African Leadership Excellence Academy
2.32K subscribers
2.52K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እየተካሄደ የሚገኘው የነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች እና አመራሮ ች 19ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በማክበር ላይ ይገኛሉ!
👍10
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)
#ከአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ #የለውጥ_Reform #የማስፋት_Scaling_Up እና #የመሰረታዊ_እመርታ_Transformation ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የቀድሞ ህንፃዎችን በማደስ ለአገልግሎት ዝግጁ የማድረግ ተግባር ስራ ተጀምሯል::

በሱሉልታ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት የቀድሞ ህንጻዎች የአስተዳደር ቢሮውን በአዲስ መልክ የማደስ ተግባር ተጀምሯል።

ለእድሳቱም #የኢትዮጵያ_መንገዶች_ባለስልጣን #ERA አጠቃላይ ወጭውን የሚሸፍን ሲሆን ለዕድሳት ደግሞ #የኢትዮጵያ_ኢንጂነሪንግ_ኮርፖሬሽን #ECC ውል ገብቶ ስራ ጀምሯል።

የህንጻው እድሳት እንደተጠናቀቀም የአካዳሚው ሰራተኞች ወደ አዲሱ ህንጻ ተዛውረው ስራ ይጀምራሉ።

በዚህም አካዳሚው ለቢሮ ኪራይ የሚያወጣውን ገንዘብ ከማስቀረቱም በላይ ለአመራር ልማት እና ለጥናትና ምርምር ስራዎች ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

የህንፃ እድሳቱ ሲጠናቀቅ የሚኖረውን ገፅታ የሚያመላክተው የ3D ቪዲዮ እንደሚያሳየው ሁሉንም አይነት መሰረተ ልማት ያካተተው ይህ የህንፃ እድሳት በወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል::
👍7
ነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ ተጠናቀቀ

ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ) ከህዳር 26 እስከ 28/2017 በአላማ መምራት፣ በቅንነት ማገልገል! በሚል መሪ ቃል ለ 3 ቀናት በሱሉልታ ሲካሄድ የቆየው ነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ ተጠናቋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (አፍሌክስ) ከኢንስፓየርድ ዲቬሎፕመንት ጋር በትብብር ያዘጋጀው ነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ ከ250 በላይ የሚሆኑ ነባር እና ተተኪ አመራሮችን ያሰባሰበ ነው። ወጣት እና ሴት አመራሮች፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሚዲያ ሰዎች እንዲሁም ሌሎችም የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች መሆን ችለዋል።
ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ንግግሮችን እና ጽሁፎችን ያቀረቡ ሲሆን፣ የፓናል ውይይቶች እና ወርክሾፖችም የኮንፈረንሱ አካል ነበሩ። በተለያዩ ቡድኖች ተከፋፍለው ወርክሾፖች ላይ የተሳተፉ የኮንፈረንሱ ታዳሚዎች የየወርክሾፖቻቸውን ውጤት በመዝጊያ ስነ ስርዐቱ ላይ አቅርበዋል።

የመዝጊያ ስነ ስርዐቱ ለተሳታፊዎች እና ለኮንፈረንሱ መሳካት አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት የዕውቅናና ስርተፍኬት አሰጣጥንም ያካተተ ነበር። የኮንፈረንሱ አዘጋጆችም የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል።

የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በማጠቃለያ ንግግራቸው “አፍሌክስ የተቋቋመበት ዋነኛ አላማ፣ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአመራር ልማት ላይ መስራት ነው። ይህንንም ለማሳካት በአመራሩ መካከል ድልድይ መገንባት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ የነጸብራቅ ኮንፈረንስ በነባሩ እና በተተኪው አመራር መካከል የተገነባ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል።” ብለዋል። አያይዘውም ይህ ኮንፈረንስ የተሳታፊው ቁጥር ጨምሮ፣ አለም አቀፋዊ ኮንፈረንስ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

አቶ ልዩነህ ታምራት የኢንስፓየርድ ዲቬሎፕመንት ዋና ስራ አስኪያጅ የኮንፈረንሱን አላማና ግብ ሲያስረዱ “በነጸብራቅ ማሳካት የምንፈልገው፣ ምሳሌ የሚሆኑ መሪዎችን ማፍራት ነው።” ብለዋል።

ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገ ስብዕናን ይገነባል! በሚል መሪ ቃል ለ 21ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በማስመልከት በአፍሌክስ የስነ ምግባር መከታተያ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ለኮንፈረንሱ ታዳሚዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም፤ ሙስና በሃገራችን ትልቅ ጉዳት እያስከተለ እንዳለ አስታውሰው ወጣቶች ከምንም በላይ ሙስናን አጥብቀው ሊታገሉ እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል።
👍7
Toastmaster Engineer Mesfin Shenkut took the spotlight with his keynote on success and the important of serving others! 🌟

His message emphasized that true achievement is not just about personal milestones, but about uplifting those around us and making a meaningful impact on others.

Let’s continue to embrace these principles as we move forward. 🙏

#NLC2024 #LeadershipForChange #YouthEmpowerment #AFLEX #InspiredLeadership #EthiopiaRising #BuildingTomorrow #EmpoweredYouth #FutureLeaders #ConnectingMinds #CollaborationForChange #Networking #BeTheChange #InspiringGenerations #LeadersOfTomorrow #EthiopianLeadership #EthiopiaRising #BoldLeaders #VoicesForChan
👍13
ክብርት ወ/ሮ መሰረት ደስታ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ በነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ ማጠቃለያ ላይ ከተናገሩት:-
🔹 አፍሌክስ የተቋቋመበት ዋነኛ አላማ፣ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአመራር ልማት ላይ መስራት ነው።
🔹 በአመራር ልማት ውጤታማ ለመሆን፤ ከተተኪ አመራር ጋር መስራት ቀዳሚው ተግባራችን ነው።
🔹 ይህንንም ለማሳካት በአመራሩ መካከል ድልድይ መገንባት አስፈላጊ ነው።
🔹 ነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ በርካታ ልምድ የቀሰምንበትና የሀገራችንን ወጣቶች የመምራት አቅም ያየንበት ነው።
🔹 ነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ በነባሩ እና በተተኪው አመራር መካከል የተገነባ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል።
🔹 በነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ ስራ ላይ ያለውን አመራር ከተተኪው ጋር በማቀናጀት ለሀገር ግንባታ ማዋል የሚቻልበትን መንገድ አይተናል።
🔹 ነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ የተሳታፊው ቁጥር ጨምሮ፣ አለም አቀፋዊ ኮንፈረንስ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነት አለኝ።
🔹 ተተኪ አመራሮች ያላቸውን እምቅ አቅም ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚችሉ ያየንበት ኮንፈረንስ ነበር።
🔹 የሚጋራ ህልም ያላቸው ነገር ግን ህልማቸውን ለማጋራት እድል ያላገኙ ወጣቶች መኖራቸውን በተግባር ያረጋገጥንበት የመሪነት ኮንፈረንስ ነበር።
👍15
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ሱሉልታን አለም አቀፍ የጉባኤ ማእከል ማድረግን በተመለከተ በነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ ሃሳቦች፦

👉አፍሌክስ ከትሞ በሚገኝባት በውቧ ሱሉልታ፤ ወደ ሌላው አለም ብትሄዱ የትም ቦታ የማታገኟቸው በርካታ ድንቅ ነገሮች ይገኛሉ።

👉በዚህች ከተማ፣ ውብ ህንፃ እና ውብ ሀሳብ ህብረት ፈጥረው፤ ከአዲስ አበባ 23 ኪሎ ሜትር ብቻ ርቀው ተሰይመዋል።

👉እኛ አፍሌክሶች ይህችን ስፍራ በስዊዘርላንድ ሀገር በምትገኘው በተክለ ሰውነቷ ትንሽ፤ ግን ደግሞ በተፅእኖዋ በአለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሽ በሆነችው ዳቮስ አምሳያ አፍሪካዊቷ ዳቮስ ስንል እንጠራታለን።

👉ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን አንድ ታላቅ ሀገራዊ ተቋም በጋራ እንፍጠር።

👉አባቶቻችንና አያቶቻችን ኢትዮጵያ ከሌላት አካፍለው፤ ለሌሎች አፍሪካውያን አስተዋፅኦ እንድታበረክት እና ሀገራችን በአፍሪካውያን ዘንድ መልካም ስምና ከበሬታን እንድትጎናፀፍ አድርገዋል። ዛሬም የእኛ ትውልድም ቢሆን ይሄን አኩሪ ታሪክ እንዳስቀጠለው ነው ።

👉አፍሌክስ የዛሬይቱ ኢትዮጰያም ከጉድለቷም ጭምር ለአፍሪካውያን መስራቷን እንድትቀጥል በፅኑ በማመኗ ብቻ ለመላ አፍሪካውያን ይሄውና እንካችሁ ያለቸው ተቋም ነው።

👉ሁሉም ስዊዘርላንዳዊ፤ ሀብታም ሆነ ድሀ ፣ሸማግሌና ወጣት፣ምሁርና ያልተማረ ሳይል ሁሉም እንደ ችሎታው አዋጥቶ ነው የዛሬዋን ዳቮስ የገነባው።

👉ሩዋንዳውያን ተመሳሳይ አይነት ተቋም ለመገንባት ደፋ ቀና እያሉ ነው። እኛም ጋር በአፍሌክስ አማካኝነት ተመሳሳይ ጥረት እየተደረገ ነው።
👍11