African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልቀት አካዳሚ በስርዓተ-ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን፣ ኤችአይቪ/ኤድስንና ሙስናን በማስቆም ላይ ስልጠና ሰጠ።
በሥርዓተ ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን፣ ኤች አይ ቪ ኤድስንና ሙስናን በማስቆም ላይ ለአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ ባለሙያዎች በሱሉሉታ ከተማ በሚገኘው የአካዳሚው የስብሰባ አዳራሽ ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ።
በመክፈቻ ንግግራቸው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረተ ደበበ ስልጠናው በእያንዳንዱ ተግባር ላይ ልምድ ለመለዋወጥ ያለውን ጠቀሜታ አንስተዋል።
ስልጠናው ራሳችንን የምንመለከትበት እና ለውጥ የምናመጣበት መሆን አለበት ብለዋል። ምንም እንኳን የቃል እና አካላዊ ጥቃትን ጨምሮ ብዙ ጥቃቶች ቢኖሩም.ስልጠናው እውቀታችንን ብቻ ሳይሆን እንደ መስሪያ ቤት፣ እንደ ኃላፊ እና እንደ ግለሰብ አመለካከታችንን መቀየር እንዳለበት ዶ/ር ምህረት አሳስበዋል።
ሀረገወይን ፋንታሁን (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ የቋንቋና ኮሙኒኬሽን ረዳት ፕሮፌሰር በሥርዓተ-ፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች፣ አጠቃላይ የአዕምሮ ውጣ ውረዶች፣ ጽንሰ-ሀሳቦቹ፣ ሥርጭቱ፣ ሥር የሰደዱ ምክንያቶች፣ ውጤቶቹ/ተጽኖዎች እና በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት ሪፖርት ለማድረግ እንቅፋት በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
በተጨማሪም በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት የትኩረት አቅጣጫዎችን በስራ አለም፣ ግጭት ተያያዥነት ባላቸው በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት እና በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት መከላከል እና ምላሽ መስጠት የሚቻልባቸውን መንገዶች ጠቁመዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ደሞዜ ደገፋ በበኩላቸው የኤችአይቪ/ኤድስን ሁኔታ እና የኢትዩጵያ ሁኔታ (በተወሰኑ መለኪያዎች) አዝማሚያዎች ፣ ኤች አይ ቪ ኤድስ በአዲሱ ወረርሽኝ (ኮቪድ-19) ፣ ስላጋጠሙት ጉዳዮች አብራርተ
የአካዳሚው ሴኔት የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አጸደቀ
የአፍሪካ አመራር ልሕቀት አካዳሚ ሴኔት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በአካዳሚው በመምህርነት ሲያገለግሉ ለነበሩት ባምላክ ታደሰ (ረዳት ፕሮፌሰር) የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በተጨማሪም ሴኔቱ በተለያዩ ምክንያቶች የመመረቂያ ፅሁፋቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች መካከል አራቱ ያጠናቀቁ በመሆናቸው እንዲመረቁ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
አካዳሚው ቅዳሜ ታህሳስ 02 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን 171 ተማሪዎችን ያስመርቃል፡፡
የአካዳሚው ሴኔት የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አጸደቀ
የአፍሪካ አመራር ልሕቀት አካዳሚ ሴኔት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በአካዳሚው በመምህርነት ሲያገለግሉ ለነበሩት ባምላክ ታደሰ (ረዳት ፕሮፌሰር) የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን 171 ተማሪዎችን አስመርቋል
በምርቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ተመራቂዎች አካዳሚው ስሙንና ተልዕኮውን ለውጦ በአዲስ መልኩ በአህጉርና በሃገር ደረጃ ከፍተኛና ተተኪ መሪዎችን የማሰልጠንና የማብቃት ስራን ለማከናወን አስፈላጊውን የለውጥ ሂደት በሚያደርግበት ጊዜ በመመረቃችሁ የአካዳሚው ታሪካዊ የለውጥ ሂደት አካል ናችሁ ብለዋል፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ በክፍተኛ ተግዳሮትና የብልፅግና ጉዞ አቋራጭ መንገድ ላይ ሆና የልዕልናና የህልውና ትግል በምታደርግበት ጊዜ ላይ የምትመረቁ ተመራቂዎች ሀገራችንን ለማፍረስ ከተነሱ ኃይላት በመከላከሉም ሆነ ህዝባችንን ወደ ዕድገትና ብልፅግና አቅጣጫ ለመምራት ልዩ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ ተመራቂዎች ፈተናዎችን ሁሉ ተቋቁማችሁ ለዛሬይቱ ቀን መብቃታችሁ ያላችሁን የመሪነት ቁርጠኝነት ጠቋሚ ከመሆኑም ባሻገር ለተማራችሁት ትምህርት ጥልቀት ተግባራዊ ገጽታ እንደሚሰጠው አምናለሁ ብለዋል፡፡
የአካዳሚው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ርዕሰ አካዳሚ የነበሩት አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው ተመራቂ አመራሮች የቀሰሙትን ንድፈ ሃሳባዊ የአመራር ዘይቤዎችን ከተሞክሯቸው ጋር በማጣመር ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባቸው አሳስበው የአካዳሚው መምህራንና ሰራተኞች ተመራቂዎች ለዚህ ታላቅ ቀን እንዲበቁ በማድረጋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሁለተኛ ዲግሪ በዘጠኝ የትምህርት አይነቶች ያስተማራቸውን 154 ወንድ እና 17 ሴት በድምሩ 171 ተማሪዎችን ቅዳሜ ታህሳስ 02/2014 ዓ.ም አስመርቋል፡፡
“የመሪ እድገት ቁልፉ የሁል ጊዜ ተማሪ፣ ንቁ ተመራማሪና አስተዋይ ተመሪ መሆን መቻሉ ላይ ነው፡፡”
ዶ/ር ምህረት ደበበ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ
አካዳሚው በሁለተኛ ዲግሪ የሁለተኛ ዙር ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ
“የመሪነት ስኬት ከማያቋርጥ የህይወት ዘመን ዕድገትና ያልተከፋፈለ ትኩረት የሚገኝ ነው፡፡”
ዶ/ር ምህረት ደበበ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ
አካዳሚው በሁለተኛ ዲግሪ የሁለተኛ ዙር ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ
“መሪ አስተማሪ ብቻ ሳይሆን ተማሪ መሆኑን፤ የሌሎች መሪ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ተመሪ መሆኑን መዘንጋት አይገባውም፡፡”
ዶ/ር ምህረት ደበበ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ
አካዳሚው በሁለተኛ ዲግሪ የሁለተኛ ዙር ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ
በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ከጦርነት ወደ ብልፅግና- በሰላም ጎዳና በሚል ርዕስ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ አመራሩና ሰራተኛው የጋራ አረዳድ እንዲኖረውና በቀረበው ሰነድ ላይ ግብዓት እንዲሰጥ ያለመ ውይይት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 30 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
የሱማሌ ክልላዊ መንግሰት የማኔጅመንት እና ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሌጅ በ አራት የስልጠናና የትምህርት መስክ ማለትም በ አመራር (Leadership) ፤ ደቨሎፕመንት ኮሚኒኬሽን (Development Communication)፤ በሰላምና ግጭት ማኔጅመንት (Peace and Conflict Management) ፤ እና በፕሮጀክት ማኔጅመንት (Project Management) ለክልሉ አመራሮች በማስተርስ ዲግሪ ደረጃ ትምህርት እና የአጫጭር ጊዜ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ኮሌጁን ወደ ዩንቨርሲቲ ደረጃ ለማሳደግ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ(HERQA) ጋር አብሮ እየሰራ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የማኔጅመንት እና ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሌጁ ዲን አመራር አካላት ለጉዳዩ መሳካት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ቀን ከሌት እየተጉ ይገኛሉ፡፡

ለዚህ ውጥን ስኬት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እያደረገ ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክልሉ መንግሰት የማኔጅመንት እና ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሌጅ ትልቅ አክብሮት አለው፡፡
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 9 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.