African Leadership Excellence Academy
2.15K subscribers
2.38K photos
90 videos
6 files
105 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
"ተቀባይነት ማጣት ለሰነፍ ተስፋ መቁረጫ፡ ለብርቱ ደግሞ የቁጭት እና የብርታት ምንጭ ነው!" ዛዲግ አብርሃ፡ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

የአፍሌክስ ስልጠና 5ተኛ ቀን ውሎ

ሱሉልታ መጋቢት 13/2017 (አፍሌክስ) - ዛሬ 5ተኛ ቀኑን ባሳቆጠረው ስልጠና አቶ ዛዲግ አብርሃ አትችልም ተብሎ ተቀባይነት ማጣትን ወደ ትልቅ እድል መቀየር ይቻላል ሲሉ ተናገሩ።

ተስፋ ያለመቁረጥን እና የሁለተኛ እድልን ላይ ትኩረት ሰጥተው በሰፊው የዳሰሱት አቶ ዛዲግ፡ በአለማችን በተደጋጋሚ ተቀባይነት አጥተው ተስፋ ባለመቁረጥ ታትረው ከስኬት የደረሱ ግለሰቦችን፤ ተቋማትን እና ሀገራትን እንደምሳሌ በማንሳት ተቀባይነት ማጣት ወድቆ መቅረት አለመሆኑን አስረድተዋል።

በንግግራቸው "ተቀባይነት ማጣት ለሰነፍ ተስፋ መቁረጫ፡ ለብርቱ ደግሞ የቁጭት እና የብርታት ምንጭ ነው!" ብለዋል።

"አፍሌክስ ሁለተኛ እድል ያገኘ ተቋም ነው!" ብለው፡ "ይህንን ሁለተኛ እድል ተጠቅሞ አካዳሚው ያነገበውን ታላቅ ራዕይ ከግብ በማድረስ ታላቅ አፍሪካዊ ተቋም ለማድረግ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል" ሲሉ አሳስበዋል።

"ኢትዮጵያ የአፍሪካን መሪዎች የማሰልጠን አኩሪ ታሪኳን በአፍሌክስ አጠናክራ እንድታስቀጥል እኛ ሃላፊነት አለብን!" ብለዋል።
"የተቋማት ግንባታ ጊዜ የሚወስድ ተግባር በመሆኑ ስራውን ዛሬ መጀመር አለብን!" ዛዲግ አብርሃ፣ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

የአፍሌክስ መለወጥ የግድ ነው ተባለ

ሱሉልታ መጋቢት 14/2017 (አፍሌክስ) -ለአካዳሚው አመራር እና ሰራተኞች ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙት የአካዳሚው ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለውጥ ለአፍሌክስ ምርጫ ሳይሆን ብልጫ ነው ብለዋል።

የሃገራዊ ሪፎርሙ አካል መሆን፣ የአሰራር ስርዐቱን ማሻሻል፣ ድርጅታዊ ቁመናውን ማሳደግ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ተቋም ማድረግ እና መሰረታዊ ከሆነው የአመራር ልማት ለውጥ ጋር መጓዝ የአካዳሚው የለውጥ ጉዞ ዋነኛ ኢላማዎች መሆናቸውን አንስተዋል።

በተቋማት የለውጥ ሒደት ውስጥ ተግዳሮቶችን ተቋቁመውና አሸንፈው የአሻጋሪነት ሚና የሚወስዱ ተቋማት እንዳሉ ሁሉ፤ በገጠማቸው የህልውና አደጋ ተሸንፈው ህልውናቸውን ያጡ ተቋማት በታሪክ እንደተመዘገቡ ጠቁመው "የአፍሌክስ ስኬት የአመራርና የሰራተኛው ስኬት በመሆኑ፤ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ እንደ ዐይኑ ብሌን ሊጠብቀውና ሊያስቀጥለው ይገባል።" ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም "የመጪውን ትውልድ መሪዎች የሚቀርጽ ተቋም ገንብተን ለትውልድ አሻራችንን እናኑር" የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል።

የተቋም ግንባታንና ስልጣኔን ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚሉት አቶ ዛዲግ፤ እውነታውን ከአፍሌክስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አዛምደው አስቀምጠዋል። "የተቋም ግንባታ ጊዜ የሚወስድ ተግባር በመሆኑ፣ ስራውን ዛሬ መጀመር አለብን!" ብለዋል።