African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት በሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሸነፍ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ዕውን የሚያደረግ አመራር ነው

ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት በየጊዜው በሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሸነፍ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ዕውን የሚያደረግ አመራረ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ያሉት በአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ሲሰጥ የነበረውን የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ማጠናቀቂያ መድረክ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

በኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ ችግሮች ቢበዙም የነገዋ ኢትዮጵያ ግን በብሩህ ተስፋ የተሞላች ናት ብለዋል።

በመሆኑም አመራሩ በየጊዜው በሚያጋጥሙ ችግሮች ሳይሸነፍ የተሻለ ነገን ዕውን ለማድረግ ሊተጋ ይገባል ነው ያሉት።

ኃላፊነት የተሰጣቸው አመራሮችም ስራዎቻቸውን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዲከውኑ አሳስበዋል።

ላለፉት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአዳዲስ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና በሁሉም ክልሎች ተሿሚ አመራሮች ዘንድ እንደሚቀጥል ተገልጿል::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አህጉራዊ የአመራር ክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት የራሱን ድርሻ ለማበርከት እንደሚሰራ የአካዳሚው ርዕሰ- አካዳሚ ዶክተር ምህረት ደበበ ገለጹ።
ዶክተር ምህረት እንደተናገሩት÷ አካዳሚው በአገሪቷና በአህጉሪቱ የአመራር ክፍተቶችን ለመሙላት የሚሰራ ተቋም ነው።
በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ መሰል የአመራር ክፍተቶች መኖራቸውን ጠቁመው አካዳሚው እነዚህን ችግሮች ለማቃለል የራሱን ድርሻ እንደሚወጣ ነው የተናገሩት።
የአካዳሚው ርዕሰ- አካዳሚ ሆነው ተቋሙን ከተቀላቀሉ ጀምሮ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ የሚቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።
አካዳሚው ብቁ አመራር ለመፍጠር የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የአመራር የሥልጠና ማዕከል መሆኑን ገልጸው የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጭምር የሚጠቅም መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህ እሳቤ መሰረት አዲስ የተሾሙ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሕዝብ አገልጋይ መሪ መሆን የሚያስችላቸው የአመራር ክህሎት ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ በአካዳሚው በነበራቸው ቆይታ ከአካላዊ እንቅስቃሴ ጀምሮ ሥነ-ልቦናቸውን የሚያነቃቁ ለሥራ ዝግጁ የሚያደርጋቸው ሥልጠና መውሰዳቸውንም ጠቁመዋል።
አዲስ የተሾሙት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ ከሰራተኞች ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡
በከፍተኛ ሹመት ወደ ሌላ የስራ ኃላፊነት ለተዘዋወሩ የቀድሞ የአካዳሚው ፕሬዝዳንትና ም/ፕሬዝዳንት የሽኝትና የምስጋና መርሃ ግብር ተካዷል፡፡
በሽኝትና በምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ የቀድሞ የአካዳሚው አመራሮች ለሰሩት ስራ ምስጋና እንደሚገባቸው በመግለጽ በሄዱበት መልካም የስራ ጊዜ አንዲሁንላቸው ተመኝተዋል፡፡
የሽኝትና የምስጋና መርሃ ግብሩ የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በአካዳሚው የሱሉልታ ማሰልጠኛ ማዕከል ተደርጓል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በረዳት ፕሮፌሰር ማዕረግ ተመራማሪ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ደሳለኝ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡
እንኳን ደስ አለዎ!! መልካም የስራ ዘመን እንመኛለን!!
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደረገ

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ ከመላው የአካዳሚው ሰራተኞች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ እንደተናገሩት የውይይቱ አላማ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝና ሰራተኛው የሚጠበቅበትን ማድረግ እንዲችል ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ምህረት የሀገራችን ሁኔታ ከህልውና ጋርና ኢትዮጵያ ትቀጥላለች ወይም አትቀጥልም የሚል ሁኔታ ላይ የደረሰና ሀገሪቱ በምዕራባውያን ከባድ ጫና እየደረሰባት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ርዕሰ አካዳሚው የሰብአዊ መብት ጉዳይ ሳይሆን ሀገሪቱን እንደ ሶሪያ፣አፍጋኒስታንና ሊቢያ ለማፈራረስ የታሰበ አጀንዳ በመሆኑ ህዝባዊ ድጋፍ ማድረግ አማራጭ የሌለው መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

የጥናትና ምርምር ምክትል ርዕሰ አካዳሚ የሆኑት አቶ ደምሴ ሽቶ በበኩላቸው የሀገሪቱን አንድነት የሚፈታተንና ህዝባችንን በተለያየ መንገድ የሚረብሸ ነገር ሲከናወን ወቅታዊ ወይይቶች ማድረግና ግንዛቤ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ ደምሴ ሀገር የማፍረስ እንቅስቃሴንና ውዥንብሮችን መከላከል፣ የሚኖርበትን አካባቢ መጠበቅና ሰላምን ማስከበር እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊቱን በተለያየ መንገድ በመደገፍ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት መወጣት የሰራተኛው ድርሻ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

የአካዳሚው ሰራተኞችና አመራሮችም በበኩላቸው ወቅታዊ ውይይቱ አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት የአንድ ወር ደመወዛቸውን በአንድ አመት ለመክፈል ተስማምተው በተጨማሪም ባላቸው አቅም በዕውቀት፣ በቁሳቁስ እንዲሁም በደም ልገሳ እንደሚሳተፉም ቃል ገብተዋል፡

በመጨረሻም በውይይት መድረኩ የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ የመስሪያ ቤቱ መዋቅር በባለሙያዎች ከ6-8 ሳምንታት ውስጥ ተሰርቶ ለሰራተኛው እንደሚቀርብም አስታውቀዋል፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጫናውን አሸንፎ መውጣት ለአፍሪካም ማሸነፍ ነው - ዶ/ር ምህረት ደበበ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ አሁን የተከፈተባትን የውጭ ጫና አሸንፎ መውጣት ለአፍሪካም ጭምር ማሸነፍ እንደሆነ መገንዘብ እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዶክተር ምህረት ደበበ ገለጹ፡፡
ዶክተር ምህረት እንደገለጹት ÷ ኢትዮጵያ አሁን የተከፈተባትን የውጭ ጫና አሸንፎ መውጣት ለአፍሪካም ጭምር ማሸነፍ እንደሆነ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ትልቅ እና ታሪካዊ ጊዜ ላይ ነን ፤ አፍሪካውያን ከጎናችን እንደሚቆሙ እያሳዩን ነው ፤ ስለሆነም ጦርነቱን ከማሸነፍ ውጪ ሌላ ምርጫ የለንም ብለዋል፡፡
በታሪካችን ኢትዮጵያ ብቻዋን ነፃነቷን አስከብራ ሌሎችንም ወደ ነፃነት ስትመራ ይሄ ሁለተኛው የነፃነት ጥሪ መሆኑን ጠቁመው ÷ ይሄንን ጦርነት በማሸነፍ የአሁኑ ትውልድ ታሪክ መጻፍ እንዳለበትም ነው የገለጹት፡፡
ምዕራባውያን የአፍሪካን አገራት እንደ አገር ማየት እና ማክበር አይፈልጉም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ÷ ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ውስጥ ያልገባች በአጭር ጊዜ ውስጥም ቢሆን በጣልያን ወረራ አባቶቻችን እጅ ሳይሰጡ የኢትዮጵያን ነፃነት እንዳስጠበቁ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያን ትልቅ እናደርጋታለን ብለው ዜጎቿ ሲነሱ ምዕራባውያን ደግሞ እንዳንሆን በአሁኑ ወቅት ተነስተውብናል ብለዋል፡፡
ይህንን እንዳይሳካ ለማድረግ እንደ ሁነኛ መሣሪያ ሆኖ ያገኙት በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት እንደሆነ ጠቅሰው ÷ የአሸባሪውን ህወሓት ኃይል ለዚህ መጠቀሚያ ስለማድረጋቸውም ነው ያነሱት፡፡
ተጨማሪ ለማንበብ - https://www.fanabc.com/የኢትዮጵያ-የውጭ-ጫናውን-አሸንፎ-መውጣት/
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሃገር መከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን ለብሔራዊ አደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን ያስረከቡት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ ይህን አስቸጋሪ ወቅት ማለፍ የሚቻለው በመደጋገፍ እንደሆነ ገልፀው ሁሉም ነገር የሚኖረው ሃገርና ህዝብ ሲኖር ነው ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የብሔራዊ አደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ አካዳሚው ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡