቻችንን ከማስዋብ በላይ የቱሪዝም ተደራሽነት እና ትራንስፖርትና ፍሰትን ከማሳለጥ አኳያ ብዙ ስራ እንደተሰራ ተናግረዋል።

ወ/ሮ መሰረት ዘላቂ ልማት ማህበራዊ አካታችነት ላይ ልማቱ ለማህበረሰቡ አንድምታ ያለው ጥቅም፣ በበጀት ዓመቱ የኢነርጂ ተጠቃሚነት በሰፊው ጭማሪ ማሳየቱ፣ የትምህርት ዘርፉን ተደራሽነት ማስፋት፣ የእናቶች እና ህፃናትን ሞት በመቀነስ ላይ ብዙ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ ሃገራችንን ከተረጅነት ለመላቀቅና ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውንም አብራርተዋል።