African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
"ኮሚዩኒኬሽን ግጭትን ለማለዘብ ያገለግላል።"

አቶ ዛዲግ አብርሃ: የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

በኮሚዩኒኬሽን እና የአመራር ልማት ላይ ስልጠና ተሰጠ

ሱሉልታ መጋቢት 17/2027 (አፍሌክስ) - የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ የኮሚዩኒኬሽንን እና የአመራር ልማት ስርዐትን ዘርፈ ብዙ ሚና ለአፍሌክስ አመራር እና ሰራተኞች በጥልቀት አብራርተዋል።

ኮሚዩኒኬሽን በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ በሁሉም መስክ የሚጫወተውን ዘርፈ ብዙ ሚና ሲያብራሩ በግጭት ውስጥ የሚኖረውን አሉታዊ እና አዎንታዊ አስተዋጽዖ ላይ ትኩረት አድርገዋል።

"ኮሚዩኒኬሽን ዋነኛ የግጭት አባባሽ ሁነት እንደሆነው ሁሉ፣ ዋነኛ የግጭት መፍቻ መሳሪያም ነው!" ብለዋል።

"ከገጽ ለገጽ ኮሚዩኒኬሽን ይልቅ ዲጂታል ኮሚዩኒኬሽን ለተዛባ አረዳድ የተጋለጠ በመሆኑ ግጭት በመቀስቀስ እና በማባባስ ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል።"

"ኮሚዩኒኬሽን ግጭትን ለማለዘብ ያገለግላል።" ብለው፣ ግጭትን በኮሚዩኒኬሽን ለማብረድ የሚረዱ ቁልፍ መንገዶችን ዘርዝረዋል።

ስለአመራር ልማት ስርዐት ሲያስረዱ "በአመራር ልማት ላይ የሚሰራው እያንዳንዱ ተግባር ድምር ውጤቱ ትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋት ነው።" ሲሉ ተደምጠዋል።

የአመራር ልማት ስርዐት አስፈላጊነት፣ ትላንት የነበረበት፣ ዛሬ ያለበት እና የወደፊት ጉዞ በፕሬዝደንቱ ማብራርያ ተዳስሠዋል።

የስኬታማ አመራር ልማት ስርዐት መገለጫዎችና የውጤታማ አመራር ልማት ማነቆዎችን ዘርዝረው፣ አፍሌክስ እንደአመራር ልማት ማዕከልነቱ እነዚህን በመለየት በአፍሪካ ሁነኛ የአመራር ልማት ስርዐት የመዘርጋት ሃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል።