African Leadership Excellence Academy
2.29K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
"ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ስትካድ የመጀመሪያዋ አይደለም፡፡" ክህደትን ማሸነፊያው ብቸኛ መንገድ ደግሞ አንድነትንና ህብረትን ማጠናከሩ ነው ብለዋል ምህረት ደበበ (ዶ/ር) የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ፡፡
በምዕራባውያንና በአሜሪካ የሚደረግብንን ጫና ልንሻገረው የምንችለው ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጉላት በመሆኑ ሁላችንም ከመቼውም በበለጠ መንገድ ትኩረት ሰጥተን መስራት እንዳለብን አስታውሰው የአገር መሪ እስከ ጦር ግንባር ድረስ እንዲዘምትና እንዲመራ የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ መገኘታችንን ሁሉም ሰው ተገንዝቦ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለተፈናቀሉ ዜጎች በአቅሙ ድጋፍና እገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ ርዕሰ አካዳሚው ተናግረዋል፡፡
የጦርነቱ ድል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ ድል መታገዝ እንደሚገባው ተገለፀ
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጦር ግንባር መገኘታቸው ከፍተኛ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም የፈጠረ መሆኑን ያነሱት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ መምህር ያሬድ አስራት (ዶ/ር) እየተገኘ ያለው ድል በፖለቲካና በዲፕሎማሲው እንዲሁም በሁሉም መስክ መታገዝ እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡
እየተገኘ ያለው ድል የሚደነቅና የሚያኮራ እንደሆነ ያነሱት ያሬድ አስራት (ዶ/ር) “አንዳንዴ ጦርነትን ማሸነፍ በራሱ በቂ አይደለም ከዚህ በፊት መቀሌ በ3 ሳምንት ውስጥ መግባት ችለናል ነገር ግን መቀሌ መግባት ግብ አይደለም፤ ስለዚህ ከጦርነቱ ማሸነፍ ባሻገር በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚውና በዲፕሎማሲው መስክ ማሸነፍ ይገባል” ብለዋል፡፡
የተፈጠረው ሃገራዊ አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከዚህ በፊት የነበሩ መከፋፈሎች ተመልሰው እንዳይመጡ ሁሉንም በእኩልነት ሊያሰባሰቡ የሚችሉ የጋራ ራዕዮችን እና የጋራ ትርክቶችን መፍጠር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ጦርነቱን እንደምናሸንፍ እርግጠኛ ነኝ ያሉት ያሬድ አስራት (ዶ/ር) አላማችን ሰፊ መሆን እንዳለበት እና የውጭውን ጫና ለመቀነስ ጦርነቱን በአጭር ጊዜ መቋጨት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በፀረ ፆታዊ ጥቃት፣ በኤች አይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር እና በስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ርዕሶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልቀት አካዳሚ በስርዓተ-ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን፣ ኤችአይቪ/ኤድስንና ሙስናን በማስቆም ላይ ስልጠና ሰጠ።
በሥርዓተ ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን፣ ኤች አይ ቪ ኤድስንና ሙስናን በማስቆም ላይ ለአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ ባለሙያዎች በሱሉሉታ ከተማ በሚገኘው የአካዳሚው የስብሰባ አዳራሽ ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ።
በመክፈቻ ንግግራቸው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረተ ደበበ ስልጠናው በእያንዳንዱ ተግባር ላይ ልምድ ለመለዋወጥ ያለውን ጠቀሜታ አንስተዋል።
ስልጠናው ራሳችንን የምንመለከትበት እና ለውጥ የምናመጣበት መሆን አለበት ብለዋል። ምንም እንኳን የቃል እና አካላዊ ጥቃትን ጨምሮ ብዙ ጥቃቶች ቢኖሩም.ስልጠናው እውቀታችንን ብቻ ሳይሆን እንደ መስሪያ ቤት፣ እንደ ኃላፊ እና እንደ ግለሰብ አመለካከታችንን መቀየር እንዳለበት ዶ/ር ምህረት አሳስበዋል።
ሀረገወይን ፋንታሁን (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ የቋንቋና ኮሙኒኬሽን ረዳት ፕሮፌሰር በሥርዓተ-ፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች፣ አጠቃላይ የአዕምሮ ውጣ ውረዶች፣ ጽንሰ-ሀሳቦቹ፣ ሥርጭቱ፣ ሥር የሰደዱ ምክንያቶች፣ ውጤቶቹ/ተጽኖዎች እና በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት ሪፖርት ለማድረግ እንቅፋት በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
በተጨማሪም በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት የትኩረት አቅጣጫዎችን በስራ አለም፣ ግጭት ተያያዥነት ባላቸው በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት እና በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት መከላከል እና ምላሽ መስጠት የሚቻልባቸውን መንገዶች ጠቁመዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ደሞዜ ደገፋ በበኩላቸው የኤችአይቪ/ኤድስን ሁኔታ እና የኢትዩጵያ ሁኔታ (በተወሰኑ መለኪያዎች) አዝማሚያዎች ፣ ኤች አይ ቪ ኤድስ በአዲሱ ወረርሽኝ (ኮቪድ-19) ፣ ስላጋጠሙት ጉዳዮች አብራርተ
የአካዳሚው ሴኔት የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አጸደቀ
የአፍሪካ አመራር ልሕቀት አካዳሚ ሴኔት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በአካዳሚው በመምህርነት ሲያገለግሉ ለነበሩት ባምላክ ታደሰ (ረዳት ፕሮፌሰር) የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በተጨማሪም ሴኔቱ በተለያዩ ምክንያቶች የመመረቂያ ፅሁፋቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች መካከል አራቱ ያጠናቀቁ በመሆናቸው እንዲመረቁ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
አካዳሚው ቅዳሜ ታህሳስ 02 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን 171 ተማሪዎችን ያስመርቃል፡፡
የአካዳሚው ሴኔት የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አጸደቀ
የአፍሪካ አመራር ልሕቀት አካዳሚ ሴኔት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በአካዳሚው በመምህርነት ሲያገለግሉ ለነበሩት ባምላክ ታደሰ (ረዳት ፕሮፌሰር) የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡