African Leadership Excellence Academy
2.32K subscribers
2.51K photos
96 videos
6 files
118 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከአፍሪካ አመራር ልህቀት ማዕከል ጋር በመተባበር እየሰጠ ባለው ስለጠና ላይ ባህል፣ ስፖርት እና ኪነጥበብ ለማህበረሰብ አንድነት እና ለሀገር ግንባታ ያለው ፋይዳ፣ ታሪካዊና ስልታዊ አመለካከቶች ፣ብሔራዊ የህግ እና የፖሊሲ ማዕቀፎች ለኢኮኖሚ ያለው አስተዋፅኦ ከአገራችን የልማት እቅድ አኳያ፣ስልታዊ ችግር አፈታት እና ውሳኔ አሰጣጥ እንዲሁም የአመራር አስተሳሰብ እና ዘላቂነት ለዘላቂ ተጵእኖ አስተሳሰብን ማሳደግ የሚሉት የስልጠናው ይዘቶች ናቸው።
በስልጠናው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች፣ የተጠሪ ተቋማቱ ዳይሬክተሮች፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የባህልና ስፖርት ቢሮ ሃላፊዎች የስልጠናው ተሳታፊዎች ናቸው።
"አፍሌክስ ነባር እና ተተኪ የአፍሪካ አመራሮች በጋራ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚያበጁበት ተቋም ነው።" ወ/ሮ መሰረት ደስታ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ
አፍሌክስ ለባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ
ታኅሣሥ 21/2017 (ሱሉልታ - አፍሌክስ):- የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከ300 በላይ ለሚሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የአመራር ልማት መስጠት ጀምሯል።
ስልጠናው የአመራሩን ብቃት በማጠናከር ኪነ ጥበብ፣ ባህል፣ እና ስፖርት ለሃገር አንድነት እና ብልጽግና ያላቸውን ሚና አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በመክፈቻ ስነ ስርዐቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ "አፍሌክስ ነባር እና ተተኪ የአፍሪካ አመራሮች በጋራ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚያበጁበት ተቋም ነው።" ብለዋል።
አያይዘውም "አፍሌክስ በሚሰጣቸው ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ውስጥ የመንግስት ተቋማትን አመራሮችን አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፣ ይህ ስልጠናም የዚሁ አካል ነው።" ሲሉ ገልጸዋል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በዚሁ የመክፈቻ ስነስርዐት ላይ ባደረጉት ንግግር "አፍሌክስ ብቁ አመራሮችን ማፍራት የሚያስችል መሰረተ ልማት እንዲሁም ብቁ አመራር እና ባለሞያዎች ያሉት ሃገራዊ ተቋም ነው።" ብለዋል።
አፍሌክስ በኢትዮጵያ የመንግስት ተቋማት አመራሮችን ብቃት ለማሳደግ አቅዶ ብሰፊው እየሰራ ይገኛል።
More conferences
AFLEX is gearing up for an amazing year ahead, focused on hosting impactful conferences across various sectors in Africa!
What to Expect⁉️
• Diverse Conferences: We will host engaging events featuring leaders from all levels - existing, emerging, women, executives. and others.
-This diversity will create a vibrant platform for sharing innovative ideas.
• Sululta as an Idea Hub: By bringing together diverse voices and perspectives, we aim to establish Sululta, Ethiopia, as an idea hub for Africa, akin to Davos in Switzerland. #This vision strengthens our commitment to making Ethiopia a premier host for global conferences, enhancing its reputation on the international stage. 🏛
Sululta Davos Project
• Networking and Problem-Solving: Our conferences will not only foster invaluable networking opportunities but also focus on collaborative problem-solving and idea generation.
-Together, we’ll tackle challenges and create actionable solutions.🤝
Your thoughts always matter!
👉What challenges do you think are most pressing in our communities, and what solutions would you like to see discussed?
#AFLEX #2025 #
የኢቢሲ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተገኝተው ኪነ ጥበብ፣ ባህል እና ስፖርት ለሃገረ መንግስት ግንባታ በሚኖራቸው ሚና ዙሪያ ለከፌዴራል፤ ከክልሎችና ከሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች ለመጡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ገለጻ አድርገዋል።

በገለጻቸውም "ሃገር ለመገንባት በቅድሚያ የጋራ ህልም፣ ቀጥሎ ህልምን የሚያሳኩ ተቋማትን መገንባት ያስፈልጋል!" ሲሉ ተናግረው ኪነ ጥበብ፣ ባህል እና ስፖርት የጋራ ትርክት ለመፍጠር ቁልፎ መሳሪያዎች ናቸው ብለዋል።
"አፍሌክስ ብቁ አመራሮችን ማፍራት የሚያስችል መሰረተ ልማት እንዲሁም ብቁ አመራር እና ባለሞያዎች ያሉት ሃገራዊ ተቋም ነው።" ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር።
Strong policies create strong nations. 🌍

The leaders who focus on inclusive and innovative policies leave a lasting legacy.

If you were to draft one policy to improve your community, what would it be?

#AFLEX #LeadershipDevelopment #FutureLeaders #EmergingLeaders #YouthEmpowerment #PurpuosefulLeadership
#AfricaRising #MakeADifference #LeadershipInAfrica #Empowerment #AfricanLeadership #Impact
#PolicyForChange #InnovationMatters
Limited-time offer: "Join the AFLEX Community by signing up today and be one of the first 100 members to receive exclusive benefits!"
"አፍሌክስ ነባር እና ተተኪ የአፍሪካ አመራሮች በጋራ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚያበጁበት ተቋም ነው።"

ወ/ሮ መሰረት ደስታ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ
🌍 A New Day for the World, Africa, and AFLEX! 🌍

As we prepare to step into 2025, the African Leadership Excellence Academy (AFLEX) is ready to make a difference like never before. Through our transformative Leadership Development Program, we aim to shape the future leaders of Africa and beyond.

Welcome, 2025! 🚀 We are excited to serve you with new ideas and renewed energy. Together, let’s create an impact and build a brighter tomorrow.

#AFLEX #ShapingFutureLeaders #Welcome2025 #LeadershipExcellence
Empowering Women Leaders!

At AFLEX, we take pride in our dedication to advancing women in leadership. Our #Women_Leadership_Development_Program is thoughtfully designed to address the unique challenges faced by women in leadership roles.

This program goes beyond traditional training by fostering confidence, building resilience, and cultivating a strong sense of self-worth. Through this initiative, we aim to empower women to lead with purpose, authenticity, and impact, shaping a future where diversity and inclusion are at the forefront of leadership.

#AFLEX # WomenIn Leadership #Leadership In Africa # Purposeful Leadership #Empowerment #Leadership Development #Diversity In Leadership #Equality In Leadership #Resilient Leadership #Advancing Women
የባህልና ስፖርት ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ሚና፣ ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች በሚል ርዕስ በአፍሌክስ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ታኅሳስ 22፣ 2017ዓ.ም (ሱሉልታ- አፍሌክስ)- በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እየተሰጠ የሚገኘው አመራሮችን በማብቃት የባህል፣ የስፖርት እና የኪነ ጥበብ ዘርፍ ለሀገር አንድነትና ብልፅግና ያለውን ሚና አጠናክሮ የማስቀጠል ስልጠና በሁለተኛው ቀን ውሎ የባህልና ስፖርት ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ሚና፣ ተግዳሮቶች እና መልካም አጋጣሚዎች በሚል ርዕስ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

የስልጠናውን ሰነድ አዳነ ካሴ (ዶ/ር ) ባቀረቡበት ወቅት ኢትዮጵያ የብዝሀ ባህል እና ቋንቋ ባለቤት፤ የልዩ ልዩ ዕይታዊ፣ ትዕይንታዊ እና ሥነ-ፅሁፋዊ እሴቶችም ባለቤት እንደመሆኗ መጠን ለሀገር ኢኮኖሚ ልማት ያለው እምቅ አቅም ከፍተኛ ድርሻ ያለው እና ያልተነካ እምቅ ሀብት ያለበት ዘርፍ ነው። በቀጣይም መንግስት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በሰጠው ትኩረት ልክ ዘርፉ ለዚህ ዕቅድ ስኬት የዕቅዱ አካል አድርጎ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

አክለውም በስፖርት ዘርፉም ልዩ የሆኑ ባህላዊ ስፖርቶች መገኛ ከመሆኗም ባሻገር ዘመናዊ ስፖርቶች የሚከናወኑባት እና ስፖርት ወዳድ የሆነ ህዝብ ያለባት ሀገር እንደመሆኗ ይህንን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የኢኮኖሚ ምንጭ ማድረግ ይገባል።

ሙሉጌታ ጌጡ (ዶ/ር) በበኩላቸው ብሔራዊ የህግ ማዕቀፎችና ዘርፉ ለኢኮኖሚ ያለው አስተዋፅኦ ከሀገሪቱ የልማት ዕቅድ አኳያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የባህል፣ የስፖርት እና የኪነ ጥበብ ዘርፍን በህግ ማቀፍ ከህገ መንግስት፣ ከስትራቴጂክ ፖሊሲ፣ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የየዘርፉ ፖሊሲዎችንና ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች አንፃር ገለፃ አድርገዋል።
ሙሉጌታ ጌጡ (ዶ/ር) የስልጠናውን ዓላማ ሲያብራሩ፦ ህጎች የተቋማት ግብ ተገማች ለማድረግ፤ ለባለድርሻ አካላት መተማመኛን ለመፍጠር፤ ለሚፈለገው ግብ መዳረሻ መሳሪያ እንዲሆን፤ ቅንጅታዊ አሰራርን ለማሳለጥ፤ ለተለያዩ አካላት ሚናና ኃላፊነት ለመደልደል የሚያግዝ መሣሪያ ነው ብለዋል።

የባህል፣ ስፖርት እና የኪነ ጥበብ ዘርፍ የሀገሪቱን ህጎች የተቋሙን ፖሊሲዎች መመሪያዎችን እና ዓለማ አቀፋዊ ተሞክሮዎችን በመቀመር ለ17ቱ የሀገሪቱ የዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት ጠንክሮ መስራት ይገባል ብለዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጥቂት ሰዎች ሃገር ይቀይራሉ!

"ሁላችንም በአንዴ ሃብታም ልንሆን አንችልም። ነገር ግን ከህዝባችን መካከል ጥቂቱ እንኳን ስኬታማ ስራ ፈጣሪ መሆን ከቻለ ኢትዮጵያ የመለወጥ እድሏ ሰፊ ነው።
ችግሩ ጥቂቶች እንኳን ስኬታማ የሚሆኑበትን እድል የሚፈጥር ሃገራዊ ስነ-ምህዳር አለን ወይ ነው?"

አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
#AFLEX
#የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴ_በአፍሌክስ

ታህሳስ 23፣ 2017ዓ.ም (ሱሉልታ- ኤፍሌክስ)

ብቁ፣ ንቁ እና አሸናፊ ትውልድን ለመፍጠር የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ልማድ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ዛሬ ማለዳ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተከናውኗል።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህል በማድረግ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እራሳችንን እንጠብቅ።