African Leadership Excellence Academy
2.29K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን 171 ተማሪዎችን አስመርቋል
በምርቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ተመራቂዎች አካዳሚው ስሙንና ተልዕኮውን ለውጦ በአዲስ መልኩ በአህጉርና በሃገር ደረጃ ከፍተኛና ተተኪ መሪዎችን የማሰልጠንና የማብቃት ስራን ለማከናወን አስፈላጊውን የለውጥ ሂደት በሚያደርግበት ጊዜ በመመረቃችሁ የአካዳሚው ታሪካዊ የለውጥ ሂደት አካል ናችሁ ብለዋል፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ በክፍተኛ ተግዳሮትና የብልፅግና ጉዞ አቋራጭ መንገድ ላይ ሆና የልዕልናና የህልውና ትግል በምታደርግበት ጊዜ ላይ የምትመረቁ ተመራቂዎች ሀገራችንን ለማፍረስ ከተነሱ ኃይላት በመከላከሉም ሆነ ህዝባችንን ወደ ዕድገትና ብልፅግና አቅጣጫ ለመምራት ልዩ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ ተመራቂዎች ፈተናዎችን ሁሉ ተቋቁማችሁ ለዛሬይቱ ቀን መብቃታችሁ ያላችሁን የመሪነት ቁርጠኝነት ጠቋሚ ከመሆኑም ባሻገር ለተማራችሁት ትምህርት ጥልቀት ተግባራዊ ገጽታ እንደሚሰጠው አምናለሁ ብለዋል፡፡
የአካዳሚው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ርዕሰ አካዳሚ የነበሩት አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው ተመራቂ አመራሮች የቀሰሙትን ንድፈ ሃሳባዊ የአመራር ዘይቤዎችን ከተሞክሯቸው ጋር በማጣመር ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባቸው አሳስበው የአካዳሚው መምህራንና ሰራተኞች ተመራቂዎች ለዚህ ታላቅ ቀን እንዲበቁ በማድረጋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሁለተኛ ዲግሪ በዘጠኝ የትምህርት አይነቶች ያስተማራቸውን 154 ወንድ እና 17 ሴት በድምሩ 171 ተማሪዎችን ቅዳሜ ታህሳስ 02/2014 ዓ.ም አስመርቋል፡፡
“የመሪ እድገት ቁልፉ የሁል ጊዜ ተማሪ፣ ንቁ ተመራማሪና አስተዋይ ተመሪ መሆን መቻሉ ላይ ነው፡፡”
ዶ/ር ምህረት ደበበ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ
አካዳሚው በሁለተኛ ዲግሪ የሁለተኛ ዙር ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ
“የመሪነት ስኬት ከማያቋርጥ የህይወት ዘመን ዕድገትና ያልተከፋፈለ ትኩረት የሚገኝ ነው፡፡”
ዶ/ር ምህረት ደበበ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ
አካዳሚው በሁለተኛ ዲግሪ የሁለተኛ ዙር ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ
“መሪ አስተማሪ ብቻ ሳይሆን ተማሪ መሆኑን፤ የሌሎች መሪ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ተመሪ መሆኑን መዘንጋት አይገባውም፡፡”
ዶ/ር ምህረት ደበበ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ
አካዳሚው በሁለተኛ ዲግሪ የሁለተኛ ዙር ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ
በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ከጦርነት ወደ ብልፅግና- በሰላም ጎዳና በሚል ርዕስ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ አመራሩና ሰራተኛው የጋራ አረዳድ እንዲኖረውና በቀረበው ሰነድ ላይ ግብዓት እንዲሰጥ ያለመ ውይይት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 30 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
የሱማሌ ክልላዊ መንግሰት የማኔጅመንት እና ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሌጅ በ አራት የስልጠናና የትምህርት መስክ ማለትም በ አመራር (Leadership) ፤ ደቨሎፕመንት ኮሚኒኬሽን (Development Communication)፤ በሰላምና ግጭት ማኔጅመንት (Peace and Conflict Management) ፤ እና በፕሮጀክት ማኔጅመንት (Project Management) ለክልሉ አመራሮች በማስተርስ ዲግሪ ደረጃ ትምህርት እና የአጫጭር ጊዜ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ኮሌጁን ወደ ዩንቨርሲቲ ደረጃ ለማሳደግ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ(HERQA) ጋር አብሮ እየሰራ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የማኔጅመንት እና ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሌጁ ዲን አመራር አካላት ለጉዳዩ መሳካት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ቀን ከሌት እየተጉ ይገኛሉ፡፡

ለዚህ ውጥን ስኬት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እያደረገ ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክልሉ መንግሰት የማኔጅመንት እና ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሌጅ ትልቅ አክብሮት አለው፡፡
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 9 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በአመራርነት  ሲያገለግሉ የነበሩት የአካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ፀጋዬ ማሞ እና የጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ደምሴ ሽቶ እንዲሁም በአካዳሚው በመምህርነት ሲያገለግሉ ለነበሩት መምህራን የሽኝትና የምስጋና መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የስነልቦና ፣ የማህበራዊና የአዕምሮ ጤና ድጋፍ አገልግሎቶችን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና መሰጠት ተጀመረ
***********************
የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የስነልቦና ፣ የማህበራዊና የአዕምሮ ጤና ድጋፍ አገልግሎቶችን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ መሰጠት ተጀመረ፡፡
ስልጠናውን በይፋ የከፈቱት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርእሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ እንደገለጹት በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ተደራሽ የሚያደረግ የማህበራዊ፣የስነልበናና የአእምሮ ጤና ስልጠና ዘረፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ገልጸው የአመራር ልህቀት አካዳሚውም ሰልጠናው በተገቢው መንገድ እንዲከናወን ድጋፍን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው እንደገለጹት በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ምክንያት የተከሰቱት ችግሮች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ካሰድሩት ተጽእኖ በተጨማሪ በዜጎች ላይ እጅግ የከፋ ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እንዳደረሰ በተለይም በአሸበሪው ህውሃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉና ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴት የህብረተሰብ ክፍሎች ከደረሰባቸው አሰቃቂ ጉዳት ተላቀው ወደ ቀደመ ህይወታቸው ለመመለስ የሁሉንም አካላት ርብርቦሽ እየጠበቁ አንደሆ ገልጸው ዛሬ በይፋ የተጀመረው በስነልቦና፣ በማህበራዊና በአዕምሮ ጤና፣ ድጋፍ ላይ ያተኮረ የአሰልጣኞች ስልጠና ይህንን ግዙፍ ሀገራዊ ችግር ለመቅረፍ የራሱን አበርክቶ ይወጣል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የማስተርስ ዲግሪ ለመማር የመግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ በ2014 ዓ.ም ትምህርት ለመጀመር በዝግጅት ላይ የነበራችሁ ተማሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ተዛውራችሁ በመደበኛ የትምህርት መርሀ ግብር እንድትቀጥሉ በተወሰነው መሰረት ዩኒቨርስቲው የምዝገባውን ቀን እና ተመዝጋቢዎች ማሟላት ያለባቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለአካዳሚው በግልባጭ አሳውቋል፡፡
በመሆኑም በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርስቲው በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳወቅን ከዩኒቨርስቲው የተላከውን ደብዳቤ ከዚህ መልዕክት ጋር አያይዘንላችኋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ስልጠና እየሰጠ ነው
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ኃላፊዎች ስልጠና እየሰጠ ሲሆን ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ (ዶ/ር) አካዳሚው የተቋቋመው ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁሉም ደረጃ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና የሀገሪቱን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም፣ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የአመራር አካላት አቅምን ለመገንባት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ርዕሰ አካዳሚው አያይዘውም አካዳሚው በንድፈ ሀሳብ የተደገፈ ተግባር ተኮር የአመራር ስልጠና እንደሚሰጥ ገልፀው ስልጠናው The Art of finishing well በተለይም the proof of Integrity and The mark of Excellence በሚልና በሌሎች ርዕሶች ላይ በተለያዩ አሰልጣኞች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በበኩላቸው ተቋም የሚመሰረተው ጠንካራና ተባብረው በሚሰሩ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መሆኑን አስታውቀው ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡