African Leadership Excellence Academy
2.17K subscribers
2.39K photos
90 videos
6 files
107 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
AFRICAN LEADERSHIP EXCELLENCE ACADEMY PRESIDENT AND SINGAPORE AMBASSADOR DISCUSS STRATEGIC PARTNERSHIP FOR AFRICAN LEADERSHIP DEVELOPMENT

Addis Ababa, Ethiopia (AFLEX) – On February 14, 2025, Mr. Zadig Abreha, President of the African Leadership Excellence Academy (AFLEX), held a high-level discussion with His Excellency A. Selverajah, Singapore’s Ambassador to the Federal Democratic Republic of Ethiopia and the African Union (AU).

The meeting underscored the shared commitment of Ethiopia and Singapore to collaborate in nurturing the next generation of African leaders through strategic partnerships in leadership development.
AFLEX and ACBF Move Forward with MOU Implementation to Drive African Development

Addis Ababa- February 14, 2025 (AFLEX):- In a significant step toward advancing African development, the African Leadership Excellence Academy (AFLEX) and the African Capacity Building Foundation (ACBF) have taken concrete steps to implement the Memorandum of Understanding (MOU) signed earlier between the two organizations.

Today, on February 14, 2025, AFLEX President Mr. Zadig Abreha and ACBF Executive Secretary Mr. Mamadou Biteye held a high-level discussion to finalize the implementation strategy of the MOU.
Both leaders expressed their commitment to accelerating the execution of the agreement, which aims to address critical challenges and opportunities across the continent.

As part of the implementation process, AFLEX has developed a detailed Action Plan, which has been shared with ACBF. The two organizations have agreed to establish a Technical Committee to oversee the execution of the initiatives outlined in the plan.

This committee will play a pivotal role in driving forward key projects, including Preparing concept notes and proposals on pressing African issues, Organizing the Future Summit and the African Think Tank Summit, Advancing the African Dream initiative and Strengthening future institutions and capacity-building programs across the continent.

Mr. Zadig Abreha emphasized the importance of collaboration, stating, “This partnership is a milestone in our shared vision for a prosperous Africa. We are ready to work hand-in-hand with ACBF to turn our plans into action."

Echoing this sentiment, Mr. Mamadou Biteye remarked, "The time for action is now. By working together, we can unlock Africa's potential and build a brighter future for generations to come."

The Technical Committee is expected to begin its work immediately, with both organizations pledging to prioritize efficiency and impact.

Stay tuned for updates as AFLEX and ACBF embark on this transformative journey to shape Africa's future!

#AfricanDevelopment #AFLEX #ACBF #Leadership #CapacityBuilding #AfricanDream #FutureSummit
🎉አፍሌክስ በኢትዮጵያ🇪🇹 ብሎም በአፍሪካ🌍 የመጀመሪያ በሆነው የሴቶች የአመራር ልማት መርሃ-ግብር ያበቃቸውን ሴት አመራሮች ሊያስመርቅ 5️⃣ ቀናት ብቻ ቀርተዋል🎉
አፍሌክስ ለገቢዎች ሚኒስቴር እየሰጠ የሚገኘው ስልጠና ቀጥሏል

ሱሉልታ የካቲት 8/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)- በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለገቢዎች ሚኒስትር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙዎች እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና በ2ተኛ ቀን ውሎው የተግባቦት ክህሎት እና የጊዜ አጠቃቀም ላይ ትኩረንቱን ያደርገ ስልጠና ተሰጥቷል።

በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፣ የተግባቦት ክህሎትን በማሳደግ ተቋማዊ ውጤታማነትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

ገለጻቸውን ኮሚዩኒኬሽን የአንድ ሃገር እና ማህበረሰብ የደም ስር ነው ብለው የጀመሩት ዶ/ር ቢቂላ፣ የተግባቦት ክህሎት ከራስ ጋር በሚደረግ ኮሚዩኒኬሽን ጀምሮ ከሌላ ሰው ጋር፣ ከቡድን፣ አልፎም ከህዝብ ጋር የሜረግ ማስ ኮሚዩኒኬሽን ወደመሆን እያደገ ይሄዳል ሲሉ ተናግረዋል።

የጠንካራ ኮሚዩኒኬሽን መገለጫዎች ምንድናቸው? ማንን እንዴት ኮሚዩኒኬት እናድርግ? የሚሉት በገለጽቸው ከተጠቀሱት ነጥቦች መካከል ጥቂቶቹ ሲሆኑ ከማብራሪያቸው በኋላ በተነሱ ነጥቦች ላይ ውይይት ተደርጓል።

ከሰአት በኋላ ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀምና አመራርን በተመለከተ በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት በመስራት ልምድ ያካበቱት የቢዝነስ አመራር አማካሪዋ ወ/ሮ እመቤት ተጫኔ ስልጠና ተሰጥቷል።

ወ/ሮ እመቤት የጊዜ አጠቃቀምን በደንብ መረዳት የሚያስገኛቸውን ዘርፈብዙ ጠቀሜታዎች አብራርተው፣ የውጤታማ ጊዜ አጠቃቀም ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎቻቸው ላይ ትኩረት አድርገው አሰልጥነዋል፣ ልምዳቸውን አጋርተዋል፣ ታዳሚዎችንም አወያይተዋል።

ለ3 ቀናት የሚቆየው የስልጠና መርሃ ግብር እሁድ በአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በሚሰጡት ስልጠና እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
Just now ·
#Happening_Now!!!
#አሁን!
"የሰው ልጅ ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን ከፈለገ ራሱን ማወቅ፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮን መረዳት ይጠበቅበታል" ዛዲግ አብርሃ
👉የሰውን ልጅ ትክክክለኛ ውሳኔ የመስጠት አቅም ከሚቀንሱት ነገሮች አንዱ ኮግኒቲቨ ባያዝ ይባላል❗️
👉ኮግኒቲቨ ባያዝ ምንድነው
🔹ስሜታዊነት
🔹ማህበረሰባዊ ተጽዕኖ
🔹ደመነፍሳዊነት
🔹ልማድ
🔹ሌሎች፣ ሌሎች ጉዳዮች በውሳኔ ሰጪነታችን ላይ ያላቸው ተጽዕኖ ምን ይመስላል
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ስነ
-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥን በተመለከተ ለገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች ስልጠና እየሰጡ ነው።
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ከNBC Ethiopia ቴሌቪዥን ጊዜ ግስ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ክፍል 2 ቆይታ ያለፈውን እና መጪውን ጊዜ ያብራራሉ "የጦርነት ሂሳብ አይገባቸውም... አደገኛውን መንገድ መርጠዋል" ይሉናል። እነማንን ይሆን? ማስፈንጠሪያውን በመጠቀም ሙሉውን እንድትከታተሉ ጋብዘናል፡-
https://www.youtube.com/watch?v=qUs4UhNa3yU
🎉አፍሌክስ በኢትዮጵያ🇪🇹 ብሎም በአፍሪካ🌍 የመጀመሪያ በሆነው የሴቶች የአመራር ልማት መርሃ-ግብር ያበቃቸውን ሴት አመራሮች ሊያስመርቅ 4 ቀናት ብቻ ቀርተዋል🎉
"ዛሬ እንደተቋምም እንደሃገርም የምንወስነው ውሳኔ ውጤት በወደፊቱ ትውልድ የምንታይበትን መንገድ ይወስናል።" አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

የገቢዎች ሚኒስቴር አመራር እና ከፍተኛ ባለሙዎች በአፍሌክስ ሲወስዱ የቆዩት ስልጠና ተጠናቀቀ።

ሱሉልታ የካቲት 9/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)- ስነ ምግባራዊ አመራር ላይ ትኩረቱን አድርጎ ለ3 ቀናት ያህል በገቢዎች ሚኒስቴር ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አመራር እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠናው ዛሬ ተጠናቋል።

በመጨረሻ ቀን ውሎው የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ስነ ምግባራዊ ውሳኔ ሰጪነትን የተመለከተ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

ውሳኔ ሰጪነት ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው ያሉት አቶ ዛዲግ፣ ውሳኔ መስጠት ለምን ያስፈልጋል ከሚለው ጥያቄ ተነስተው፣ ትክክለኛ ውሳኔ እንዳንሰጥ የሚያደርጉን ነገሮች ምንድናቸው፣ አንድ ሰው ትክክለኛ ውሳኔ ለመወሰን ምን ምን ሂደቶችን ማለፍ አለበት የሚሉትን ሃሳቦች አንስተዋል።

ውሳኔ ሰጪነት ሳይንስ ነው፣ ስለዚህ ሳይንስ ማወቅ ትክክለኛ ውሳኔ መስጠት እንድንችል ይረዳናል ብለዋል።

የገቢዎች ዘርፍ ለሃገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆኑ በዚህ ዘርፍ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ተጽዕኖአቸው የጎላ ነው ሲሉ ተናግረው የውሳኔ ሰጪነትን ጥበብ ከዘርፉ ጋር እያገናኙ አስረድተዋል።

አመራሮች ስነ-ምግባርን የተላበሱ እንዲሆኑ የሚያደርጓቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው፣ የስነ-ምግባራዊ አመራር ባህርያትን አብራርተዋል።

በአፍሌክስ አዘጋጅነት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠናው ተሳታፊዎች ዘርፈብዙ እውቀት እንዲጨብጡ ያስቻለና አሳታፊ እንደነበር ተገልጿል።
🎉አፍሌክስ በኢትዮጵያ🇪🇹 ብሎም በአፍሪካ🌍 የመጀመሪያ በሆነው የሴቶች የአመራር ልማት መርሃ-ግብር ያበቃቸውን ሴት አመራሮች ሊያስመርቅ 3 ቀናት ብቻ ቀርተዋል🎉
Always Matter, Never Mind? Always
Mind, Never Matter in Leadership

In leadership, balancing what truly matters and what can be dismissed is essential.

"Always Matter" emphasizes prioritizing core values, team well-being, and the mission, fostering trust and inspiring collective goals. "Never Mind" encourages leaders to focus on what is essential and dismiss distractions that hinder progress.

"Always Mind" highlights the importance of being aware of team dynamics and the broader implications of decisions, fostering open communication and adaptability.

Lastly, "Never Matter" reminds leaders to let go of ego and unnecessary conflicts, promoting a learning environment where growth is valued over perfection.

By embodying these principles, leaders can create a thriving and empowering environment for their teams.
ለምን መሪዎች?

መሪነት በማዕረግ ወይም በሹመት ብቻ የተገደበ አይደለም:: እያንዳንዳችን ልንይዘው የምንችለው አስተሳሰብ እና ኃላፊነት ነው።

መሪ ለመሆን በምንመርጥበት ጊዜ በአካባቢያችን ያሉትን የመምራት፣ የማነሳሳት እና የማበረታታት ሚና እንጫወታለን። ግን ሁል ጊዜ መሪ ለመሆን መጣር ያለብን ለምንድን ነው?

መሪዎች ለውጥ ይፈጥራሉ። ተግዳሮቶችን እና እድሎችን ይለያሉ፣ ሌሎችን በጥልቅ እንዲያስቡ እና አዲስ ነገር እንዲፈጥሩ ያበረታታሉ። የመሪነት ባህልን በማጎልበት ችግሮችን በጋራ መፍታትና በማህበረሰባችን ውስጥ እድገትን ማምጣት እንችላለን።

አመራር ጽናትን ያዳብራል። ጠንካራ መሪዎች መመሪያ እና ድጋፍ ይሰጣሉ፣ ሌሎች ተግዳሮቶችን እንዲያስሱ ይረዷቸዋል። ሁላችንም የመሪነት አስተሳሰብን ስንከተል፣ መሰናክሎችን ለማሸነፍ የጋራ አቅማችንን የሚያጠናክር የድጋፍ መረብ እንገነባለን።

ከዚህም በላይ መሪ መሆን ማለት አርአያ መሆን ማለት ነው። የእኛ ተግባራቶች እና ውሳኔዎች ለሌሎች አርአያ ይሆናሉ፣ በባህሪያቸው እና በአስተሳሰባቸው ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ።

የታማኝነት፣ የመተሳሰብ እና የተጠያቂነት ባህሪያትን በማካተት፣ በዙሪያችን ያሉትን ወደ አቅማቸው እንዲወጡ እናበረታታለን።

በመጨረሻም፣ አመራር ስለ ግንኙነት ነው። ግንኙነቶችን መገንባት እና ትብብርን ማጎልበት ነው። በዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ ለመሪነት ቅድሚያ ስንሰጥ ሁሉም ሰው ዋጋ ያለው ሆኖ የሚሰማውን እና የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ ስልጣን ያለው አካባቢ እንፈጥራለን።

ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለበለጠ ጥቅም ሁሌም መሪ ለመሆን መጣር አለብን። በጋራ፣ በሁሉም የህይወታችን ዘርፍ እንደ መሪ ሚናችንን በመቀበል ብሩህ የወደፊት ጊዜ መፍጠር እንችላለን።
Leadership-centered systems thinking Is essential for effective leadership in today’s complex environment.

This approach emphasizes understanding the needs, perspectives, and experiences of people within the system, fostering a culture of empathy and collaboration.

Leaders who adopt this mindset prioritize the well-being of their team members, recognizing that engaged and satisfied individuals drive organizational success.

By actively listening to feedback and involving team members in the decision-making process, leaders create an inclusive atmosphere where everyone feels valued.

Moreover, human-centered system thinking encourages leaders to view challenges holistically.

Instead of addressing problems in isolation, they consider the interconnectedness of various elements within the organization, enabling more sustainable and effective solutions.
አፍሌክስ ለጤና ሚኒስቴር እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ

ሱሉልታ የካቲት 10/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)-በአመራር መስኩ የጾታ እኩልነትን የማረጋገጥ አላማ ያለው የፐብሊክ ሊደሺፕ ፎር ጀንደር ኢኳሊቲ (PL4GE) ፕሮጀክት ለጤና ሚኒስቴር እና በስሩ ለሚገኙ ተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች በአፍሌክስ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

የአፍሌክስ፣ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የግሎባል ሴንተር ፎር ጀንደር ኢኳሊቲ ትብብር ውጤት የሆነው ይህ ፕሮጀክት በአመራር ዘርፍ የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በመስራት ላይ ይገኛል።

ዛሬ ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል የተጀመረው ስልጠናም የዚሁ አካል ሲሆን የጤና ሚኒስቴር አመራሮችን እንዲሁም በስሩ የሚገኙ ተጠሪ ተቋማትን የስራ ሃላፊዎች ያሳተፈ ነው።

የጤና ሚኒስቴርን ወክለው ስልጠናውን በንንግር ያስጀመሩት ዶ/ር አስናቀ ዋቅጅራ በጤናው አመራር ዘርፍ የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አበክሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት ትፍስሂት ሰለሞን (ዶ/ር) በሃገራችን በየመስኩ ባለው አመራር ዘንድ የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ አካል የሆነው ይህ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ወደትግበራ መግባቱ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ገልጸው፣ በጤናውም ሆነ በሌላው መስክ የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ የስራ ሃላፊ ኢሳያስ ታዬ (ዶ/ር) PL4GE በርካታ ሂደቶችን አልፎ ለዚህ በቅቷል ብለው፣ ለዚህም ጉልህ አስተዋጽዖ ላበረከቱ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

ስልጠናው ከየካቲት 10 እስከ 12 እንደሚቆይ ተገልጿል።