African Leadership Excellence Academy
2.32K subscribers
2.52K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
Together we stand, Pan-African and proud,
AFLEX empowers leaders, speaking strong and loud.
With diverse voices, we weave a rich tapestry,
Uniting our strengths, a shared destiny.
In collaboration, we rise to the call,
For a brighter tomorrow, where all can stand tall
👍4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔹አንድን ነገር ብቻ ማወቅ አዋቂ አያሰኝም፡፡

🔹ምሉዕ ለመሆን ተነፃፃሪ ዕውቀት ያስፈልጋል፡፡

🔹የሀሳብ ጥራት መሰረቱ ምንድን ነው

🔹ጊዜው ደርሶ የተወለደን ሀሳብ መመከትና ማስቆም ይቻላል ወይ

🔹የአፍሌክስ ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሃ ማብራሪያ #ክፍል_5👇👇👇👇
👍4
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ታህሳስ 24/2017 (አፍሌክስ- ሱሉልታ) የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በአመራር አቅም ግንባታ ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ክብርት ሸዊት ሻንካ ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተገኝተው ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር እና አፍሌክስ የአመራር ዕውቀትና ክህሎትን በማስፋት ላይ ያተኮሩ የጋራ የሥልጠና፣ የምርምር እና የማማከር ሥራዎችን ወደ ፊት የሚያሳድጉበት እና በአመራር አቅም ግንባታ ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በስምምነት ፊርማው ወቅት እንደገለጹት፥ ባህል እና ስፖርት ለሀገር ያለውን ጉልህ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሚና ጠቅሰው ስምምነቱ በኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ላይ ጉልህ የአመራር ለውጥ እንደሚያመጣ እና ዘርፉ ብቃት ባላቸው አመራሮች እንዲመራ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ክብርት ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው፤ ስምምነቱ በዋናነት የሴክተሩን የማስፈፀም አቅም ለማሳደግና፣ የተሻለ ስልጠና ለመስጠት እና የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማፍራት የሚያግዝ ነው፡፡
👍8
Myth vs. Reality: Knowing all the answers

🌟 Myth: Great Leaders Have All the Answers 🌟

Reality Check: No one knows it all! 🤔

The best leaders acknowledge their limits, seek diverse perspectives, and foster open dialogue. This approach cultivates trust and drives collective success!
👍7
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉ከሀሳብ እና ከመሪ የቱ ይቀድማል

👉የሀሳብ ሀያልነት መነሻው ከየት ነው ሀሳብስ እንዴት ይሸጣል

👉ህልማችንን ከቀጣዩ ትውልድ ጋር እንዴት እንጋራለን

👉የተሻለ ሀሳብ ያመነጩ፤ የተገበሩና ተከታይ ያፈሩ ዛሬ የት ደርሰዋል

👉ሁሉም ጥያቄ ትክከል ነው ወይ የትክክለኛ ጥያቄ ማረጋገጫውስ ምንድን ነው

የአፍሌክስ ፕሬዝደንት ክቡር #አቶ_ዛዲግ_አብርሃ ማብራሪያ #ክፍል_6 👇👇👇
👍9
In line with its mission to promote excellence, AFLEX has introduced a Leadership Award Program that recognizes outstanding African leaders across various sectors.

Inspired by the prestigious Nobel Prize, this award celebrates achievements in government, civil society, business, and more. Winners are selected through a rigorous process involving public nominations, expert panels, and online voting, ensuring transparency and credibility.

#AFLEX #AFLEXLeadershipAward #AfricanLeadershipAward #LeadershipExcellence #TransformativeLeadership #AfricanLeaders #LeadershipDevelopment #AfricanExcellence #InspirationalLeaders
👍8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔹ለራሳችን የምንሰጠው ዋጋ ምን ያህል ነው

🔹ሂሳዊ ትችታችን ምን ይመስላል

🔹ራሳችንን በደንብ እንፈትሻለን ወይ

🔹እያለን የሌለን፤ ያለንን የማናውቅና ጀግኖቻችንን የማናከብር ትውልድ ከመሆን መውጫው መንገድ ምንድን ነው

🔹የስልጣኔ ተምሳሌቶቻችን እነማን ናቸው

🔹መሰልጠናችን ምልክትስ የፈረንጅን ሀሳብ መቀበልና ማነብነብ ነው ወይ

🔹ስለ ሀገር በቀል ዕውቀቶቻችን ያለን ግንዛቤ ምን ያህል ነው

የአፍሌክስ ፕሬዝደንት ክቡር #አቶ_ዛዲግ_አብርሃ ማብራሪያ #ክፍል_7
👍7
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉ትክክለኛ ጥያቄ የትኛው ነው

👉ያለንበትን ሁኔታ የምንረዳበት መንገድ ትክክል ነው ወይ

👉ከችግር ጋር ተላምዶ መኖር እስከመቼ

👉ትልልቅ ነገሮችን ጀምረን መቋጨት የሚያቅተን ለምንድን ነው

👉ተንሸረተን ወድቀን ከነበርንበት አሁን ለመነሳት ሞክረን የተሳካልን በምን ምክንያት ነው

👉ኢትዮጵያ የአጓጓዊ ጅምሮች ባለቤት ያልተቋጩ ትልልቅ መቋረጦች ሀገር ሆና እስከመቼ

የአፍሌክስ ፕሬዝደንት ክቡር #አቶ_ዛዲግ_አብርሃ ማብራሪያ #ክፍል_8
👍6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💥ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? እንዴት እናየዋለን

💥ዕጣ ፈንታችን አንድ ነው ወይ

💥ተስፋና ስጋቶቻችንስ እንጋራለን ወይ

💥ኢትዮጵያውያን መሆን ያለብን ዝሆን ወይስ ከርከሮ

💥ችግሮቻችንን እንርሳ ስንል ትምህርት አንወስድባቸውም ማለት ነው ወይ

የአፍሌክስ ፕሬዝደንት ክቡር #አቶ_ዛዲግ_አብርሃ ማብራሪያ #ክፍል_9
👍7
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ ልዑክ አፍሌክስን ጎበኘ
ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ- ሱሉልታ) - የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ ሰራተኞችን እና ተማሪዎችን ያካተተ ልዑክ ዛሬ ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል ተገኝቶ ጉብኝት አድርጓል።
ጉብኝቱ ለሰራዊቱ አመራሮች ስልጠና መስጠት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከአፍሌክስ ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እና ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።
አፍሌክስ በሃገራችን ብሎም በአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማእከል ሆኖ ለሚሰራው ስራ የአመራር ልማት እና የስልጠና ማእከሉ ወሳኝ መሆኑ በጉብኝቱ ላይ ተገልጿል።
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ልዑክ በሃገራችን እንዲህ ያለ የአመራር ልማት ማዕከል መኖሩ የሚያኮራ እና ይበል የሚይሰኝ ነው ብለዋል።
በጉብኝቱ ላይ ስለአፍሌክስ፣ እየሰራ ስላለው ስራ እና የወደፊት እቅዶች ገለጻ ተደርጓል።
በተቋማቱ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር ስለሚቻልባቸው ሁኔታዎችም ውይይት ተካሂዷል።
የዋር ኮሌጅ ልዑክ አፍሌክስ እና አመራሮቹ ከኮሌጃቸው ጎን በመቆም አጋርነታቸውን ስላረጋገጡ አመስግነው፣ አፍሌክስ ቀዳሚ የአመራር ልህቀት ማዕከል ለመሆን ራሱን የማስተዋወቅ ስራ በሰፊው ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
አፍሌክስ እና የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በዋናነት በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ለመተባበር ተስማምተው በጋራ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ምን አይነት የአመራር ትውልድ ነን

መተሳሰባችን፤ መረዳዳታችን እና መተጋገዛችን ምን ድረስ ነው

ተያይዘን እንወድቃለን ወይስ ተጋግዘን ከጫፍ እንደርሳለን

አንዳችን ለአንዳችን ምንድን ነን

የእርስ በእርስ ፉክክራችን ወደ ትብብር የሚያድገው መቼ ነው

የአፍሌክስ ፕሬዝደንት ክቡር #አቶ_ዛዲግ_አብርሃ ማብራሪያ #ክፍል_10
👍11