በሃሳብ እና በፈጠራ ወይም ግኝቶች መካከል ንጽጽራዊ መረጃ አቅርበው ሃሳብ በሁሉም ነገር ላይ ፍጹም የበላይነት እንዳለው አሳይተዋል። “አሁን ላይ መሪ የሚባለው በጉልበት ሳይሆን በሃሳብ ልቆ የተገኘ ነው!” ብለዋል በገለጻቸው።
“እድገት ማስመዝገብ ከፈለግን የት ነበርን፣ አሁን የት ነን፣ ወዴት መሄድስ እንፈልጋለን? የሚሉትን ጉዳዮች ጠንቅቀን ልናውቅ እና ልንመልስ ይገባል።” ብለዋል።
“እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ስለ ጉዞአችን እና ስለሚገጥሙን ፈተናዎች ጥልቅ መረዳት እንዲኖረን እናም ሁሉን አቀፍ እድገት ማስመዝገብ እንድንችል ይረዳናል።” ሲሉም ተናግረዋል።
አመራር እና ሰራተኛው የአካዳሚውን የለውጥ ጉዞ በብቃት እንዲመራ ክህሎቶችን የማስታጠቅ አላማን የሰነቀው ስልጠና አሁንም መካሄዱን ቀጥሏል።

የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በአፍሌክስ የአመራር ልማት ስልጠና መውሰድ ጀመረ
ሱሉልታ መጋቢት 11/2017 (አፍሌክስ) - የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን አመራሮች ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና መውሰድ ጀምረዋል።
መርሃ ግብሩ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የቡድን መሪዎች፣ ስራ አስፈፃሚዎችና የጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ 30 ተሳታፊዎችን ይዟል።
ጅማሮውን ዛሬ ያደረገውና ለተከታታይ 4 ቀናት የሚቆየው ስልጠናው እንደ ትራንስፎርሜሽን እና አገልጋይ አመራር፣ የለውጥ አስተዳደርና የሰራተኞች ልማትን የመሳሰሉ ለተቋም አመራር ወሳኝ የሆኑ ርዕሶችን አካቷል።
የስልጠናው ርዕሶች የተመረጡት ተሳታፊዎች በተቋማቸው ውስጥ ውጤታማ አመራር እንዲኖራቸው አስፈላጊ የሆኑት ክህሎቶችን ለማስታጠቅ ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል።
ስልጠናው መሪዎቹ በስራ ላይ የሚገጥሙ ውስብስብ ፈተናዎችን በመፈተሽ እና አወንታዊ የስራ አካባቢን በመፍጠር ውጤታማ የለውጥ አመራርን መተግበር እንዲችሉ ማገዝን አላማው አድርጓል።
የአመራር መርሆዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችሉ ገለጻዎች እና ውይይቶች የስልጠናው አካላት ናቸው።

የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር በአፍሌክስ የፈተና ንድፍ በማዘጋጀት ላይ ነው
ሱሉልታ መጋቢት 13/2017 (አፍሌክስ) - የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እያካሄደ ያለውን ሪፎርም ተከትሎ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ለራሱና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች የሙያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ንድፍ በአፍሌክስ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።
ንድፉ በዋናነት እቅድ፣ የአየር ንብረት፣ ፖሊሲ እና ስታቲስቲክስ ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን፡ የማውጣት ሂደቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ ከፍተኛ ባለሞያዎች፣ መካከለኛ አመራሮች እና አማካሪዎች የተሳተፉበት ነው።
ከሰኞ ጀምሮ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዘጋጅነት እየተከወነ ያለው የማዘጋጀት ሂደት በተለያዩ ባለሞያዎች፣ በተለያዩ ዙሮች የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል።
ዝግጅቱ ንድፉን ማጠናቀቅ፣ ማስገምገም፣ የፈተና ረቂቅ ማዘጋጀት .....እያለ በርካታ ሂደቶችን የሚያልፍ ይሆናል።
አፍሌክስ ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ጋር በጋራ በመስራት ተቋማቱ ስልጠና፣ ኮንፈረንስና የብቃት ምዘና ስርዐት ማዘጋጀትን ጨምሮ የተለያዩ የአመራር ብቃትን እና የስራ አፈጻጸማቸውን ለማሳደግ የሚረዱ ተግባራትን እንዲከውኑ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ላይ ይገኛል።

ተለዋዋጭ በሆነው አለም አፍሌክስን ተወዳዳሪ ለማድረግ ተቋሙን ከአዳዲስ ሃሳቦች እና ግኝቶች ጋር ማስተሳሰር ይገባል ተባለ።
ሱሉልታ መጋቢት 13/2017 (አፍሌክስ) - በአፍሌክስ የአስተዳደር እና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ተቋማዊ ልህቀትን በተመለከተ ስልጠና ሲሰጡ እንደጠቀሱት፤ ብቁ እና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት የላቀ አፈጻጸም ያስፈልጋል ብለዋል። በስልጠናው ላይ በተነሱ ሃሳቦች ዙሪያም ውይይቶች ተደርገዋል።
በስልጠናው ላይ የተነሱ ሃሳቦችን ከአፍሌክስ ተልዕኮ ጋር በማስተሳሰር ተቋሙን ወደስኬት ማድረስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች በውይይቶቹ ተዳሰዋል።
ውይይቶቹ የቀሪውን በጀት ዓመት ወሳኝ የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የአመራር ልማትን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና የአካዳሚውን ተልዕኮ ከግብ በማድረስ ወደ ስኬት መጓዝ ላይ ትኩረት አድርገዋል።
ተለዋዋጭ በሆነው አለም አፍሌክስን ተወዳዳሪ ለማድረግ ከአዳዲስ ሃሳቦች እና ግኝቶች ጋር ተቋሙን ማስተሳሰር እንደሚገባ በውውይቶቹ ላይ ተጠቁሟል።
የአፍሌክስ አመራር እና ሰራተኞች እየወሰዱ ያሉት ስልጠና በመድረክ ከሚቀርቡ ማብራሪያዎች በተጨማሪ ተሳታፊው ሃሳብ የሚያነሳባቸውን አሳታፊ ውይይቶች ያካተተ ነው።