African Leadership Excellence Academy
2.33K subscribers
2.52K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የሁለት መሪዎች ወግ ✍🏾

⚫️በደቡባዊ አፍሪካ የጸረ ቅኝ ግዛት ትግል ሲነሳ የ2 ሰዎች ስም ሁሌም አብሮ ይነሳል። ማንዴላ እና ሙጋቤ።

ሁለቱም በየሃገራቸው የቅኝ ግዛት ውጤት የሆነውን ኢ-ፍትሃዊነት ታግለዋል፣ አታግለዋል። ድልም አድርገዋል።

🔹ከነጻነት በኋላ ግን የቅኝ ግዛቱን ዘመን ጠባሳ ለመሻር የሄዱበት መንገድ ግን ለየቅል ነው።

🇿🇦ኔልሰን ማንዴላ ከአርባ አመት በላይ ከቆየው የአፓርታይድ ስርዐት ደቡብ አፍሪካን ነጻ ሲያወጣ፣ ያለፈውን እንርሳው፣ የሚያስፈልገን ዕርቅ ነው ብሎ የነጩም የጥቁሩም የጋራ የሆነች ሃገር ለመመስረት በአፓርታይድ ስርዐት ውስጥ ገዢ መደብ የነበሩትን ነጮች ሃብትና ንብረታቸውን ይዘው እንዲቆዩ፣ በመንግስት አስተዳደር ውስጥም በአመራርነት ጭምር እንዲሳተፉ ፈቀደላቸው።

🇿🇦የማንዴላ መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ያስቻለ፣ ሃገሪቱ የጥሩ ኢኮኖሚ ባለቤት እንድትሆን ያደርገ ቢሆንም፣ ዛሬም ድረስ ነጮች በደቡብ አፍሪካ በጥቁሮች ላይ ላላቸው የኢኮኖሚ የበላይነት ዋነኛው ተጠያቂ ነው ይሉታል። እንዲያውም ጥቂት የማይባሉ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን በዚህ የማንዴላ መንገድ የመከዳት ስሜት ተሰምቶናል ይላሉ።

🇿🇼የዚምባብዌው ሮበርት ሙጋቤ በበኩሉ ሃገሩን በኢያን ስሚዝ ከሚመራው ዘረኛ የነጭ መንግስት ነጻ ሲያወጣ፣ የቅኝ ግዛት ጠባሳ የሚሻረው ተበዳዩ ሲካስ ነው ብሎ፣ የዚምባብዌን መሬት ከነጮች ነጥቆ ለጥቁሮች አከፋፈለ።

🇿🇼ይህ የሙጋቤ አካሄድ በወቅቱ ዚምባብዌ ከአለም መድረክ እንድትገለል አድርጓል፣ ኋላ ላይም ሃገሪቱን ለኢኮኖሚ ውድቀት ዳርጓል እየተባለ ቢወቀስም፣ በብዙዎች ዘንድ ውሳኔው ዚምባብዌን ለዚምባብዌያውያን የመለሰ ነው ይባልለታል።

⁉️እርስዎስ በመሪዎቹ ቦታ ቢሆኑ ኖሮ የትኛውን አካሄድ ይመርጡ ነበር? ሃሳብዎን ያጋሩን።
👍4
Well-deserved recognition!

🎉AFLEX President Mr. Zadig Abreha and Mr. Alex Munive, Director of Global Center for Gender Equality presented certificates to the PL4GE program's amazing trainees and facilitators recognizing their commitment to empowering women in Public leadership.

#AFLEX
#PL4GE #GenderEquality #WomenInLeadership  #Ethiopia #LeadershipDevelopment #EmpoweringWomen #PublicLeadership #InclusiveLeadership #PartnershipForEquality
👍11
🌍 Ethiopia has always been a land of firsts the cradle of humanity, the birthplace of civilizations, and the heart of African unity. Now, it’s home to AFLEX, the African Leadership Excellence Academy a place where leadership isn’t just taught but lived and experienced.
📍 From the highlands of Sululta, where ideas meet action, we’re building a generation of leaders ready to take Africa forward.
The future starts here. The future starts with you. https://aflexacademy.gov.et
#AFLEX #EthiopianExcellence #PurpuosefulLeadership #LeadershipDevelopment #ShapeTheFuture #PurpuosefulLeadership #MakeADifference #Sululta #BuildingTheFiture #visionaryLeaders
👍8
🌟Exciting Plans for 2025!🌟
As we wrap up 2024, AFLEX is gearing up for an amazing year ahead:
🎙 Podcast Launch: Engaging discussions with
leadership experts.
🌍 More Conferences: Inspiring events for collaboration and growth.
📚 New Publications: Fresh insights to empower African leaders.
Join us in shaping the future of leadership in Africa! 🚀
#AFLEX #LeadershipDevelopment #2025
👍7
#upcomingevents

WHAT: Signing of Letter of Intent for Cooperation between Africa Leadership Excellence Academy (AFLEX) and IGAD

Participant: AFLEX Management and IGAD Management team

When: Tuesday 24 December 2024 at 2:30 pm

WHERE: IGAD Head Office, Addis Ababa

Telegram: https://t.me/afleexac
Website: https://aflexacademy.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/@aflexacademy.gov.et
LinkedIn: https://www.linkedin.com/.../african-leadership...
X (Twitter): https://x.com/Afleexacademy
#Partnership #LeadershipDevelopmentProgram #Collaboration #AFLEX
#IGAD
👍8
AFLEX: Building Strong Public-Private Partnerships for Africa’s Future 🌍🤝

At AFLEX, we believe in the power of collaboration! By partnering with private sector institutions, we create impactful initiatives that drive sustainable development in Ethiopia and beyond.

These partnerships leverage resources and expertise, fostering innovation and progress for all.

Together, we’re shaping a brighter future for Africa! Let’s make a difference! 🚀
👍11
🌍 AFLEX! Center for Behavioral Science in Public Policy Implementation! 🌍

Introducing our Center for Behavioral Science in Public Policy Implementation! 🚀

At AFLEX, we believe that evidence-based and context-specific policies are key to tackling the unique social, economic, and environmental challenges faced by Africa. 🌿

Our Center is dedicated to:

🔍 Conducting In-Depth Policy Analysis: We’ll dive into data and insights to craft meaningful solutions that resonate with local communities.

📊 Evaluating Impact: We’ll assess the effectiveness of policies to ensure they’re making a real difference in people's lives.

📢 Advocacy for Change: We aim to influence decision-making at all levels, amplifying voices for a brighter, more sustainable future.

Through innovative approaches rooted in behavioral science, we’re committed to bringing transformative change to public policy across the continent.

Join us in shaping a better tomorrow for Africa! 🤝
👍11
🌍 Establishing the Center for Asia, the Middle East, and Africa! 🌍

AFLEX is proud to announce the establishment of the Center for Asia, the Middle East, and Africa at the African Leadership Excellence Academy’s Sululta campus.

This initiative is driven by the deep economic, social, and political connections between Africa, Asia, and the Middle East—historically and in shaping our shared future.

The center aims to:

Strengthen existing ties across these regions.

Forge new partnerships with countries in Asia and the Middle East.

Organize and manage connections for more impactful collaborations.

Position Ethiopia as a vital link between Africa, Asia, and the Middle East.

We believe this center will serve as a hub for meaningful dialogue, partnerships, and progress on shared social and economic issues.

💡 Join Us!

AFLEX invites local and international partners to collaborate with us and bring this vision to life.

Let’s create a brighter future together!
👍8
ኢትዮጵያ ካላት የቱሪዝም ሃብት የበለጠ ተጠቃሚ እንድትሆን ዘርፉን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ማስተዋወቅ እንደሚገባ ተገለፀ
______________________

ታኀሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. (ሱሉሉታ):- በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አዘጋጅነት ለነባር ዲፕሎማቶች እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እየተሰጠ ባለው ሥልጠና በዛሬ ውሎ የሀገር ገፅታ የማስተዋወቅ ክህሎት፣ እንግዶች አያያዝ እና እንክብካቤ ዙሪያ ያተኮረ ገለፃ ተሰጥቷል ።

ሁለቱም የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታዎች ክቡር አቶ ስለሽ ግርማ እና ዶ/ር እንደገና አበበ ገለፃውን ሰጥተዋል ።

በያዝነው ዓመት የካቲት ወር አጋማሽ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ እና በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት የጎላ መሆኑን ገልፀዋል ።

ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ በቱሪዝም ሀብቷ እጅግ የበዛ በመሆኑ ያሉንን አቅሞች በሚገባ ለውጭ አገር ጎብኝዎች እና እንግዶች ይበልጥ ማስተዋወቅ እንደሚገባ ገልፀዋል።

መንግስት ለቱሪዝም ልማት እና እድገት በሰጠው ልዩ ትኩረት አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተገልፆል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለስ በበኩላቸው በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን እና አዲስ አበባን ቀዳሚ የአፍሪካ የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በተመለከተ ገለፃ ሰጥተዋል ።

በቀጣይም በጎ ፈቃደኛ ሰልጣኝ ወጣቶች (ካዴቶች) የአገራቸውን ገፅታ በማስተዋወቅ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።
👍9
“አፍሌክስ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር፤ የአመራር ልማት ተግባሩን ለማስፋት በሩ ሁልጊዜም ክፍት ነው።” ወ/ሮ መሰረት ደስታ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ

#ፖላር_ፕላስ_ኤክሰለንስ_ሃብ እና #አጋሮቹ አፍሌክስን ጎበኙ

ታህሳስ 14/2017 (ሱሉሉታ- አፍሌክስ) - የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል ዛሬ ከፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሃብ እና አጋር ድርጅቶች የተወጣጡ ልዑካንን አስተናግዷል።

ሱሉልታ በሚገኘው የአመራር ልማት ማዕከል ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት የፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሃብ እና አጋር ድርጅቶቹ የሆኑት #የዌብ_አክሰስ#የሻላ_ዌልነስ_ሴንተር እና #የአፔክስ_ቬንቸርስ አመራሮች ናቸው።

ልዑካኑ በማዕከሉ የሚገኙ ዘመናዊ የሲኒዲኬትስ ክፍሎችን እና ጂምናዚየምን ጨምሮ ሌሎች ዘመናዊ መገልገያዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም እንዲህ ያለ የተሟላ የአመራር ልማት ማዕከል በኢትዮጵያ መገኘቱ ትልቅ እመርታ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ አፍሌክስ ለአመራር ልማት ምቹ አካባቢን ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት አጉልቶ ያሳያል ብለዋል።

ጉብኝቱን ተከትሎ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ ከልዑኩ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም ላይ "አፍሌክስ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ ትብብር፤ ለሁለንተናዊ እድገት ያለውን አስፈላጊነት በመገንዘብ በትብብር ለመስራት በሩን ክፍት አድርጎ እየጋበዘ ነው።" ብለዋል።

በውይይቱ አፍሌክስ እና ልዑካኑ የጋራ የትብብር አቅጣጫዎችን ለይተው አጋርነት መፍጠር ስለሚችሉበት ሁኔታ የተነጋገሩ ሲሆን፣ ከትብብር መስኮቹ መካከል የጤናው ዘርፍ እና የስትራቴጂክ ኮሙዩኒኬሽን ሊካተቱ የሚችሉ እንደሆኑ ተጠቁሟል።
👍7